31/07/2026
ድሮጋ ቼይን ፋርማሲ በዲጂታል ቴክኖሎጂ እና በታካሚ ተኮር አገልግሎቶች የታገዘ ዘመናዊ የፋርማሲ አሰራርን በ46ኛው የኢትዮጵያ ፋርማሱቲካል ማህበር ጉባኤ ላይ ይፋ አደረገ!
በጉባኤው ወቅት የድሮጋ ቡድን ለተሳታፊዎች ያስተዋወቃቸው ዘመናዊ አሰራሮች የሕመምተኞችን የመድኃኒት አቅርቦት ፍላጎት፣ ምቾት እና የፋርማሲ የመድኃኒት አቅርቦት ጥራት በከፍተኛ ደረጃ የሚያሻሽሉ ናቸው።
ድሮጋ ቼይን ፋርማሲ (Droga Chain Pharmacy) በኢትዮጵያ ፋርማሱቲካል ማህበር (EPA) 46ኛው ዓመታዊ ሳይንሳዊ ጉባኤ እና ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በታላቅ ኩራት የተሳተፈ ሲሆን፣ ከመላው ኢትዮጵያ ከተሰበሰቡ የፋርማሲ ባለሙያዎች ጋር በቅርበት ተወያይቷል።
ካስተዋወቃቸውም አዳዲስ አገልግሎቶች መካከልም
• Droga Digital Pharmacy (ድሮጋ ዲጂታል ፋርማሲ)፦ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ የመድኃኒት አቅርቦትና አገልግሎት ሲሆን፣ ታካሚዎች ያሏቸውን የመድኃኒት ማዘዣዎች (Prescriptions) በቀላሉ በማስገባት የመድኃኒት አቅርቦትንና መረጃን በጥራትና በፍጥነት እንዲያገኙ ያመቻቻል።
• 💳 Yene Loyalty Card, Reward & Discount Programs (የኔ ካርድ እና የቅናሽ ፕሮግራሞች)፦ ደንበኞች በየጊዜው ለሚያደርጉት የመድኃኒትና የጤና ቁሳቁሶች ግዢ ልዩ ልዩ ማበረታቻዎችን፣ ነጥቦችን እና የቅናሽ እድሎችን የሚያገኙበት አሰራር ነው።
• Medication Therapy Management - MTM (የመድኃኒት ሕክምና አስተዳደር)፦ በፋርማሲስቶች የሚሰጥ ታካሚ-ተኮር የህክምና ክትትል ሲሆን፣ ታካሚዎች የሚወስዷቸው መድኃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት እንዳያመጡ፣ እርስ በእርስ እንዳይጋጩ እና ትክክለኛውን ፈውስ እንዲሰጡ በቅርበት የመከታተል አገልግሎት ነው።
እነዚህን ዘመናዊ የድሮጋ አገልግሎቶች ለማግኘትም
• በቅርንጫፎቻችን በመገኘት፦ በማንኛውም የድሮጋ ቼይን ፋርማሲ ቅርንጫፍ በመገኘት የ"የኔ" የታማኝነት ካርድ አባል መሆን እና የቅናሽ ፕሮግራሞች ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ።
• በዲጂታል አማራጭ፦ በድሮጋ ዲጂታል ፋርማሲ አማካኝነት የህክምና ማዘዣዎን በመላክ እና የባለሙያ ምክር በማግኘት ጊዜዎን እና ጉልበትዎን መቆጠብ ይችላሉ።
• የፋርማሲስት ክትትል፦ ስለሚወስዷቸው መድኃኒቶች አወሳሰድ እና ጥንቃቄዎች በ MTM ፕሮግራማችን አማካኝነት ከባለሙያ ፋርማሲስቶቻችን ጋር በግል መማከር ይችላሉ።
ዋናው መልዕክት
በፈጠራ፣ በትብብር እና በላቀ የፋርማሲ ሙያ አሰራር አማካኝነት ጤናማዋን ኢትዮጵያ በጥሩ የመገንባት ጉዟችንን አጠናክረን እንቀጥላለን። የሕመምተኞችን ተደራሽነትና ምቾት ማረጋገጥ ሁልጊዜም የመጀመሪያ ግባችን ነው!
ለተጨማሪ ጠቃሚ የጤና እና የፋርማሲ መረጃዎች ገጻችንን Follow ያድርጉ!
Droga Pharmacy
Looking After Your Health !!!