ዶ/ር ይህዓለም ታምሩ-Yihalem Tamiru Ph.D.

ዶ/ር ይህዓለም  ታምሩ-Yihalem Tamiru Ph.D. Politician & researcher. Yihalem Tamiru, Ph.D. in Food Science & Nutrition, Addis Ababa University. Dr. Yihalem Tamiru Semegn holds a Ph.D.

in Food Science and Nutrition, along with Master’s and Bachelor’s degrees in Public Health, all from Addis Ababa University. With nearly 15 years of experience, he specializes in public health, food science, and nutrition, focusing on School Food and Nutrition, Food Safety, and Hygiene. His research has been published in prominent journals, including the Journal of Nutritional Science and Clinical

Nutrition Open Science. Dr. Yihalem served as a national consultant for HIV/AIDS counseling and testing with the World Health Organization for three years. He was the Senior HCT HIV/AIDS Advisor at JHU-TSEHAI, working closely with the Ministry of Health. Additionally, he has led the national expert group on the HIV/AIDS Counseling and Testing Technical Working Group for over six years. His diverse experience includes roles as a public health analyst at the Ethiopian Public Health Institute and as Nutrition Manager for EOTC-DICAC. Most recently, Dr. Yihalem was Chief of Party/Program Director for a USAID HIV Epidemic Control Grant, where he managed resources and implemented strategic programs to combat the HIV epidemic and support vulnerable children through Love in Action Ethiopia.

የዘንድሮን የጌታችን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በአልን ከትብብር ለኢትዮጰያ አንድነት የበላይ አመራሮች ጋር አንድ ላይ በመሆን በቂሊንጦ እስር ቤት ውስጥ ከሚገኙት የህሌና ና...
13/04/2026

የዘንድሮን የጌታችን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በአልን ከትብብር ለኢትዮጰያ አንድነት የበላይ አመራሮች ጋር አንድ ላይ በመሆን በቂሊንጦ እስር ቤት ውስጥ ከሚገኙት የህሌና ና የግፍ እስረኞች ከሆኑት ከአማራ ሙህራን እና ጋዜጠኞች እንዲሁም የሰባዊ መብት ተማጋቾች ጋር በማሳለፊ እጅግ ትልቅ ኩራት ይሰማኛል:: ካሳለፍኃቸው ብዙ የፋሲካ በአላትም በአይነቱ ወርቃማ ና የተለየ ያደርገዋል!
በሂደቱም ካስተዋልኳቸው ሁነቶች ውስጥ ከእያንዳንዳቸው ወንድሞች በግልፅ የሚነበብ የስነ ልቦና ጥንካሬ ና ያይበገሬነት የመንፈስ ዕናት እንዲሁም የሚንቦገቦግ የወንድም ና የሀገር ፍቅርን ማየት ችያለሁ!
በዚህ ሂደት ውስጥ እድሉን አግገኝቼ ከአወጋኃቸው ወንድሞቼ መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል
1. የተከበሩ ክርስቲያን ታደለ
2. የተከበሩ ዮሐንስ ቡያለው
3. የተከበሩ ዶ/ር ካሳ ተሻገር
4. ዶ/ር ቴዎድረስ ኃ/ማሪያም
5. ዶ/ር ሲሳይ አውግቼው
6. ረዳት ፕ/ሮ ማረጉ ብያብን
7. ዶ/ር ጫኔ ከበደ
8. ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ
9. ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው…ና የመሳሰሉት የሀገር የቁርጥ ቀን ልጆች ይገኙበታል!
በመጨረሻም ለሀገራችን ሹማምንቶች ማሳሰብ የምፈልገው ሩቅ እንዳታስቡ ወይም እንዳታዩ አይናቸውን የጋረደውን ጉም እግዚአብሔር እንዲገፍላቸው እየተመኘሁ! በሀገራችን ውስጥ ዘላቂ ሰላም ፍትህ ነፃነት ና እኩልነት እንዲሰፍን ላማድረግ አንዲሁም በጭንቅ ውስጥ ያለውን ና ጥርቅም ብሎ ለመዘጋት የተቃረበውን የዲሞክራሲዊ ስርዓትን ና የፖለቲካ ምህዳር በሚፈለገው ደረጃ ለማስፋት የፖለቲካ ውሳኔ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች ልዩ ትኩረት በመስጠት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ኃላፊነት እንደሚሰማው አንድ ዜጋ ማሳሰብ እፈልጋለሁ!. እግዚአብሔር ኢትዮጴያን ይባርክ!

ዶ/ር ይህዓለም ታምሩ
አዲስ አበባ ኢትዮጰያ
ቀን 4/8/2018 ዓ.ም

የምረጡኝ መእልክት*****,***********1- በ ተከበሩ ዶ/ር አበባው ደሳለውምርጫ ክልል 11: 6 ኪሎ መነን ሽሮሜዳዎች በዙሪያው ያላችሁ በሙሉ ለመምረጥ ተዘጋጅ  ባለፉት 5 ዓመታት ለመ...
07/04/2026

የምረጡኝ መእልክት
*****,***********

1- በ ተከበሩ ዶ/ር አበባው ደሳለው

ምርጫ ክልል 11: 6 ኪሎ መነን ሽሮሜዳዎች በዙሪያው ያላችሁ በሙሉ ለመምረጥ ተዘጋጅ ባለፉት 5 ዓመታት ለመላ ህዝባችን ድምጽ በመሆን በንቃት ና በትጋት እንዲሁም በታማኝነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዉስጥ በሀገራችን ሁለንተናዊ ጉዳዮች ላይ ያለምንም መታከት ሲሞግት የኖረ የህዝብ ልጅ አደራውን በብቃት ና በታማኝነት የተወጡ የተከበሩ ዶ/ር አበባው ደሳለው እየመጡላችሁ ነው ለመምረጥ ተዘጋጅ ሰንዳ ሰንዳም በሉ!

2- በዶ/ር ይህዓለም ታምሩ

ምርጫ ክልል 6: የተከበራችሁ የአማኑኤል መሳለሚያ ሠፈረ ሰላም አጠና ተራ እህል በረንዳ በዙሪያው ያላችሁ ኗሪዎች በሙሉ እየመጣንላችሁ ነው በካርዳችሁ ነፃነታችሁን እንድታረጋግጡ ና እንድትመርጡን እየጠየቅን ለቀጣይ 5 ዓመታት ሊደርሱባችሁ ከሚችሉት ያንዣበቡ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ልንታደጋችሁ ና በፖርላማ ልንከራከርላችሁ ከተፍ ብለናል እናንተም አታሳፍሩንም እኛም እንደማናሳፍራችሁ እርግጠኞች ነን!

በቀጣይም ህዝባችን ድምጽን ከሠጠን የኢትዮጵያ ህዝብ ሉዓላዊነት ና የስልጣን ምንጭነት በሕግ የሚረጋገጥበት በእኩልነት የተመሠረተ የሕዝብ ና የሀገር አንድነት የሚጠበቅበት የእምነትና የሀሳብ ነፃነት የሚከበርበት ስርዓት ለመፍጠር ና ለማረጋገጥ እንታገላለን!

መንገዳችን ሩቅ ነው።ህልማችን ትልቅ ነው።እግዚአብሔር ልመናየን ሰማ።እግዚአብሔር ጸሎቴን ተቀበለ።
05/04/2026

መንገዳችን ሩቅ ነው።
ህልማችን ትልቅ ነው።
እግዚአብሔር ልመናየን ሰማ።
እግዚአብሔር ጸሎቴን ተቀበለ።

ትብብር ለኢትዮጰያ አንድነት የ2018 መጭዉን የ 7ኛ ዙር ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ የፋዊ የአደባባይ ቅስቀሳ መርሐ ግብር  በሚያስጀምርበት ኘሮግራም ላይ በቀን 26, 2018 ዓ.ም የተወሠደ ማ...
05/04/2026

ትብብር ለኢትዮጰያ አንድነት የ2018 መጭዉን የ 7ኛ ዙር ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ የፋዊ የአደባባይ ቅስቀሳ መርሐ ግብር በሚያስጀምርበት ኘሮግራም ላይ በቀን 26, 2018 ዓ.ም የተወሠደ ማስታወሻ!
በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይቶችን በማድረግ ና በጋራ በመቆም የጋራ ችግሮቻችንን ለመፍታት ቀትጋት እንሠራለን!

መላው የ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለሆሳዕና በዓል በሠላም ና በጤና አደረሳችሁ  አደረሠን!ይህ የስምንተኛው ሳምንት ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት በነቢዩ በዘካር...
05/04/2026

መላው የ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለሆሳዕና በዓል በሠላም ና በጤና አደረሳችሁ አደረሠን!

ይህ የስምንተኛው ሳምንት ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት በነቢዩ በዘካርያስ ላይ የተጻፈው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ጌታችንም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ተብሎ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ መግባቱ የሚታሰብበት ዕለት ነው፡፡ ሆሳዕና ማለት ‹‹እባክህ አሁን አድን አሁን ባርከን›› ማለት ነው፡፡በሰሞነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሃት ጸሎተ አስተስርዮ ስለማይፈጸም ጸሎተ ፍትሃትና አስተስርዮ የሚደረገው በዚሁ ዕለት ነው::

"በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ብሩክ ነው!"
መዝ 117:25

“የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም፦ ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።”

ማቴዎስ 21፥9

መልካም በዓል

መጋቢት 27 ቀን 2018 ዓ.ም

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ዶ/ር ይህዓለም ታምሩ

04/04/2026
15/03/2026

ዘወትር እሁድ የምትጠብቁት የሪፖርተር ጋዜጣ ዛሬም እንደተለመደው የተለያዩ ወቅታዊ ዜናዎች፣ ጥልቅ ትንታኔዎች፣ ልዩ ዘገባዎች እና ተወዳጅ አምዶችን ይዞ በገበያ ላይ ይገኛል። 🗞️

በቀላሉ በድረገጻችን ላይም ያንብቡ፦🌐 https://www.ethiopianreporter.com/

----------||----------
📱 የሪፖርተርን ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች ይቀላቀሉ

🔗 ፌስቡክ ↠ bit.ly/2Iv9bZB
🔗 ትዊተር ↠ bit.ly/35qeNwV
🔗 ሊንክድኢን ↠ bit.ly/3S0k6uB
🔗 ኢንስታግራም ↠ bit.ly/44Iiuxb
🔗 ቴሌግራም ↠ bit.ly/3Qb4N1M
🔗 ዩቲዩብ ↠ bit.ly/3p0jUQY
🔗 ቲክቶክ ↠ bit.ly/3Ruxsyv
🔗 ትሬድስ ↠ bit.ly/466VBCG

🧾 የስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
📢 የጨረታ ማስታወቂያዎች ↠ ReporterTenders.com

📩 ለዜና ጥቆማ እና መረጃ፡ [email protected]

✍️ ነጻ ፕሬስ፣ ነጻ ሐሳብ፣ ነጻ መንፈስ

14/03/2026

የትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ( ለኢትዮጵያ ) ዕጩዎቻችንን እናስተዋውቅዎ:
ዶ/ር ይህዓለም ታምሩ ስመኝ
:- የኢሕአፓ አባል

የምርጫ ክልል: 6 (መርካቶ አማኑኤል እና አካባቢው)ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት (ለኢትዮጵያ)'ን ወክለው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይወዳደራሉ። የመራጭነት ካርድዎን ይያዙ፤ ድምጽዎን ለ - ለኢትዮጵያ ይስጡ!

የምርጫ ምልክታችን የአውራ ጣት ነው።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዶ/ር ይህዓለም ታምሩ-Yihalem Tamiru Ph.D. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ዶ/ር ይህዓለም ታምሩ-Yihalem Tamiru Ph.D.:

Share