Hiruy Hcare

Hiruy Hcare Medical doctor, PH expert, Hiruy Hcare-Service and art, Digital health and telemed advocate(mhealth), Healthcare marketing.

16/11/2025
12/11/2025
📍Happy New Year 2018 EC📍! 🎯Hiruy Hcare wishes all Families new year filled with good health, wellness , and fresh beginn...
10/09/2025

📍Happy New Year 2018 EC📍!
🎯Hiruy Hcare wishes all Families new year filled with good health, wellness , and fresh beginnings.As we celebrate, let’s care for our health.
Hcare
Hiruy Hcare

✨Medical innovation✨tiny robots rocks down kidney stons👏👏👏👏
28/08/2025

✨Medical innovation✨
tiny robots rocks down kidney stons
👏👏👏👏

✨ሱካር ህመም በሚከተሉት ምርመራዎ እንደሚረጋገጥ ያውቃሉ✨1-ምግብ ሳይበሉ በሚደረግ የደም ምርመራ(FBS)>=126mg/dl ከሆነ2-በማንኛውም ሰዓት በሚሰጥ ምርመራ(RBS)>=200mg/dl3- ...
28/08/2025

✨ሱካር ህመም በሚከተሉት ምርመራዎ እንደሚረጋገጥ ያውቃሉ✨
1-ምግብ ሳይበሉ በሚደረግ የደም ምርመራ(FBS)>=126mg/dl ከሆነ
2-በማንኛውም ሰዓት በሚሰጥ ምርመራ(RBS)>=200mg/dl
3- የ 3 ወር አማካይ የስኳር መጠን (HbA1c) >6.5 ከሆነ.

✨Diabetic diet ✨
14/07/2025

✨Diabetic diet ✨

ሰላም የ "Hiruy Hcare" ቤተሰቦች👋 በአለማችን 11.1% የሚሆኑ ከ20-79 የእድሜ ክልል ያሉ ሰዎች ከስኳር ህመም ጋር አብረው ይኖራሉ (International diabetes federa...
13/07/2025

ሰላም የ "Hiruy Hcare" ቤተሰቦች👋

በአለማችን 11.1% የሚሆኑ ከ20-79 የእድሜ ክልል ያሉ ሰዎች ከስኳር ህመም ጋር አብረው ይኖራሉ (International diabetes federation 11th edition -Atlas 2025).

🎯የስኳር በሽታ ምንድነው?
• የስኳር በሽታ በደምዎ ውስጥ የስኳር መጠን በላይ ሲሆን የሚከሰት ህመም ነው።

🎯 የሚከሰትባቸው መንገዶች
►ሰውነትዎ በቂ ኢንሱሊን ሳይሠራ ሲቀር እና
►ሰውነታችን ኢንሱሊንን በትክክል ሳይጠቀም ሲቀር (insulin resistance) የሚከሰት ነው።

🎯ዓይነቶች በ4 የሚከፈል ሲሆን በብዛት የሚታወቁት የሚከተሉት ናቸው

►Type 1 Diabetes
✨በተለይ በህጻናት እና በወጣትነት ይጀምራል።
✨ኢንሱሊን በሰውነታችን ሳይመረት ሲቀር ።
✨ይህም ዕለት ከዕለት ኢንሱሊን መድኃኒት ያስፈልጋል።

►Type 2 Diabetes
✨የተለመደው እና በብዛት የሚከሰተው ነው ።
✨እድሜ ሲጨምርና በአዋቂዎች ላይ የሚከሰት ሲሆን ነገር ግን አሁን በወጣቶች የመከሰት እድሉ በመጨመር ላይ ነው (በውፍረት ምክንያት)።
✨ሰውነት ኢንሱሊንን በትክክል ካለመጠቀም እና በሂደት የኢንሱሊን መመረት መቀነስ ሲከሰት።

► ሌላው በእርግዝና ወቅት የሚከሰት ሲሆን ወደ Type 2 የመቀየር እድሉ ከፍተኛ ነው።

🎯ማወቅና መመርመር ለምን አስፈላጊ ነው?
📍የዓይን ችግር (ዓይነስውርነት)
📍የኩላሊት ጉዳት
📍የነርቭ ጉዳት (ህመም, የእግር ቁስለት-የማድን ቁስል)
📍Heart attack, Stroke
📍ዋና ዋናዎቹ ችግሮች ሲሆን በተጨማሪም በርካታ የጤና እክሎች ይዳርጋል።

🎯ምልክቶች
📍ከፍተኛ (የረሀብ ስሜት, ውሃ ጥማት, ሽንት መብዛት
📍ክብደት መቀነስ( በተለይ type 1)
📍ድካም

እነዚህንና መሰል ምልክቶችን ካዩ በደምዎት ውስጥ ያለውን የሱካር መጠን በምርመራ ማወቅ ይጠበቅብዎታል።

ዶ/ር ኅሩይ ተክሌ
Hcare

መረጃውን ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ🙏
►መልካም ምሽት◄

ሰላም የ "Hiruy Hcare" ቤተሰቦች👋 በተለምዶ ባት በሚባለው የእግራችን ክፍል “ሁለተኛ ልብ” እንዳለ ያውቃሉ? ይህ ቃል ለእግር ጡንቻችን የተሰጠ ስም ነው፣ ምክንያቱም በጣም አስደናቂ ...
12/07/2025

ሰላም የ "Hiruy Hcare" ቤተሰቦች👋

በተለምዶ ባት በሚባለው የእግራችን ክፍል “ሁለተኛ ልብ” እንዳለ ያውቃሉ?

ይህ ቃል ለእግር ጡንቻችን የተሰጠ ስም ነው፣ ምክንያቱም በጣም አስደናቂ ነው።

ስንራመድ ፣ ዳገት ስንወጣ፣ ወይም ስንቆም ፣ ጡንቻወቻችን ተጠንክረው ይቆማሉ እና እንደ ተፈጥሮ Pump( ማውጫ) ይሆናሉ። ደምን ወደ ከስበት ህግ በተቃራኒ ላይ ወደ ወደ ልብ እንዲሄድ ይረዳሉ🩸❤

ጥቅሞቹስ?
✔ የደም ዝውውርን ያፋጥናል.
✔ በእግር ደም እንዳይረጋ ይከላከላል.
✔ በደም ስር መለጠጥ ምክንያት የሚመጣ እብጠትን ፣ የህመም ምልክትን ይቀንሳል.
✔ የደም መርጋት (DVT) እና ተያያዥ ጉዳቶችን ይቀንሳል.

ይህ የሚከናወነው በጡንቻችንና በደም ቫልቮች ምክንያት ነው፣ ይህም ደም ወደ ታች እንዳይመለስ ይከላከላል።

👉 ስለዚህ ብዙ መቆም ወይም መቀመጥ ጉዳት አለው ፣ ቀለል ያለ እንቅስቃሴም ቢሆን የደም ዝውውር እንዲሻሽል ይረዳል።

💡 የምንወደው እያንዳንዱ እርምጃ ለልባችን ስጦታ ነው። መራመድ፣ መንቀሳቀስ፣ መዝለውወጥ… እነዚህ ቀላል ነገሮች ቢሆኑም ለጤና አስፈላጊ ናቸው።

❤️ NB፦ እግራችንን መንከባከብ ልባችንን መንከባከብ ነው።

ዶ/ር ኅሩይ ተክሌ (MD, Digital H & Telemed enthusiast- certified)
Hcare,
መረጃውን ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ🙏
►መልካም ምሽት◄

ሰላም የ "Hiruy Hcare" ቤተሰቦች👋 ስለ ቴሌ ህክምና( Telemedcine) ምን ያህል ያውቃሉ?✨🎯በአሁኑ ሰአት ቴሌህክምናን በመጠቀም ታካሚ ወደ ሀኪሙ ሳይሆን ሀኪሙ በይበልጥ ወደ ታካ...
07/05/2025

ሰላም የ "Hiruy Hcare" ቤተሰቦች👋

ስለ ቴሌ ህክምና( Telemedcine) ምን ያህል ያውቃሉ?
✨🎯በአሁኑ ሰአት ቴሌህክምናን በመጠቀም ታካሚ ወደ ሀኪሙ ሳይሆን ሀኪሙ በይበልጥ ወደ ታካሚ እየቀረበ ይገኛል, ለዚህም አስተዋፅኦ የሚያደርገው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ያለው የቴሌ ህክምና ነው.
✨🎯ቴሌህክምና(Telemedcine) ማለት ታካሚው በአካል ወደ ጤና ተቋም ሳይሄድ የታካሚን መረጃ በተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ መንገዶች በመጠቀም የህምናውን ውጤት ማሳለጥ ነው። ይህም ሲባል በጣም የተወሳበ ቴክኖሎጂን መጠቀም ብቻ ሳይሆን የእጅ ስልክን በመጠቀም መረጃ ከመስጠት ይጀምራል።
✨🎯ጥቅሞቹ:-
►የታካሚ እንግልትን ይቀንሳል
►ወጪን ይቀንሳል
►ለሐኪሞችም ታካሚን በቀላሉ ወደ ተሻለ ህክምና ተቋም እንዲልኩ ያግዛል.
►ታካሚ ባለበት ቦታ ሆኖ የተሻለ የህክምና አማራጭ መረጃ እንዲያገኝ ያደርጋል.

ዶ/ር ኅሩይ ተክሌ (MD, Digital H & Telemed enthusiast- certified)
Hcare,
መረጃውን ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ🙏

ሰላም የ "Hiruy Hcare" ቤተሰቦች👋 የጤና ባለሙያዎችን ምክር ለማግኘት የምንጠቀማቸው መንገዶች ክፍል 2 (ways to get advise from health proffesionals part...
03/04/2025

ሰላም የ "Hiruy Hcare" ቤተሰቦች👋

የጤና ባለሙያዎችን ምክር ለማግኘት የምንጠቀማቸው መንገዶች ክፍል 2 (ways to get advise from health proffesionals part 2)።

✨🎯 ከፋርማሲ ባለሙያ ጋር ውይይቶች (Pharmacy Consultations)
►ፋርማሲስቶች አነስተኛ የጤና እክሎችን ማማከር ፣ በሐኪም እና ያለ ሐኪም ትዕዛዝ ለሚወሰዱ መድኃኒቶች ገለፃና ምክር በመስጠት(advice on minor ailments, prescribed and over the counter medications)!

✨🎯 የጤና የስልክ አገልግሎቶች እና የምክር መስመሮች (Health Hotlines)
► በመንግስታዊ ወይም በግል ተቋማት የሚተላለፉ መረጃዎች ለምሳሌ የመድኃኒቶች ደህንነትና፣ የሥነ-አእምሮ የጤና ምክር ድጋፎች(Government or NGO run medical guidance , drug info, mental health guidance)!

✨🎯 ድጋፍ ሰጪ ቡድኖች እና የማህበረሰብ ጤና ፕሮግራሞች (Support Groups & Community Health Programs)
►ድጋፍ ቡድኖች በተለይ ዘላቂ በሽታዎች ላይ ( ስኳር፣ HIV-AIDS, ካንሰር),
►የህዝብ ጤና ተቋማት-የበሽታ መከላከልና ትምህርቶች!

ዶ/ር ኅሩይ ተክሌ (MD, Digital H & Telemed enthusiast- certified)
Hcare,
መረጃውን ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ🙏
►መልካም ቀን◄
25/07/17►ሐሙስ◄

ሰላም የ ኅሩይ ጤና ቤተሰቦች👋የጤና ባለሙያዎችን ምክር ለማግኘት የምንጠቀማቸው መንገዶች ክፍል 1(ways to get advise from health proffesionals part 1)።  ✨🎯 ...
31/03/2025

ሰላም የ ኅሩይ ጤና ቤተሰቦች👋

የጤና ባለሙያዎችን ምክር ለማግኘት የምንጠቀማቸው መንገዶች ክፍል 1(ways to get advise from health proffesionals part 1)።

✨🎯 በአካል የሚገኝ የጤና ምክር (In-Person Consultation)
◈ የዶክተር ቢሮ ወይም ክሊኒክ ጉብኝት(Doctor's office or clinic visit) የተለመደና ቆየት ያለ የፊት-ለፊት የህክምና አገልግሎት ።
◈የሆስፒታል ጉብኝት(hospital visit)– ለአስቸኳይ ወይም ልዩ የሆነ የጤና እንክብካቤ።
◈የማህበረሰብ ጤና ማእከሎች (community health centers)– ብዙውን ጊዜ ሊገጥሙ የሚችሉ የጤና እክሎች እንዲሁም ወረርሽኞች የመረጃ አገልግሎት ይሰጣሉ።

✨🎯 በቴሌሜዲስን እና የመስመር ላይ የህክምናና ማማከር (Telemedicine & Online Consultations)
◈የቪዲዮ ጥሪዎች(video calls)– ከዶክተሮች ጋር virtual መንገድ ወይም የፊት-ለፊት ውይይት።
◈የስልክ ጥሪዎች(phone calls)– ከጤና ባለሙያዎች ጋር በቀጥታ የስልክ ውይይት።
◈የፅሁፍ) ውይይቶች- የስልክ መተግበሪያዎችን : email: የሆስፒታል ፖርታሎችን በመጠቀም።

✨🎯 በቤት ለቤት የሚገኙ የጤና አገልግሎቶች (Home Visits by Healthcare Providers)
ለአረጋውያን እንክብካቤ፣ ከሰርጀሪ በኋላ ቶሎ ለማገገም የሚደረግ ክትትል፣ ከሆስፒታል ከወጡ በኋላ የሚደረግ እንክብካቤ: በቤት ውስጥ መድኃኒት መስጠት: የዘላቂ በሽታ የቤት ውስጥ የነርሲንግ ክትትል ድጋፍ የመሳሰሉትን ያጠቃልላል።

ዶ/ር ኅሩይ ተክሌ (MD)
Hiruy Hcare,
መረጃውን ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ
►መልካም ቀን◄
►22/07/17◄ ሰኑይ

stay tuned for part 2...

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hiruy Hcare posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share