14/08/2026
ከመጠን ያለፈ ውፍረት እና መካንነት
ከመጠን ያለፈ ውፍረት (Obesity) የሰውነት ሆርሞን ሚዛንን እና የስነ-ተዋልዶ ስርዓትን ሊያዛባ ስለሚችል በሴቶችም ሆነ በወንዶች የመፀነስ እድልን ሊቀንስ ይችላል። ይህ ማለት ውፍረት ያለባቸው ሰዎች ልጅ መውለድ አይችሉም ማለት አይደለም፤ ተገቢ ግምገማና እንክብካቤ እድሉን ሊያሻሽል ይችላል።
👩 በሴቶች ላይ እንዴት ይጎዳል?
⭐️ የእንቁላል መልቀቅ (Ovulation) መዛባት ወይም መቋረጥ
⭐️ የወር አበባ ዑደት መዛባት
⭐️ ከፍ ያለ የኢንሱሊን መቋቋም (Insulin Resistance) እና የሆርሞን ሚዛን መዛባት
⭐️ በተለይ ከPCOS ጋር ተያይዞ የመፀነስ ችግር መጨመር
⭐️ በIVF ህክምና ወቅት የህክምና ውጤቶችን ሊያውክ የሚችል ተፅዕኖ
👨 በወንዶች ላይ እንዴት ይጎዳል?
⭐️ የTestosterone መጠን መቀነስ
⭐️ የወንድ ዘር ብዛትና እንቅስቃሴ መቀነስ
⭐️ የወንድ ዘር ጥራት መጎዳት
⭐️ የፆታ ፍላጎት ወይም የብልት መቆም ችግር ሊከሰት መቻል
ውፈረትን የመከላከያ መንገዶች
🥗 የተመጣጠነ ምግብ መመገብ
🚶 መደበኛ የአካል እንቅስቃሴ
💧 በቂ ውሃ መጠጣት
👩⚕️ ከሐኪም ወይም ከአመጋገብ ባለሙያ ጋር ተገቢ የክብደት ቅነሳ እቅድ ማዘጋጀት
ከመጠን ያለፈ ውፍረት የመፀነስ እድልን ሊቀንስ ቢችልም መካንነት ብቻውን የሚያመጣ ምክንያት አይደለም። የመካንነት ምክንያቱን ለማወቅ ሁለቱም ጥንዶች ተገቢውን የመፀነስ ምርመራ ማድረግ ይገባቸዋል።
እርስዎ ወይም ባለቤትዎ የመፀነስ ችግር ካለባችሁ፣ ምክንያቱን በትክክል ለማወቅ በAdo Fertility Clinic ተገቢውን የወሊድ ምርመራ እና ምክር ያግኙ።
ቀጠሮ ለማስያዝ በ 09127777780 ይደውሉልን።
📍 አድራሻችን፡ አዲስ አበባ፣ ኬንያ ኢምባሲ ፊት ለፊት፣ ሀ ቤት ህንፃ 1ኛ ፎቅ ያገኙናል።