20/06/2026
✅ 💊💊የደም ግፊት መቆጣጠሪያ መድሀኒትዎን ያለ ሐኪም መመሪያ ማቋረጥ ከባድ መዘዞችን ሊያመጣ እንደሚችል ያውቃሉ ❓❓
➡ በአሁን ወቅት በሀገራችን ከሚገኙ ተላላፊ ካልሆኑ ህመሞች መካከል የደም ግፊት መጨመር እና እሱን ተከትለው የሚመጡ ችግሮች በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመሩ ይገኛሉ።
➡በኢትዮጵያ ከ19%-28% የሚሆኑ ዜጎች በደም ግፊት መጨመር በሽታ እንደሚጠቁ ጥናቶች ያሳያሉ።
➡ ለዚህም የአኗኗር ዘይቤ መቀየር እንደምክንያት የሚጠቀስ ሲሆን በከተሞች ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር (~24%) ያላቸው ተጠቂ ዜጎች ይገኛሉ።
➡ የደም ግፊት መቆጣጠሪያ መድሀኒት እንደ አስፈላጊነቱ በሀኪም በሚታዘዘው መሠረት በመውሰድ የደም ግፊት መጨመር ከሚያስከትላቸው በርካታ ችግሮች ራስን መጠበቅ ይቻላል❕❕
➡ ስለ መድሀኒቶቹ አሉታዊ መረጃ ተቀብሎ መድሀኒት አለመጀመር ወይም የተጀመረውን መድሀኒት ማቋረጥ ታክሞ ለማይመለስ የጤና እክል እንደሚዳርግ መገንዘብ ያሻል።
➡ የደም ግፊት ክትትል መድሀኒቶች ማቋረጥ ስትሮክ የመከሰት ዕድልን ከ 25%-28% ይጨምራል። እንዲሁም በጭንቅላት ውስጥ የደም መፍሰስ ዕድልን በ 4 እጥፍ ይጨምራል።
➡ የግፊት መድሀኒቶች መቋረጥ ተከትሎ የሚመጡ የስትሮክ አደጋዎች በአብዛኛው የሚከሰቱት መድሀኒቶቹ በተቋረጡ የመጀመሪያዎቹ ጥቂት ቀናት ወይም ሳምንታት ውስጥ ነው።
✔አንዳንድ ጥናቶች እንዲሚያሳዩት ከሆነ ከ50% በላይ የሚሆኑት ተጠቂዎች ስትሮክ የሚያጋጥማቸው መድሀኒቶቹ በተቋረጡ የመጀመሪያዎቹ 15 ቀናት ውስጥ ነው።
🚫 አብዛኛውን ጊዜ ታካሚዎች መድሀኒታቸውን ለምን ያቋርጣሉ🤔🤔
1.የሀኪም ትዕዛዝ ከመከተል ይልቅ በአካባቢያቸው የሚነገሩ አሉታዊ ምክሮችን በመስማት
2.የመድሀኒት መውሰጃ ሰዓትን ጠብቆ አለመውሰድ እና ደካማ የሆነ የክትትል ስርዓት መኖር
3. የግፊት መድሀኒቶችን ግዜያዊ መድሀኒቶች አድርጎ ማሰብ
4. አንዳንድ ታካሚዎች በመድሀኒት የተስተካከለ ግፊትን በዘላቂነት እንደተስካከለ ወይም ችግሩ እንደተወገደ በማሰብ የክትትል መድሀኒቶችን በራሳቸው ወይም በሌላ ሰው ግፊት ምክንያት ማቋረጥ
5. በአንዳንድ መድሀኒቶች ላይ አልፎ አልፎ የሚታዩ የጎንዮሽ ጉዳቶች ሲከሰቱ ቶሎ ሀኪምን በማማከር በሌላ መድሀኒት ከመቀየር ይልቅ በራሳቸው ውሳኔ ማቋረጥ እና የመሳሰሉት
⭕ የደም ግፊት መቆጣጠሪያ መድሀኒት ሀኪምን ሳያማክሩ ማቋረጥ ምን ምን ችግሮችን ያስከትላል 🤔🤔
1) የደም ግፊት በድንገት መጨመር (Rebound hypertension)
-መድሀኒቱን በድንገት ሲያቋርጡ ግፊቱ በፍጥነት በከፍተኛ ሁኔታ ሊጨመር ይችላል።
2) የልብ ችግር
-የልብ ድካም
-የልብ ምት መዛባት
- የትላልቅ የደም ቧንቧዎች መሰንጠቅ እና በደም መሞላት (dissection) ሊያጋጥም ይችላል።
3) የአንጎል ጉዳት
-ስትሮክ (የአንጎል ውስጥ ደም መፍሰስ ወይም የደም ስር መዘጋት)
-ራስ ምታት
- ማዞር
-ራስን መሳትና ማንቀጥቀጥ
4) የኩላሊት ጉዳት
-ከፍተኛ ግፊት ኩላሊትን ይጎዳል።ይኸውም እስከ ኩላሊት ስራ መቀነስ እና ማቆም የሚደርስ ሊሆን ይችላል ።
5) የዓይን ጉዳት
- የዓይን የደም ስሮችና ነርቮች ሊጎዱ ይችላሉ፣ ይህም የእይታ መቀነስ ሊያመጣ ይችላል።
✅ የደም ግፊት በከፍተኛ ደረጃ መጨመር ምልክቶች ምን ምን ናቸው🤔
-ከፍተኛ ራስ ምታት
- የደረት ህመም
-እጅ/እግር መደንዘዝ
-የዕይታ መቀነስ
-ከአፍንጫ ደም መፍሰስ ወይም መንሰር
-ራስን መሳት
✅ የጥንቃቄ ምክር 🗣
☑ የግፊት መድሀኒት በራስዎ ፍቃድ አያቋርጡ