22/07/2026
🚨 ኩፍኝ (Measles) ምንድን ነው?
ኩፍኝ በቫይረስ የሚከሰት እጅግ ተላላፊ በሽታ ሲሆን በአየር እና በሳል ወይም በማስነጠስ በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል። በተለይ ህጻናት ላይ ከባድ የጤና ችግር ሊያስከትል ይችላል፣ ነገር ግን በክትባት በቀላሉ ሊከላከል የሚችል በሽታ ነው።
ዋና ምልክቶተቹ
💠 ከፍተኛ ትኩሳት
💠 ሳል
💠 የአፍንጫ ፈሳሽ
💠 ዓይን መቅላትና እንባ መፍሰስ
💠 ከጥቂት ቀናት በኋላ ከፊት ጀምሮ ወደ መላ ሰውነት የሚሰራጭ ቀይ ሽፍታ
⚠️ ሊያስከትላቸው የሚችሉ ችግሮች
💠 የሳንባ ምች
💠 ተቅማጥና ድርቀት
💠 የጆሮ ኢንፌክሽን
💠 የአንጎል እብጠት (Encephalitis)
💠 በከባድ ሁኔታ ለሕይወት አደገኛ ሊሆን ይችላል።
🛡️ እንዴት እንከላከል?
✅ ህጻናትን በወቅቱ የኩፍኝ ክትባት ማስወሰድ
✅ የታመመ ሰውን ከሌሎች ለይቶ ማቆየት
✅ እጅን በተደጋጋሚ መታጠብ እና የሳል ሥነ-ምግባርን መከተል
📢 ልጅዎ ትኩሳት ከቀይ ሽፍታ ጋር ካለበት ወይም ኩፍኝ ተጠርጥሮ ከሆነ፣ በፍጥነት ወደ ጤና ተቋም ይሂዱ።
ቀጠሮ ለማስያዝ
ስልክ፡ 0930505015 / 0906060663
📍 አድራሻችን፡ ልኳንዳ ታክሲ ተራ