05/03/2026
ውሃው ከገበያ ታግዷል‼️
“ፋይን” የታሸገ ውሃ የምርት ቁጥር 620 እንዳይጠጣ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ‼️
የአዲስ አበባ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን “ፋይን” (Fine) የታሸገ ውሃ ላይ ባደረገው ምርመራ፣ ምርት ቁጥር 620 ጥራትና ደህንነቱን ያልጠበቀ መሆኑን አረጋግጧል።
ኅብረተሰቡ ይህንን የምርት ቁጥር ያለውን ውሃ እንዳይጠቀም ጥብቅ ማሳሰቢያ ተላልፏል።
ባለስልጣኑ ምርመራውን ያካሄደው ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ሲሆን፣ በውሃው ውስጥ ዝልግልግ ያለ ባዕድ ነገር መገኘቱንና የማምረት ሂደቱም የጤና መስፈርቶችን ያልተከተለ መሆኑን ገልጿል።የተላለፉ ውሳኔዎች፦
📌 ድርጅቱ ችግሩን በቋሚነት ማስተካከሉ ተረጋግጦ በጽሁፍ ፈቃድ እስካላገኘ ድረስ ከየካቲት 24 ጀምሮ ምርት ወደ ገበያ እንዳያሰራጭ ታግዷል።
📌 በገበያ ላይ የሚገኘው የምርት ቁጥር 620 ውሃ በ 5 ቀናት ውስጥ ተሰብስቦ ለባለስልጣኑ ሪፖርት እንዲደረግ ታዟል።
📌 ኅብረተሰቡ ይህንን የምርት ቁጥር በገበያ ላይ ሲያገኝ በነፃ ስልክ መስመር 8864 ላይ በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ ዳይሬክተር እስጢፋኖስ ጌታቸው አሳስበዋል።
=====================