Decha Tube

Decha Tube good like

➕➕ የወገብ ህመም ለሚያስቸግረው➕➕ 🖲 የወገብ ህመም ያለበት ሰው ሁሉ ሀኪምጋ መቅረብ አለበት ማለት አይደለም፣ ነገር ግን፣ የወገብ ህመም ያለበት ሰው ላይ፣ አንዳንድ ተጨማሪ  ምልክቶች ከታ...
02/04/2026

➕➕ የወገብ ህመም ለሚያስቸግረው➕➕

🖲 የወገብ ህመም ያለበት ሰው ሁሉ ሀኪምጋ መቅረብ አለበት ማለት አይደለም፣ ነገር ግን፣ የወገብ ህመም ያለበት ሰው ላይ፣ አንዳንድ ተጨማሪ ምልክቶች ከታዩ፣ በቶሎ ህክምና ማድረግ ሊያስፈልግ ይችላል።

🖲 የዲስክ መንሸራተት ብቸኛው የወገብ ህመም አምጪ በሽታ አይደለም፣ የአከርካሪ አጥንት፣ የጡንቻ ፣ የነርቭ እና የውስጥ ደዌ ህመሞችም፣ የወገብ ህመምን ሊፈጥሩ ይችላሉ

🖲 አንድ ሰው ላይ ፣የወገብ ህመም መኖሩ ብቻ ሁልግዜ አሳሳቢ ችግር ነው ማለት አይደለም፣ ነገር ግን፣ አንዳንድ ግዜ ተያይዘው የሚታዩ ምልክቶች፣ የወገብ ህመሙ አደገኛ መሆኑን የሚያመላክቱ ናቸው

🖲 የወገብ ህመም እንደቆይታ ግዜው በ 4 አይነት መንገድ ይከፈላል፣ ማለትም፣ የወገብ ህመሙ ከ 6 ሳምት በታች የቆየ ከሆነ የአጭር ግዜ የወገብ ህመም ወይም ( acute back pain) ተብሎ ይጠራል።

🖲 ወይም ደሞ፣ የወገብ ህመሙ ከ 6 ሳምንት እስከ 3 ወር ድረስ የቆየ ከሆነ ፣( subacute back pain) ተብሎ ይጠራል: ሲተረጎም፣ ከፍያለ ደረጃ ያለው የአጭር ግዜ የወገብ ህመም እንደማለት ነው።

🖲 የወገብ ህመሙ ፣3 ወር እና ከዛ በላይ የቆየ ከሆነ፣ (chronic back pain) ወይም ስር የሰደደ የወገብ ህመም እንደሆነ ያመላክታል።

🖲 ከዚህ ውጪ ፣ አንዳንድ ሰዎች ላይ የሚያጋጥም፣ በመሀል ለተወሰነ ግዜ እረፍት እየሰጠ የሚመላለስ እና ለረጅም ግዜ የሚቆይ የወገብ ህመም ያጋጥማቸዋል፣

🖲 ይህ አይነቱ የወገብ ህመም በህክምናው (recurrent back pain ) ተብሎ ይጠራል ወይም ተመላላሽ የወገብ ህመም ማለት ነው።

🖲 የወገብ ህመምን በዚህ መልኩ በቆይታ ግዜው መከፋፈል ያስፈለገበት ዋነኛው ምክኒያት፣ የወገብ ህመም መንስኤ የሆነውን በሽታ ለመለየት እና ትክክለኛውን ምርመራ እና ህክምና ለመስጠት ታስቦ ነው።

🖲 ምክኒያቱም፣ ከ 30 በላይ የሚሆኑ የበሽታ አይነቶች፣ የወገብ ህመም ስሜትን የመፍጠር አቅም ስላላቸው ማለት ነው

🖲 አብዛኛውን ግዜ፣ ከ 6 ሳምንት በታች የሚቆይ የወገብ ህመም በቀላል ህክምና ወይም በቀላል የህመም ማስታገሻዎች ብቻ የሚድን ሆኖ ይገኛል።

🖲 80 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች ላይ የሚያጋጥመው የወገብ ህመም አይነትም፣ ይሄው አጭር የግዜ ቆይታ ያለው የወገብ ህመም ነው፣ ከነዚህ ውስጥ፣ 90 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች በ 6 ሳምንት ውስጥ ሲሻላቸው ይታያል።

🖲 የወገብ ህመም አሳሳቢ የሚሆነው ታዲያ መቼ ነው? አንድ ሰው በራሱ ላይም ሆነ፣ በቤተሰብ አባል ላይ የሚታይ የወገብ ህመም ሲያጋጥመው ፣ሀኪም ጋር ከመምጣቱ በፊት ምን ማድረግ አለበት?
ሙሉውን መረጃ በቪዲዮ ዩቲዩብ ላይ አስቀምጫለሁ።

➕➕ የእግር እብጠት➕➕ 🖲 ሁለት እግር አንድ ላይ የሚያብጥ ከሆነ አንዳንዴ ጥሩ ምልክት አይደለም፣ 🖲 ለወራት የሚቆይ ተቅማጥ ፣ የጉበት ችግር፣ የኩላሊት በሽታ፣ እና የልብ ድክመት ሲኖር፣ ...
02/04/2026

➕➕ የእግር እብጠት➕➕

🖲 ሁለት እግር አንድ ላይ የሚያብጥ ከሆነ አንዳንዴ ጥሩ ምልክት አይደለም፣

🖲 ለወራት የሚቆይ ተቅማጥ ፣ የጉበት ችግር፣ የኩላሊት በሽታ፣ እና የልብ ድክመት ሲኖር፣ ከተለያዩ ተጓዳኝ ምልክቶች ጋር ሁለቱም እግር ሊያብጥ ይችላል።

🖲 እብጠቱ በኩላሊት ድክመት ምክኒያት የመጣ ከሆነ፣ በእግር ላይ እብጠት ከመጀመሩ በፊት፣ የአይን ዙሪያ እብጠት ይኖራል

🖲 በልብ ህመም ምክኒያት የሚመጣ የእግር እብጠት፣ እንደ ደረጃው ራስ መሳት፣ አቅም ማነስ፣ ሳል እና አየር ማጠር ሊኖረው ይችላል

🖲 የእግር እብጠት በጉበት ድክመት ምክኒያት የመጣ ከሆነ ደሞ፣ ሆድ ማበጥ እና የአይን ቢጫ መሆን ሊከሰት ይችላል።

🖲 አንዳንዴ ደሞ፣ የከፋ የጤና ችግር በሌለበት ሁኔታም፣ አንድ ሰው ላይ የእግር እብጠት ሊያጋጥም ይችላል።

🖲 ለምሳሌ፣ ነብሰጡር ሴት ላይ እርግዝናው እየገፋ ሲሄድ፣ ሁለቱም እግር ሊያብጥ ይችላል፣

08/03/2026

Big shout-out to my newest top fans! Sosina Ye Mariyam Lije, Love Gder, Gizachew Meseret, Wiz Artan Artan

16/10/2025

Big shout out to my newest top fans! Sosina Ye Mariyam Lije, Love Gder, Gizachew Meseret, Wiz Artan Artan

Address

Addis Ababa

Telephone

+251939979509

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Decha Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Decha Tube:

Share