Marza specialty clinic woreta

Marza specialty clinic woreta Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Marza specialty clinic woreta, Medical and health, Woreta, Gondar.

12/07/2026
11/07/2026

ማርዛ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ በወረታ ቀበሌ 01 ተከፍቶ የተለያዩ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል።
ይህንንም አገልግሎት ለማስፋፋት የተለያዩ ምርመራወችንም ማሽኖችንም እያስገባን መሆኑን እየገለፅሁ ECHO ወይም የልብ አልትራሳውድ በስፔሻሊስት ሀኪም መጀመራችን እየገለፅሁ በቅርቡ የሰውነት ፈሳሽ ምርመራ(Body fluid analysis) እና Electrolyt ምርመራ የምጀምር መሆኑን ሳበስር በታላቅ ደስታ ነው።

05/07/2026

© ልብዎ ከሁሉ የተሻለ እንክብካቤ ይገባዋል

በማርዛ ስፔሻሊቲ ክልኒክ የECG (የልብ ኤሌክትሪክ ምርመራ) እና Echocardiography / ECHO (የልብ አልትራሳውንድ) ምርመራ አገልግሎቶችን በዘመናዊ መሣሪያዎች እና በሙያዊ እንክብካቤ እንሰጣለን። ፈጣን፣ ትክክለኛ እና የተሟላ የልብ ምርመራ በአንድ ቦታ ያግኙ።

🫀 የECG አገልግሎት
• ያልተለመዱ የልብ ምቶችን (Arrhythmias) ለመለየት
• የደረት ህመም, የልብ ምት መፍጠን ወይም የልብ ምት በግልጽ መሰማት (Palpitations), የልብ ደም ስሮች መጥበብ/መዘጋት ( Acute/Chronic Coronary Syndrome ) እና ሌሎችን ምክንያቶችን ለመገምገም
• የልብ ጤናን በፍጥነትና በትክክል ለመመዘን

🫀 Echocardiography (የልብ አልትራሳውንድ)
• የልብ አወቃቀርና ሥራ በዝርዝር ለመገምገም
• የልብ ቫልቮችንና የልብ ደም መደፍቅ አቅምን (Pumping Function) ለመመርመር
• ምንም የጎንዮሽ ጉዳቶች የሌለው፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ህመም የማያስከትል
ምርመራ
° ምርመራውን ከሰኞ እስከ እሁድ ያገኛሉ

✅ ፈጣንና ትክክለኛ ውጤት
✅ ዘመናዊ መሣሪያዎች
✅ ጥራት ያለው የታካሚ እንክብካቤ

የደረት ህመም፣ የትንፋሽ ማጠር፣ ወይም ሌሎች ከልብ ጋር የተያያዙ ምልክቶች ካሉብዎ ወይም የልብዎን ጤና ለማረጋገጥ ከፈለጉ፣ እኛ ለማገልገል ዝግጁ ነን።

Marza Internal Medicine , Obstetric and Gynecology Clinic

አድራሻ: ወረታ ቀበሌ 01 ሐይስኩል ጀርባ

ማርዛ ለጤናችን !!

02/07/2026

Comprehensive Laboratory Services at Marza Internal Medicine & Obstetric snd Gynecology Clinic

🩸 Hematology Services
✅ Complete Blood Count (CBC)
✅ ESR, CRP
✅ Blood Film Examination
✅ Blood Group & Rh Typing

🧬 Hormone & Endocrine Testing

✅ Thyroid Function Tests (TSH, Free T4, Free T3)
✅ Prolactin
✅ LH & FSH
✅ Other hormonal tests

🦠 Viral Marker & Infectious Disease Testing

✅ HBsAg (Hepatitis B Surface Antigen)
✅ HCV Antibody
✅ HIV Testing

⚗️ Clinical Chemistry Services

✅ Liver Function Tests (LFT)
✅ Kidney Function Tests (RFT)
✅ Blood Glucose & HbA1c
✅ Lipid Profile
✅ Uric Acid
✅ CRP and other inflammatory markers

25/06/2026

“የግፊት መድሀኒት አልጀምርም ፤ በምግብ አስተካክለዋለሁ”

✅ እውነታ (Fact): ጤናማ አመጋገብ እና የአኗኗር ለውጦች የደም ግፊትን ለመቆጣጠር በጣም አስፈላጊ ናቸው። ነገር ግን ለብዙ ሰዎች እነዚህ ብቻ በቂ አይሆኑም።

የደም ግፊቱ ከፍ ያለ ከሆነ ወይም ሌሎች እንደ ስኳር በሽታ፣ የኩላሊት ችግር እና የልብ በሽታዎች ካሉ፣ መድሀኒት መጀመር ሊያስፈልግ ይችላል።

ብዙ ሰዎች:
• "ጨው መተው ብቻ በቂ ነው"
• "ምልክት የለኝም፣ ስለዚህ መድሀኒት አያስፈልገኝም"
• "አንዴ ከጀመርኩት እድሜ ልኬን መውሰድ አለብኝ"
• "መድሀኒት ኩላሊቴን ይጎዳል"
ብለው ይፈራሉ። ይህ ግን ትክክል አይደለም።

⚠️ የደም ግፊት መድሀኒት የሚረዳው:
• የደም ግፊትን በትክክለኛው መጠን (range )ለማቆየት
• የአንጎል ደም መፍሰስን (stroke) ለመቀነስ
• የልብ ድካምን እና የልብ ህመምን ለመከላከል
• የኩላሊት ጉዳትን ለመቀነስ
• ለረጅም ጊዜ የልብና የደም ሥር ጤናን ለመጠበቅ
ነው።

❗️ የደም ግፊት ብዙ ጊዜ (silent killer) ነው።
ብዙ ሰዎች ምንም ምልክት ሳይኖራቸው ለዓመታት ከፍተኛ የደም ግፊት ሊኖራቸው ይችላል። ስለዚህ "ምልክት የለኝም" ማለት የደም ግፊቱ ትክክለኛ መጠን(normal range) ነው ማለት አይደለም።

⚠️ የግፊት መድሀኒትን በሀኪም ምክር አለመጀመር ወይም ማቆም ሊያስከትላቸው የሚችላቸው ጉዳቶች:

• የአንጎል ደም መፍሰስ (stroke)
• የልብ ድካም (heart failure)
• የልብ ህመም (heart attack)
• የኩላሊት ሥራ መቀነስ
• የዓይን ደም ሥሮች ጉዳት
• ድንገተኛ የግፊት መጨመር (hypertensive crisis)

❗️ **አንዳንድ ሰዎች ጤናማ አኗኗር ከተከተሉ በኋላ የመድሀኒት መጠናቸው ሊቀንስ ወይም አንዳንድ መድሀኒቶች ሊቆሙ ይችላሉ። ይህ ግን በሀኪም ምክር ብቻ መደረግ አለበት።

✅ የደም ግፊት መድሀኒት ለመጉዳት ሳይሆን፣ ልብን፣ አንጎልን፣ ኩላሊትን እና የደም ሥሮችን ከከባድ ጉዳት ለመጠበቅ የሚረዳ ሕክምና ነው።

📚 References:
• 2024 ESC Guidelines for the Management of Elevated Blood Pressure and Hypertension.
• 2020 International Society of Hypertension Global Hypertension Practice Guidelines.
• 2017 ACC/AHA Guideline for the Prevention, Detection, Evaluation, and Management of High Blood Pressure in Adults.



Dr. Ermias Nigusie Balcha: MD Internist
SPHMMC

24/06/2026

ስኳር በሽታ (Diabetes Mellitus) ከመደበኛው የደም ውስጥ የስኳር መጠን ከፍ ሲል የሚከሰት ህመም ነው። ይህም ማለት በሰውነት ውስጥ ኢንሱሊን (Insulin) የተባለ ንጥረ ነገር በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን እንዳይጨምር እንዳይቀንስ የሚቆጣጠር ሲሆን አንድ ሰው ስኳር የሚከሰትበትም የኢንሱሊን (insulin) መስራት መዳከም ነው።
ዋና አይነቶች:
አይነት 1 (Type 1 Diabetes)
በሰውነታችን ውስጥ የኢንሱሊን ምርት በሙሉ የሚቋረጥ ነው።
ብዙ ጊዜ በሕፃናትና በወጣቶች ዘንድ ይታያል።
የበሽታው ሕክምናም ኢንሱሊንን መውሰድ ነው።
አይነት 2 (Type 2 Diabetes)
ኢንሱሊን ቢሰራም ሰውነት መስራቱን አይሰማውም (insulin resistance)።
በዕድሜ ምክኒያት ዕድሜ እየጨመረ ሲመጣ በትልልቅ ሰወች ላይ ይታያል።
በመመገብ ልምድ፣ በስራ እና በመድሀኒት መቆጣጠር ይቻላል።
የስኳር በሽታ ምልክቶች:
-በብዙ ጊዜ ውሃ መጠጣት
-ብዙ ጊዜ ማዞር (መሽከርከር)
-እንቅልፍ መውሰድ አለመቻል
-እጅና እግር መደንዘዝ
-ሽንት ሽንት ማለት
-አፍ መድረቅ
-እይታ መደብዘዝ(ብዥ ማለት)
-ዝቅተኛ ኃይል እና ድካም
እንዴት መከላከል እችላለን?
-እንቅስቃሴ በየቀኑ ማድረግ
-በሚገባ መመገብ ወይም አመጋገብን ማስተካከል
-ክብደትን መቆጣጠር
-የደም ስኳር መለኪያ በቀጥታ መከታተል
እንዲያውም ሕክምና መቀበል፣ የሚያስተምሩ ባለሙያዎችን መጠየቅ
አዘጋጅ:- ግዛቸው ማሩ
ላቦራቶሪ ቴክኖሎጅስት!!

አጠቃላይ የደም ቆጠራ (CBC) ማለት ምን ማለት ነው?

አጠቃላይ የደም ቆጠራ (CBC - Complete Blood Count) ማለት በሰው ደም ውስጥ ያሉ የደም ንጥረ ነገሮችን ለመመዘንና ለመገምገም የሚደረግ የምርመራ አይነት ነው። ይህ ምርመራ ህክምናዊ ሁኔታዎችን ለማወቅ ፣ ለማስቀመጥ እና ለመከታተል በጣም አስፈላጊ ነው።
CBC የሚመዘኑት ዋና ነገሮች:
ነጭ የደም አሳንሰሶች (WBC - White Blood Cells):
ሰውን ከበሽታዎች የሚከላከሉ አካላት ናቸው። አንድ ሰው ነጭ የደም ሴሉ ከጨመረ ወይም ከቀነስ ያ ሰው በሰውነቱ ውስጥ
በሽታ፣ እብጠት፣ ነቀርሳ፣ እና ሌሎችም በሰውነቱ እንደተከሰተ ማረጋገጥ ይቻላል።
ነጭ የደም ሴል (White Blood Cells - WBCs) በአካል ውስጥ ከሚገኙ ደም ሴሎች አንዱ ነው። ነጭ የደም ሴል በአካል ውስጥ በእንግዳ ተፅዕኖ ላይ ወይም በበሽታ ሲከሰት እንደ መከላከያ ሚና ይጫወታል።
ነጭ የደም ሴል መብዛት (Low WBC count): ይህ ማለት በሰውነቱ አካላችን ከነዚህ እንደ ቫይረሶች ወይም በሌሎች እንግዳ ተፅዕኖዎች ተጋላጭ ሲሆን ከሚከሰቱ በሽታዎች አንዱ ነው። እንደ ምሳሌ ቫይረስ ተጠቂ ወይም በአንዳንድ መድሀኒቶች የተነሳ ሊሆን ይችላል።
ነጭ የደም ሴል መብዛት (High WBC count): ይህ ሊሆን ይችላል በአካል ከተባለ እንግዳ ከሆነ በሽታ ሲከሰት ወይም ከአካል ውስጥ ከሚከሰቱ እንግዳ ከተባለ ማንኛውም የተለየ በሰውነታችን የሚታይ ነገር ሊሆን ይችላል። እንደ ምሳሌ በተቋማዊ እንቅስቃሴ ሲሰራ (infection), በሽታዎች (inflammation), እና ከአንዳንድ አኗኗር ስርዓቶች የሚከሰት ሊሆን ይችላል።
አጠቃላይ እንደሚታወቀው ነጭ የደም ሴል አካል የአካል መከላከያ ሲሆን ብዛቱ በሽታዎችና በአካል ሁኔታዎች መሰረት ሊቀነስ ወይም ሊጨምር ይችላል።

ቀይ የደም ሴሎች (RBC - Red Blood Cells):
ኦክሲጅንን ወደ ሰውነት የሚያስተላለፉ ናቸው።
እነዚህ ቁጥራቸው ከመደበኛው በታች ከሆነ አንሚያ (anemia) እንደሆነ ይገልጻል።
ቀይ የደም ሴል (Red blood

03/06/2026

በማርዛ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ በዘመናዊ መሳሪያ በመታገዝ የሚሰጡ የላቦራቶሪ ምርመራወች:-
1, HDL( high desity lipid profile test) ( በሰውነታችን ያለውን የኮሌስትሮል መጠን ምርመራ)
2,LDL(low density lipid profile test) (በሰውነታችን ያለውን የኮሌስትሮል መጠን ምርመራ)
3, AST (Aspartate aminotransferase) (የጉበት ምርመራ ወይም በተለምዶ የወፍ በሽታ እየተባለ ሚጠራው)
4, ALP(Alanine aminotransferase) (የጉበት ምርመራ ወይም በተለምዶ የወፍ በሽታ እየተባለ ሚጠራው)
5,Urice acide test (የሪህ ምርመራ)
6, Creatinine test ( የኩላሊት ምርመራ)
7, HgA1c ( የ3 ወር የስኳር መጠን ምርመራ)
8, Vitamin D deficiency ( የቫይታሚን ዲ እጥረት ምርመራ ወይም የአጥንት መሳሳት ምርመራ)
9, TSH( Thyroid stimulating hormone) (የእንቅርት ምርመራ)
10, T3(Triiodothyronine) (የእንቅርት ምርመራ)
11,T4( Thyroxine) (የእንቅርት ምርመራ)
12,FSH(Follicle stimulating hormone) (የመካንነት ምርመራ)
13,LH (Luteinizing hormone) (የመካንነት ምርመራ
14, CBC( Complet blood count) (አጠቃላይ የደም ቆጠራ)

እነዚህን ከላይ የተዘረዘሩትን እና ሌላም ምርመራወችን በወረታ ከተማ ቀበሌ 01 ወፍ አምሳ በብቁ ባለሙያወች አገልግሎት እየሰጠን እንገኛለን።
ለማንኛውም አገልግሎት በማንኛውም ሰአት ቢመጡ ያገኙናል በአገልግሎታችን ተደስተው ይመለሳሉ።
ለበለጠ መረጃ +251937379710
+251928292069
ደውለው ማማከር ይችላሉ!!!!!!!

21/05/2026

ህክምናው ደግሞ ምንድን ነው?
እንደየደረጃቸው ይለያያል።
በእኛ ሀገር ያለው ብዙ ጊዜ ደረጃው ከጨመረ በኋላ ስለሆነ የሚከሰተው አብዛኞቹ የቀዶ ህክምና ይፈልጋሉ።
ደረጃው ዝቅ ያለ ከሆነ ግን በየወሩ በሚሰጥ መድሀኒት ይድናል።
አሁን ባህርዳር ላይ የገጠመን ግን በጣም ብዙ የቀዶ ህክምና የሚፈልጉ ናቸው።

ሰላማዊ ህይወት ፣ ረጅምና ጤናማ እድሜ ተመኘሁላችሁ።

21/05/2026

Rheumatic Heart Disease (በእኔ አረዳድ የልብ በሮች ቁርጥማት)
ምንድነው?
ለምን ይከሰታል?
እንዴት ይታወቃል?
የሚለውን ትንሽ ማለት ወደድኩ።
ብዙዎቹ የህክምና ቃላት አቻ ፍች የላቸውም። እንደ ክቡር ዶር ከበደ ሚካኤል አገላለጽና አረዳድ ቋንቋ መፈልሰፍ ያለባቸው የቋንቋ ባለሙያዎች ናቸው፣ የሳይንስ ባለሙያዎች ሙያቸውን በማሳደግ ከቋንቋ ባለሙያዎች ጋር አብረው ሊሰሩ ይገባል። በዚህ መንገድ ነው እድገት የሚገኘው።
ወደ ርዕሴ ስመለስ ግን
የልብ ቁርጣማት ብየ የምጣረው በሽታ ልብን ለከፍተኛ ችግር ይዳርጋል። ልባችን አራት ዋና ዋና የሚከፈቱና የሚዘጉ በሮች (Valves) አሏት። እነዚህም ደም ለማስገባትና ለመርጨት ይጠቅማሉ።
በመሆኑም እነዚህ በሮች ችግር ሲገጥማቸው ወይ አይዘጉም ወይም ደግሞ አይከፍቱም። በር ሲበላሽ ደግሞ ወይ መጠገን አለበለዚያ ደግሞ መቀየር ይገበዋል።

ለምን የልብ በሮች ይበላሻሉ?
የልብ በሮች የሚበላሹት በዋነኝነት በባክቴሪያ ቁስለት ወይም ደግሞ በተፈጥሮ ነው። በእኛ አገር የሚበዛው በባክቴሪያ የሚመጣው ነው። ይህም ባክቴሪያ Streptococcus ይባላል። ብዙ ጊዜ በህፃንነት እድሚያችን ይህ ባክቴሪያ እንጣላችንና ጉረሯችን ያቆስላል። በዚህም የተነሳ ፣ ሰውነታችን ራሱን ለመከላከል የራሱን ጥይት ያመርታል ። ይህ የተመረተ ጥይት ደግሞ ባክቴሪያውን ለማጥፋት ይጠቅማል። ግን አንዳንዴ ጥይቱ ይባርቅና ልብንና ኩላሊትን ያጠቃል። በዚህም ምክንያት የልብ ወይም የኩላሊት ችግር ይፈጠራል ማለት ነው።
ይህ የባረቀ ጥይት የልብ በሮችን ጉዳት ያደርስና ልብ ላይ ከፍተኛ ጫና ያመጣል ።

ምልክት
ከፍተኛ የሆነ ድክም፣ ሽርጋታ/ድቅድቃት/ልብ ስትመታ ምቾት መንሳት ፣ ሰውነት ማበጥና ትንፋሽ መቆራረጥ ናቸው።
ህሙም ሁለት አይነት ባህሪይ አለው። የመጀመሪያው ድንገት የሚፈጠር ነው። መገጣጠሚያ ማበጥ፣ ሙቀትና የልብ ችግር ነው። ይሄ በቀላሉ ይድናል። ሁለተኛው ደግሞ እንደ ክፉ ጠላት ቀስ ብሎ ውስጥ ውስጡን ሲጎዳ ይኖርና ደረጃው የማይመለስበት ሲደረስ ይታወቃል። ይህም ብዙ ጊዜ እስከ 16 ዓመት ዕድሜ ይቆያል። በዚህ ጊዜ አብዛኞቹ ሰዎች ምልክት ያሳያሉ።

እነማን ተጋላጭ ናቸው?
በአንድ ቤት ውስጥ ብዙ ሆነው የሚኖሩ ፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው፣ ለህፃናት ኢንፌክሽን የተጋለጡ ሰዎች ለልብ ቁርጥማት ይጋለጣሉ ።
መከላከያያው ምንድንነው?

Address

Woreta
Gondar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Marza specialty clinic woreta posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share