Ethioscandic Clinics

Ethioscandic Clinics ኢትዮ ስካንዲክ የቀድሞ የወንድይራድ ተማሪዎች እና የኮተቤ ልጆች የተቋቋመ ሲሆን አላማው ለአካባቢው ደረጃውን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት መስጠት ነው

ልጆችን በቤት ውስጥ ስራ ማሰራት======================= ጥናቶች እንደሚያሳዩት ልጆች የቤት ውስጥ ስራ ወላጆቻቸውን የሚያግዙ ከሆነ፣ በመጪ ዘመናቸው ፡-1-  ከወላጆቻቸው ጋር የ...
07/04/2026

ልጆችን በቤት ውስጥ ስራ ማሰራት
=======================
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ልጆች የቤት ውስጥ ስራ ወላጆቻቸውን የሚያግዙ ከሆነ፣ በመጪ ዘመናቸው ፡-
1- ከወላጆቻቸው ጋር የተሻለ ተግባቦት ይኖራቸዋል፡፡
2- ኃላፊነት የሚሰማቸው ግለሰቦች ይወጣቸዋል፡፡
3- ቤት ውስጥ አስፈላጊ የቤተሰቡ አባል እንደሆኑ እንዲሰማቸውና ለራሳቸው የሚኖራቸው ክብር እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
4- ሥራ አጥ የመሆን እድላቸው ዝቅተኛ ነው፡፡ ሥራቸውን ጠብቀው የመቆየት እድላቸውም ከፍ ያለ ነው፡፡
4- ለሱስ የሚኖራቸው ተጋላጭነትም ዝቅተኛ ነው፡፡

ስለዚህ ልጆችን ቤት ውስጥ ስራ እንዲያግዙን ማድረግ እንደሕጻናት ጉልበት ብዝበዛ ሊቆጠር አይገባም፡፡ ምን ምን ይስሩ?

አልጋ ማንጠፍቤት ማስተካከል፣ ቤት ማጽዳትምግብ ማዘጋጀት፣ ምግብ ለቤተሰቡ ማቅረብ፣ የተበላባቸውነ ዕቃ እንዲመልሱ ማድረግ ፣ እንዲያጥቡ ማድረግ (ሁለቱም ጾታዎች እኩል ማሳተፍዎን አይዘንጉ) የጓሮ አትክልት መንከባከብ፣ የቤት እነስሳት መንከባከብ መላላክ እና የመሳሰሉትን መስራት ይችላሉ።

"እናንተ ልጆቻችሁን ታሰራላችሁ ወይ?" ለሚለው ጥያቄ፡ "እየሞከርን ነው! " 😊
https://www.facebook.com/1368127853/posts/10242088210286283/?app=fbl
Via
Mezgeb Gedefe Molla

የጥለዛ ሰንሰለት==========አንድ የሥራ ኀላፊ ወደ ቢሮው ሲጓዝ ከሌላ አሽከርካሪ ጋራ ይጨቃጨቅና ይበሳጫል። ከነብስጭቱ ቢሮው ሲገባ ጠረጴዛ ላይ ወረቀት ተዝረክርኮ ያገኛል። ይህ በአብዛኛ...
03/04/2026

የጥለዛ ሰንሰለት
==========
አንድ የሥራ ኀላፊ ወደ ቢሮው ሲጓዝ ከሌላ አሽከርካሪ ጋራ ይጨቃጨቅና ይበሳጫል። ከነብስጭቱ ቢሮው ሲገባ ጠረጴዛ ላይ ወረቀት ተዝረክርኮ ያገኛል። ይህ በአብዛኛው ቀናት ያለ ሁነት ነው። ነገር ግን ከቁጣ ፈረሱ ገና አልወረደምና ጸሓፊዋን ጠርቶ ዝርክርክነቷን ነግሯት ሁለተኛ እንዲህ ያለ ነገር እንዳይለመድ ያስጠነቅቃታል። ከሌላ ቀናት የተለየ ነገር ባለመኖሩና በዚህ ልክ ሲጮህባት ጸሐፊ ትበሳጫለች።
ከአለቃዋ ቢሮ እንደወጣች ጽዳቷን በር ላይ ታገኛታለች።
“ጠረጴዛውን አይተሽው ታውቂያለሽ?” በቁጣ፤
“አዎ ጠዋት አፅድቼዋለሁ፤ ንጹህ ነው። ዛሬ ደግሞ ምን ሆነሻል መዓዚ?”
“መዓዚ አትበይኝ ሂጂና እይው” … “ከዛሬ ጀምሮ ከኔ ቀድመሽ ገብተሸ ሁሉንም ነገር ዕፅድተሸ ትጠብቂኛለሽ፤ ጽዳት ማለት ወለል ብቻ አይደለም፤ ጠረጴዛውም፣ ወንበሩም ግድግዳውም ይመለከትሻል”
“እሱን ዐውቃለሁ፤ የኖርኩበት ሥራ እኮ ነው” እያጉረመረመች ትወጣለች።
🤦‍♂️
ይች የጽዳት ሠራተኛ ቀኑን ሙሉ ስትብሰከሰክ ትውልና ቤት ትደርሳለች። የአምስት ዓመት ልጇ ውጪ ወጥቶ እየተጫወተ አቧራ በአቧራ ሆኖ ታገኘዋለች። “ማን እንዲያጥብልህ ነው፤ ልብሱን እንዲህ ያበሻቀትከው?” … “ና ግባ!” ብላ እያስጮኸች ጎትታ ታስገባዋለች።
እናቱ ከጨዋታው ስላቋረጠችውና ስለጮኸችበት የተናደደ ሕጻን የበሩ ደፍ ላይ የተኛችን ምስኪን ድመት ይጠልዛታል።
---
- እንዲህ ያሉ ምላሾች “ምስኪን ድመትን መጠለዝ” ነው የሚባሉት።
😿 አዎ! ድመት ጠላዥ አንሁን!

ከሰዎች ጋራ የሚኖረን ተግባቦት (በተለይ ከልጆች ጋራ) በነቃ አእምሮ የተቃኘ ሊሆን ይገባል፡፡







Mezgeb Gedefe Molla

Address

የካ ክ/ከ ወረዳ 13 ወሰን ግሮሰሪ አካባቢ
Addis Ababa

Telephone

+251930031317

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethioscandic Clinics posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share