AhadCare - ፩ ኬር

AhadCare - ፩ ኬር AhadCare is a platform that connects Doctors and Healthcare seekers remotely, bypassing geographic, infrastructure, and economic limitations.

ለመላው የሙስሊም ቤተሰብ፦እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በጤና አደረሳችሁ!
27/05/2026

ለመላው የሙስሊም ቤተሰብ፦
እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በጤና አደረሳችሁ!

🫁 የሳንባ ነቀርሳ (ቲቢ/TB) በሽታ፡ ማወቅ ያለብን መሠረታዊ መረጃዎች!ጤና ይስጥልን! ዛሬ በአገራችን ሰፊ ሥርጭት ስላለውና ነገር ግን በቀላሉ መከላከልም ሆነ ማከም ስለሚቻለው የሳንባ ነቀ...
20/05/2026

🫁 የሳንባ ነቀርሳ (ቲቢ/TB) በሽታ፡

ማወቅ ያለብን መሠረታዊ መረጃዎች!

ጤና ይስጥልን! ዛሬ በአገራችን ሰፊ ሥርጭት ስላለውና ነገር ግን በቀላሉ መከላከልም ሆነ ማከም ስለሚቻለው የሳንባ ነቀርሳ (ቲቢ) በሽታ አጭር እና ጠቃሚ መረጃዎችን በአጭሩ ይዘን መጥተናል።

🔬 መግቢያ (Introduction)

የሳንባ ነቀርሳ (ቲቢ) 'ማይኮባክቴሪየም ቱበርክሎሲስ' (Mycobacterium tuberculosis) በሚባል ባክቴሪያ አማካኝነት የሚመጣ ተላላፊ በሽታ ነው። ምንም እንኳን በሽታው በብዛት ሳንባን የሚያጠቃ ቢሆንም፣ አልፎ አልፎ ሌሎች የሰውነት ክፍሎችንም (እንደ ኩላሊት፣ አጥንት፣ ቆዳ፣ አንጎልን፣ ንፍፊት፣ አንጀት፣ ወዘተ) ሊያጠቃ ይችላል።

🌬️ መተላለፊያ (Transmission)

ቲቢ ከአንድ በሽታው ካለበት ሰው ወደ ጤነኛ ሰው የሚተላለፈው በአየር (ትንፋሽ) አማካኝነት ነው። የሳንባ ቲቢ ያለበት ታካሚ፡

ሲያስል
ሲያስነጥስ
ሲዘፍን ወይም ሲናገር
የቲቢ ባክቴሪያዎች ከትንፋሹ ጋር ወደ አየር ይሰራጫሉ። በአካባቢው ያለ ጤናማ ሰው ይህንን የተበከለ አየር ወደ ውስጥ ሲተነፍስ በበሽታው ሊያዝ ይችላል።
ልብ ይበሉ፦ የቲቢ በሽታ ዋና መተላለፊያው በትንፋሽ ይሁን እንጅ ጥሬ ወተት መጠጣትም ቲ ቢ ሊያስይዘን ይችላል - የአንጀት ቲ ቢ ።

🛡️ መከላከያ (Prevention)

በሽታውን ለመከላከል የሁላችንም ርብርብ ያስፈልጋል፦

አፍና አፍንጫን መሸፈን፡ ሲያስሉ ወይም ሲያስነጥሱ ሁልጊዜ በሶፍት፣ በክንድዎ ወይም በጨርቅ ይሸፍኑ።

አየር ዝውውርና የፀሐይ ብርሃን፡ ፡ በቤት ውስጥ፣ በሥራ ቦታ እና በትራንስፖርት ውስጥ በቂ የአየር ዝውውር እንዲኖር መስኮቶችን መክፈት። ለቲቢ ባክቴሪያ የፀሐይ ብርሃን ስለማይመቸው፣ ቤቶን ለፀሐይ ብርሃን ክፍት ማድረግ።

ጥሬ ወተት አለመጠጣት። ጥሬ ወተት የአንጀት ቲ ቢ ሊያመጣ ስለሚችል የላም ወተትን አፍልቶ በማቀዝቀዝ መጠቀም።

ክትባት፡ ለሕጻናት በወቅቱ የቢሲጂ (BCG) ክትባት ማሰጠት።

ምርመራ፡ ከሁለት ሳምንት በላይ የዘለቀ ሳል፣ የሌሊት ላብ፣ ትኩሳት ወይም ያልታሰበ የክብደት መቀነስ ካለ በፍጥነት ወደ ጤና ተቋም በመሄድ መመርመር።

💊 ሕክምና (Treatment)

ቲቢ ሙሉ በሙሉ የሚድን በሽታ ነው!
ሕክምናው በተለምዶ ከ6 እስከ 9 ወራት የሚወስድ የጸረ-ባክቴሪያ መድኃኒት ነው። መድኃኒት የተላመደ ከሆነ ግን ክዛም በላይ ረዘም ላለ ጊዜ ሊታዘዝ ይችላል።

በጣም ወሳኙ ነገር፡ ሐኪም ያዘዘውን መድኃኒት በሰዓቱ እና ያለማቋረጥ ሙሉ በሙሉ መጨረስ ነው!

መድኃኒቱን አቋርጦ መተው በሽታው መድኃኒትን እንዲላመድ (Drug-resistant TB) የሚያደርግ ሲሆን፣ ይህም ለማከም እጅግ አስቸጋሪ እና አደገኛ ነው።

በብዙ የጤና ተቋማት የቲቢ ምርመራ እና ሕክምና በነጻ ስለሚሰጥ ከሁለት ሳምንት በላይ የዘለቀ ሳል፣ የሌሊት ላብ ወይም መውዛት፣ ትኩሳት ወይም የክብደትና ምግብ ፍላጎት መቀነስ ከገጠሞት ወደጤና ተቋም በመሄድ ይመርመሩ።

መልእክቱን ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ያካፍሉ፤ ኅብረተሰባችንን ከቲቢ እንጠብቅ!
በዘርፉ ልምድ ያላቸውን የውስጥ ደዌ ሐኪሞች ባሉበት ሆነው ማማከር ከፈለጉ አሐድኬር ላይ በስልክ ወይም በኦንላይን ማግኘት ይችላሉ!

ድረገጽ ፡- https://ahadcare.com
ስልክ፦ 0943722272

AhadCare - ፩ ኬር ን ፎሎ ያድርጉ!

12/05/2026

በተለያየ ዘርፍ ስፔሻሊስት ና ሰብ ስፔሻሊስት ሐኪም በማንኛውም ሰዓት በስልክ ወይም በቪድዮ ባሉበት ሆነው ለማማከር AhadCare - ፩ ኬር ድረ ገፅን ይጎብኙ::

የህጻናት ስፔሻሊስት
የማህፀን ና ፅንስ ስፔሻሊስት
የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት
የቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት
የኩላሊት: ሽንት ቱቦ: ፕሮስቴትና ፊኛ ቀዶ ሕክምና ሰብስፔሻሊስት
የጨጉአራ: አንጀት ና ጉበት ሰብ ስፔሻሊስት
የራድዮሎጅ ስፔሻሊስት
የልብ ሕክምና ሰብ ስፔሻሊስት
ድረገፅ :- https://ahadcare.com

ስልክ:- 0943722272

🕊️ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ! 🕊️ዛሬ በመላው የኢትዮጵያ ክርስቲያን አማኞች ዘንድ የሚከበረው የትንሳኤ በዓል የሰላም፣ የፍቅር እና የአዲስ ተስፋ ተምሳሌት ነው።AhadC...
12/04/2026

🕊️ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ! 🕊️

ዛሬ በመላው የኢትዮጵያ ክርስቲያን አማኞች ዘንድ የሚከበረው የትንሳኤ በዓል የሰላም፣ የፍቅር እና የአዲስ ተስፋ ተምሳሌት ነው።

AhadCare - ፩ ኬር ለመላው የሀገራችን ህዝቦች እንኳን ለ2018 ዓ.ም የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ለማለት ይወዳል።

ትንሳኤ ማለት ድል ነው - በሽታን በጤና፣ ጨለማን በብርሃን፣ ተስፋ መቁረጥን ደግሞ በአዲስ ህይወት የምንተካበት በዓል!

በዓሉ የጤና፣ የሰላም እና የበረከት ይሁንላችሁ!

፩ ድኬር - ለተሻለ ጤና፣ ለተሻለ ህይወት!

ሰላም ለኢትዮጵያ! ሰላም በዓለም ሁሉ!

#ትንሳኤ #ጤና #ኢትዮጵያ #2018

14/03/2026

አሐድ ኬር....
ባሉበት ሆነው ሐኪም ካስፈለገዎ፣
አሐድኬር ላይ በእጅ ስልክዎ፣
ወይም በድረገጽ ኢንተርኔት ካለዎ፣
"ሀሎ" ቢሉ!
ስፔሻሊስት እና ሰብስፔሻሊስት ያገኛሉ!

ጤና ለሁሉም!

በስልክ ሐኪም ለማግኘት፦
0943722272
በኦንላይን ሐኪም ለማግኘት፦
ahadcare.com

07/03/2026

ጤና ለሁሉም! ሰላም ለኢትዮጵያ!

ባሉበት ሆነው ሐኪም ካስፈለጎት፣
አሐድኬር ላይ ከታች በተቀመጠው ስልክ በመደወል ወይም የአሐድኬርን ድረገጽ በመክፈት የሚፈልጉትን ስፔሻሊስትም ሆነ ሰብስፔሻሊስት ሐኪም ማግኘትና ማማከር እንደሚችሉ ያውቃሉ?

በተለያዩ የአገራችን ክፍል፣ በገጠርም ሆነ በከተማ፣ እንዲሁም በውጭ አገር በተለያዬ ምክንያት የሐኪም ምክር ና ሕክምና ለሚያስፈልጋቸው እንዲደርስ ለሌሎችም መልዕክቱን ያጋሩ ።

ስልክ፦ +251943722272
ድረ - ገጽ:- ahadcare.com

AhadCare

#አሐድኬር
#ጤናለሁሉም

ጤና ለሁሉም! ሰላም ለኢትዮጵያ!በእኩለ ሌሊት ድንገተኛ እና ሊቋቋሙት በማይቻል ከፍተኛ የጀርባ ወይም የጎን ውጋት ከእንቅልፍዎ ነቅተው ያውቃሉ? ለብዙ ኢትዮጵያውያን፣ በተለይም በሞቃት ፀሐይ ...
02/03/2026

ጤና ለሁሉም! ሰላም ለኢትዮጵያ!

በእኩለ ሌሊት ድንገተኛ እና ሊቋቋሙት በማይቻል ከፍተኛ የጀርባ ወይም የጎን ውጋት ከእንቅልፍዎ ነቅተው ያውቃሉ?

ለብዙ ኢትዮጵያውያን፣ በተለይም በሞቃት ፀሐይ ላይ ረጅም ሰዓት ለሚሰሩ ወይም ሞቃታማ አካባቢዎች ለሚኖሩ ሰዎች፣ ይህ ከፍተኛ ህመም የኩላሊት ጠጠር የመጀመሪያው ምልክት ሊሆን ይችላል።

የኩላሊት ጠጠር በሀገራችን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ሲሆን፣ አብዛኛውን ጊዜ በስራ ላይ ያሉ እና አምራች የሆኑ የቤተሰብ አባላትን ሰለባ ያደርጋል። ይህ ከፍተኛ የጤና ቀውስ በቀላሉ መከላከል የምንችለው ወይም ችግር ሳይፈጥር ታክመን የምንድነው ዓይነት በሽታ ነው።

ቀደም ብሎ ማወቅ፣ በቂ ውሃ የመጠጣት ልማድ እና መቼ የህክምና እርዳታ ማግኘት እንዳለብን መረዳት ከከፋ የህመም ስቃይና የኩላሊት ጉዳት ያድነናል፤ የረጅም ጊዜ ጤናችንንም ይጠብቃል።
የበለጠ መረጃ አሐድኬር ድረገጽ ላይ ያገኛሉ።

https://ahadcare.com/kidney-stones-ethiopia/

ባሉበት ሆነው ሐኪም ማማከር ካስፈለጎት አሐድኬር ላይ ዶክተሮችን ያገኛሉ። 👇
https://ahadcare.com/listing-category/online-doctors/

#አሐድኬር


የኩላሊት ጠጠር በሀገራችን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ሲሆን፣ አብዛኛውን ጊዜ በስራ ላይ ያሉ እና አምራች የሆኑ የቤተሰብ አባላትን ሰለባ ያደርጋል። ይህ ከፍተኛ ስቃይ እና የኩ...

የጡት ካንሰርን ቀድሞ በማወቅ የራስን፣ የእናትን፣ የእህትንና የሚስትን ሕይወት መታደግ እንደሚቻል ያውቃሉ? 🌸ውድ የAhadcare ቤተሰቦችና ኢትዮጵያውያን፤ጥናቶች እንደሚያሳዩት በኢትዮጵያ የ...
23/02/2026

የጡት ካንሰርን ቀድሞ በማወቅ የራስን፣ የእናትን፣ የእህትንና የሚስትን ሕይወት መታደግ እንደሚቻል ያውቃሉ? 🌸

ውድ የAhadcare ቤተሰቦችና ኢትዮጵያውያን፤

ጥናቶች እንደሚያሳዩት በኢትዮጵያ የጡት ካንሰር በሴቶች ላይ በብዛት የሚከሰትና ለህልፈተ ሕይወት ዋነኛ መንስኤ እየሆነ የመጣ በሽታ ነው። ነገር ግን አንድ መልካም ዜና አለን፦ ካንሰሩ ገና በጅምሩ ከተደረሰበት በሕክምና መዳን ይችላል!

አስቀድሞ የማወቅ፣ የመጠንቀቅ ና ትኩረት የመስጠት አስፈለጊነት

🔍 በኢትዮጵያ አዳዲስ በካንሰር ከሚታመሙ ታካሚ እናቶች 32% ያህሉ የካንሰር ዓይነቱ የጡት ካንሰር እንደሆነ፣ እና በካንሰር ከሚሞቱት ውስጥ ከ17% በላይ የሚሆነው ሞት በዚህ አሰቃቂ በሽታ ምክንያት እንደሆነ፤

🔍 እንዲሁም በሽታው ዘግይቶ ከተገኘ ለ5 ዓመት በሂወት የመቆየት ዕድሉን ወደ 22% ዝቅ እንዳደሚያደርገውና ይህ ችግር ከሰሃራ በታች ካሉ ደሃ አገራት በላይ በአገራችን የባሰ መሆኑ፣ ይህም በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ባሉ እናቶች ላይ የበለጠ አስከፊ መሆኑን በቅርቡ በአገራችን የተሰራ ጥናት አመላክቷል።

🔍 የጡት ካንሰር በአብዛኛው መጀመሪያ ላይ ምንም ዓይነት የህመም ስሜት ላይኖረው ቢችልም ስር እየሰደደ ሲሄድ ግን ለማዳን የሚያስቸግርና በማስታገሻ መድሃኒት ስሜቱን መቀነስ የማንችለው እጅግ ከፍተኛ የህመም ስቃይና ለአስታማሚም የሚከብድ አስቀያሚ መጥፎ ጠረን ጭምር በመፍጠር ለሞት የሚዳርግ አስከፊ በሽታ ነው።

🔍 ይሁን እንጅ ቀድሞ በማወቅ ይህንን ታሪክ መለወጥ ይቻላል!

ሊያደርጓቸው ከሚገቡ ቀላል እርምጃዎች ዋናዎቹ፡-

2. በየወሩ እራስዎን ይመርምሩ፡- የወር አበባ በቆመ ከ3ኛው እስከ 5ኛው ባሉ ቀናት ጡትዎን በመስታወት ፊት በመቆም ወይም በሚመች ቦታ በመተኛት ይፈትሹ። (አሃድኬር ድረገጽ ላይ ሙሉ ቅደም ተከተሉን እንዲያነቡ ከዚህ ጽሁፍ ስር መስፈንጠሪያውን ይጠቀሙ )

3. በባለሙያ ይታዩ፡- እድሜዎት ከ 40 ዓመት በላይ ከሆነ ጡትዎት ጤነኛ ቢመስሎትም በአመት አንዴ በባለሙያ ቼክ ይደረጉ።

3. ምልክቶችን ይለዩ፡- በጡት ላይ አዲስ እብጠት፣ የቆዳ ቀለም መቀየር፣ ወይም የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መሳብ፣ ቁስለት፣ ወይም የጡት ጫፍ ፈሳሽ ካዩ በፍጥነት ወደ ሐኪም ይሂዱ።

4. ጤናማ አኗኗርን ይከተሉ፡- የሰውነት ክብደትን መቆጣጠር፣ ስፖርት መስራት እና ጡትን ማጥባት የጡት ካንሰር ተጋላጭነትን ከሚቀንሱ ጥንቃቄዎች ዋናዎቹ ናቸው።

በቤትዎ ውስጥ ማድረግ ያለቦት የምርመራ ብልሃት፣ በ ሐኪም ስለሚደረጉ ምርመራዎች እና ስለ ሕክምና አማራጮች የበለጠ መረጃ በአሃድኬር ድረ-ገጽ ላይ ያንብቡ።

👉 ሙሉ ጽሁፉን እዚህ ያንብቡ፡ https://ahadcare.com/breast-cancer-ethiopia/

ይህንን መረጃ ለእናቶችና ለእህቶችዎ በማጋራት ግንዛቤ ይፍጠሩ!

#የጡትካንሰር #ጤና #አሃድኬር World Health Organization (WHO)

የፊንጢጣ ኪንታሮትን መከላከልና በቤት ውስጥ ማከም  እንደሚችሉ ያውቃሉ?
14/02/2026

የፊንጢጣ ኪንታሮትን መከላከልና በቤት ውስጥ ማከም እንደሚችሉ ያውቃሉ?

ኪንታሮት በፊንጢጣ ቱቦ ውስጥ እና ዙሪያ የሚገኙ የደም ስሮች እና ህብረ ህዋሳት ሲያብጡ ወይም ሲቆጡ የሚፈጠር ችግር ነው። በአኗኗር ዘዴ መከላከልና ማከም ይቻላል።

Address

Addis Ababa
1000

Opening Hours

Monday 02:00 - 21:30
Tuesday 02:00 - 21:30
Wednesday 02:00 - 21:30
Thursday 02:00 - 21:30
Friday 02:00 - 21:30
Saturday 02:00 - 21:30

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AhadCare - ፩ ኬር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share