23/09/2026
የአርባ ምንጭ ደም እና ሕብረ-ህዋስ ባንክ አገልግሎት ከጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት እና የጊዶሌ ከተማ ክርስቲያን ወጣቶች ህብረት ጋር በመተባበር የደም ልገሳ መርሃ-ግብር አከናወነ።
መስከረም 13/2019 ዓ.ም
አርባ ምንጭ
በመርሃ-ግብሩ የሕብረቱ አባላት የሆኑ ወጣቶች ደም በመለገስና በማሰተባበር እንዲሁም ሌሎቸ በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ አካላት ከስጦታዎች የላቀ ስጦታ የሆነውን ደም በመለገስ ክቡር የሆነውን የሰውና ልጅ ህይወት ታድገዋል ።
የጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት እና ክርስቲያን ወጣቶች ህብረት በጋራ በመቀናጀት ላደረጉት ትብብር እንዲሁም በደም ልገሳ መርሃ ግብሩ ለተሳተፉ ሁሉ የአርባ ምንጭ ደም እና ሕብረ-ህዋስ ባንክ አገልግሎት እጅግ ከፍ ያለ ምስጋናዉን ያቀርባል።