29/05/2026
ሁልጊዜ የመዛል እና የድካም ስሜት ይሰማዎታል? 🥱
ድካም ከተለያዩ የጤና እና የኑሮ ዘይቤ ምክንያቶች ሊመነጭ ይችላል። ዋና ዋናዎቹን እነሆ፦
☕ ቡና/ማኪያቶ ማዘውተር
ከሰዓት በኋላ ወይም በምሽት ቡና መጠጣት የእንቅልፍ ጥራትን ስለሚቀንስ ድካምን ያስከትላል
🍛 የአመጋገብ ሁኔታ
ጠዋት ቁርስ መዝለል፣ በፆም ወቅት አልሚ ምግብ አለማግኘት፣ የተቀነባበሩ ምግቦችን ማዘውተር እና ስኳር ማብዛት፣ በቂ ካሎሪ እና ፕሮቲን/ንጥረ ነገሮች አለማግኘት እና የውሃ እጥረት💧
💤 የእንቅልፍ እጦት
በቂ እንቅልፍ አለማግኘት፣ መደበኛ ያልሆነ የእንቅልፍ መርሀ ግብር፣ ጥራት የሌለው እንቅልፍ (በተደጋጋሚ መንቃት)
🏃♂️ የእንቅስቃሴ ማነስ ወይም መብዛት
ቀኑን ሙሉ መቀመጥ በሚገርም ሁኔታ የሰውነትን ጉልበትን ያዳክማል እንዲሁም ከመጠን በላይ እንቅስቃሴ ያለ እረፍትና በቂ ምግብ ማድረግም ድካም ያመጣል
🧠 ውጥረት/ጭንቀት እና ድብርት
ከልክ ያለፈ የአእምሮ ውጥረት እና ሃሳብ የአካልና የአእምሮ ብርታትን በእጅጉ ያሟጥጣሉ
🩺 የጤና እክሎች
የደም ማነስ፣ የቪታሚን እጥረት፣ የታይሮይድ ችግር፣ የስኳር በሽታ ወይም የእንቅልፍ አፕኒያ (በእንቅልፍ ሰዐት የትንፋሽ መቆራረጥ)
💊 አንዳንድ መድሃኒቶች
የተወሰኑ መድሃኒቶች እንቅልፍ እንቅልፍ ማለትን ያስከትላሉ፣ ከመጠን በላይ አልኮልም ከቆየ በኋላ ድካምን ሊያመጣ ይችላል
❗ከድካም ስሜቱ ጋር አብሮ የክብደት መቀነስ፣ ትንፋሽ ማጠር፣ የደረት ህመም፣ ትኩሳት፣ ማዞር ካለ ወይም ድካሙ ከሳምንታት በላይ ከቀየ ምርመራ ማድረግ ይመከራል