Goro Health Center - Dire Dawa

  • Home
  • Goro Health Center - Dire Dawa

Goro Health Center - Dire Dawa Welcome to Goro Health Center-Dire official page, serving the vibrant 02 Kebele area known as Sapiyan with compassion and expertise.

We are dedicated to providing high-quality healthcare services to our community, promoting wellness to society!.

መልካም አዲስ ዓመት
11/09/2026

መልካም አዲስ ዓመት

11/09/2026
10/09/2026

መልካም አዲስ ዓመት!

ጎሮ ጤና ጣቢያ  በጳጉሜ 4 «የኅብር ቀን» በማስመልከት 150 ሺህ ብር የሚገመት  የማእድ ማጋራትና የዓመት በአል መዋያ ድጋፍ አበርክቷል።​ጎሮ ጤና ጣቢያ ጳጉሜ 4 «የኅብር ቀን» በማስመል...
09/09/2026

ጎሮ ጤና ጣቢያ በጳጉሜ 4 «የኅብር ቀን» በማስመልከት 150 ሺህ ብር የሚገመት የማእድ ማጋራትና የዓመት በአል መዋያ ድጋፍ አበርክቷል።

​ጎሮ ጤና ጣቢያ ጳጉሜ 4 «የኅብር ቀን» በማስመልከት ደሞዛቸው አነስተኛ ለሆኑ ሠራተኞች የማእድ ማጋራትና የበዓል መዋያ በማበርከት ቀኑ በደመቀ ሁኔታ አክብሯል።

​በድጋፍ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሜዲካል አገልግሎት ዳይሬክቶሬትበዳይሬክተር አቶ አብዶ ሙሜ ጳጉሜ –4 የህብር ቀን ተብሎ መከበሩ ዛሬ በተቋሙ የተደረገው የማዕድ ማጋራት የተቋሙ ሠራተኞች እርስ በእርስ የመደጋገፍ ባህል እንዲዳብሩ ያግዛል ብለዋል።

በድጋፍ ስነ -ስርአቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የጎሮ ጤና ጣቢያ ኃላፊ እንዳላማው እርቅይሁን በበኩላቸው ይህ ድጋፍ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሠራተኞች በዓሉን በደስታና በጋራ እንዲያሳልፉ ለማስቻል የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸው፤ በቀጣይም እንደዚህ ያሉ የበጎ አድራጎት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

Goro Health Center
Center of Excellence

Email: [email protected]
Telegram: https://t.me/GoroPHCU
Facebook: https://www.facebook.com/share/1B4gWe7v2Q/
Website: https://ghcdd.gov.et

ለበለጠ መረጃ በ0986200277 ይደውሉ

በተቋማችን ጎሮ ጤና ጣቢያ ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ። ተቋማችን ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ጥራት ለማሻሻልና የተገልጋዮችን እርካታ ለማሳደግ የሚያግዙ  የጥራት ማ...
08/09/2026

በተቋማችን ጎሮ ጤና ጣቢያ ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ።

ተቋማችን ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ጥራት ለማሻሻልና የተገልጋዮችን እርካታ ለማሳደግ የሚያግዙ የጥራት ማሻሻያ ፕሮጄክቶችን ቀረፃና ትግበራ ለማሻሻል ለአራት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የአሰልጣኞች ስልጠና (Taining of Trainers on Quality Improvement) ስልጠና በጥሩ ሁኔታ ተጠናቋል።

በስልጠናው የተሳተፉ ከጎሮ ጤና ጣቢያ እና የጎሮ EPAQ Cluster አባል ተቋማት (አዲስ ከተማ፣ ቦረን ደቻቱ፣ መልካ ጀብዱና ዶር አቤል መታሰቢያ ጤና ጣቢያዎች የተሳተፉ ባለሙያዎች ወደ መጡበት ተቋም ሲመለሱ የሚተገብሩት QI Project ግብዓት የሚሆን መነሻ እቅድ ያዘጋጁ ሲሆን በቆይታቸው ከስልጠናው ለስራ የሚያግዛቸው በቂ እውቀትና ልምድ እንደቀሰሙ ገልፀዋል።

በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ የተገኙት የጎሮ ጤና ጣቢያ ኃላፊ እንዳላማው እርቅይሁን ስልጠናው የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻልና የተገልጋዮችን ፍላጎት ለማሟላት እንደሚያግዝ ገልፀው ተሳታፊዎች ከየተቋማቸው የለዩትን ክፍተት ለመቅረፍ ያዘጋጁትን የ QI Project እቅድ በመተግበር በሚቀጡሉት 6ወራት እርስ በእርስ ልምድና ተሞክሮ የምንማማርበት ለውጥ እንዲያስመዘግቡ አስታውሰው ጎሮ ጤና ጣቢያ በEPAQ ክላስተር የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ QI ቲም አስተባባሪ አቶ ያሬድ ሀይሉ በበኩላቸው ተሳታፊዎች በቆይታቸው ያገኙትን ግንዛቤ ወደ ተቋማቸው ወስደው ትርጉም ያለው የአገልግሎት ጥራት መሻሻል ማምጣት እንደሚገባቸው የገለፁ ሲሆን በቀጣይ አጭር ጊዜ ስልጠናውን በየተቋማቸው ካስኬድ እንዲያደርጉ በጤና ቢሮ ስም መልዕክ አስተላልፈዋል።

Goro Health Center
Center of Excellence

Email: [email protected]
Telegram: https://t.me/GoroPHCU
Facebook: https://www.facebook.com/share/1B4gWe7v2Q/
Website: https://ghcdd.gov.et

ለበለጠ መረጃ በ0986200277 ይደውሉ

06/09/2026
ተቋማችን ጎሮ ጤና ጣቢያ የሚሰጠውን አገልግሎት ጥራት ለማሻሻል የሚያግዝ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ። ተቋማችን ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ጥራት ለማሻሻልና የተገልጋዮችን እ...
02/09/2026

ተቋማችን ጎሮ ጤና ጣቢያ የሚሰጠውን አገልግሎት ጥራት ለማሻሻል የሚያግዝ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ።

ተቋማችን ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ጥራት ለማሻሻልና የተገልጋዮችን እርካታ ለማሳደግ የሚያግዙ የጥራት ማሻሻያ ፕሮጄክቶችን መቅረፅና መተግበር የሚያስችል የአሰልጣኞች ስልጠና (Taining of Trainers on Quality Improvement) በጎሮ ጤና ጣቢያ መስጠት ጀምሯል።

በስልጠናው ከጎሮ ጤና ጣቢያ እና የጎሮ EPAQ Cluster አባል ተቋማት (አዲስ ከተማ፣ ቦረን ደቻቱ፣ መልካ ጀብዱና ዶር አቤል መታሰቢያ ጤና ጣቢያዎች የተውጣጡ ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛል።

Goro Health Center
Center of Excellence

Email: [email protected]
Telegram: https://t.me/GoroPHCU
Facebook: https://www.facebook.com/share/1B4gWe7v2Q/
Website: https://ghcdd.gov.et

ለበለጠ መረጃ በ0986200277 ይደውሉ

አከብሮትና ርህራሄ፣ ጥራትና ቅልጥፍና የአገልግሎታችን መለያዎች ናቸው።
27/08/2026

አከብሮትና ርህራሄ፣ ጥራትና ቅልጥፍና
የአገልግሎታችን መለያዎች ናቸው።

Address

HRWR+36W

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Goro Health Center - Dire Dawa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Goro Health Center - Dire Dawa:

Shortcuts

  • Want your business to be the top-listed Health & Beauty Business?

Share