11/09/2026
Amen 🙏
በአዲስ ዓመት ዋዜማ በሞተር ሳይክል አደጋ የC6 አከርካሪ አጥንት ስብራት ደርሶብኝ ነበር። በእግዚአብሔር ፀጋ ተርፌያለሁ። ስብራቱን ያወቅኩት ከአደጋው በኋላ የተሰማኝ የእጅ መደንዘዝ ምክንያት ምርመራ ሳደርግ ነው።
የC6 ጉዳት በጊዜው ካልታወቀና ካልታከመ ከባድ የነርቭ ጉዳትና አራቱም እጅና እግሮች ሽባ መሆን (quadriplegia) ሊያስከትል ይችላል። ስለዚህ ከአደጋ በኋላ ምንም እንኳን ትንሽ ምልክት ቢኖር አስቸኳይ የሕክምና ምርመራ አድርጉ።
በዚህ አጋጣሚ በመጀመሪያ እግዚአብሔርን ከልብ አመሰግናለሁ፤ ሕይወቴን ስለጠበቀኝና ከዚህ አደጋ ስላዳነኝ። 🙏❤️
እንዲሁም ለዶ/ር በረከት ኃይሉ፣ ኒውሮሰርጀን በSoddo Christian Hospital (SCH) ላደረጉልኝ እንክብካቤ፣ ሙያዊ እገዛና ትጋት ከልብ አመሰግናለሁ። እንዲሁም ለመላው የSCH ሰራተኞች ላደረጋችሁልኝ እንክብካቤ፣ ድጋፍና ትብብር በጣም አመሰግናለሁ።
ይህ ዓመት ጤና ፣ ሰላምና በረከት ይዞ ይምጣ። በተለይም በትራፊክ አደጋ ጊዜ እባካችሁ በጣም ተጠንቀቁ።
እግዚአብሔር ሁላችሁንም ይጠብቅ። መልካም አዲስ ዓመት! ❤️🙏
ዶ/ር ጌትነት ኤልያስ: ጠቅላላ ሐኪም
Telegram: t.me/HakimEthio