28/08/2026
ላለፉት አምስት ሳምንታት በከፍተኛ ግለት እና ፉክክር ሲካሄድ የቆየው የመተሳሰብ ዲላ ጤና ስፖርት ማህበር የወንድማማችነት የውስጥ ውድድር በዚህ ሳምንት ፍጻሜዉን የሚያገኝ ይሆናል።
አራቱም ቡድኖች የመጨረሻ ደረጃቸዉን ያለዩ ሲሆን ኡራጋና ሮቢን ሻምፕዮን ለመሆን ሲፎካከሩ አቤ ሆቴል ደግሞ ሁለተኛ ሆኖ ለመጨረስ ብርቱ ፉክክር ያደርጋል።
በተጨማሪም በተጫዋቾች መካከል ለኮከብነት የሚደረገዉ ፉክክር በጉጉት ይጠበቃል ።
እሁድ በ24/12/2019 በዲላ እስታዲዮም ትንሿ ሜዳ ሁላችሁም ተጋብዛቿል