ሀሪሰን

ሀሪሰን ✨ Unlocking the Secrets to a Healthier You! ✨
Welcome to our Facebook Acount! In today’s post, we're diving deep into the world of health and wellness.

Are you ready to transform your lifestyle and achieve your health goals? Join us as we explore:

02/06/2026
 #መቃብር እስካልገባህ ድረስ ብትወድቅ እንኳን የሰው ልጅ ክፋትና ጭካኔ ገደብ የለውም።እግዚአብሔር ይማርህሀሪሰን የቲክቶክ አካውንቴን ተከታተሉ
30/05/2026

#መቃብር እስካልገባህ ድረስ ብትወድቅ እንኳን የሰው ልጅ ክፋትና ጭካኔ ገደብ የለውም።
እግዚአብሔር ይማርህ

ሀሪሰን የቲክቶክ አካውንቴን ተከታተሉ

በጤና እና በጥንካሬ ረጅም እድሜ የመኖር ሚስጥሮች!ረጅም ዕድሜን የመኖር ሚስጥር ማለት አስማታዊ መፍትሄ ማግኘት ማለት አይደለም፤ ይልቁንም በየቀኑ የሰውነት/አዕምሮ ጤና እና ጥንካሬን የሚጠብ...
28/05/2026

በጤና እና በጥንካሬ ረጅም እድሜ የመኖር ሚስጥሮች!

ረጅም ዕድሜን የመኖር ሚስጥር ማለት አስማታዊ መፍትሄ ማግኘት ማለት አይደለም፤ ይልቁንም በየቀኑ የሰውነት/አዕምሮ ጤና እና ጥንካሬን የሚጠብቁ ትናንሽ ልምዶችን ማዳበር ማለት ነው

🥗 ጤናማ አመጋገብ እና የሰውነት ክብደት

• ላልተቀነባበሩ የተፈጥሮ ምግቦች ቅድሚያ ይስጡ! አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ጥራጥሬ፣ ሙሉ እህሎች፣ ጤናማ ስቦች (ለውዝ፣ አቮካዶ ...) እና ከእፅዋት የሚገኙ ፕሮቲኖች ላይ ትኩረት ያድርጉ

• የተቀነባበሩ ምግቦችና ስኳርን ይቀንሱ እንዲሁም ጤናማ የሰውነት ክብደት እንዲኖርዎ ያድርጉ

​🏃‍♂️ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ

• እንደ ፑሻፕ፣ ክብደት ማንሳት አይነት የጥንካሬ ስፖርቶችን መስራት የጡንቻ መመናመንና የአጥንት መሳሳትን ይከላከላል

• ፈጣን መራመድ እና ሳይክል መንዳት የመሳሰሉ የትንፋሽና ካርዲዮ እንቅስቃሴዎች ለልብና አዕምሮ ጤንነት ጠቃሚ ናቸው

• የማሳሳብ እና የፍሌክሰቢሊቲ እንቅስቃሴዎች ደግሞ ለመገጣጠሚያዎች ጤንነትና የሰውነት ቅልጥፍናን ለማስጠበቅ ይረዱናል

​💤 ጥሩ እንቅልፍ ማግኘት እና ጭንቀትን መቆጣጠር

• በአማካይ ከ7-9 ሰዐት ጥራት ያለው እንቅልፍ ያግኙ፣ እንዲሁም በተመሳሳይ ሰዐት መተኛትና መነሳትን ልምድ ያድርጉ

• ስር የሰደደ ጭንቀትን በጥሩ ማህበራዊ ግንኙነት፣ ፀሎት፣ በአካል እንቅስቃሴ፣ ከተፈጥሮ ጋር ጊዜ በማሳለፍ በመሳሰሉት መቆጣጠር ያስፈልጋል

​👥 ማህበራዊ ግንኙነትን ማጠናከርና የህይወት አላማ መኖር

• ከቤተሰብ፣ ከጓደኞች ወይም ከማህበረሰብ ጋር ጥብቅ ግንኙነት መኖር ለረጅም ዕድሜ ትልቅ ሚና አለው። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ብቸኝነት ለጤና አደገኛ ነው

• ጠንካራ የህይወት ዓላማ መኖር አእምሮን ንቁ ያደርጋል፣ ጭንቀትን ይቀንሳል እንዲሁም በጤና ረጅም እድሜ ለመኖር አስተዋፅኦ አለው

​🚫 ቅድመ ጥንቃቄዎች እና ክትትሎች

• ማጨስን ያቁሙ እና የአልኮል መጠጥን ይቀንሱ

• የሕክምና ምርመራዎችን ያድርጉ! የደም ግፊትን፣ ኮሌስትሮልን እና የደም ስኳርን በየጊዜው መመርመር በሰውነት ክፍሎችዎ ላይ ዘላቂ ጉዳት ከመድረሱ በፊት ችግሮችን አስቀድሞ ለማወቅና ለመቆጣጠር ይረዳል

በጥንቃቄ ጤናን እየጠበቁ 100 አመት መኖር ወይስ የፈለጋቹትን እየበላችሁ እና እያደረጋችሁ 70 አመት መኖር? የቱን ትመርጣላችሁ❓❔

የኔ ውዶች የት ከተማ ነው ያላችሁ እንተዋወቅ እኔ የምኖረው አዲስ አበባ ነኝ እናተስ
28/05/2026

የኔ ውዶች የት ከተማ ነው ያላችሁ እንተዋወቅ እኔ የምኖረው አዲስ አበባ ነኝ እናተስ

የተመቻችሁን አለባበስ በኮመንት ያካፍሉኝ
27/05/2026

የተመቻችሁን አለባበስ በኮመንት ያካፍሉኝ

24/05/2026
የትኛው ሙዝ ነው ለመብላት ዝግጁ
23/05/2026

የትኛው ሙዝ ነው ለመብላት ዝግጁ

ያስረጃል የሚባለው ስጋ በአግባቡ ከተመገብነው እርጅናን እንደሚያዘገይ ያውቃሉ?ምንም እንኳን በተለምዶ ስጋ ያስረጃል ቢባልም በሳይንስ የተረጋገጠው ግን ተቃራኒው ነው ፣ ስጋ እርጅናን ለማዘግየ...
21/05/2026

ያስረጃል የሚባለው ስጋ በአግባቡ ከተመገብነው እርጅናን እንደሚያዘገይ ያውቃሉ?

ምንም እንኳን በተለምዶ ስጋ ያስረጃል ቢባልም በሳይንስ የተረጋገጠው ግን ተቃራኒው ነው ፣ ስጋ እርጅናን ለማዘግየት የሚያግዙ ንጥረ ነገሮችን በውስጡ ይዟል

ስጋ እርጅናን ለማዘግየት የሚያግዝባቸው መንገዶች :-

◈ ቆዳችን እንዳያረጅ ያደርጋል

ስጋ ከፍተኛ ጥራት ያለው ፕሮቲን ስለሚይዝ ማለትም ፕሮሊን እና ግላይሲን የተባሉ አሚኖ አሲዶች ስላሉት ኮላጅንን በደምብ በማምረት ቆዳ እንዳይሸበሸብ እና እንዳያረጅ ያደርጋል

◈ ጡንቻችንን ያስጠብቃል

አንደኛው የእድሜ መግፋት ምልክት የጡንቻ መሳሳት ነው፣ ጡንቻ ደግሞ እድሜያችን በገፋ ቁጥር ጥንካሬያችንን ጠብቀን ለመቆየት የሚያስፈልገን ዋነኛው ነገር ነው፤ ስጋ በውስጡ ሉሲን የሚባል አሚኖ አሲድን ይይዛል፤ ይህም ሰውነታችን ጡንቻን እንዲጠግንና እንዲገነባ ትዕዛዝ የሚያስተላልፍ "ኬሚካላዊ ሲግናል" ነው

◈ ጉልበት እንዲኖረን ያደርጋል

እድሜ በገፋ ቁጥር ዋናው የሚያስቸግረን ነገር ጉልበት ማጣት ነው፤ ስጋ ከፍተኛ ሀይል ሰጪ ምግብ ሲሆን ስኳር ከፍ የማያደርግ የማይቋረጥ ሀይል ይለቃል። በተጨማሪም እድሜ ሲገፋ የምግብ ፍላጎት ስለሚቀንስ ትንሽ በልተን ብዙ የምናገኝበት ምግብ ነው

◈ መርሳትና የአዕምሮ መድከምን ይከላከላል

ስጋ ቢ12፣ ካርኖሲን እና ክሬቲንን ስለሚይዝ የማሰብ ፍጥነት፣ ትኩረት እና ንቃት እንዲኖረን ያደርጋል እንዲሁም የማስታወስ ችሎታ መቀነስን ይከላከላል

◈ ሰውነታችን እንዳይዝግ ይከላከላል

ስጋ የካርኖሲን ብቸኛ መገኛ ነው። ይህ ሞለኪውል ስኳር በሰውነታችን ውስጥ ፕሮቲኖችንና ዲ ኤን ኤን እንዳያጠቃ በመከላከል፣ የውስጥ አካላታችን፣ ጡንቻዎች፣ መገጣጠሚያዎች፣ ጭንቅላታችንና ቆዳችን እንዳይዝጉ ይንከባከባል

✅ እንዴት ብንመገበው እነዚህን ጥቅሞች እናገኛለን?

◈ በመጠኑ እና አለፍ እያልን መመገብ (በየቀኑ እና ብዙ መጠን አለመመገብ- በሳምንት ከግማሽ ኪሎ ባይበልጥ ይመከራል)

◈ ከአትክልቶች ጋር አመጣጥኖ መመገብ (አንታይ ኦክሲደንቶችን ከአትክልቶች ለማግኘት እንዲሁም ድርቀት እና የምግብ አለመፈጨት እንዳይኖር ያደርጋል)

◈ ጨው/ቅባት ሳይበዛበት እና ሳያር/በጣም ሳይጠበስ ማብሰል እንዲሁም ጮማ/ስብ የሌለውን ስጋ መብላት

🔴 ስጋ ያስረጃል የሚለው አባባል ከየት እንደመጣ ያውቃሉ?
👇👇👇

🚨ከአንድ ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት መሰጠት የሌለባቸው ምግቦች !!🚼ህፃናት 6 ወር ሲሞላቸው ከእናት ጡት ወተት ወይም ከፎርሙላ በተጨማሪ ተጨማሪ ምግቦችን መጀመር ይኖርባቸዋል። ይህ ማለት ግ...
16/05/2026

🚨ከአንድ ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት መሰጠት የሌለባቸው ምግቦች !!

🚼ህፃናት 6 ወር ሲሞላቸው ከእናት ጡት ወተት ወይም ከፎርሙላ በተጨማሪ ተጨማሪ ምግቦችን መጀመር ይኖርባቸዋል። ይህ ማለት ግን ሁሉም ምግቦች እና መጠጦች ተስማሚ ናቸው ማለት አይደለም። አንዳንድ ምግቦች በፍጹም ከ አንድ ዓመት በታች ላሉ ህፃናት መሰጠት የለባቸውም። እነዚህም

🍯ማር (Honey)

ማር ዕድሜያቸው ከ12 ወር በታች ለሆኑ ሕፃናት በፍጹም መሰጠት የለበትም። ማር "ቦቱሊዝም" (botulism) የተባለ አደገኛ የነርቭ ችግር ሊያስከትል ይችላል።

🐟ከፍተኛ ሜርኩሪ ያላቸው ዓሳዎች

እንደ ቱና (tuna) ያሉ አንዳንድ ዓሳዎች ከፍተኛ የሜርኩሪ መጠን አላቸው። ይህም የሕፃናትን በማደግ ላይ ያለ አእምሮ እና የነርቭ ሥርዓት ሊጎዳ ይችላል።

🥛የላም ፣ የፍየል ወይም የበግ ወተት

የላም ወተትን ከ12 ወር በፊት ለልጅዎ መስጠት ለአንጀት መድማት ሊዳርገው ይችላል። ከዚህ በተጨማሪም ከፍተኛ የፕሮቲን እና የሚነራል ይዘት ስላለው በሕፃኑ ኩላሊት ላይ ጫና ይፈጥራል። ለሕፃናት የሚያስፈልጉ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችንም በተመጣጣኝ ሁኔታ አይዝም። የፍየል እና የበግ ወተትም ተመሳሳይ ችግር ሊያስከትሉ እና የአለርጂ ስሜትን ሊቀሰቅሱ ስለሚችሉ ተስማሚ አማራጮች አይደሉም።

🧀በቤት ውስጥ የተዘጋጁ በፋብሪካ ያልተጣሩ (Unpasteurized ) እርጎዎች ወይም አይብ

በቤት ውስጥ የተዘጋጁ በፋብሪካ ያልተጣሩ (Unpasteurized ) እርጎዎች ወይም አይብ ለከባድ ህመም እና ተቅማጥ የሚዳርጉ ጎጂ ባክቴሪያዎችን ሊይዙ ይችላሉ። ለሕፃናት ሁልጊዜ በፋብሪካ የተጣሩ (pasteurized) አማራጮችን ይምረጡ።

🍰ስኳር የተጨመረባቸው ምግቦች እና መጠጦች

ከአንድ ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት ተጨማሪ ስኳር አያስፈልጋቸውም። ስለዚህ እንደ ኩኪስ፣ ኬክ፣ ጣፋጭ እርጎዎች እና የታሸጉ ጭማቂዎችን ያሉ ስኳር ያላቸውን ምግቦች አይስጧቸው። ገና በልጅነት ስኳር መውሰድ ለጥርስ መበስበስ፣ ለውፍረት እና ለሌሎች የጤና ችግሮች ተጋላጭነትን ይጨምራል።

☕️ካፌይን ያላቸው መጠጦች

ዕድሜያቸው ከ2 ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት እንደ ሻይ ወይም ቡና ያሉ ካፌይን የያዙ መጠጦችን መስጠት ፈፅሞ አይመከርም። የሕፃናት ሰውነት ካፌይንን የማጣራት አቅም ስለሌለው ለእንቅልፍ መዛባት፣ለልብ ምት መጨመር ፣ለሰውነት ፈሳሽ እጥረት እንዲሁም ለመነጫነጭ ይዳርጋቸዋል። ካፌይን ለአጥንት ጥንካሬ የሚያስፈልገውን የካልሲየም ንጥረነገር በሰውነት እንዳይወሰድ ያደርጋል።

🌭ከፍተኛ ጨው (ሶዲየም) ያላቸው ምግቦች

እንደ ሃም፣ ቋሊማ(sausages) ያሉ የተለያዩ የታሽጉ ምግቦች በውስጣቸው ከፍተኛ የጨው ወይም የሶዲየም ይዘት ስላላቸው ከአንድ ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት አይመከሩም። ምክንያቱም ኩላሊታቸው ገና በማደግ ላይ ስለሆነ ከፍተኛ ጨውን ማጣራት አይችልም።

👩‍⚕️👨‍⚕️ጤና ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ወይንም ለማማከር ☎️ 0910755626 ላይ ይደውሉ ።

10/05/2026

🌬 የአስም በሽታን ለመቆጣጠር የሚረዱ የጤና ምክሮች! | Health Tips for Managing Asthma!
✦────────────────────────✦

አስም በመተንፈሻ አካላት ላይ በሚፈጠር መቆጣት እና መጥበብ ምክንያት የመተንፈስ ችግር የሚያስከትል የጤና እክል ነው።

ነገር ግን ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ፤ አብዛኞቹ አስም ያለባቸው ሰዎች ንቁ እና ጤናማ ህይወት መምራት ይችላሉ።

▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰

✅💥 ለአስም በሽታ የሚረዱ የጤና ምክሮች!
――――――――――――――――――――

🫁 1️⃣. አስም ቀስቃሽ ነገሮች (Triggers) ይለዩ!
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

የአስም ምልክቶች በአካባቢ ሁኔታዎች ወይም በአኗኗር ዘይቤ ሊቀሰቀሱ ይችላሉ። በብዛት አስምን ከሚያስነሱ ነገሮች መካከል፦

🔸 አቧራ እና የአበባ ብናኞች
🔸 ጭስ (የሲጋራ፣ የከሰል ወይም የማገዶ ጭስ)
🔸 ቅዝቃዜ ወይም ድንገተኛ የአየር ሁኔታ ለውጥ
🔸 ኃይለኛ ወይም ሃይለኛ ሽታ ያላቸው ነገሮች (ሽቶዎች፣ የጽዳት ኬሚካሎች)
🔸 የሳምባና የጉሮሮ ኢንፌክሽኖች (እንደ ጉንፋን ያሉ)
👉 አስምዎን የሚቀሰቅሱብዎን ነገሮች ለይተው ይወቁ እናም ከእነሱ ለመራቅ ይሞክሩ።

💊 2️⃣. መድሃኒቶችን በአግባቡ ይውሰዱ!
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

የአስም ህክምና አብዛኛውን ጊዜ ሁለት አይነት መድሃኒቶችን ይይዛል፦

🔹 አፋጣኝ እፎይታ የሚሰጡ (Relievers)፦ የትንፋሽ ማጠር ሲከሰት ወዲያውኑ የሚረዱ።
🔹 ለመከላከያነት የሚያገለግሉ (Controllers)፦ የሳምባ መቆጣትን ለመቀነስ በቋሚነት (በየቀኑ) የሚወሰዱ።

👉 ምንም እንኳ ደህና እንደሆኑ ቢሰማዎትም መድሃኒትዎን በሰዓቱ ይውሰዱ፣ እንዲሁም ያለ ሐኪም ትዕዛዝ አያቋርጡ።

🏠 3️⃣. የመኖሪያ አካባቢዎን ንጽህና ይጠብቁ!
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

🔸 የአልጋ ልብሶችን በሞቀ ውሃ አዘውትረው ይጠቡ።
🔸 በቤት ውስጥ አቧራና እርጥበት (ሻጋታ) እንዳይኖር ያድርጉ።
🔸 ለቤት እንስሳት የፀጉር ብናኝ አለርጂ ካለብዎት የቤት እንስሳትን ያርቁ።
🔸 በቤትዎ ውስጥ በቂ የአየር ዝውውር እንዲኖር ያድርጉ።

🚭 4️⃣. ከሲጋራና ከሌሎች ጭሶች ይራቁ!
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

ጭስ የመተንፈሻ አካላትን ያቆስላል፤ እንዲሁም የሳምባን የመሥራት አቅም ይቀንሳል።

👉 ከሚያጨሱ ሰዎችና ጭስ ከበዛበት አካባቢ ይራቁ፤ በቤት ውስጥም ጭስ እንዳይኖር ጥንቃቄ ያድርጉ።

🏃♂️ 5️⃣. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ (በጥንቃቄ)!
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

አዘውትሮ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ሳምባን ያጠነክራል። ነገር ግን በጣም ከባድ እንቅስቃሴ አስምን ሊቀሰቅስ ይችላል።

👉 እንቅስቃሴ ከመጀመርዎ በፊት ሰውነትዎን በደንብ ያሟሙቁ፤ የታዘዘልዎትን የድንገተኛ ጊዜ ኢንሄለር (Inhaler) ሁልጊዜ ይያዙ።

🧊 6️⃣. ራስዎን ከቅዝቃዜ ይከላከሉ!
••••••••••••••••••••••••••••••••••••

ቀዝቃዛና ደረቅ አየር የመተንፈሻ ቱቦዎችን ሊያቆስልና ሊያጠብ ይችላል።

👉 በቀዝቃዛ አየር ወቅት አፍና አፍንጫዎን በሻርፕ ወይም በጭንብል (Mask) ይሸፍኑ።

🦠 7️⃣. ራስዎን ከኢንፌክሽን ይጠብቁ!
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

የመተንፈሻ አካል ኢንፌክሽኖች

Address

Addis Ababa

Telephone

+251934198668

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሀሪሰን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share