ዶ/ር አለሙ የቆዳ ስፔሻሊቲ-Dr.Alemu Dermatology Clinic Injibara

  • Home
  • Ethiopia
  • Injibara
  • ዶ/ር አለሙ የቆዳ ስፔሻሊቲ-Dr.Alemu Dermatology Clinic Injibara

ዶ/ር አለሙ የቆዳ ስፔሻሊቲ-Dr.Alemu Dermatology Clinic Injibara #የቆዳ ፤ የፀጉር ፤ የጥፍርና የአባላዘር ምርመራና ህክምና
09 7028 8028 ቀጠሮ ለማስያዝ ወይም ለማማከር

05/07/2026

I got over 3,650 reactions on my posts last week! Thanks everyone for your support! 🎉

አድራሻ  #እንጅባራ ፤  #ቻግኒ  #መውጫ 09 7028 8028
03/07/2026

አድራሻ #እንጅባራ ፤ #ቻግኒ #መውጫ
09 7028 8028

 #በግብረ  #ስጋ  #ግንኙነት  #እንደሚተላለፍ  #ያውቃሉ???ሞለስከም- Molluscum contagiosumበቫይረስ ምክንያት የሚመጣ  የቆዳ ኢንፌክሽን ነውመተላለፊያ መንገድበቫይረሱ ከተያዘ...
01/07/2026

#በግብረ #ስጋ #ግንኙነት #እንደሚተላለፍ #ያውቃሉ???

ሞለስከም- Molluscum contagiosum

በቫይረስ ምክንያት የሚመጣ የቆዳ ኢንፌክሽን ነው

መተላለፊያ መንገድ
በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ቀጥተኛ በሆነ የቆዳ ለቆዳ ንክኪ
በቫይረሱ የተበከሉ እንደ ፎጣ፣ ልብስ፣ የጨዋታ እቃዎች ወይም መዋኛ ገንዳ ያሉ ቁሳቁሶችን በመጠቀም
ራስን በራስ ማስተላለፍ :የታመመውን የቆዳ ክፍል በመቧጨር ቫይረሱን ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ማዳረስ
በጎልማሶች ላይ #በግብረ #ሥጋ #ግንኙነት አማካኝነት ሊተላለፍ ይችላል

ምልክቶቹ
የእብጠቶች፡ በቆዳ ላይ ክብ፣ ለስላሳ፣ ከቆዳ ቀለም ጋር የሚቀራረቡ የሚያብረቀርቁ እብጠቶች ይወጣሉ።
መሃል ላይ መጎድጎድ
ህመም የላቸውም
የሚገኙበት የሰውነት ክፍል፡ በህፃናት ላይ ብዙ ጊዜ ፊት ላይ ሲታዩ፤
በአዋቂዎች ላይ ግን በብልት አካባቢ፣ በታችኛው የሆድ ክፍል በብዛት ይታያሉ

ህክምናው
የበረዶ ህክምና
እብጠቶቹን በህክምና መሳሪያ ማንሳት
የቆዳ ቅባቶች እና ጠብታዎችን መጠቀም

 #ኤክቲዮሲስ-   የቆዳ ሴሎች በአግባቡ ባለመላጣታቸው ምክንያት የዓሳ ቅርፊት የሚመስል በጣም ደረቅ ቅርፊቶች በቆዳ ላይ የሚፈጥር የዘረመል (የጂን) በሽታ ነው 1. መንስኤዎችየዘረመል ችግር...
30/06/2026

#ኤክቲዮሲስ-

የቆዳ ሴሎች በአግባቡ ባለመላጣታቸው ምክንያት የዓሳ ቅርፊት የሚመስል በጣም ደረቅ ቅርፊቶች በቆዳ ላይ የሚፈጥር የዘረመል (የጂን) በሽታ ነው

1. መንስኤዎች
የዘረመል ችግር (Genetic Mutation)፦ ዋናው መንስኤ ቆዳ እርጥበትን እንዲይዝ የሚያደርገውን ፊላግሪን (Filaggrin) የተባለ ፕሮቲን የሚያመርተው ጂን መጎዳት ነው
ተያያዠ ህመሞች ፦ ከካንሰር፣ ከኩላሊት እጥበት ወይም ከተወሰኑ መድኃኒቶች ጋር ተያይዞ ሊከሰት ይችላል
2. ምልክቶች
ደረቅ እና የተሰነጠቀ ቆዳ፦ በተለይም በእግር እና በእጅ ላይ በጣም የደረቀ ቆዳ ይታያል
የዓሳ ቅርፊት መሰል ቅርፊቶች፦ ነጭ፣ ግራጫ ወይም ጠቆር ያሉ ቅርፊቶች በቆዳ ላይ ይፈጠራሉ
የእጅ እና እግር መስመሮች መብዛት፦ የእጅ መዳፍ እና የእግር ጫማ መስመሮች በጣም ጎልተው ይወጣሉ፣ ሊሰነጠቁም ይችላሉ
በብርድ ወራት መባባስ፦ ምልክቶቹ በክረምት (በቀዝቃዛ እና ደረቅ አየር) ይብሳሉ
3. ሕክምናዎች
በሽታው ሙሉ በሙሉ ፈውስ የሌለው ቢሆንም፣ በተከታታይ የቆዳ እንክብካቤ እና ቅባቶች ምልክቶቹን በሚገባ መቆጣጠር ይቻላል
ቆዳን ማለስለስና ማርጠብ (Moisturizing)፦ ገላን ከታጠቡ በኋላ ወዲያውኑ እንደ ቫዝሊን (Vaseline) ያሉ ወፍራም ቅባቶችን መቀባት።
ክሬሞች: በቆዳ ሀኪም ትዕዛዝ የሚቀቡ እንዲሁም የሚቀመሙ መድኃኒቶች ይወሰዳሉ

 #ላሽ-    ይህ የጤና ችግር የሰውነታችን በሽታ ተከላካይ ስርአት  በስህተት የራስ ቆዳን እና የሰውነት ፀጉር ስሮችን በሚያጠቃበት ጊዜ የሚከሰት በሽታ ነው1. መንስኤዎችየበሽታ ተከላካይ ስ...
28/06/2026

#ላሽ-

ይህ የጤና ችግር የሰውነታችን በሽታ ተከላካይ ስርአት በስህተት የራስ ቆዳን እና የሰውነት ፀጉር ስሮችን በሚያጠቃበት ጊዜ የሚከሰት በሽታ ነው
1. መንስኤዎች
የበሽታ ተከላካይ ስርአት ስህተት: የሰውነታችን ነጭ የደም ሴሎች ፀጉር በሚበቅልበት የፀጉር ስር ላይ ጥቃት ይሰነዝራሉ
የዘር ውርስ: በቤተሰብ ውስጥ የዚህ በሽታ ታሪክ ካለ የመያዝ እድሉ ከፍተኛ ነው
ጭንቀት
ኢንፌክሽን
2. ምልክቶች
ክብ ወይም ኦቫል ቅርጽ ያላቸው የራሰ በራ ቦታዎች
የጥፍር ለውጦች
3. ህክምና
እንደ ህመሙ ደረጃ ቢለያይም በቆዳ ሀኪም የሚታዘዙ
የሚቀቡ መድሀኒቶች
የመርፌ ህክምና
የሚዋጥ መድኃኒት
ጭንቀት መቀነስ

26/06/2026
 #የንጽህና  #ጉድለት-  Neglecta*የቆዳ ክፍሎችን በአግባቡ ባለማጠብ ሳቢያ የሚከሰት የቆዳ ችግር ነው*ላብ፣ ቅባት እና የሞቱ የቆዳ ህዋሶች በመከማቸት የጠነከሩ፣ ቡናማ ወይም ጥቁር ቀ...
26/06/2026

#የንጽህና #ጉድለት- Neglecta

*የቆዳ ክፍሎችን በአግባቡ ባለማጠብ ሳቢያ የሚከሰት የቆዳ ችግር ነው

*ላብ፣ ቅባት እና የሞቱ የቆዳ ህዋሶች በመከማቸት የጠነከሩ፣ ቡናማ ወይም ጥቁር ቀለም ያላቸው ቅርፊቶች ይፈጠራሉ
#ታካሚያችን ከኦፕሬሽን በኋላ ቦታውን ለረጅም ጊዜ አልታጠቡም ነበር

ምልክቶች
*ወፍራም ቅርፊቶች
*የጠቆረ ቆዳ
*መጥፎ ጠረን

መፍትሔ
*መታጠብ እና መፋቅ
*የህክምና አልኮል በመጠቀም መታጠብ
*ቅባቶችን መጠቀም
09 7028 8028

25/06/2026
 #ለምጽ-   ይህ በሽታ የቆዳ ቀለምን የሚያመርቱ ህዋሳት ( ) ሲሞቱ ወይም ስራ ሲያቆሙ የሚፈጠር የቆዳ ችግር ነውመንስኤዎችየ Vitiligo ትክክለኛ መንስኤ በሳይንስ ሙሉ በሙሉ ባይረጋገጥ...
25/06/2026

#ለምጽ-

ይህ በሽታ የቆዳ ቀለምን የሚያመርቱ ህዋሳት ( ) ሲሞቱ ወይም ስራ ሲያቆሙ የሚፈጠር የቆዳ ችግር ነው
መንስኤዎች
የ Vitiligo ትክክለኛ መንስኤ በሳይንስ ሙሉ በሙሉ ባይረጋገጥም፣ በርካታ ምክንያቶችን ይጠቁማሉ፦
• ራስን በራስ የሚያጠቁ የሰውነት መከላከል (Autoimmune disorder)
• የዘረመል ተጽእኖ (Genetics)
• የነርቭ ስርዓት ችግሮች
• ቀስቃሽ ሁኔታዎች: ከባድ የፀሐይ ቃጠሎ፣ የኬሚካል ንክኪ ወይም ከፍተኛ የጭንቀት ስሜት በሽታውን ሊቀሰቅሱት ይችላሉ
#በሀገራችን ለየት ያለ መነሻ: በገጠር አካባቢ #ኮንጎ #ጫማ የሚለብሱ ሰዎች ላይ ከእግራቸው አካባቢ ይጀምራል
ምልክቶች
• ነጭ የቆዳና የፀጉር ቀለም
• የአፍ እና የአፍንጫ ውስጠኛ ክፍል ነጭ መሆን

ህክምና
1. የሚቀቡ መድኃኒቶች
2. የጨረር ህክምና (Phototherapy)
3. ቀዶ ጥገና
4 የፀሐይ መከላከያ
5.ስነ-ልቦናዊ ድጋፍ

Address

Injibara
Injibara

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዶ/ር አለሙ የቆዳ ስፔሻሊቲ-Dr.Alemu Dermatology Clinic Injibara posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share