MeQrez Health Services S.C

MeQrez Health Services S.C MeQrez health Services S.C. aspires to bring a healthcare system with top notch quality

በበዓላት ወቅት ደስታችንን እየገለጽን ጤናችንን መጠበቅ የምንችልባቸው 5 ወሳኝ ነጥቦች 1. የውሃ በደምብ መጠጣት፦ በበዓላት ወቅት የሚዘጋጁ ምግቦች ጨውና ስኳር ሊበዛባቸው ስለሚችል፣ ሰውነታ...
13/04/2026

በበዓላት ወቅት ደስታችንን እየገለጽን ጤናችንን መጠበቅ የምንችልባቸው 5 ወሳኝ ነጥቦች

1. የውሃ በደምብ መጠጣት፦ በበዓላት ወቅት የሚዘጋጁ ምግቦች ጨውና ስኳር ሊበዛባቸው ስለሚችል፣ ሰውነታችን እንዳይደርቅና የምግብ መፈጨት ሥርዓታችን እንዲቀላጠፍ በቀን ቢያንስ 8 ብርጭቆ ውሃ መጠጣት ያስፈልጋል።

2. አትክልትና ፍራፍሬን መመገብ፦ ቅባታማ ምግቦችን ከመመገባችን በፊት በፋይበር የበለጸጉ ሰላጣዎችንና አትክልቶችን መመገብ ቶሎ የመጥገብ ስሜት እንዲሰማን በማድረግ ከመጠን በላይ እንዳንመገብ ይረዳናል።

3. የምግብ መጠንን መቆጣጠር፦ ሁሉንም አይነት የበዓል ምግቦች መቅመስ ብንፈልግ እንኳ፣ በትንሽ ሳህን በመጠቀም የምንወስደውን መጠን መገደብ ይኖርብናል። ይህ አላስፈላጊ የክብደት መጨመርን ይከላከላል።

4. ስኳር የበዛባቸው መጠጦችን መቀነስ፦ ለስላሳ መጠጦች እና እንደ ቢራ የመሳሰሉ መጠጦች ከፍተኛ ካሎሪ ስላላቸው፣ በእነሱ ፋንታ የተፈጥሮ ጭማቂዎችን ወይም ንጹህ ውሃን መምረጥ ለጤናችን ተመራጭ ነው።

5. እንቅስቃሴ ማድረግ፦ ከበዓል ግብዣ በኋላ ወዲያው ከመተኛት ወይም ማረፍ ይልቅ፣ ለጥቂት ደቂቃዎች በእግር መጓዝ ወይም ቀለል ያሉ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ የተመገብነውን ምግብ ለማቃጠል ይረዳል።

ይህ የበዓል ሰሞን የደስታና የጤና እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!

መቅረዝ ጠቅላላ ሆስፒታል
የጥራት ፈርጥ!!
ለበለጠ መረጃ ወይም ቀጠሮ ለማስያዝ በ 6757 ፣ በ 0921636465 ወይም በ 0952272727 ላይ ይደውሉ ::
#የበዓልቅናሽ

12/04/2026

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ!
ይህ የትንሳኤ በዓል የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር እና የደስታ እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞታችንን እየገልጽን፤ ከቤተሰብ እና ከወዳጅ ዘመድ ጋር መልካም የበዓል ጊዜ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።
መቅረዝ ሆስፒታል
የጥራት ፈርጥ

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ!የመቅረዝ የጤና አገልግሎት አ.ማየቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ፕሮፌሰር ማኅተመ በቀለ እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑ...
11/04/2026

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ!
የመቅረዝ የጤና አገልግሎት አ.ማ
የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ፕሮፌሰር ማኅተመ በቀለ እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶክተር ናትናኤል ታዬ ይህ የትንሣኤ በዓል ለእናንተና ለቤተሰባችሁ የፍቅርና የጤና እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞታቸውን ይገልጻሉ።
መቅረዝ የጤና አገልግሎት አ.ማ

09/04/2026

የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በመቅረዝ ጠቅላላ ሆስፒታል በሁሉም ህክምና የማማከር አገልግሎቶች (consultation) ላይ የ25% ቅናሽ አዘጋጅተናል!
ጤናዎ ለኛ የሁልጊዜ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው!
ይህ የልዩ ቅናሽ እድል በሚያዝያ ወር ሙሉ የሚቆይ ሲሆን ጤናዎን በመንከባከብ በዓሉን በደስታ ያሳልፉ።
መቅረዝ ጠቅላላ ሆስፒታል
የጥራት ፈርጥ!!
ለበለጠ መረጃ ወይም ቀጠሮ ለማስያዝ በ 6757 ፣ በ 0921636465 ወይም በ 0952272727 ላይ ይደውሉ ::
#የጥራትፈርጥ #የበዓልቅናሽ

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረስዎ!የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በመቅረዝ ጠቅላላ ሆስፒታል  በሁሉም ህክምና የማማከር አገልግሎቶች (consultation) ላይ የ25% ቅናሽ ...
08/04/2026

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረስዎ!
የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በመቅረዝ ጠቅላላ ሆስፒታል በሁሉም ህክምና የማማከር አገልግሎቶች (consultation) ላይ የ25% ቅናሽ አዘጋጅተናል!

ጤናዎ ለኛ የሁልጊዜ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው!
ይህ የልዩ ቅናሽ እድል በሚያዝያ ወር ሙሉ የሚቆይ ሲሆን ጤናዎን በመንከባከብ በዓሉን በደስታ ያሳልፉ።

መቅረዝ ጠቅላላ ሆስፒታል
የጥራት ፈርጥ!!
ለበለጠ መረጃ ወይም ቀጠሮ ለማስያዝ በ 6757 ፣ በ 0921636465 ወይም በ 0952272727 ላይ ይደውሉ ::
#የጥራትፈርጥ #የበዓልቅናሽ
Instagram| Facebook| TikTok | LinkedIn| Website

07/04/2026

በዛሬ እለት የዓለም ጤና ቀንን ስናከብር፣ የህክምና ባለሙያዎች ለራሳቸው ጤና ምን እንደሚያደርጉ ጠይቀናቸዋል?
ሳይንስን መሰረት ያደረጉ የጤና ልምዶችን ከባለሙያዎቹ አንደበት ይስሙ።
ለተሻለ ጤና አብረን እንቁም!

መቅረዝ ጠቅላላ ሆስፒታል
የጥራት ፈርጥ!!

ለበለጠ መረጃ ወይም ቀጠሮ ለማስያዝ በ 6757 ፣ በ 0921636465 ወይም በ 0952272727 ላይ ይደውሉልን ::

ብርሃንዎን በ4 ቀላል መንገዶች ይጠብቁ!1.ንፅህናን መጠበቅፊት እና እጅን መታጠብ፦ እንደ ትራኮማ ያሉ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል ሁልጊዜ በሳሙናና በውሃ ይታጠቡ።አይንን አለመንካት፦ ቆሻሻ...
05/04/2026

ብርሃንዎን በ4 ቀላል መንገዶች ይጠብቁ!
1.ንፅህናን መጠበቅ
ፊት እና እጅን መታጠብ፦ እንደ ትራኮማ ያሉ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል ሁልጊዜ በሳሙናና በውሃ ይታጠቡ።
አይንን አለመንካት፦ ቆሻሻ እጅ ለአይን ህመም ዋነኛ መንስኤ ነው።
2. አመጋገብን ማስተካከል
ቫይታሚን 'ኤ'፦ እንደ ካሮት ያሉ ምግቦች የአይንን ውስጣዊ ጥንካሬ ይገነባሉ።
የዕይታ ድክመትን ይከላከሉ፦ ጤናማ ምግብ ለጠራ እይታ መሠረት ነው።
3. የስክሪን ጊዜን ማስተካከል
የ20-20-20 ደንብ፦ በየ20 ደቂቃው፣ ለ20 ሰከንድ ያህል፣ 20 ጫማ (6 ሜትር) ርቀት ላይ ያለን ነገር በመመልከት አይንዎን ያሳርፉ።
የመከላከያ መነፅር፦ ከስልክና ኮምፒውተር የሚወጣውን ብልጭታ የሚቀንሱ መነፅሮችን ይጠቀሙ።
4. የፀሐይ መከላከያ ጥራት ያለው መነፅር፦ ከፀሐይ የሚወጣውን ጎጂ ጨረር ለመከላከል የፀሐይ መነፅር (Sunglasses) ያድርጉ።
ወሳኝ ማሳሰቢያ፦
ማንኛውም የአይን ብዥታ፣ መቅላት ወይም እንባ መፍሰስ ሲያጋጥም በራስዎ መድኃኒት ከመጠቀም ወደ ህክምና ተቋም ቢሄዱ ይመረጣል።

ለበለጠ መረጃ በ6757፣ 0952272727 & 0921636465 ላይ በመደወል ይችላሉ።
መቅረዝ ጠቅላላ ሆስፒታል
የጥራት ፈርጥ!

03/04/2026

የህይወት የመጀመርያ 1000 ቀናት የልጆት ህይወት ላይ ያለውን ትፅእኖ ያውቃሉ?
የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት ሃኪም ዶ/ር የምስራች ደረሰ ስለ ጤናማ እርግዝና እና ህፃናት እድገት ጠቃሚ የጤና ምክሮችን ታካፍለናለች።
በመቅረዝ የውስጥ ደዌና የህፃናት ህክምና ማዕከል ከእርግዝና ጀምሮ ለእናቶች እና ለህፃናት የተሟላ የህክምና ክትትል እናደርጋለን።
የነገ ተረካቢዎችን ጤና ዛሬ ላይ እንጠብቅ!

መቅረዝ የውስጥ ደዌ እና የሕጻናት ሕክምና ማዕከል
የጥራት ፈርጥ!!
ለበለጠ መረጃ ወይም ቀጠሮ ለማስያዝ በ 6757 ፣ በ 0921636465 ወይም በ 0952272727 ላይ ይደውሉ ::

ጤናዎ የህይወትዎ መሰረት ነው! መቅረዝ የውስጥ ደዌ እና የህጻናት ሕክምና ማዕከል ዘመናዊ መሣሪያዎችን እና ልምድ ያላቸውን ባለሙያዎች በመያዝ ጥራት ያለው የሕክምና አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል...
02/04/2026

ጤናዎ የህይወትዎ መሰረት ነው!
መቅረዝ የውስጥ ደዌ እና የህጻናት ሕክምና ማዕከል ዘመናዊ መሣሪያዎችን እና ልምድ ያላቸውን ባለሙያዎች በመያዝ ጥራት ያለው የሕክምና አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል እርሶም ቀጠሮ ለማስያዝም ሆነ የበለጠ መረጃ ለማግኘት በ6757፣ 0921636465 ወይም በ 0952272727 ላይ ይደውሉልን.
አድራሻችን ከአያት አደባባይ ወደ ጣፎ አደባባይ በሚወስደው መንገድ ላይ
መቅረዝ የውስጥ ደዌ እና የሕጻናት ሕክምና ማዕከል
የጥራት ፈርጥ!!

በልጆች ላይ የሚከሰት የትርፍ አንጀት እብጠት እና የቀዶ ጥገና አስፈላጊነት.የትርፍ አንጀት እብጠት (Appendicitis) በህፃናት ላይ ለሚደረግ የድንገተኛ የሆድ ቀዶ ጥገና ዋነኛ ምክንያት...
01/04/2026

በልጆች ላይ የሚከሰት የትርፍ አንጀት እብጠት እና የቀዶ ጥገና አስፈላጊነት.

የትርፍ አንጀት እብጠት (Appendicitis) በህፃናት ላይ ለሚደረግ የድንገተኛ የሆድ ቀዶ ጥገና ዋነኛ ምክንያት ነው። ትርፍ አንጀት በትልቁ አንጀት መጀመሪያ ላይ የሚገኝ ትንሽዬ የጣት ቅርጽ ያላው አካል ሲሆን፣ በቆሻሻ ወይም በኢንፌክሽን ምክንያት ሲዘጋ ያብጣል። ይህ ችግር በፍጥነት ካልታከመ ትርፍ አንጀቱ ሊፈነዳ እና በሆድ ውስጥ ከፍተኛ አደጋ ሊያስከትል ይችላል።

ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
በህፃናት ላይ የትርፍ አንጀት ምልክቶች ከትላልቅ ሰዎች ሊለዩ ይችላሉ።
•የሆድ ህመም፦ መጀመሪያ ላይ በእምብርት አካባቢ ይጀምርና ቀስ እያለ ወደ ታችኛው የቀኝ የሆድ ክፍል ይወርዳል።
•ትኩሳት፦ መጠነኛ የሆነ የሰውነት ሙቀት መጨመር።
•ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ፦ ህፃኑ ምግብ መመገብ ፍላጎት ያጣል።
•ሆድ መንፋት፦ በተለይ በህፃናት ላይ ህክምና በጊዜ ካልተገኘ ሆድ ተወጥሮ ሊታይ ይችላል።

ቀዶ ጥገና
በመድሃኒት ብቻ ሊድን የማይችልበት ደረጃ ላይ ሲደርስ ብቸኛው እና አስተማማኝ መፍትሄ ቀዶ ጥገና (Appendectomy) ነው።

ከቀዶ ጥገና በኋላ ምን ይጠበቃል?
•የቀዶ ጥገናው ቁስል ንጽህናውን መጠበቅ።
•ከባድ እንቅስቃሴዎችን ለተወሰኑ ሳምንታት እንዲቀንሱ ማድረግ።
•ሐኪሙ ያዘዘውን የህመም ማስታገሻ እና ሌሎች መድሃኒቶች በአግባቡ መስጠት።

እርሶም አያድርገው እና ልጅዎ እንደዚህ አይነት ህክምና ካስፈለገው/ጋት በሆስፒታላችን እውቅ በሆኑ የህጻናት ቀዶ ጥገና ሃኪሞች መፍትሄ ማግኘት ይችላሉ።
ለበለጠ መረጃ በ6757፣ 0952272727 & 0921636465 ላይ በመደወል ይችላሉ።
መቅረዝ ጠቅላላ ሆስፒታል
የጥራት ፈርጥ!

የልጅዎ ፈገግታ እና ጤንነት የእኛም ኩራት ነው! ✨👶ልጆች ህመማቸውን ሁልጊዜ በንግግር ሊገልጹልን ስለማይችሉ፣ ወላጆች ለሚያሳዩት አካላዊ ምልክቶች ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግና ምልክቶቹን መለየት...
31/03/2026

የልጅዎ ፈገግታ እና ጤንነት የእኛም ኩራት ነው! ✨👶
ልጆች ህመማቸውን ሁልጊዜ በንግግር ሊገልጹልን ስለማይችሉ፣ ወላጆች ለሚያሳዩት አካላዊ ምልክቶች ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግና ምልክቶቹን መለየት ይኖርባቸዋል።
ወደ ህፃናት ህክምና ባለሙያ (Pediatrician) በአፋጣኝ መሄድ የሚያስፈልግዎ መቼ ነው? በምስሉ ላይ የተጠቀሱት እነዚህ 5 ወሳኝ ምልክቶች ከታዩ በምንም መልኩ ችላ ሊባሉ አይገባም፦
1️⃣ ከፍተኛ ትኩሳት፦ የሰውነት ሙቀት ከፍ ካለ።
2️⃣ አስቸጋሪ ሳል ወይም የመተንፈስ ችግር፦ አተነፋፈሳቸው ፈጣን ወይም አስቸጋሪ ከሆነ።
3️⃣ ተከታታይ ተቅማጥ እና ትውከት፦ ከሰውነት ፈሳሽ መቀነስ ጋር ተያይዞ አደጋ ሊያስከትል ስለሚችል።
4️⃣ ራስን መሳት ወይም መንቀጥቀጥ፦ አስቸኳይ የህክምና እርዳታ የሚጠይቅ ምልክት በመሆኑ።
5️⃣ የሰውነት ማበጥ፦ በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ የሚታይ ያልተለመደ እብጠት።
በመቅረዝ የጤና ተቋማት በቂ ልምድ ባላቸው የህፃናት ስፔሻሊስት ሃኪሞችና በዘመናዊ መሣሪያዎች የታገዘ የተሟላ የህክምና አገልግሎት በ24 ሰዓት ዝግጁነት እንሰጣለን።
📍 አድራሻ፡
-ቁጥር አንድ፡ ካዛንቺስ፣ ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ (የቀድሞው ዮርዳኖስ ሆቴል) ፊት ለፊት።
-ቁጥር ሁለት፡ ከአያት አደባባይ ወደ ጣፎ በሚወስደዉ መንገድ ላይ

ለበለጠ መረጃ ወይም ቀጠሮ ለማስያዝ በ 6757 ፣ በ 0921636465 ወይም በ 0952272727 ላይ ይደውሉ ::
መቅረዝ ጠቅላላ ሆስፒታል
የጥራት ፈርጥ!!

ለልጅዎ የተሟላ እና አስተማማኝ የሕፃናት ሕክምና አገልግሎት ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ.....በመቅረዝ የዉስጥ ደዌ እና የሕጻናት ሕክምና ማዕከል ጥራት ያለው የህፃናት ሕክምና እውቅና ባላቸው የ...
30/03/2026

ለልጅዎ የተሟላ እና አስተማማኝ የሕፃናት ሕክምና አገልግሎት ይፈልጋሉ?
እንግዲያውስ.....በመቅረዝ የዉስጥ ደዌ እና የሕጻናት ሕክምና ማዕከል ጥራት ያለው የህፃናት ሕክምና እውቅና ባላቸው የህክምና ባለሙያዎች እየሰጠን እንገኛለን።
-ለልጅዎ ጤና ሰዓት አንመርጥም! በ24/7 ዝግጁነት፣ ሁሌም ለልጅዎ ደህንነት እንተጋለን።

መቅረዝ የውስጥ ደዌ እና የሕጻናት ሕክምና ማዕከል
የጥራት ፈርጥ!!
ለበለጠ መረጃ ወይም ቀጠሮ ለማስያዝ በ 6757 ፣ በ 0921636465 ወይም በ 0952272727 ላይ ይደውሉ ::

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when MeQrez Health Services S.C posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share