Dr. Ketsela Lemma Eshete Women’s Health & Reproductive Wellness

Dr. Ketsela  Lemma Eshete  Women’s Health & Reproductive Wellness Dr. Ketsela Lemma Eshete, MD,MPH specialist in obstetrics and gynecology and maternal fetal medicine

ድንገተኛ ህመም መጥቶ ያፈሩትን ንብረት በአንዴ ሲያራቁት አይተው ያውቃሉ?የሕክምና ወጪን በቀጥታ ከኪስ መክፈል የብዙ ቤተሰቦችን ኢኮኖሚ እያመሰቃቀለ ይገኛል። ይህንን አዙሪት በዘላቂነት ለመስ...
04/09/2026

ድንገተኛ ህመም መጥቶ ያፈሩትን ንብረት በአንዴ ሲያራቁት አይተው ያውቃሉ?

የሕክምና ወጪን በቀጥታ ከኪስ መክፈል የብዙ ቤተሰቦችን ኢኮኖሚ እያመሰቃቀለ ይገኛል። ይህንን አዙሪት በዘላቂነት ለመስበር በሀገራችን የጤና ፋይናንስ ላይ ትልቅ እና አስገዳጅ ለውጥ መጥቷል!

አዲሱ የጤና መድን ሕግ እርስዎን እና ቤተሰብዎን እንዴት እንደሚነካ ያውቃሉ?

ለሁለንተናዊ የጤና ሽፋን (UHC) ስኬት እና ለጠንካራ የጤና ሥርዓት ግንባታ ማህበረሰቡን ያሳተፈ ወጥ የፋይናንስ ሥርዓት መዘርጋት እጅግ ወሳኝ ነው።

የጤና ፋይናንስን በተመለከተ ህብረተሰቡ ሊገነዘባቸው የሚገቡ መሠረታዊ እና ቁልፍ ጉዳዮችን ከዚህ በታች በዝርዝር እንመለከታለን።

1. የስጋት ተጋሪነት (Risk Pooling) ፋይዳ እና የከኪስ ወጪ አደጋ

በማንኛውም ሀገር የህክምና ሥርዓት ውስጥ "የስጋት ተጋሪነት" (Risk Pooling) ዋነኛው የህልውና መሠረት ነው። የሕክምና ወጪን በህመም ጊዜ በቀጥታ ከኪስ መክፈል (Out-of-Pocket Payment) ህብረተሰቡን ለከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ያጋልጣል። ቤተሰቦች በድንገተኛ ህመም ጊዜ ወጪን ለመሸፈን ሲሉ ከብቶቻቸውን፣ መሬታቸውን እና ንብረታቸውን እስከመሸጥ ይደርሳሉ፤ ይህም በቀጥታ ወደ ከፋ ድህነት ይመራቸዋል። ይህንን አዙሪት ለመስበር ጤነኛው ከታማሚው፣ አቅም ያለው አቅም ከሌለው ጋር አስቀድሞ ወጪ የሚጋራበት ሥርዓት የግድ ይላል።

2. የኢትዮጵያ ምርጫ : ወደ አስገዳጅ የጤና መድን

የተለያዩ ሀገራት የጤና ሽፋንን ለማረጋገጥ የተለያዩ ሞዴሎችን (በታክስ የተደገፈ፣ ማህበራዊ የጤና ፈንድ ወይም የግል መድን) ይጠቀማሉ። ኢትዮጵያ በተጨባጭ ሁኔታዋ መደበኛ እና መደበኛ ያልሆነውን ዘርፍ ለይተው የሚያስተናግዱ ሁለት አስገዳጅ (Mandatory) የጤና መድን ሥርዓቶችን መርጣለች፤ እነሱም CBHI እና SHI ናቸው። በተለይም ማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድን (CBHI) በፈቃደኝነት ላይ ከተመሰረተ የሙከራ (Pilot) ትግበራ ወጥቶ፣ ዛሬ ላይ ሙሉ በሙሉ በሕግ ወደሚያስገድድ ሀገር አቀፍ ማዕቀፍ ተሸጋግሯል።

3. የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድን (CBHI) የሕግ መሠረት
ይህ ሥርዓት አርሶ አደሩን እና መደበኛ ባልሆነው ዘርፍ የተሰማራውን አብዛኛውን ህብረተሰብ ያቀፈ ነው። አሁን ላይ የሚመራው በሁለት ጠንካራ የሕግ ማዕቀፎች ነው፦
አዋጅ ቁጥር 1273/2014፡ ይህ አዋጅ አባልነትን አስገዳጅ ያደረገ ሲሆን፣ ሥርዓቱ በድንገተኛ የፋይናንስ እጥረት እንዳይፈርስ ከሚሰበሰበው መዋጮ 5% የሚሆነው በተጠባባቂ ፈንድ (Reserve Fund) እንዲቀመጥ ደንግጓል። ሰዎችን ሲታመሙ ብቻ እንዳይመዘገቡ (Adverse Selection) ለመከላከል የምዝገባ እና የእድሳት ጊዜ በዓመት ውስጥ በተወሰኑ ወራት ብቻ እንዲከናወን ተገድቧል።

ደንብ ቁጥር 535/2015፡ የቀድሞውን ወጥ የክፍያ ተመን በማስቀረት፣ የመክፈል አቅምን ያገናዘበ (Tiered Premium) አሰራርን ዘርግቷል። አባወራዎች እንደየገቢያቸው መጠን በደረጃ (ክፍል ሀ፣ ለ፣ ሐ) ይከፍላሉ። የመክፈል አቅም ለሌላቸው (Indigent) ወገኖች ደግሞ መንግሥት መዋጮውን 100% በመሸፈን የነፃ ሕክምና ተጠቃሚ ያደርጋቸዋል።

4. የማህበራዊ የጤና መድን (SHI) ለመደበኛው ዘርፍ
ይህ ሥርዓት በአዋጅ ቁጥር 690/2002 እና በደንብ 271/2004 የተዘረጋ ሲሆን ለመንግሥት ሰራተኞች፣ ለግል ድርጅት ተቀጣሪዎች እና ለጡረተኞች ያገለግላል።

መዋጮው፡ ተቀጣሪው ከደሞዙ 3% ሲያዋጣ፣ አሠሪው ድርጅት ተጨማሪ 3% ይሸፍናል። ጡረተኞች ደግሞ ከወርሃዊ አበላቸው 1% ያዋጣሉ።
ትግበራው፡ አዋጁ ከወጣ አመታት ቢቆጠሩም፣ የመንግሥት ሆስፒታሎች የአገልግሎት ጥራት እና የመድኃኒት አቅርቦት ላይ በነበረው ክፍተት ምክንያት ትግበራው ሲጓተት ቆይቷል። ነገር ግን አሁን ማዕቀፉ እየተጠናከረ ወደ ሙሉ ትግበራ ለመግባት ከፍተኛ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው። በሕጉ መሠረት ውጭ ሀገር የሚደረጉ ሕክምናዎች፣ የውበት (Cosmetics) ቀዶ ጥገናዎች እና ከመደበኛ ህመም ጋር ያልተያያዙ ምርመራዎች በሽፋኑ ውስጥ አይካተቱም።

5. ሥርዓቱ ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዲሆን ምን መደረግ አለበት?

የጤና መድን አሰራሮቹ ከወረቀት ባለፈ የተሟላ ስኬት እንዲያመጡ የሚከተሉት እርምጃዎች ወሳኝ ናቸው::

የአሰራር ዲጂታላይዜሽን፡ በኢትዮጵያ የጤና መድን አገልግሎት (EHIS) በኩል የተጀመረውን የ "Etnhis" ዲጂታል ሥርዓት ሙሉ በሙሉ ማስፋት ግድ ይላል። የአባላት ምዝገባን በማዘመን፣ እንዲሁም ሆስፒታሎች የሚያቀርቡትን የክፍያ ጥያቄ (Claims Management) በዲጂታል መንገድ በማስተናገድ ማጭበርበርን (Fraud) እና ብክነትን ማስቀረት ይቻላል።

ጥብቅ የሪፈራል ሥርዓት፡ ከጤና ጣቢያ ወደ ሆስፒታል የሚደረገው የቅብብሎሽ (Referral) ሥርዓት በጥብቅ መተግበር አለበት። ይህ ካልሆነ የፋይናንስ ሥርዓቱ በአላስፈላጊ ወጪ ይሽመደመዳል።

የመድኃኒት አቅርቦት እና ተቋማዊ ቅንጅት

በክልል ጤና ቢሮዎች፣ በጤና ተቋማት እና በመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለቱ (Supply Chain) መካከል ጠንካራ የኮሚዩኒኬሽን ስትራቴጂ መዘርጋት አለበት። የመድኃኒት እጥረት መኖሩ ህብረተሰቡ በሥርዓቱ ላይ ያለውን እምነት ስለሚሸረሽር አቅርቦትን ማረጋገጥ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል።

የግሉን የጤና ዘርፍ ማሳተፍ እና የታሪፍ ቁጥጥር

የጤና መድን ሥርዓቱ የመንግሥት ሆስፒታሎች ላይ ብቻ መጫን የለበትም። የግል ጤና ተቋማት ከጤና መድኑ ጋር ውል ገብተው አገልግሎት እንዲሰጡ ማበረታታት ያስፈልጋል። ለዚህ ደግሞ በግል ሆስፒታሎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ዋጋ (Pricing) በማጥናት ወጥ እና አዋጭ የሆነ ታሪፍ መተመን ያስፈልጋል። ይህ ሲሆን፣ ከፍተኛ ግብር ከፋይ ሆኑት የኮርፖሬት ተቋማት እና ሰራተኞች በ SHI ሥርዓት ላይ ሙሉ እምነት አሳድረው ተሳትፎ ያደርጋሉ።

6. የግል የጤና መድን (Private Health Insurance) ቀጣይ ሚና

የመንግሥት የጤና መድን ሥርዓቶች (CBHI እና SHI) አስገዳጅ ቢሆኑም፣ የግል የጤና መድን ኩባንያዎች ሚና አያበቃም፤ ይልቁንም አጋዥ በመሆን የራሳቸውን ወሳኝ ድርሻ ይወጣሉ ::

በመንግሥት መድን የተከለከሉ አገልግሎቶችን (ለምሳሌ፡ የውጭ ሀገር ሕክምና፣ ውድ የሆኑ ብራንድ መድኃኒቶችን) በመሸፈን ተጨማሪ ዋስትና (Supplementary Coverage) ይሰጣሉ።
ከፍተኛ ገቢ ያላቸው ግለሰቦች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የመንግሥት የጤና ተቋማትን መጨናነቅ በማለፍ፣ በቀጥታ ከፍተኛ ደረጃ ወዳላቸው የግል ሆስፒታሎች መሄድ እንዲችሉ የፕሪሚየም አማራጭ (Duplicate Coverage) ያቀርባሉ።
እርስዎስ ምን ያስባሉ? እስኪ በዚህ ጉዳይ ላይ በኮመንት እንወያይ!
#የጤናመድን #ኢትዮጵያ

Face book what is in your mind አለኝ የሚከተለው ብልጭ አልኝ የእድር ባህላችን  እና የጤና መድህን 🤔ኢትዮጵያ ውስጥ ከትውልድ ትውልድ የተሸጋገረውና ሕዝባችን የሚተማመንበት ...
29/08/2026

Face book what is in your mind አለኝ የሚከተለው ብልጭ አልኝ

የእድር ባህላችን እና የጤና መድህን 🤔

ኢትዮጵያ ውስጥ ከትውልድ ትውልድ የተሸጋገረውና ሕዝባችን የሚተማመንበት እጅግ የጠነከረው "የእድር" አብሮነት ሥርዓት አለን። ነገር ግን ወደ መደበኛ የጤና ፋይናንስ (የጤና መድን) ስንመጣ ለምን እንቸገራለን?

ሲታይ ሁለቱም አንድ ዓይነት መሠረታዊ “ዲ ኤን ኤ (DNA)” አላቸው—ይኸውም አብሮነት እና የጉዳት ማካካሻ (Risk Pooling)። ነገር ግን የጤና መድንን ስናይ ብዙ ጊዜ እንደንግድ ወይም እንደ ሸቀጥ እንጂ እንደ ማኅበራዊ አብሮነት አንመለከተውም።

ሊገቡንና ሊስተካከሉ የሚገቡ ቁልፍ ነጥቦች፦
🔹 1. የ"ባከነ ገንዘብ" የተሳሳተ አመለካከት
ሰዎች ዓመቱን ሙሉ ለጤና መድን እየከፈሉ ሕመም ካልገጠማቸው ገንዘባቸው እንደባከነ ይሰማቸዋል። ነገር ግን ማንም ሰው ለእድር ዓመት ሙሉ ገንዘብ ሲያዋጣ “እንዲህ ዓይነቱ ዘመዴ ይሙትና የእደሩን ገንዘብ ልውሰድ” ብሎ አያስብም! እድር ለአእምሮ ሰላም እና ለጋራ ዋስትና የሚደረግ ነው። ጤናማ ሆኖ መቆየት እና የመድን ካርድን አለመጠቀም የገንዘብ ኪሳራ ሳይሆን ታላቅ ጸጋ ነው።

🔹 2. የሞራል ኃላፊነት እና ጥንቃቄ
እድር አለ ብሎ ማንም ሰው የቤተሰቡን ሕይወት ቸል አይልም። ልክ እንደዚሁ፣ የጤና መድን አለ ማለት ራሳችንን ከበሽታ መጠበቅ ትተን ራስን ለበሽታ ማጋለጥ አለብን ማለት አይደለም ።

🔹 3. መፍትሔው መዋቅሩን ከባህላችን ጋር ማዋሃድ!
የጤና መድን ሽፋንን ለማስፋት እና ግንዛቤን ለመፍጠር፦
የእድር መሪዎችንና ሽማግሌዎችን ማሳተፍ (ማኅበረሰቡ ቀድሞውኑ የሚተማመናቸው በመሆኑ)
ቋንቋውን እንደ “የጤና እድር” አድርጎ ማስተዋወቅ
የጋራ ማኅበራዊ ተጠያቂነትን መፍጠር
የጤና መድንን በእድር ባህላዊ ማዕቀፍ ውስጥ ካስገባነው፣ የመተማመን ክፍተቱን ጠግነን ጠንካራ እና ጤናማ ንቃተ-ህሊና ያለው ኅበረሰብ መገንባት እንችላለን!
እንዲያዉ ለምሳሌ እና ግንዛቤ ለመፍጠር ስለሚጠቅም ይኸን አነሳሁ እንጂ እንሹራንስ እንዳይስፉፉ በርካታ ምክንያቶች አሉ ።

የተራዘመ እርግዝና  ( post term pregnancy)  ምንድን ነው ? የተለመደዉ የሰው ልጅ የመወለጃ ግዜ  እናቲቱ ለመጨረሻ ግዜ የወር አበባ   ካየችበት የመጀመሪያ ቀን ሲቆጠር  40 ...
11/08/2026

የተራዘመ እርግዝና ( post term pregnancy) ምንድን ነው ?

የተለመደዉ የሰው ልጅ የመወለጃ ግዜ እናቲቱ ለመጨረሻ ግዜ የወር አበባ ካየችበት የመጀመሪያ ቀን ሲቆጠር 40 ሳምንት ወይም 9 ወር ከ አስር ቀን ነው ይህ ማለት ግን ሁሉም እናቶች በዚህ ቀን ይወልዳሉ ማለት አይደለም

ህፃናት ተጨማሪ ጊዜ ሲወስዱ ወይም ቀደም ብለዉ ሲወለዱ ማየት የተለመደ ነው።

ዶክተሮች እርግዝናው ከ 41 ሳምንታት (ከተጠበቀው ቀን 1 ሳምንት ሲያልፍ) ጀምሮ ስጋት የሚገባቸው ሲሆን፣ እርግዝናው 42 ሳምንታት (ከተጠበቀው ቀን 2 ሳምንት) እና ከዚያ በላይ ከተራዘመ በህክምናው ዘርፍ የተራዘመ እርግዝና (Post-Term Pregnancy / Postdates) ተብሎ ይመደባል።

የተራዘመ እርግዝና ለምን ይከሰታል?

በአብዛኛዎቹ አጋጣሚዎች የእርግዝና ጊዜ ለምን እንደሚራዘም በትክክል አይታወቅም። ነገር ግን ለዚህ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የታወቁ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፦

1. የመጀመሪያ እርግዝና በበኩር እርግዝና ወቅት የመውለጃ ቀን የማለፍ እድሉ ከፍተኛ ነው።

2.ቀደም ሲል የተራዘመ እርግዝና ታሪክ መኖር ፣ ቀደመው የወለዱት ህፃን ቀን አልፎት የተወለደ ከሆነ፣ ቀጣይ እርግዝናዎችም የመራዘም እድላቸው ሰፊ ነው።

3. በቤተሰብ ውስጥ ቀንን አሳልፎ የመወለድ ታሪክ ካለ

4. የመውለጃ ቀን ስሌት መሳሳት በእርግዝናመጀመሪያ ላይ የተሰላው የመውለጃ ቀን ስህተት ከሆነ እርግዝናው ከተጠበቀው በላይ እንደረዘመ ሊያስመስለው ይችላል።

ከ41 እና 42 ሳምንታት በኋላ መወለድ የሚያስከትላቸው አደጋዎች

ቀናቸው አልፎ ከ41 ወይም 42 ሳምንታት በኋላ የሚወለዱ አብዛኛዎቹ ህፃናት ጤናማ ቢሆኑም፣ በሚከተሉት ምክንያቶች ችግሮች የመከሰት እድላቸው ይጨምራል

በፅንሱ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ

1. የፅንስ መጠን በጣም መጨመር (ከ4.5 ኪሎ ግራም በላይ) ህፃኑ በጣም ትልቅ ከሆነ በወሊድ ቦይ (Birth Canal) በኩል ለማለፍ ስለሚያስቸግር ለጉዳት ሊዳረግ ይችላል። በእናትየው አካል ላይም ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል በኦፕሬሽን (C-section) የመወለድ ፍላጎትን ይጨምራል።

2. የሽርት ዉሀ መወፈር
ህፃናት ከመወለዳቸው በፊት የመጀመሪያ ቆሻሻቸውን ማህፀን ውስጥ ባለው የፅንስ ውኃ ውስጥ የመልቀቅ እድላቸው ከፍተኛ ሲሆን፣ ይህንን ውኃ ወደ ሳንባቸው ካስገቡ ከወሊድ በኋላ የመተንፈስ ችግር ያጋጥማቸዋል።

3.የእንግዴ ልጅ (Placenta) ስራ መቀነስ እንግዴ ልጅ ለፅንሱ ምግብና ኦክስጅን የሚያቀርብ አካል ነው። የእርግዝና ጊዜው ሲረዝም ስራውን በትክክል የመወጣት ብቃቱ ይቀንሳል።

4 የፅንስ ውኃ / ሽርት ዉሀ መቀነስ (Oligohydramnios) በፅንሱ ዙሪያ ያለው ውኃ ሲቀንስ የእምብርት ገመድ ሊጨመቅ ይችላል። ይህም ህፃኑ በቂ ኦክስጅንና ምግብ እንዳያገኝ ያደርጋል።

በእናት ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ

1.በህክምና እገዛ ምጥ እንዲመጣ የመደረግ (Labor Induction) እድል መጨመር።

2.የወሊድ ወቅት የብልት መቀደድ ወይም በወሊድ መሳሪያዎች ወይም በቀዶ ህክምና የመወለድ እድል መጨመር።

የመውለጃ ቀን ካለፈ በኋላ ምን ይደረጋል?

እርግዝናዎ ከተጠበቀው ቀን ካለፈ የጤና ባለሙያዎ ከእርስዎ ጋር በመመካከር የሚከተሉትን አማራጮች ያቀርባሉ

1.ምጥ እንዲመጣ ማድረግ (Labor Induction) ብዙ ባለሙያዎች እርግዝናው 41 ሳምንት ሲሞላው መድኃኒቶችን በመጠቀም ምጥ እንዲመጣ ማድረግን ይመክራሉ። እነዚህ መድኃኒቶች በአብዛኛው ውጤታማ ናቸው።

2.የፅንስ ክትትል እያደረጉ መጠበቅ ; ምጥ በራሱ ጊዜ እስኪመጣ ወይም እርግዝናው 41-42 ሳምንት እስኪደርስ መጠበቅ ከተመረጠ፣ የህፃኑን ደህንነት ለማረጋገጥ የሚከተሉት ምርመራዎች ይደረጋሉ፦
1.የህፃኑ የልብ ምት ክትትል (Heartbeat)
2. የህፃኑ የእስትንፋስ እና የሰውነት እንቅስቃሴዎች መከታተል
3 .በማህፀን ውስጥ ያለው የፅንስ ውኃ መጠን መለካት

ምጥ ማምጫ መድኃኒቶች ካልሰሩ፣ ህፃኑ በጣም ትልቅ ከሆነ ወይም በወሊድ ወቅት የፅንሱ ደህንነት አደጋ ላይ ከወደቀ፣ ዶክተርዎ በቀዶ ህክምና (Cesarean birth) እንድትወልዱ ሊመክር ይችላል።

የተጠበቀው የመውለጃ ቀንዎ አልፎ ከሆነ አይደንግጡ! አብዛኛዎቹ ቀናቸው ያለፈባቸው ህፃናት በሰላም እና ያለ ምንም ችግር ይወለዳሉ። ከጤና ባለሙያዎ ጋር ቅርብ የሆነ ግንኙነት ያድርጉ፣ የህፃኑን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ይከታተሉ፣ እና የተቀጠሩበትን የፅንስ ክትትል ቀናት አይለፉ።

ለተጨማሪ መረጃ
የ ticktock, you tube and face book page ይከታተሉ
Dr. Ketsela Lemma Eshete Women’s Health & Reproductive Wellness

07/08/2026

🤰 በእርግዝና ወቅት የሚከሰት ድንገተኛ የደም ግፊት (ፕሪኤክላምፕሲያ) ምንድነው?

በእርግዝና ወቅት (ብዙውን ጊዜ ከ5ኛው ወር ወይም ከ20ኛው ሳምንት በኋላ) የሚከሰተውን «ፕሪኤክላምፕሲያ» የተባለውን የጤና ችግር ብዙዎቻችን የምናውቀው ከተራ የደም ግፊት መጨመር ጋር ብቻ አያይዘን ነው። ነገር ግን ይሄ ትልቅ ስህተት ነው!

1. ፕሪኤክላምፕሲያ ተራ የደም ግፊት ብቻ አይደለም!

ይህ ችግር የደም ግፊት ከመጨመር ባለፈ በእናቲቱ ኩላሊት ;ጉበት፣ አንጎል እና የደም ዝውውር ስርአት ላይ ድንገተኛ እና ከባድ ጉዳት የሚያደርስ፣ መላውን የሰውነት አካል የሚያጠቃ ውስብስብ የህክምና ሁኔታ ነው።

2. ካልታከመ ወደ «ኤክላምፕሲያ» ይቀየራል!

ይህ በሽታ በጊዜ ታይቶ የደም ግፊቱ ካልተቆጣጠረ እና አስቸኳይ የሕክምና እርዳታ ካልተገኘ፣ በቀጥታ ወደ ኤክላምፕሲያ (Eclampsia) ይለወጣል። ኤክላምፕሲያ ማለት ነፍሰ ጡሯ እናት ላይ ከባድ የመንቀጥቀጥ (የሚጥል በሽታ መሰል) አደጋ እና ራሷን የመሳት ሁኔታ መከሰት ማለት ነው። ይህ ደግሞ ለእናቲቱም ሆነ ለፅንሱ ለሕይወት አስጊ የሆነ የመጨረሻው አስፈሪ ደረጃ ነው!

🚨 እያንዳንዱ እናት ልታውቃቸው የሚገቡ የድንገተኛ አደጋ ምልክቶች

በሽታው በውስጣችን የአካል ክፍሎችን እያጠቃ መሆኑን እና ወደ ኤክላምፕሲያ (መንቀጥቀጥ) እየተቀየረ መሆኑን የምናውቅባቸው ምልክቶች ስለሆኑ ሳይዘገዩ በአስቸኳይ ወደ ሆስፒታል መሄድ ያስፈልጋል

1. 🛑 በምንም አይነት ማስታገሻ የማይለቅ ከባድ የራስ ምታት (በአንጎል ላይ ጫና መኖሩን ያሳያል)

2. 🛑 የዓይን እይታ መስተጓጎል (ብዥ ማለት፣ በዓይን ላይ ጥቁር ነጠብጣቦች ማየት ወይም ብርሃን መፍራት)

3. 🛑 በሆድ የላይኛው ክፍል - በተለይ በቀኝ በኩል የሚሰማ ከባድ ህመም (ጉበት መጎዳቱን ያሳያል)

4. 🛑 የፊት፣ የእጅ እና የእግር ድንገተኛ እብጠት

5. 🛑 ለመተንፈስ መቸገር ወይም የትንፋሽ ማጠር (በሳንባ ውስጥ ፈሳሽ መከማቸቱን ያሳያል)

👥 ለዚህ ችግር ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑት እነማን ናቸው?

* ከዚህ ቀደም በነበረ እርግዝና ላይ የደም ግፊት ችግር የነበረባቸው እናቶች

* ለመጀመሪያ ጊዜ የፀነሱ እናቶች

* ከእርግዝና በፊት የቆየ ከፍተኛ የደም ግፊት፣
የስኳር ወይም የኩላሊት ህመም ያለባቸው

* መንትያ ልጆችን የፀነሱ እናቶች

የፕሪኤክላምፕሲያ በሽታ ምንም ውጫዊ ምልክት ሳያሳይ በውስጥ አካላችን ላይ ጉዳት ሊያደርስ እና በድንገት ወደ የሚጥል በሽታ (ኤክላምፕሲያ) ሊያመራ ይችላል። ስለዚህ እርጉዝ መሆንዎን ካወቁበት ቀን ጀምሮ ክትትልዎን ሳያቋርጡ ያድርጉ። የደም ግፊትዎን በየጊዜው መለካት የራስዎንና የልጅዎን ህይወት ይታደጋል!

🤰🏽በእርግዝና ወቅት የሚያጋጥሙ አደጋዎች እና ወሳኝ የጥንቃቄ እርምጃዎች በእርግዝና ወቅት ያልታሰቡ አደጋዎች (እንደ መውደቅ ወይም የመኪና አደጋ) ሲያጋጥሙ የራስዎን እና የፅንሱን ህይወት ለ...
27/07/2026

🤰🏽በእርግዝና ወቅት የሚያጋጥሙ አደጋዎች እና ወሳኝ የጥንቃቄ እርምጃዎች

በእርግዝና ወቅት ያልታሰቡ አደጋዎች (እንደ መውደቅ ወይም የመኪና አደጋ) ሲያጋጥሙ የራስዎን እና የፅንሱን ህይወት ለመጠበቅ ፈጣን እና ትክክለኛ እርምጃ መውሰድ ወሳኝ ነው። መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከ12 ነፍሰ ጡር እናቶች መካከል አንዷ በእርግዝና ጊዜዋ ውስጥ አደጋ (Trauma) ያጋጥማታል።

ለደህንነትዎ ሲባል ሁላችንም ልንገነዘባቸው የሚገቡ ዋና ዋና ነጥቦች እነሆ

🚨 ቀላል የሚመስሉ አደጋዎችን ችላ አይበሉ፡ አደጋው ቀላል ቢመስልም ወይም ሆድዎን በቀጥታ ባይመቱትም እንኳን (ለምሳሌ መንሸራተት እና መውደቅ)፣ በሆድ ውስጥ የእንግዴ ልጅ መላቀቅ (Placental Abruption) ሊያጋጥም ይችላል። 90% የሚሆኑት አደጋዎች ቀላል ቢመስሉም፣ ከ60 እስከ 70% ለሚሆነው የፅንስ ሞት ምክንያት ናቸው።

🚗 የደህንነት ቀበቶን በትክክል ይጠቀሙ፡

የመኪና አደጋ በእርግዝና ወቅት ከሚያጋጥሙ የአደጋ አይነቶች ውስጥ ቀዳሚው ነው። የደህንነት ቀበቶን በአግባቡ ማሰር የፅንስ ሞት አደጋን በእጅጉ ይቀንሳል።
ቀበቶውን ሲያስሩ : የታችኛው ክፍል ከሆድዎ በታች (በዳሌዎ አጥንት ላይ)፣ የላይኛው ክፍል ደግሞ በጡቶችዎ መካከል መሆን አለበት።

የአየርከረጢት (Airbag) : የመኪናዎ የአየር ከረጢት መጥፋት የለበትም፤ ከደህንነት ቀበቶ ጋር ተዳምሮ የተሻለ ጥበቃ ይሰጣል።

🏥 ወዲያውኑ ወደ ህክምና ተቋም ይሂዱ፡ ማንኛውም አይነት አደጋ ካጋጠመዎት ምንም አይነት የህመም ስሜት ባይኖርዎትም እንኳን ወደ ሆስፒታል መሄድዎን አይዘንጉ። የህክምና ባለሙያዎች ፅንሱን ቢያንስ ከ4 እስከ 6 ሰዓታትበቅርበት ክትትል (Fetal Monitoring) ሊያደርጉለት ይገባል።

⚠️ እነዚህን አደገኛ ምልክቶች ያስተውሉ፡ ከአደጋው በኋላ የሚከተሉትን ምልክቶች ካስተዋሉ በአስቸኳይ የድንገተኛ ህክምና እርዳታ ያግኙ

የሆድ ህመም ወይም የጀርባ ህመም
ከማህፀን ደም መፍሰስ
የማህፀን መወጠር ወይም የምጥ ስሜት
የፅንስ እንቅስቃሴ መቀነስ

የእርስዎ እና የልጅዎ ጤንነት ከምንም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው። ሁልጊዜም ጥንቃቄ ያድርጉ፤ አደጋ ሲያጋጥም ደግሞ ሳይዘገዩ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ!
ይህን የህብረተሰብ ጤና መረጃ ለሌሎች እናቶች እና ቤተሰቦች በማካፈል ግንዛቤ እንፍጠር!

08/06/2026

Address

Addis Ababa
0000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr. Ketsela Lemma Eshete Women’s Health & Reproductive Wellness posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share