15/05/2026
በ 1 አመት ጊዜ ውስጥ ከ 3 ቢሊየን ብር ብላይ ወጪ ተደርጎ የተገነባው ሆስፒታል በመዲናችን ተከፍቶ ለስራ ክፍት ሁኗል።
አገልግሎታችንም ከሃገር ውስጥ ፍላጎት በተጨማሪ የጎረቤት ሃገራትን የህክምና ፍላጎት በሚያሟላ መልኩ የተደራጀ በመሆኑ ሃገራችን ለያዘችው የሜዲካል ቱሪዝም እቅድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ. መሀመድ ሳሊህ ገልፀዋል። እንዲሁም እጅግ ዘመናዊ የሆነ የህክምና ቴክኖሎጂዎችን ያካተተ ሲሆን ለአብነትም የ1.5 ቴስላ ኤም.አር.አይ ማሽን ፣ የ160 ስላይስ ሲቲ ስካን እና የሰው ሰራሽ አስተምህሮት የተቀናጀባቸው የአልትራሳውንድ መሳሪያዎች ተጠቃሽ ናቸው ሲሉ አክለዋል።
ተያይዞም "የጤና ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ከመንግስት ጋር በጋራ ቁማችሁ አላማችንን እውን ለማድረግ ያደረግነውን ጥሪ ተከትላችሁ ይህን የመሰለ ተቋም በመገንባታችሁ እናመሰግናለን" ሲሉ የከተማችን ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል።
ተያያዥ ዜናውን ከላይ ያያዝን ስለሆነ እንድትከታተሉት ጋበዝን።
ኢትዮ ቢዝነስ ግሩፕ መጥታችሁ የምርቃት ፕሮግራማችን ተካፋይ ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን !