04/12/2022
ጠቃሚ ምክር ለወላጆች -ልጆች ከወላጆች በሚለዩበት ጊዜ የሚፈጠር ጭንቀትን ለመቀነስ
:::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
የመለያየት ጭንቀት (Separation anxiety) ምንድን ነዉ?
===============================
የመለያየት ጭንቀት(Separation anxiety) ማለት ልጅዎን ለቀው ሲወጡ (ለአጭር ጊዜም ቢሆን) ልጆች ላይ የሚከሰት ማልቀስ ወይም የሙጥኝ ማለት ሊሆን ይችላል።
ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው ከ6 ወር እስከ 3 ዓመት ባለው የልጆች እድሜ ጊዜ ውስጥ ሲሆን የልጅዎ የተለመደ የእድገት አካል ነው።
ብዙ ልጆች ወላጆቻቸውን ወይም ተንከባካቢዎቻቸውን በየቀኑ በሁሉም ሰአታት ከጎናቸው ማድረግን የተላመዱ ናቸዉ።
ልጆች ወደ መዋለ ሕጻናት ማእከላት፣ ትምህርት ቤቶች ሲሄዱ እንዲሁም ወላጆች ለስራ ከቤት ሲወጡ ልጅዎ የመለያየት ጭንቀት መኖሩ በጣም የተለመደ ነዉ፡፡
ልጄን ለዕለት ተዕለት ተግባር ስለየዉ ደህንነት እንዲሰማው እንዴት መርዳት እችላለሁ?
===============================
ልጅዎን ወደ ትምህርት ቤት ሲመላለስ ወይም ስራዎ ለዕለት ተዕለት ተግባር ከልጅዎ ሲለዩ ልጅዎ ደህንነት እንዲሰማው ለማድረግ ጊዜ እና እቅድ የሚወስድ ሂደት ሊሆን ይችላል።
ይህ ዓይነት ጭንቀት እንዲቀንስ/እንዲስተካከል የሚረዱዎት አንዳንድ ምክሮች የሚከተሉት ናቸዉ።
1. ልጅዎን ያዳምጡ
ጭንቀታቸውን በቁም ነገር ይያዙ እና ልጆችዎ ስለሚያሳስቧቸው ነገር ያነጋግሩ።
2. እንዲዘጋጁ እርዷቸው
በመጀመሪያዎቹ ቀናት አብረዋቸዉ ከልጆች ጋር ወደ ትምህርት ቤት በመሄድና በመመለስ የትምህርት ቤት ህጎች እንዲማሩ እና እንዲለማመዱ ያድርጉ ።
ልጅዎን ወደ ትምህርት ቤት ሲመላለሱ ምን እንደሚሰማቸው ይጠይቁ እና ጉልህ ስጋት ካላቸው መምህራቸውን ማሳወቅዎን ያረጋግጡ።
3. ረጋ ይበሉ
ልጆች የአዋቂዎችን ባህሪ ምልክቶች እንደሚወርሱ ያስታውሱ
ልጅዎ ዘና ብሎ እንዲቆይ እና ደህንነት እንዲሰማው ለማገዝ፤ ረጋ ያለ ባህሪን እራስዎ ሞዴል ሆነዉ ማሳየት በጣም አስፈላጊ ነው።
4. የመልቀቅ እቅድ ይኑርዎት
በትልልቅ ልጆች ላይ ስንብት እንዳይከብድ ለማድረግ የሚከተሉትን ይሞክሩ።
☑️ስንብትዎን አዎንታዊ ያድርጉ
☑️እንደሚሄዱ ለልጅዎ ያስታውቁ
☑️የት እንደሚሄዱ ፣ለምን እንደሚሄዱ ማብራሪያዎን ግልጽ እና አጭር ያድርጉት
☑️ለልጅዎ ቶሎ እንደሚመለሱለት ያስታዉሱት
☑️በሚወጡበት ጊዜ አያመንቱ
☑️ወጠዉ ለመቆት ከአቀዱበት ጊዜ ቀድመዉ ወይም ዘግይተዉ አይመለሱ
☑️ልጅዎን በሚለዩበት ጊዜ ሁሌ ተመሳሳይ አሰራርን ይከተሉ
❤️❤️❤️ጠቃሚ መረጃ ነዉ ብለዉ ካሰቡ ለሌሎች እንዲደርስ & ያድርጉት፤ ጥያቄ አስተያየት ካለዎት ያድርጉ❗️❗️❗️
👇👇👇ጤና ነክ የሆኑ በስፔሻሊስትና ሰበ ስፔሻሊስት ሀኪሞች የሚቀርቡ እጅግ ጠቃሚ መረጃዎችን ለመከታታል የሚከተለዉን ሊንክ & " ያድርጉ❗️
ቴሌግራም፡ https://t.me/+UrIjm3JWTW1MMZWp
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/profile.php?id=100087253516806&mibextid=ZbWKwL