Hawassa millennium primary health care unit

Hawassa millennium primary health care unit Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Hawassa millennium primary health care unit, Medical and health, Beyond theTesfaye Gizaw business center, Awassa.

Hawassa Millennium Primary Health Care Unit is a leading health center in Hawassa City, providing quality services to over 86,000 people both within and outside its catchment area..

  ተቋማችን ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ፤ በበሽታ መከላከልና ጤና ማጎልበት ተግባራት እንዲሁም በEPAQ 2nd Cycle አፈፃፀም ዙሪያ በ2018 በጀት ዓመት የላቀ ውጤት በማስመዘገቡ፣ ከሲዳማ ክልል...
29/08/2026


ተቋማችን ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ፤ በበሽታ መከላከልና ጤና ማጎልበት ተግባራት እንዲሁም በEPAQ 2nd Cycle አፈፃፀም ዙሪያ በ2018 በጀት ዓመት የላቀ ውጤት በማስመዘገቡ፣ ከሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ የበሽታ መከላከልና ጤና ማጎልበት ዳይሬክቶሬት የሜዳሊያና የሰርተፍኬት እውቅና ተበርክቶለታል።

አ/ጣቢያ
#ሀዋስ

‎መልካም ዜና‎  አ/ጣቢያ ተገልጋዮች በሙሉ:-ከዚህ በፊት ተቋማችን ይገለገልበት የነበረው ጀነሬተር በመበላሸቱ ምክንያት ባለፉት ወራት ያልተቋረጠ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት በሚደረገው እን...
16/08/2026

‎መልካም ዜና
‎ አ/ጣቢያ ተገልጋዮች በሙሉ:-
ከዚህ በፊት ተቋማችን ይገለገልበት የነበረው ጀነሬተር በመበላሸቱ ምክንያት ባለፉት ወራት ያልተቋረጠ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት በሚደረገው እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ማነቆ ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል።

‎ይህን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት እና የአገልግሎት መስጫ ክፍሎቻችን ሙሉ በሙሉ ያለ ምንም መቋረጥ ሥራቸውን ማከናወን እንዲችሉ የሚያስችል አዲስ እና ዘመናዊ ጀነሬተር ተገዝቶ ሥራ ማስጀመሩን በደስታ እንገልጻለን።

#ምስጋና
‎ #ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ እና ለሀዋሳ ከተማ ፋይናንስ:- ይህ አዲሱ ጀነሬተር ተገዝቶ ለአገልግሎት እንዲበቃ ተቋማችን ላቀረበው ጥያቄ ተቀበሎ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ላደረጉልን ድጋፍ እና ትብብር የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

‎ #ሚሊኒየም ጤና አ/ጣቢያ
‎ #ሀዋሳ

እንኳን ደስ አላችሁ / ደስ አለን!‎‎ተቋማችን ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ፤ በእናቶችና ሕፃናት፣ በአፍላ ወጣቶችና ወጣቶች ጤና እንዲሁም በሥርዓተ-ምግብ ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት የላቀ ውጤት በማ...
11/08/2026

እንኳን ደስ አላችሁ / ደስ አለን!

‎ተቋማችን ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ፤ በእናቶችና ሕፃናት፣ በአፍላ ወጣቶችና ወጣቶች ጤና እንዲሁም በሥርዓተ-ምግብ ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት የላቀ ውጤት በማስመዘገብ ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ስር ካሉ ጤና አ/ጣቢያዎች 1ኛ በመዉጣት ከሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ የሜዳሊያና የሰርተፍኬት እውቅና ተበርክቶለታል።

በ‎ተጨማሪ በዚህ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበረከት ውቁሮ ቀበሌም ተሸላሚ ሆኗል።

‎ይህ ስኬት እንድገኝ ልዩ አስተዋጽኦ ላደረጉ የእናቶችና ሕፃናት ክፍል እንድሁም የውቁሮ ቀበሌ ጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች እንኳን ደስ አላችሁ።

#ሚሊኒየም ጤና አ/ጣቢያ
#ሀዋሳ
#ሲዳማ _ኢትዮጵያ

  ‎‎የሚሊኒየም ጤና አ/ጣቢያ ላቦራቶሪ በዓለም አቀፉ የደረጃ ዕድገት የጥራት ማሻሻያ ( ) መስፈርት ተመዝኖ የኮከብ 2 (Star 2) ደረጃን በማስመዝገብ ከሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢ...
30/07/2026



‎የሚሊኒየም ጤና አ/ጣቢያ ላቦራቶሪ በዓለም አቀፉ የደረጃ ዕድገት የጥራት ማሻሻያ ( ) መስፈርት ተመዝኖ የኮከብ 2 (Star 2) ደረጃን በማስመዝገብ ከሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (SPHI) የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶለታል::

‎ይህ ስኬት ወደ አለም አቀፍ የISO ደረጃ ለመድረስ ትልቅ እርምጃ ሲሆን ለዚህ ስኬት ሌት ተቀን የደከማችሁ የላቦራቶሪ ባለሙያዎቻችን እና መላው የጤና አ/ጣቢያው ሰራተኞች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ!

‎ #ሚሊኒየም ጤና አ/ጣቢያ
‎ #ሐዋሳ

‎ #ጥራትን ማረጋገጥ ቀዳሚ ተግባራችን ነው!

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባት በሚሊኒየም ጤና ጣቢያ የመስክ ጉብኝት አደረጉ። #ሐምሌ 21/2018 ዓ/ምበጤናው ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎችንና የተመዘገቡ ውጤቶችን በተጨባጭ ለመገምገ...
28/07/2026

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባት በሚሊኒየም ጤና ጣቢያ የመስክ ጉብኝት አደረጉ።

#ሐምሌ 21/2018 ዓ/ም

በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎችንና የተመዘገቡ ውጤቶችን በተጨባጭ ለመገምገም ይረዳቸው ዘንድ፣ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ፋንታዬ ከበደ የሚመሩት የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎችና አመራሮች በሚሊኒየም ጤና ጣቢያ በመገኘት የመስክ ጉብኝት አድርገዋል።

በጉብኝታቸውም ተቋሙ የገበራቸውን በርካታ ከወረቀት ነፃ የአገልግሎት (paper-free digitalization services) እና የተመዘገቡ ውጤቶችን እንዲሁም አዲሱ የG+3 ማስፋፊያ ሕንፃ እየሰጠ ያለውን አገልግሎት በአካል በመገኘት ተመልክተዋል።

#ሚሊኒየም _ጤና አ/ጣቢያ
#ሀዋሳ

በሚሊኒየም ጤና አጠባበቅ የተዘጋጀው የክረምት ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር  ተካሄደ።የ"ፅዱ ጤና ተቋም" መርሃ-ግብር አካል በሆነው በዚህ መድረክ ላይ የጤና ባለሙያዎቻችን በመሳተፍ አረንጓዴ አሻ...
16/07/2026

በሚሊኒየም ጤና አጠባበቅ የተዘጋጀው የክረምት ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ተካሄደ።

የ"ፅዱ ጤና ተቋም" መርሃ-ግብር አካል በሆነው በዚህ መድረክ ላይ የጤና ባለሙያዎቻችን በመሳተፍ አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።

በሚሊኒየም ጤና አጠባበቅ የ4ኛ ሩብ ዓመት የቦርድ ስብሰባ ተካሄደ። #ሐምሌ 01/2018 ዓ.ምበዛሬው ዕለት የሚሊኒየም ጤና አ/ጣቢያ የ2018 ዓ.ም የ4ኛ ሩብ ዓመት መደበኛ የቦርድ አባላት ...
08/07/2026

በሚሊኒየም ጤና አጠባበቅ የ4ኛ ሩብ ዓመት የቦርድ ስብሰባ ተካሄደ።

#ሐምሌ 01/2018 ዓ.ም

በዛሬው ዕለት የሚሊኒየም ጤና አ/ጣቢያ የ2018 ዓ.ም የ4ኛ ሩብ ዓመት መደበኛ የቦርድ አባላት ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን በመድረኩም የሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት እና በቀጣይ ትኩረት በሚሹ የተለያዩ አጀንዳዎች ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

/አ/ጣቢያ
#ሀዋሳ

የሚሊኒየም ጤና ጣቢያ EPAQ 2nd Cycle BRIDGE ክላስተር የ2018 ዓ.ም የአራተኛ ሩብ ዓመት ክላስተር meeting እና የዓመቱ ማጠቃለያ መድረክ አካሄዱ። #ሰኔ 25/2018 ዓ.ም ...
02/07/2026

የሚሊኒየም ጤና ጣቢያ EPAQ 2nd Cycle BRIDGE ክላስተር የ2018 ዓ.ም የአራተኛ ሩብ ዓመት ክላስተር meeting እና የዓመቱ ማጠቃለያ መድረክ አካሄዱ።

#ሰኔ 25/2018 ዓ.ም

ዛሬ ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው ክላስተር የማጠቃለያ መድረክ ላይ ሁሉም የክላስተሩ ጤና ጣቢያዎች እና የሀዋሳ ከተማ ጤና መምሪያ የEPAQ 2nd Cycle BRIDGE መሪዎች የተገኙ ሲሆን፣ በመድረኩ ላይ የ2018 ዓ.ም የአራተኛ ሩብ ዓመት እና የዓመቱ ማጠቃለያ ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

/አ/ጣቢያ
#ሀዋሳ

ሚሊንየም ጤና አጠባበቅ ጣቢያ  የ4ኛ ሩብ ዓመት ደም ልገሳ መርሃግብር አካሄደ:: #ሰኔ - 09/2018 ዓ/ምበዛሬው ዕለት የጤና ጣቢያው  ባለሙያዎች ደም የለገሱ ሲሆን፥ በደም እጥረት ምክን...
16/06/2026

ሚሊንየም ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የ4ኛ ሩብ ዓመት ደም ልገሳ መርሃግብር አካሄደ::

#ሰኔ - 09/2018 ዓ/ም

በዛሬው ዕለት የጤና ጣቢያው ባለሙያዎች ደም የለገሱ ሲሆን፥ በደም እጥረት ምክንያት ሊያጋጥሙ የሚችሉ የህይወት መጥፋት አደጋዎችን ለመታደግ የበኩላቸውን አስተዋፅዖ አበርክተዋል።

#ደም በመለገስ በደም እጥረት የሚሞቱ ወገኖቻችንን ህይወት እንታደግ!

አ/ጣቢያ

"የሚሊኒየም ጤና ጣቢያ MCC ከበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ጋር በመተባበር ያስገነባውን የአቅመ ደካማ አረጋውያን መኖሪያ ቤት አስረከበ።"
12/06/2026

"የሚሊኒየም ጤና ጣቢያ MCC ከበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ጋር በመተባበር ያስገነባውን የአቅመ ደካማ አረጋውያን መኖሪያ ቤት አስረከበ።"

Address

Beyond TheTesfaye Gizaw Business Center
Awassa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hawassa millennium primary health care unit posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share