Qulubi Times

Qulubi Times It is about drug and health information

Our Pharmacists⁉️▬እውነት 5 ዓመት ተምረዋል?--ጧት ማለት ስንት ሰዓት ነው?ማታ ማለት ስንት ሰዓት ነው?የእጅ ፅሑፉ ለታካሚ የሚገባ ነው?******  ---
28/08/2026

Our Pharmacists⁉️
▬
እውነት 5 ዓመት ተምረዋል?
--
ጧት ማለት ስንት ሰዓት ነው?
ማታ ማለት ስንት ሰዓት ነው?
የእጅ ፅሑፉ ለታካሚ የሚገባ ነው?
******

---

በመድኃኒት ረገድ የሀገሪቷን ትልቅ ራዕይ የሰነቀው ተቋም".....to see a competitive pharmaceutical industry"....🙏♦️▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ሀገራችን ኢትዮጵያ በመድኃኒ...
14/08/2026

በመድኃኒት ረገድ የሀገሪቷን ትልቅ ራዕይ የሰነቀው ተቋም
".....to see a competitive pharmaceutical industry"....🙏
♦️▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ሀገራችን ኢትዮጵያ በመድኃኒትና ተያያዥ ግብዓቶች ራሷን ለመቻል ከፍተኛ ጥረት እያደረገች ነው። ጥረቱም መዋቅራዊና ስትራቴጂካዊ ነው። ከዚህ ትልቁን ድርሻ የወሰደው አርሞውር ሃንሰን የምርምር ተቋም ነው። አርሞውር እና አርማወር እንደማያጣለን ተስፋ አደርጋለሁ።
▬▬▬
ይሄንን ተቋም ከስዊዲንና ከኖርዌይ ሀገራት ትብብር በመጋቢት 1962 ዓም ያቋቋሙት አፄ ኃይለስላሴ ነበሩ። ተቋሙም የተሰየመው በተለምዶ የስጋ-ደዌ(Leprosy) ተብሎ የሚታወቀውን በሽታ ባገኘው የኖርዌይ ተወላጅ ሳይንቲስት ጌራርድ ሄንሪክ አርሞውር ሃንሰን(Gerhard Henrick Armaeur Hansen) ነበር። ትኩረቱም ከዚያ የራቀ አልነበረም።
▬
ይሄ ተቋም በሚንስትሮች ምክር ቤት ደምብ 530/2015 እንደ አዲስ ከተቋቋመ በኋላ ምርምርን፣ፈጠራንና የመድኃኒት ኢንዱስትሪን በምርምር በታገዘ ሂደት የማሳደግን ኃላፊነት ተረከበ።
➠መድኃኒት ሲባል ባህላዊውንም፣ዘመናዊውንም ያጠቃልላል። ➠በተጨማሪ ተቋሙ የክትባት ምርቶች፣ዳያግኖስቲክስ፣የሕክምና መሳሪያ፣ባዮሎጂካዊ ምርቶችን ኃላፊነት(Mandate) ተቀብሏል።
➠ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችም አሉበት!
-------
ግዙፉ ተቋም ታዲያ ታላቅ ኃላፊ አግኝቷል። ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ ይባላል። ፕ/ር አፈወርቅ አቅሙና ልምዱ ከትህትናው ጋር ተደምሮ ለተቋሙ ግርማ ሞገስ ሆኗል።
****
አብረውት ምክትል ዳይሬክተሮቹ ዶ/ር አለምሰገድ አብዲሳና መሳይ ወልደማርያም አሉ። ወደ 10 የሚጠጉ ጠንካራ ዳይሬክተሮችም አሉ።
--
በተለይ ለባህላዊ መድኃኒቶችና ለknowledge management ቦታ መስጠታቸው ትልቅና ወሳኝ ጉዳይ ነው!
--
ተቋሙ ሲቋቋምም ጀምሮ አለም-ዓቀፋዊ ሚናን ሲጫወት ቆይቷል። አሁንም እየሰፋና ተጨማሪ ኃላፊነቶችን እየተረከበ ነው። ከዩኒቨርሲቲዎች ጋርም በቅርበት ይሰራል።
********
ከዚህ ተቋም ብዙ እንጠብቃለን፣ፍሬም እንደምናይ ሙሉ ተስፋ አለን!
********
🙏🙏🙏

14/08/2026
የመድኃኒት ሬጉሌሽን (Regulation) ጉዞ በኢትዮጵያ♦️▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬በአፄ ምንሊክ ጊዜና በአፄ ኃይለስላሴ ጊዜ ለፋርማሲ ሙያ የተሻለ መሠረት ተጥሎ ነበር። በጂኦርጂያው ሐኪም...
13/08/2026

የመድኃኒት ሬጉሌሽን (Regulation) ጉዞ በኢትዮጵያ
♦️▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
በአፄ ምንሊክ ጊዜና በአፄ ኃይለስላሴ ጊዜ ለፋርማሲ ሙያ የተሻለ መሠረት ተጥሎ ነበር። በጂኦርጂያው ሐኪም ዶ/ር ሜራብ ስለተከፈተው ታሪካዊ ፋርማሲ ባለፈው አንስተናል። የፋርማሲ ትምህርቱም ከዲፕሎማ እስከ ዲግሪ የተጀመረው ያነ ነበር።
➠የመጀሪያው መድኃኒት ፋብሪካም የተቋቋመው ያነ ነበር።
----
ዛሬ ስለ ሬጉሌሽን እናነሳለን።
--
በ1930ዎቹ አጋማሽ የፋርማሲስትና የዲራግስት አዋጅ (43/1942) ወጣ። ያ ባለሙያውንም፣ተቋሙንም የሚመመለከት አዋጅ ነበር። በ1950ዎቹ አጋማሽ ሙያውን ለመቆጣጠር የሚያመች ደምብ(Regulation 288/1964) ወጣ።ይህ ደግሞ የመድኃኒት ፋብሪካዎችንም፣ሽያጩንም የሚመመለከት ነበር።
▬
በደርግ ጊዜ በጤና ሚንስቴር ያለው የፋርማሲ ዲፓርትመንት ሁሉንም ስራ እንዲያከናውን ተደረገ።
---
በኢህአዴግ ጊዜ ወደ 1991 ዓም ገደማ ራሱን የቻለ የመድኃኒት ተቆጣጣሪ አካል በአዋጅ (176/1999) እንዲቋቋም ተደረገ። የተቋሙም ስም የመድኃኒት አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን (Drug Adminstration and Control Authority-DACA) ይባል ነበር። የዚህ ታሪካዊ ተቋም ኃላፊም አቶ ኃይለስላሴ ቢሆን ሆነ። ተቋሙ ለተቋማት ፈቃድ መስጠትም(licensing) ቻለ።
▬▬▬▬
በ2000/1 ዓም ይሄ ተቋም በአዋጅ (661/2009) ወደ ግዙፍ ተቋም አደገ። ምግብንም፣የጤና ተቋማትንም፣ባለሙያዎችንም እንዲቆጣጠር ተደረገ። ስሙም የምግብ፣የመድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን (Food,Medicine and Healthcare Adminstration and Control Authority-FMHACA) ተባለ። በዚህን ጊዜ አቶ ኃይለስላሴ የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎትን(በወቅቱ PFSA ይባል ነበር) እንዲመራ ስለተዛወረ አቶ የሁሉ ደነቀው FMHACAን እንዲመራ ተደረገ።
▬▬
ከ2010 ዓም በኋላ ሄራን ገርባ ተቋሙን እንድትመራ ተሾመች። በዚህም የመጀመሪያዋ ሴት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ሆነች።
----
በሄራን አስተዳደር ጊዜ ተቋሙ ሪፎርም ተደርጎ ምግብ፣ መድኃኒት፣ኮስሞቲክስና የሕክምና መሳሪዎች ላይ ብቻ እንዲያተኩር ተደረገ። በተጨማሪም ቶባኮንና አልኮልንም እንዲቆጣጠር ተደረገ። ባለሙያንና የጤና ተቋማትን የሚመለከት ቁጥጥር ወደ ጤና ሚንስቴርና ጤና ቢሮዎች እንዲመለሱ ተደረጉ። በ2013 አካባቢ የአሁኑን ስም (EFDA) በአዋጅ (1263/2021) ያዘ። በደምብ(531/2023) ም ያለማንም ጣልቃ ገብነት ስራውን እንዲሰራ አቅጣጫ ተቀመጠ።
-
ተቋሙ በአጭር ጊዜያት ብዙ ውጣ ውረዶችን አሳልፏል። ብዙ ስኬቶችንም አስመዝግቧል።
▬
➠ራሱን ችሎ መቆሙ ራሱ አንድ ስኬት ነው!
➠ላብራቶሪዎች ተገንብተዋል።
➠በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር ተዘርግቷል።
➠Clinical trialን የመቆጣጠር አቅም አዳብሯል።
➠ቶባኮና አልኮል ቁጥጥር ላይ ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሻግሯል።
➠በመድኃኒት ቁጥጥር ረገድ የWHO maturity level-3ን አግኝቷል። የምግብ፣የክትባትና ሕክምና መሳሪያ ይቀራል!
▬
ፈተናዎች አሁንም አሉ። ፈተናዎቻቸውን እነርሱም ያውቃሉ። ያንን በሂደት እየፈቱ በአፍሪካ ግዙፉ የሬጉሌተሪ ተቋም ይሆናሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን።
▬▬▬▬▬▬▬
🙏🙏🙏

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ተቋም ጉዞ          ➠"EPSS መስሪያ ቤት ሆኗል"♦️▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🔹🔹-ስሙን ብዙ ጊዜ ቀያይሯል ‼️1-Pharmacy Store2-Epharmcore ...
13/08/2026

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ተቋም ጉዞ
➠"EPSS መስሪያ ቤት ሆኗል"
♦️▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🔹🔹-ስሙን ብዙ ጊዜ ቀያይሯል ‼️
1-Pharmacy Store
2-Epharmcore
*በዚህን ጊዜ ብቸኛው የኢትዮጵያ መድኃኒት ፋብሪካ (EPHARM) ተጠሪነቱ ለEpharmcore እንደነበር ሰምተናል!
3-PHARMED
4-PFSA
5-EPSA........EPSS
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🔸🔸-ኃላፊዎቹንም ብዙ ጊዜ ቀያይሯል ‼️
የመጀመሪያው የተቋሙ ኃላፊ አቶ ታዲዮስ ጌታሁን ነበሩ።
ቀጥሎ አቶ ተስፋዬ ደገፋ፣አቶ ላዕከዐገብረስላሴ፣አቶ ብርሃኑ ዘለቀ፣አቶ ግርማ በዳሶ፣አቶ ኃይለስላሴ ቢሆን፣አቶ መስቀሌ ሌራና ዶ/ር ሎኮ አብርሃም ተቋሙን ለአጭርና ለረጅም ጊዜ መርተውታል።
አሁን EPSSን እየመራ ያለው ዶ/ር አብዱልቃዲር ገልገሎ ነው!
▬▬▬▬▬
ለምሳሌ አቶ ታዲዮስና አቶ ተስፋዬ ከ3 ዓመት በታች የመሩ ሲሆን አቶ ብርሃኑና አቶ ኃይለስላሴ ከ5 ዓመት በላይ፣አቶ ግርማ በዳሶ ከ10 ዓመት በላይ መርቷል። ቀሪዎቹ ከ3-5።
-------
በአፄ ኃይለስላሴ ዘመን የተቋቋመ ዕድሜ ጠገብ ተቋም እንደመሆኑ መጠን 9 ኃላፊዎች ቢፈራረቁበት አይገርምም። እንዲያውም ትንሽ ነው። ምናልባት ስሙን 5 ጊዜ መቀየሩ ነው ጥያቄ የሚያጭረው። ከዚህ በኋላ ይቀይራል ብለን አንጠብቅም!
*******
የስም ለውጥ ብቻውን ተቋምን ይለውጣል ብለን ባናምንም የኃላፊዎች ለውጥ ግን ለውጥ እንደሚመያጣ አይተናል።በርግጥ ኃላፊውን የሾመው መንግስትም ከኃላፊው ጋር መተባበር የራሱ የሆነ አዎንታዊ ተፅዕኖ እንዳለው ብናውቅም የኃላፊው የአመራር ብቃትና ቁርጠኝነት ከፍተኛ ድርሻ አለው። በአጠቃላይ መልኩ እስካሁን ተቋሙን የመሩት የተቋሙ ኃላፊዎች የበበኩላቸውን ጥረት አድርገዋል፣ለውጥም አምጥተዋል። ለውጡ ግን ውሱን ነበር።
▬▬
በአሁኑ ኃላፊ (The Incumbent General Directpt) የመጣው ለውጥ ግን አስደናቂ ነው። ለውጡ ግዙፍ ስለሆነ በዚህች ፅሑፍ አንዳስሰውም! ምስጢሩ ግን የአመራር ብቃት፣ ቁርጠኝነት.......እና የጋራ ራዕይና ተቋሙ የኔ ነው የሚለውን ስሜት(Team Spirut) ማስረፅ ነው። ከዚያ አቅምን መገንባት ነው። በተጨማሪ ተጠያቂነትን (Accountability) መተግበር ነው። በመጨረሻም በቴክኖሎጂ የታገዘና ጥራት ያለው፣ደረጃውን የጠበቀ አሰራርን ከHead እስከ toe መዘርጋት ነው። ሲጨመቅ ይሄ ሁሉ ተቀናጅቶ ተፈላጊ መድኃኒቶችን በሚፈለጉበት ቦታ በአግባቡና በወቅቱ በማድረስ ረገድ እንዲገመገም ማድረግ ነው። የሆነው ይሄ ነው!
----
አንድ የሌላ ተቋም EPSSን ከጎበኘ በኋላ ያለውን አባባል ጠቅሼ ልጨርስ "EPSS መስሪያ ቤት ሆኗል" ነው ያለው!
▬▬
🙏🙄

13/08/2026
አንድ ሰው በአጋጣሚ ያጫወተኝ ነገር አስገርሞኛልም፣አስደንቆኛልም።▬▬▬▬ለአጭር ጊዜ የመስክ ስራ ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ ሄዶ ሕመም ቢጤ ይሰማዋል። ከዚያ ከልምድ የሚያውቀውን ኤዝትሮማይሳን...
11/08/2026

አንድ ሰው በአጋጣሚ ያጫወተኝ ነገር አስገርሞኛልም፣አስደንቆኛልም።
▬▬▬▬
ለአጭር ጊዜ የመስክ ስራ ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ ሄዶ ሕመም ቢጤ ይሰማዋል። ከዚያ ከልምድ የሚያውቀውን ኤዝትሮማይሳን (Azithromycin) መድኃኒት ለመግዛት ወደ አንዱ ፋርማሲ ጎራ ይላል። ማዘዣ ጠየቁት። አካባጅ፣ያለ አንተ ፋርማሲ የለም ወይ ብሎ ወደ ሌላ ይሄዳል። ተመሳሳይ ነገር ገጠመው። እስከ 5 ሞከረ....ተበሳጨ፣ተስፋ ቆረጠ‼️
▬
ወደ አዲስ አበባ ተመለሰ። እርግጠኛ ሆኖ ወደ አንዱ ፋርማሲ ገባ፣....ለምን ፈለግህ ራሱ አላሉትም። ብራንድና ዋጋ ነበር ያማረጡት....መርጦ ገዛ።
----
አንድ ወስጄ ተሻለኝና ሌላውን ተውኩት አለኝ።
********
ተወያየን፣ከተወያየን በኋላ የድሬዳዋ ፋርማሲዎችን አድንቆ፣ ተፀፅቶ ይቅርታዬ ይድረስልኝ ብሏል። መድኃኒቱን የጀመረበት መንገድም፣ ያቆመበት መንገድም ትክክል እንዳልሆነም ተገንዝቧል።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬
እኔም የድሬዳዋ ፋርማሲዎችን ላመሰግን እፈልጋለሁ። በርቱ፣በዚሁ ቀጥሉ እያልኩኝ፣መጠነኛ ምክር መጨመር እፈልጋለሁ። በፋርማሲ ውስጥ ማዘዣ በማይፈልጉ መድኃኒቶች(Over The Counter-OTC) የመጀመሪያ ደረጃ ሕክምና መስጠት ይቻላል። ለምሳሌ ተገልጋዩ ኤዝትሮማይሲን ጠየቀ.....ያለ ማዘዣ አይሰጥም የሚለው መልስ ትክክል ነው። ግን በቂ አይደለም። ችግሩን ጠይቀን፣ የሕመም ስሜቶቹን (symptoms)፣ ምልክቶቹን(signs)ገምግመን በቀላሉ የሚታከም ከሆነ እዚያው ማዘዣ በማይፈልጉ መድኃኒቶች ሕክምና ማግኘት እንደሚችል አስረድቶ አገልግሎቱን መስጠት ይቻላል። ከዚያ አቅም በላይ ከሆነ ወደ ሐኪም መምራት(referral) ያስፈልጋል።
-------------
የአዲስ አበባ ፋርማሲዎችን ለመምከር አልሞክርም። ችግሩ የማወቅና ያለማወቅ አይመስለኝም!
➠ብዙ በስነምግባር የሚሰሩ እንዳሉ አውቃለሁ፣ከዚያ የሚያፈነግጥም ቁጥሩ ቀላል አይደለም።
*********
🔸🔹-ለማንኛውም፣
ኮሙኒቲ ፋርማሲዎች ብዙ ኃላፊነቶችን ለመረከብ መዘጋጀት አለባቸው። የጊዜ እጥረትም ይፈትናቸዋል ብዬ አላምንም።
----
🙏
----
Dire Dawa Administration Health Bureau

Addis Ababa Health Bureau

11/08/2026

የአፋር ክልል ጤና ቢሮ ተሸላሚ ሆነ
_________

የአፋር ክልል ጤና ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በክልሉ የተሻለ አፈጻጸምና ውጤት ካስመዘገቡ አምስት የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ውስጥ አንደኛ ደረጃ በመሆን ተሸላሚ ሆኗል።

ቢሮው በክልል በጀት አጠቃቀምና በኦዲት ሥራዎች ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው አሰራር በመከተሉ በኦዲት የሽልማት ዘርፍም የላቀ ውጤት ካሳዩ ተቋማት አንዱ በመሆን በደጋሜ ተሸልመዋል።

ይህ የተመዘገበው ስኬት ከጤና ተቋማት እስከ ክልል ቢሮ ድረስ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችና አጋዥ ሠራተኞች የጋራ ጥረትና የትብብር ውጤት መሆኑ ተገልጿል።

Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Qulubi Times posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share