Gish Abay Sekela Health Center

Gish Abay Sekela Health Center Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gish Abay Sekela Health Center, Medical and health, West Gojjam Sekela Ethiopia, Gish Abay.

17/05/2026

የወንዶች የብልት መቆም ችግር (Erectile Dysfunction) ምንድን ነው?

የብልት መቆም ችግር የሚባለው ወንድ ልጅ ለግብረ-ሥጋ ግንኙነት በቂ የሆነ የብልት ጥንካሬ ማግኘት ወይም ለረጅም ጊዜ ማቆየት ሲያቅተው ነው። ይህ ችግር አልፎ አልፎ ሊከሰት ቢችልም ተከታታይነቱ ከጨመረ ግን በራስ መተማመን እና በትዳር ህይወት ላይ ጫና ስለሚፈጥር የህክምና እርዳታ ያስፈልገዋል።

🌟ዋና ዋና መንስኤዎች

💠 የደም ዝውውር ችግር- እንደ ስኳር ,ደም ግፊትና የልብ ህመም ያሉ የጤና እክሎች።

💠 የሆርሞን መዛባት-የቴስቶስትሮን (Testosterone) ሆርሞን መጠን ማነስ።

💠 ስነ-ልቦናዊ ምክንያቶች-ከመጠን ያለፈ ጭንቀት (Stress), ድብርት ወይም የፍርሃት ስሜት።

💠 የአኗኗር ዘይቤ- ሲጋራ ማጨስ, አልኮል እና ጫት ማዘውተር።

🚨 ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ነገሮች

💠 ዕድሜ- ዕድሜ እየጨመረ ሲሄድ የመነቃቃት ፍጥነት ሊቀንስ ይችላል።

💠 ከመጠን ያለፈ ውፍረት- የሆርሞን መዛባትንና የደም ዝውውር መዘጋትን ያመጣል።

💠 መድኃኒቶች- ለአንዳንድ ህመሞች የሚወሰዱ መድኃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት።

💊 እንዴት መቆጣጠር ይቻላል?

💠 የባለሙያ ምክር- ችግሩን በግልጽ ለሃኪም በማማከር ትክክለኛውን መነሻ ማወቅ።

💠 የአኗኗር ለውጥ- አካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ,ሲጋራና ጫት ማቆም, ክብደትን መቀነስ።

💠 የዘመናዊ ሕክምና አማራጮች-እንደ ሆርሞን ማስተካከያ እና የተለያዩ ውጤታማ መድኃኒቶች።

💠 ስነ-ልቦናዊ ድጋፍ- ከጭንቀት መራቅና ከትዳር አጋር ጋር ግልጽ ውይይት ማድረግ።

🌟ጤናማ የትዳር ህይወት ለመኖር ችግሩን በጊዜው ማማከር አስፈላጊ ነው!በራስ መተማመንዎን ይመልሱ!
via health for all

17/05/2026

በእንጅባራ ከተማ የምትገኝ አንዲት ህፃን ቤተሰቦቿን እየፈለገች ነው ።

የእንጅባራ ከተማ ቀበሌ 05 አስተዳደር በአሁኑ ሰዓት በአስተማማኝ ጥበቃ ስር ለምትገኝ አንዲት ህፃን አስቸኳይ የቤተሰብ ፍለጋ ጥሪ አስተላለፈ።

ህፃኗ የተገኘችው በእንጅባራ ከተማ ቀበሌ 05 ልዩ ስሙ «ታቦት ማደሪያው» ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑ ታውቋል። የመንግስት አካላት ህፃኗን ተረክበው ደህንነቷ በተጠበቀ ሁኔታ እንክብካቤ እያደረጉላት ይገኛል።

ስለሆነም ይህችን ህፃን የምታውቁ፣ ቤተሰቦች ወይም የቅርብ ዘመዶች በአስቸኳይ በቀበሌው 05 ጽህፈት ቤት በመገኘት እንድትረከቡ የከተማው አስተዳደር በጥብቅ አሳስቧል።

የህፃናትን ደህንነት ለመጠበቅና ይህችን ህፃን ከወላጆቿ ጋር ለመቀላቀል መረጃውን #ሼር በማድረግ ይችን እምታሳሳ ህፃን ቤተሰቦቿን እናገናኛት ፦Via እንጅባራ ከተማ ኮሙኒኬሽን

ግዮን ማለዳ

17/05/2026
17/05/2026

Address

West Gojjam Sekela Ethiopia
Gish Abay

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gish Abay Sekela Health Center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share