Ethio Amazone

Ethio Amazone ➠import and export Ethiophian information center

02/12/2021

ለተወሰነ ጊዜ ትምህርት ተዘግቶ የዘማቾች ሰብል እንዲሰበሰብ ውሳኔ ተላለፈ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2014 የትምህርት ማህበረሰቡ ለህልውና ዘመቻው ደጀን እንዲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ከህዳር 27 እስከ ታህሳስ 3 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ዝግ እንደሚሆን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታወቁ፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ትምህርት በሚዘጋበት በዚህ ወሳኝ ወቅት መምህራን አገራዊ ድርሻቸውን እንዲወጡ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

መምህራኑ ሰብል በመሰብሰብ እንዲሁም በስንቅ ዝግጅት ጭምር ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባም ገልጸዋል።

ለተማሪዎችም የሚዘጋው የትምህርት ጊዜ ማካካሻ የሚሰጣቸው ሲሆን÷ ዝግ በሚሆንበት ሳምንት ለአገራቸው ጥሪ የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

አገርን በጋራ ለማቆም በሚደረገው ትግል ውስጥ የትምህርት ማህበረሰቡን ተሳትፎ ለማጠናከር የትምህርት ሚኒስቴር እና ክልሎች ስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል ።

ፋና እንደዘገበው:-

09/09/2021
06/05/2021

ሰበር ዜና🚨

ትምህርት ሚንስቴር ማለፊያ ነጥብ ዝቅ ለማድረግ ወሰነ

ሙሉ መረጃ ለማግኘት👇

👉OPEN👈

01/05/2021

🕺 በዚህ አመት ዩኒቨርሲቲ የምትገቡ የ ተፈጥሮ ሳይንስ( Natural science) ተማሪዎች በመጀመሪያው ሴሚስተር ስለምትወስዷቸው ኮርሶች መረጃ።

✍✍ በ Concise ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ።

የመጀመሪያ አመት የመጀመራያው ሴሚስተር ላይ የ ተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የምትወስዷቸው ኮርሶች👇👇👇

🪤 MATHEMATICS ( for natural science)

🪤GENERAL PHYSICS

🪤 GEOGRAPHY

🪤LOGIC & CRITICAL THINKING

🪤 COMMUNICATIVE ENGLISH SKILL

🪤 PSYCHOLOGY

🪤 PHYSICAL FITNESS

🥺 እስኪ አሁን ደግሞ እያንዳንዱን ኮርሶች እንመልከት።

❇️ MATHS

11 ኛ እና 12 ኛ ክፍል የተማራችሗቸው ናቸው አብዛሀኞቹ ፡ የተወሰነ ለውጥ( modification) ነው ያለው። ስለዚህ ብዙም አትቸገሩበትም ፡ አሪፍ ውጤት መስራት ትችላላችሁ በደንብ ካነበባችሁ👌። A 🙈

❇️ General Physics

ይኸም 11 ኛ እና 12 ኛ የተማራችሗቸው ናቸው አብዛኞቹ👌።

❇️ Logic and critical thinking

ይህ course ለእናንተ አድስ ነው። ምክንያታዊነት እና ፍልስፍስና የትምህርቱ መሰረት ናቸው። የ concept ተማሪ ከሆናችሁ እና English ቋንቋ የምትሞክሩ ከሆናችሁ ትሰሩታላችሁ። ይህ ኮርስ በዋናነት የእናንተን የመረዳት ክህሎት ይጠይቃል ፡ እጅግ በጣም በጣም በጣም ደስ የሚል ኮርስ ነው🙈። ነገር ግን ጥልቅ ንባብ እና መረዳት ይጠይቃል ። ላይ ላዩን ማንበብ የለባችሁም☹️።

ለማንኛውም ለ logic and critical thinking የሚያግዝ እጅግ በጣም ምርጥ አጋዥ መፅሀፎች አሉ።

1ኛ) Concise introduction to logic

2ኛ) freshman logic

📌 Concise introduction to logic የሚለው መፅሀፍ በጣም አሪፍ አድርጎ ያስረዳል። በጣም አሪፍ አሪፍ የሚባሉ እና ከበድ ያሉ ጥያቄዎችም አሉት😴። የዚህን መፅሀፍ ጥያቄዎቹን ገብቷችሁ በአግባቡ ከሰራችሁ ፡ በእርግጠኝነት ግቢ ላይ የሚወጣውን ፈተና ትሰሩታላችሁ😸 ምክንያቱም የከባድ ጥያቄዎች ጣሪያ የሚባሉ ጥያቄዎች መፅሀፉ ላይ አሉ። ኸረ እንዳውም ከመፅሀፉ Exercise ላይ ያሉትን ጥያቄዎች ፈተና ላይ ቀጥታ ያወጡታል🙈🙈። የግቢ መምህሮች በጣም የሚጠቀሙት መፅሀፍ ነው👏👏።

📌 Freshman logic የሚለው መፅሀፍ ደግሞ የ logic and critical thinking ትምህርትን በቀላሉ እንድትረዱት ያደርጋል ምክንያቱም በ አማርኛ እየተረጎመ ስለሚያስረዳ👏😘። የትምህርቱን ፅንሰ ሀሳብ ( concept) በቀላሉ ለመረዳት freshman logic የሚለው መፅሀፍ በጣም ምርጥ ነው። በዛ ላይ እጅግ በጣም ደስ ደስ የሚሉ የ concept ጥያቄዎችም አሉት😴😍። ስለዚህ እኛ የምንመክራችሁ

1ኛ) መምህሩ የሚሰጣችሁን ኖት ፡ ፒዲኤፍ ማንበብ ፡መምህሩ ሲያስተምር በ ደንብ መከታተል። ጥሩ አድርጎ የማያስተምር መምህር ሊያጋጥማችሁ ስለሚችል ነባር ተማሪዎችን ጠይቆ መረዳት።

2ኛ) freshman logic የሚለውን መፅሀፍ ማንበብ ምክንያቱም መፅሀፉ ላይ የቀረቡት ኖቶችን በቀላሉ ስለምትረዷቸው።

3ኛ) Concise introduction to logic የሚለው መፅሀፍ ላይ ሂዳችሁ ጥያቄ መፍለጥ🕺 ፡ የሚገራርሙ ጥያቄዎች አሉት😴። ከዛ A+ ታመጡና መቀወጥ🕺💃🕺💃😁😁።

❇️ Communicative English skill

ይህ ኮርስ ላወቀበት ተማሪ የሚሰራ ኮርስ ነው፡ ግቢ ላይ ውጤታችሁን ከሚያነሱ ኮርሶች መካከል ነው🙈። በውስጡ ምን ምን ይዟል መሰላችሁ🤔

📌 Speaking skill ( ራሳችሁን በ እንግሊዝኛ ማስተዋወቅ🙈 ፡ ከዛ መምህሩ የሆነ ርዕስ ይሰጣችሁ እና ስለዛ ነገር በ እንግሊዝኛ presentation ማቅረብ (የሆነ ማርክ%)

📌 Reading skill ( አንድ passage ይሰጣችሗል ፡ በዛ መሰረት ጥያቄ ይሰጣችሗል( የሆነ ማርክ%)

📌 Writing skill ( letter , descriptive , narrative,argumentative , expository ከነዚህ ባንዱ ትፅፋላችሁ( ከዛ የሆነ ማርክ)

Grammar ( Tense , Active and passive voice , conditional sentence, reported speech ... እነዚህ ነው የምትማሩት ፡ ደግሞ ቀላል ናቸው ፡ Concise ላይ የተለቀቁ ኖቶችም ሊጠቅማችሁ ይችላል።)

❇️ Geography

ለ Geography ም አዲስ አይደላችሁም።

❇️ Psychology

ይህ ኮርስ በብዙ መልኩ አድስ ሊሆንባችሁ ይችላል ፡ ግን biology ማንበብ ስለለመዳችሁ አትቸገሩም። theory ነው ፡ ከእናንተ የሚጠበቀዉ ማንበብ ብቻ ኘው።

❇️ Physical fitness

ሜዳ ወጥታችሁ ሱምሶማ መስራት መሮጥ ነው😁። ስለዚህ የ ስፖርት ትጥቅ ያስፈልጋችሗል ፡ እንዳትረሱ😂። ይህ ኮርስ ውጤት የለውም ማለቴ ውጤት አይሰራለትም ዝም ብላችሁ ሜዳ ወታችሁ ትሰራላችሁ እንጅ Grade ( A , A- , B+ ,B , C ....) የለውም። pass or fail ነው የምትባሉት። Attendance ወይም በዚህ ኮርስ ክፍለ ጊዜ ካልቀራችሁ pass ትሆናላችሁ።

እሽ እስከአሁን የ natural science ተማሪዎች የመጀመሪያው ሴሚስተር ላይ የምትወስዷቸውን ኮርሶች አየን።

🥺 ነገር ግን አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች የመጀመሪያው ሴሚስተር ላይ በ Logic and critical thinking ቦታ emerging technology የሚያስተምሩ አሉ ። ከዛ second semester ላይ ደግሞ logic and critical thinking ያስተምራሉ። ብቻ ምንም ለውጥ የለውም ፡ እንድታውቁት ያክል ነው።

❇️ Emerging technology

ይህ ኮርስ ለእናንተ አዲስ አይደለም። ከ 9 - 12 የተማራችሗቸው የ Ict ትምህርቶችን ያካትታል ( Ms word , Ms PowerPoint, Ms excel , database ..... ወዘተ)

በቃ አለቀ። እነዚህን ኮርሶች ወስዳችሁ እንደጨረሳችሁ

ህክምና ( Medicine , Dental Medicine , Veterinary medicine , pharmacy...) መግባት የምትፈልጉ

ቴክኖሎጂ( Engineering, Architecture, Computer science, It , software engineering...) መግባት የምትፈልጉ

ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇

ሼር ═══◉❖◉════

30/03/2021

የ2012ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ከግማሽ በላይ ተማሪዎች ከ350 በላይ ማምጣታቸው ተገለፀ❗️

⚡️የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን በተመለከተ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል።

⚡️የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዲላሞ ኦተሪ(ዶ/ር) የ2012ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በተመዝጋቢ፣ በተፈታኝም እንዲሁም በውጤትም ደረጃ ከፍተኛ መሆኑ ገልፀዋል።

⚡️ ፈተናውን ከወሰዱ አጠቃላይ ተፈታኞች ውስጥ 55.7 ፐርሰንቱ ከ 350 በላይ አምጥተዋል።

⚡️ በመግለጫው የፈተና ውጤት ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የተሻለ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም ከ 600 በላይ ያመጡ ተማሪዎች 702 መሆናቸው ተገልጿል።

⚡️የዓመቱ ከፍተኛ ውጤትም 669 ሆኖ መመዝገቡን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል ።

⚡️ተማሪዎችም ውጤታቸውን በፈተናዎች ኤጀንሲ ድረገፅ እንዲሁም በአጭር የፁሁፍ መልዕክት 8181 የፈተና መለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ከነገ ጀምሮ ውጤታቸውን መመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል።

⚡️ወደ ዪኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜን እና ማለፊያ ነጥብን በተመለከተ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር እየተሰራ መሆኑም ዳይሬክተሩ በመግለጫው አስታውቀዋል።

23/03/2021

Braking news

12ተኛ ክፍል ፈተና ላይ አይመጣም የተባልነው Part ፈተናው ላይ መጥቶ ነበረ ብላቹህ ለጠየቃችሁት ጥያቄ ትምህርት ሚኒስቴር በሰጠውን መግለጫ ፈተናው ሙሉ ለሙሉ የወጣው ቃል በገባነው መሰረት 11ኛ ክፍል ከተማሩት ሁለት ሴሚስተር እና 12ኛ ክፍል ከተማሩት የመጀመሪያ ሴሚስተር ብቻ ነው በማለት ምላሽ ሰተዋል።

ሼር ═══◉❖◉═══

22/03/2021

Grade 12
የ 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት በቅርብ ጊዜ ይገለፃል

የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መጠናቀቁን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫውም ከየካቲት 29 - መጋቢት 02 ,2013ዓ.ም ሲሰጥ የነበረው የ2012ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ የሁሉም ድርሻ ከፍተኛ እንደነበረ ገልፀው ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላት፣ ተማሪዎች እና ወላጆች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

እንደ ሀገር የተለያዩ ውሳኔዎችን በማስተላለፍ የትምህርት ጊዜ ወደ ኋላ እንዳይቀር እና የተማሪዎች የትምህርት ዘመን እንዳይራዘም መደረጉንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

በዘንድሮው የፈተና አሰጣጥ ስርቆትን ለማስቀረት 8 ፈተናዎችን በ 32 ስብጥር በማድረግ ኩረጃ እንዳይኖር መደረጉም በመግለጫው ተነስቷል።

የፀጥታ ችግር ያለባቸውን አካባቢዎች ጨምሮ በሁሉም ክልሎች ፈተናውን በስኬት ማጠናቀቅ መቻሉንም ሚኒስትሩ በመግለጫው አንስተዋል።

የሀገር አቀፍ ፈተና ውጤቱም በቅርብ ጊዜ እንደሚገለፅ እና ተፈታኞችም በዚሁ አመት ወደ ዩኒቨርስቲ እንደሚገቡ ተገልጿል።

የ2012 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተናውን ከ 358 ሺህ በላይ ተማሪዎች መውስዳቸው ተነግሯል

ምንጭ፡- ትምህርት ሚኒስቴር

F•R•I•E•N•D•S 🎮 Game zone and lounge bahirdar Ethiostar hotel 1st floor 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
01/03/2021

F•R•I•E•N•D•S
🎮 Game zone and lounge
bahirdar Ethiostar hotel
1st floor 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Amazone posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio Amazone:

Share