Gazer Primary Hospital

Gazer Primary Hospital የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን በጋዘር ከተማ አስተዳደር ሥር የሚትገኝ የመንግስት ጤና ተቋም ነው።ከ300 ሽ በላይ ለሆኑት ህዝብ አገልግሎት ይሰጣል።በ2010 ዓም አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

‎በጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የኤክስሬይ (X-ray) የምርመራ አገልግሎት በሙሉ አቅም ሥራ ጀመረ!‎‎ውድ የማህበረሰባችን አባላት፤‎‎ሆስፒታላችን ጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሕክምና...
13/08/2026

‎በጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የኤክስሬይ (X-ray) የምርመራ አገልግሎት በሙሉ አቅም ሥራ ጀመረ!

‎ውድ የማህበረሰባችን አባላት፤

‎ሆስፒታላችን ጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሕክምና አገልግሎት ጥራቱን ለማሻሻልና የሕሙማንን እንግልት ለመቀነስ በሚያደርገው የማያቋርጥ ጥረት፣ ተቋርጦ የነበረው የኤክስሬይ (X-ray) የምርመራ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ የጥገና ሥራው ተጠናቆ ከዛሬ ጀምሮ ወደ ሥራ መግባቱን በደስታ እንገልጻለን።

‎ይህ አገልግሎት ዳግም በመጀመሩ፡

‎ 🔹 ለኤክስሬይ ምርመራ ወደ ሩቅ ቦታዎች የሚደረገውን የጉዞ እንግልትና ተጨማሪ ወጪ ያስቀራል።
‎🔹 ፈጣንና ትክክለኛ የሕክምና ውሳኔ በመስጠት የሕሙማንን ሕይወት የመታደግ አቅማችንን ያጎለብታል።
‎ 🔹 በዘመናዊ መሣሪያና በባለሙያ የታገዘ የዲያግኖስቲክ አገልግሎት በቅርብዎ ያገኛሉ።

‎አገልግሎቱ ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች ክፍት ስለሆነ ወደ ሆስፒታላችን በመምጣት መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

‎"ጤናዎ ቅድሚያ የምንሰጠው ግባችን ነው!"

‎📰 ጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት የበጎ አደራጊነት አገልግሎት መርሃ-ግብር በይፋ አስጀመረ!‎‎[ጋዘር፣ ደቡብ ኢትዮጵያ   ነሀሴ 7/2018 ]‎‎ በደቡብ ኢ...
13/08/2026

‎📰 ጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት የበጎ አደራጊነት አገልግሎት መርሃ-ግብር በይፋ አስጀመረ!

‎[ጋዘር፣ ደቡብ ኢትዮጵያ ነሀሴ 7/2018 ]

‎ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን በጋዘር ከተማ አስተዳደር የሚገኘው ጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ አጠቃላይ የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት በጎ ተግባር መርሃ-ግብሩን ዛሬ በይፋ አስጀምሯል።

‎ይህ በታላቅ ድምቀት የተጀመረው የበጎ አደራጊነት አገልግሎት መርሃ-ግብር ዛሬ በጋዘር ሐሙስ ገበያ አዳራሽ የተካሄደ ሲሆን፣ በስነ-ስርዓቱ ላይ የጋዘር ከተማ አስተዳደር ዋና ከንቲባ ኢንጂነር በለጠ ማጎ፣ የከተማ አስተዳደሩ የጤና ዩኒት መሪ ሲስተር እታክቱ ዱቅላ፣የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ያዕቆብ ጥላሁን፣ የአሪ ዞን ጤና መምሪያ ደጋፊዎች እንዲሁም የሆስፒታሉ የራእይ አባላት፣ የጤና ባለሙያዎች እና በርካታ የከተማውና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት በይፋ ተከፍቷል።

‎ይህ ከሀምሌ ወር ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 5 / 2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆየው የክረምት በጎ ተግባር መርሃ-ግብር፤ የማህበረሰቡን ሁለገብ የጤና ችግሮች ለመቅረፍ እና የህክምና ተዳራሽነትን ለማስፋት ያለመ ሲሆን፣ የሚከተሉትን ዋና ዋና አገልግሎቶች በነፃ ያካትታል፦

‎ 🩸 የደም ልገሳ፦ ከበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች ወሳኝ እና ህይወት አድኚ ደም ማሰባሰብ፣
‎ 🩺 አጠቃላይ የጤና ምርመራ፦ የግፊት፣ የስኳር፣ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ (HIV/AIDS) እንዲሁም የሌሎች ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ምርመራና ህክምና፣
‎🎗️ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር፦ ቅድመ-ምርመራ (Screening) ማድረግ እና አስፈላጊውን ህክምና ማስጀመር፣
‎🦟 የወባ በሽታ፦ፈጣን የወባ ምርመራ እና የህክምና አገልግሎት መስጠት፣
‎🤰 የእናቶች እና ህፃናት ጤና፦ የነፍሰ ጡር እናቶች የጤና ክትትል (ANC) እና ከ5 ዓመት በታች ህፃናት የምግብ እጥረት (Malnutrition) ልጅነትና ልዩነት ስራ፣
‎📢 የግንዛቤ ማስጨበጫ፦ በተለያዩ አንገብጋቢ የጤና ትምህርቶች ዙሪያ ለማህበረሰቡ ሰፊ ግንዛቤ መፍጠር፣
‎ 🤝 የበጎ አድራጎት ማሰባሰብ፦ በኢኮኖሚ ምክንያት የህክምና ክፍያ መክፈል ለማይችሉ ወገኖች የሚውል የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ።

‎በአሁኑ ሰዓት በጋዘር ሐሙስ ገበያ አዳራሽ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች በቦታው በመገኘት እነዚህን ሁለገብ አገልግሎቶች በመቀበል ላይ ይገኛሉ።

‎ማሳሰቢያ፦የስራውን አጠቃላይ ሂደት እና የተደረሰበትን ውጤት የሚያሳይ የተጠናከረ ዘገባ እና አሃዛዊ ሪፖርት በሚቀጥሉትዎች ይዘን የምንመለስ ይሆናል።

‎ጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል "ለህብረተሰብ ጤና እና ደህንነት በትጋት እንሰራለን!"

‎የጤናዎ ጉዳይ ያሳስበናል! ለጋዘር ከተማ አስተዳደርና አካባቢው ማህበረሰብ የተደረገ ታላቅ የጤና ጥሪ‎       ‎    ነሀሴ 5/2018_ጋዘር‎     ዛሬ የሆስፒታሉ ማንጅሜንት አባላት በ...
11/08/2026

‎የጤናዎ ጉዳይ ያሳስበናል! ለጋዘር ከተማ አስተዳደርና አካባቢው ማህበረሰብ የተደረገ ታላቅ የጤና ጥሪ

‎ ነሀሴ 5/2018_ጋዘር
‎ ዛሬ የሆስፒታሉ ማንጅሜንት አባላት በክረምት በጎ ተግባር እና በሌሎች አብይ አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ ቀጣይ ሐሙስ ከሆስፒታሉ ጤና ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ትልቅ ማህበረሰብ ተኮር ሥራ እንደምኖር ውይይት ተደርጓል።
‎👉 በተለይ ትኩረት ለኤች.አይ.ቪ (HIV/AIDS)!
‎በአሁኑ ወቅት ኤች.አይ.ቪን በቸልተኝነት ዘንግተነዋል፤ ነገር ግን ቫይረሱ በህብረተሰባችን ውስጥ እንደገና እንደ ወረርሽኝ በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል። ጤናችንን በምርመራ ማወቅ የወደፊት ህይወታችንን የማዳን ትልቁ እርምጃ ነው!

‎በዚህ የበጎ አድራጎት ክረምት፣ በጤናው ዘርፍ ህብረተሰባችንን ለመደገፍ የታለመ ሙሉ በሙሉ ነፃ የጤና ምርመራ ተዘጋጅቶልዎታል።

‎🩺 የሚሰጡ ነፃ የምርመራ አገልግሎቶች፦

‎🩸 የኤች.አይ.ቪ (HIV) ምርመራ
‎🍬 የስኳር በሽታ ምርመራ
‎💓 የደም ግፊት ምርመራ
‎🌸 የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምርመራ (ለሴቶች)
‎እና የወባ ምርመራ

‎📅 የቀንና ቦታ መረጃ፡

‎🗓 ቀን፦ በሚመጣው ሐሙስ ነሃሴ 7/2018
‎⏰ ሰዓት፦ ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ
‎📍 ቦታ፦ ጋዘር ሀሙስ ገበያ አዳራሽ
‎👨‍⚕️ አገልግሎቱን የሚሰጡት፦ የጋዘር ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች እና የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ጋር በመተባበር

‎ያስታውሱ!!ቅድመ-ምርመራ ህይወትን ያድናል! እርስዎም መጥተው ይመረመሩ፤ ለወዳጅ ዘመድዎም ይህንን ጥሪ በማጋራት (Share) የዜግነት ድርሻዎን ይወጡ!

‎ #ጋዘር

‎ስኬታማ የውጤት ዓመት እና አዲስ ምዕራፍ!‎‎    ነሐሴ 4/2018_ጋዘር‎‎የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 ዕቅድ ትውውቅ በጋራ...
10/08/2026

‎ስኬታማ የውጤት ዓመት እና አዲስ ምዕራፍ!

‎ ነሐሴ 4/2018_ጋዘር

‎የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 ዕቅድ ትውውቅ በጋራ አካሄደ!

‎ዛሬ ነሐሴ 4/2018 ዓ.ም የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

‎በግምገማውም በሁሉም የሥራ ክፍሎች የታየው አፈጻጸም በጣም አበረታች እና ስኬታማ እንደነበር የተገመገመ ሲሆን፣ በተለይም በእናቶች እና ሕፃናት ጤና አገልግሎት ዘርፍ የተመዘገበው ውጤት አስደናቂ ነበር፦
‎✍️የሆስፒታሉ የጥራት ማሻሻያ ክፍል ኃላፊ አቶ ተፈራ አዳሙ አድስ Project title ንድፍ ለማንጅሜንቱ አቅርቧል።ቀጣይ በ5 ወር ውስጥ በHIV Risk Assessment Tool's ላይ ለመሥራት ለማንጅሜንቱ ቀርቧል።
‎✍️በዚህ 2018 የማህበረሰብ በጎ(Social service)ተግባር ለ 23 አቅሜ ደካማ ታካሚዎች ሙሉ ወጪያቸውን ሸፍኖ አገልግሎት ሰጥቷል።ከ24000ብር በላይ በገንዘብ እንደተረዱ የሆስፒታሉ ሜድካል ዳይረክተር ዶክተር ወንድሙ ገዛኸኝ ለማንጅሜንቱ አቅርቧል።
‎የወሊድ ሽፋን፦በዓመቱ 1,595 እናቶች በሰላም የተገላገሉ ሲሆን፣ ይህም የታቀደውን ከ100% በላይ ማሳካት የተቻለበት ትልቅ ስኬት ነው!
‎🏥 የቀዶ ጥገና አገልግሎት፦280 እናቶች በቀዶ ጥገና ህክምና የወሊድ አገልግሎት አግኝተው በሰላም ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል። በስተመጨረሻም
‎የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ያዕቆብ ጥላሁን በዓመቱ ሙሉ በትጋት፣ በቁርጠኝነት እና በቅንነት ለህብረተሰቡ አገልግሎት ሲሰጡ ለነበሩ የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያዎች እና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በሙሉ የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

‎"የሕዝባችንን ጤና ለመጠበቅ የምናደርገው ጉዞ በ2019 በጀት ዓመትም በተሻለ ቁርጠኝነት እና ጥራት ተጠናክሮ ይቀጥላል!"


‎ለህብረተሰባችን ጤና እና ደህንነት ሁልጊዜም በትጋት እንሰራለን!

በጋዘር ከተማ የተከናወነው "አዎንታዊ ምድጃ" (PD/Hearth) እና የትኩረት ነጥቦቹ! ‎‎በትላንትናው ዕለት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን ጋዘር ከተማ አስተዳደር (በአይዳ እና ዞምባ ...
05/08/2026

በጋዘር ከተማ የተከናወነው "አዎንታዊ ምድጃ" (PD/Hearth) እና የትኩረት ነጥቦቹ!

‎በትላንትናው ዕለት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን ጋዘር ከተማ አስተዳደር (በአይዳ እና ዞምባ ቀበሌዎች) ከወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ እና ከደቡብ አሪ ወረዳ ጤና ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር የተካሄደው የ PD/Hearth (አዎንታዊ ምድጃ) የምረቃ ፕሮግራም ትልቅ ተስፋን ያበሰረ ክስተት ነው።

‎ይህ በምረቃው ላይ የተገለጸው የ PD/Hearth ስራ በስነ-ምግብ sector ውስጥ ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ ሳይንሳዊ እና ማህበረሰብ አቀፍ አሰራር ሲሆን፣ ዋና ዋና ፅንሰ-ሀሳቦቹ (Core Concepts) የሚከተሉት ናቸው፡

‎"በእጃችን ባለው ሀብት ህፃናትን ጤናማ ማድረግ ይቻላል!"
‎በማንኛውም ማህበረሰብ ውስጥ አብዛኞቹ ቤተሰቦች በኢኮኖሚ እጥረት ምክንያት ልጆቻቸው ለምግብ እጥረት (Malnutrition) ሲጋለጡ፣ በተመሳሳይ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ ሆነው ነገር ግን ልጆቻቸውን ጤናማ እና ብሩህ አድርገው የሚያሳድጉ ጥቂት "አዎንታዊ ልዩነት" ያላቸው እናቶች አሉ።

‎ይህ አሰራር ከእነዚህ እናቶች መልካም ልምድ በመቅሰም፣ ውድ የሆኑ ምግቦችን ሳይሆን በአካባቢ የሚገኙ እህሎችንና ምግቦችን (Dietary Diversification) proper መንገድ አቀናጅቶ በማብሰል ህፃናትን ከቀጨጫ (Stunting) እና ከተመጣጠነ ምግብ እጥረት መታደግ እንደሚቻል ያሳያል።

‎ አዎንታዊ ምድጃ (The Hearth)
‎"የተግባር ልምምድ እና የማህበረሰብ አንድነት!"

‎"ምድጃ" ሲባል እናቶች እና የህፃናት ተንከባካቢዎች በአንድ አቅራቢያ በሚገኝ መኖሪያ ቤት ወይም ማዕከል ለ 10 እስከ 12 ተከታታይ የሚሰበሰቡበት ቦታ ነው።

‎በዚህ ቦታ እናቶች በፅንሰ-ሀሳብ ብቻ ሳይሆን በተግባር ገንፎ እና ሌሎች ጤናማ ምግቦችን አብረው ያዘጋጃሉ፣ ህፃናቱን ያበላሉ።
‎ከምግብ ዝግጅት ጎን ለጎን ስለ ፅዳት አጠባበቅ፣ ስለ ምግብ አመጋገብ እና ስለ ጤና ጥበቃ ልምድ ይለዋወጣሉ።


‎የዚህ ፕሮግራም ዘላቂ ጥቅም (Sustainability)

‎እንደ ጋዘር ከተማ አስተዳደር ባሉ ቀበሌዎች የተካሄደው ይህ የ 12 ቀን ተግባራዊ ልምምድ፣ እናቶች በቤታቸው ውስጥ የምግብ አዘጋጀት ባህሪያቸውን እንዲቀይሩ (Community Social Behavioral Change - CSBC) ትልቅ በር ይከፍታል። ይህም የውጭ እርዳታን ሳይጠብቁ ማህበረሰቡ በራሱ አቅም የነገ ተተኪ ህፃናትን ጤና እንዲታደግና ዘላቂ ለውጥ (Sustainability) እንዲያመጣ ያስችለዋል።
‎ለጋዘር ከተማ አስተዳደር፣ ለደቡብ አሪ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት፣ ለወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ እንዲሁም ለሰለጠናችሁ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች እና የጎጥ ጤና መሪዎች (VHL) ለሰራችሁት ድንቅ ስራ የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ያመሰግናችኋል።

‎በተጨማሪም በሌሎች ክላስተሮች (በርካ፣ ቶልታ እና ቴምበል) ያላችሁ ባለሙያዎች ይህንን መልካም ተሞክሮ ወደ ተግባር በመቀየር የነገ ሀገር ተረካቢ ህፃናትን ከምግብ እጥረት እንታደግ! 🌾

‎ #ጋዘር #አሪዞን #የህፃናትጤና #የስነምግብለዉጥ

‎🌿 በጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል 'ተስፋን እንተክላለን' በሚል መሪ ቃል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በታላቅ ስኬት ተከናወነ! 🌿‎‎ዛሬ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረ...
03/08/2026

‎🌿 በጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል 'ተስፋን እንተክላለን' በሚል መሪ ቃል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በታላቅ ስኬት ተከናወነ! 🌿

‎ዛሬ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ "ተስፋን እንተክላለን" በሚል መሪ ቃል በተካሄደውና በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመተከል ታሪካዊ መርሃ ግብር፤ የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ማህበረሰብ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ አሻራውን አኖሯል።

‎በዚሁ ታላቅ ሀገራዊ ጥሪ መሰረት በጋዘር ከተማ አስተዳደር በሚገኘው የሆስፒታላችን ግቢና ዙሪያ፡

‎* የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞች፣
‎* በሆስፒታሉ በተግባር ልምምድ (Practice) ላይ የሚገኙ የኮሌጅ ጤና ተማሪዎች፣
‎* ህክምናቸውን በመከታተል ላይ ያሉ ታካሚዎች እና የታካሚ አስታማሚዎች በጋራ በመሆን 400 የግራቬላ (Gravillea) ችግኞችን በተሳካ ሁኔታ ተክለዋል።

‎ይህ ህይወትን የማዳን ቅዱስ ተግባር አካል የሆነው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር፣ ለአካባቢያችን አየር ንብረት ጥበቃና ለፅዱ የህክምና መፈጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል።

‎ተክለን ለማፅደቅና አረንጓዴዋን ኢትዮጵያ ለትውልድ ለማስተላለፍ የጀመርነውን ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለን!

‎"የጤናችን ዘላቂነት ለአካባቢያችን ጥበቃ!"

‎ #የአረንጓዴአሻራ #ተስፋንእንተክላለን #ጋዘርመጀመሪያደረጃሆስፒታል

"በጎ ፈቃደኝነት ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር አበርክቶው የጎላ ነው!”                            አቶ ናፍቆት ብርሃኑ   ምክትል ቢሮ ኃላፊና የህክምና አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ“...
28/07/2026

"በጎ ፈቃደኝነት ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር አበርክቶው የጎላ ነው!”

አቶ ናፍቆት ብርሃኑ
ምክትል ቢሮ ኃላፊና የህክምና አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ

“በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በማለት የክረምት በጎ ተግባር ማስጀመሪያ ፕሮግራም በወላይታ ዞን ጠበላ ከተማ ተካሄደ።

ሐምሌ 21/2018 ዓ.ም ጤና ቢሮ ኮሚኒኬሽን | ጂንካ
_____________

የጠበላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ታረቀኝ ገቸሬ (ዶ/ር) የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት ከተማ አስተዳደሩ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት በዞኑ ሞዴል መሆኑን ጠቅሰዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የሕክምና አገልግሎቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ናፍቆት ብርሃኑ በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በጎ ፈቃደኝነት ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር አበርክቶው የጎላ መሆኑን ጠቁመዋል።

ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የህብረተሰባችን ስውር ጠላቶቻችን ናቸው ያሉት ኃላፊው እነዚህ በሽታዎችን በምርመራ በማወቅ ተቆጣጠጥረን መኖር እንችላለን ሲሉም ጠቁመዋል።

የዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በቅድመ ምርመራ ላይ ያተኮረ መሆኑን የገለፁት አቶ ናፍቆት በዚህም 50 ሚሊዮን ብር የሚገመት የቅድመ ምርመራ አገልግሎት ለማድረግ መታቀዱንም አብራርተዋል።

የአከባቢው ማህበረሰብ በጠበላ አጠቃላይ ሆስፒታል የተጀመረው የነፃ ህክምና አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑም አቶ ናፍቆት አሳስበዋል።

በ2018 የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ2000 በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና በማድረግ እይታቸው እንዲመለስ ተደርጓል ሲሉም ጠቁመዋል።

የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳዊት ደሳለኝ በበኩላቸው ጥራቱን የጠበቀ ፍትሃዊና ተደራሽ የሆነ የጤና አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለማድረስ በተሰራ ስራ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል።

ተቋሙ ወጣቶችን በማስተባበር ጊዜያቸውን ገንዘባቸውንና ጉልበታቸውን ለህብረተሰቡ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲሰጡ እያደረገ ይገኛል ሲሉም ጠቁመዋል።

በ2018 በጀት ዓመት በዞኑ የሚገኙ ሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ከ474 ሺህ 765 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በማሳተፍ 812 ሺህ 440 የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ኃላፊው ጠቁመዋል።

በዚህም ከ25 ሚሊዮን 851 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ሀብት ማዳን ተችሏል ሲሉ የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳዊት ደሳለኝ አብራርተዋል።

በመርሃ ግብሩ ነፃ ምርመራ፣ የችግኝ ተከላ፣ የደም ልገሳ፣ የጠበላ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጉብኝትም ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

በመድረኩ የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች፣ የዞን እና የሪጂዮ ፖሊስ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ኃላፊዎች፣ ተጠሪ ተቋማት ሥራ አስኪያጆች፣ የሆስፒታል አስኪያጆች እና ተጋባዥ እንግዶች ተሳትፈዋል።

‎ በጋዘር ከተማ አስተዳደር ሰፊ የህክምና ዘመቻ ተጀመረ!‎‎   ሐምሌ 13/2018_ጋዘር‎‎ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን በጋዘር ከተማ አስተዳደር ጤና ዩኒት አስተባባሪነት፣ ዕድሜያቸው...
20/07/2026

‎ በጋዘር ከተማ አስተዳደር ሰፊ የህክምና ዘመቻ ተጀመረ!

‎ ሐምሌ 13/2018_ጋዘር

‎ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን በጋዘር ከተማ አስተዳደር ጤና ዩኒት አስተባባሪነት፣ ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በላይ ለሆኑ ሕፃናትና ለአዋቂዎች በሙሉ የሚሰጥ የኦንኮሰርኪያሲስ (Onchocerciasis / የናይል ዓይነ ስውርነት) በሽታ መከላከያ መድኃኒት ዕድል ዘመቻ በይፋ ተጀምሯል።

‎ 📅 የዘመቻው የጊዜ ሰሌዳ፦

‎ይህ እጅግ ወሳኝ የሆነ የህዝብ ጤና ጥበቃ ዘመቻ ከሐምሌ 13 እስከ ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ለ10 ተከታታይ ቀናት በከተማው አስተዳደር ስር በሚገኙ ሁሉም አካባቢዎች ይካሄዳል።
‎ 🩺 በዘመቻው ወቅት የሚከናወኑ ተጨማሪ ነጻ የህክምና አገልግሎቶች፦

‎በጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች አማካኝነት የመድኃኒት ዕድሉ ብቻ ሳይሆን የሚከተሉት ተጓዳኝ የጤና አገልግሎቶች በጥምረት ይሰጣሉ፦

‎1. የዓይን ሕመም ምርመራና ሕክምና፦የዓይን ጤና ችግሮችን የመለየትና የክትትል ሥራ።
‎2. የወባ ወረርሽኝ መከላከልና ቁጥጥር፦ የወባ ስርጭትን ለመግታት የሚያስችሉ የግንዛቤና የህክምና ሥራዎች።
‎3. የማህፀን ጫፍ ካንሰር ቅድመ-ምርመራ (ልየታ)፦ ለእናቶችና እህቶች የሚሰጥ ወሳኝ የቅድመ-ካንሰር መከላከያ ልየታ።
‎4. ሌሎች ተጓዳኝ የጤና አገልግሎቶች፦ አጠቃላይ የጤና ምክርና የቤት ለቤት የጤና ኤክስቴንሽን ጥቅል ሥራዎች።

‎🎤 የጋዘር ከተማ አስተዳደር ጤና ዩኒት ያስተላለፈው ጥሪ፦

‎"ጤናማ ማህበረሰብ ለተሟላ ልማት መሰረት ነው! የጋዘር ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች በሙሉ፣ ይሄንን ወርቃማ ዕድል በመጠቀም ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በላይ የሆኑ ሕፃናትንና ቤተሰቦቻችሁን በመያዝ፣ በአቅራቢያችሁ በሚገኙ የጤና ኬላዎችና በተዘጋጁ ጣቢያዎች በመገኘት መድኃኒቱን እንድትወስዱና ተጓዳኝ የሕክምና አገልግሎቶችን እንድትጠቀሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።"

‎"በጋራ እንከላከል፤ ጤናችንን እንጠብቅ!"

‎የጋዘር ከተማ አስተዳደር ጤና ዩኒት
‎📍 ጋዘር፣ አሪ ዞን፣ ደቡብ ኢትዮጵያ

‎ማሳሰቢያ፦ ይህንን መልዕክት ሼር በማድረግና ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት የዜግነት ድርሻዎን ይወጡ!

‎🩸 "የአንድ ሰው ደግነት የሌላውን ሰው ህይወት ይታደጋል፤ ደም እንለግስ፣ ህይወትን እናትርፍ!" 🩸‎   ‎      ሀምሌ 11/2018_ድመካ‎‎በአሁኑ ወቅት በአካባቢያችን (በዞናችን) በተከ...
18/07/2026

‎🩸 "የአንድ ሰው ደግነት የሌላውን ሰው ህይወት ይታደጋል፤ ደም እንለግስ፣ ህይወትን እናትርፍ!" 🩸

‎ ሀምሌ 11/2018_ድመካ

‎በአሁኑ ወቅት በአካባቢያችን (በዞናችን) በተከሰተው ከፍተኛ የወባ በሽታ ስርጭት ምክንያት በርካታ ወገኖቻችን፣ በተለይም አገር ተረካቢ ህጻናት እና ነፍሰጡር እናቶች ለከፍተኛ የደም ማነስ ችግር እየተዳረጉ ይገኛሉ። ወባ የሰውን ልጅ የደም ሴሎች በፍጥነት የሚያጠፋ በሽታ በመሆኑ፣ ታካሚዎቻችን ከበሽታው አገግመው ወደ ህይወት ለመመለስ በአስቸኳይ የደም ልገሳ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።

‎በሆስፒታላችን አልጋ ላይ ተኝተው የርስዎኑን ደም የሚጠባበቁት የነገ አገር ተረካቢ ህጻናት እና በወሊድ ምክንያት ደም የፈሰሳቸው እናቶች ናቸው። የአንድ እናት ህይወት ማለፍ የቤተሰብ መፍረስ ነው፤ የአንድ ህጻን ህይወት መጥፋት የነገ ተስፋ መቅጨት ነው።
‎ይህንን የደም እጦት ጫና የምንቀንሰው ደግሞ እኔና እናንተ ስንረባረብ ብቻ ነው!

‎ ደም መለገስ ለምን አስፈለገ?

‎* ፋብሪካ የሌለው ህይወት፡ ደም በላብራቶሪ ወይም በፋብሪካ የማይመረጥ፣ ሰው ለሰው ብቻ ሊሰጠው የሚችል የፈጣሪ ውድ ስጦታ ነው።
‎* ጊዜው አሁን ነው፡በወባ ምክንያት የሚከሰት የደም ማነስ ሰዓታትን አይጠብቅም። ዛሬ የሚለገስ አንድ ከረጢት ደም የነገዋን እናት እና ህጻን በህይወት ያቆያል።
‎* ለራስም ጤንነት ነው፡ ደም መለገስ ለተቀባዩ ብቻ ሳይሆን ለሚለግሰውም ሰው አዲስ የደም ሴሎች እንዲተኩ በማድረግ የልብና የደም ዝውውር ጤንነትን ያሻሽላል።

‎🎯 ማሳሰቢያ፡ ማን ደም መለገስ ይችላል?
‎* እድሜው ከ18 እስከ 65 ዓመት የሆናችሁ፣
‎* ክብደትዎ ከ45 ኪሎ ግራም በላይ የሆነ፣
‎* በማንኛውም ተላላፊ በሽታ ዙሪያ ስጋት የሌለባችሁ እና በአሁኑ ወቅት ጤንነታችሁ የተሟላ ሙሉ ዜጎች።

‎📞 የት መጥተን እንለግስ?
‎ለበለጠ መረጃ፡ 👉+251916399883,+251916856995 ይደውሉ።

‎ ✍️የ2019 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት እንደ ሆስፒታላችን ቀጣይ ነሀሴ ወር ውስጥ የደም ልገሳ ፕሮግራም በሆስፒታሉ ሰራተኞች ይኖራል።

‎እናቶች በደም እጦት እንዳይሞቱ፣ ህጻናት ያለጊዜያቸው እንዳይቀጠፉ ሁላችንም በአንድነት እንረባረብ! ሼር በማድረግ ለሌሎችም አድርሱ!

‎ለህሊናችን እና ለጤናዎ እንተጋለን!

በጋዘር ከተማ አስተዳደር የጋዘር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት የምግብ ቤቶች ጽዳትና ውበት ስራዎችን ክትትልና ድጋፍ መጀመራቸውን አሳወቁ።         ሐምሌ 10/2018 ዓ/ም       ...
17/07/2026

በጋዘር ከተማ አስተዳደር የጋዘር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት የምግብ ቤቶች ጽዳትና ውበት ስራዎችን ክትትልና ድጋፍ መጀመራቸውን አሳወቁ።

ሐምሌ 10/2018 ዓ/ም
ጋዘር
የጋዘር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት የምግብ ቤቶች ጽዳትና ውበት ክትትል ስራ በዛሬው ቀን በይፋ የተጀመረ ስሆን፦ ከዚህ ቀደም ክትትልና ድጋፍ ባደረጉት መሰረት ለምግብ ቤቶች አስተያየት እና ግንዛቤ ባስቀመጡት መሰረት ዛሬ የክትትልና ድጋፍ ግብረሃይሉ መውጣታቸውን አሳውቀዋል።

በዚህም መሰረት ከተማዋን የተሻለ እና ለተመጋቢ ግለሰቦች ምቹ እንድሆን እየተሰራ ስሆን፦ ምግብ የሚያዘጋጁ የምግብ ቤት ባለቤቶችና ባለሙያዎች የሚሰጡትን አስተያየት በመቀበል ተግባራዊ እንድያደርጉ ከትትል የወጡት የጠና ባለሙያዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ።
ምንጭ፦የጋዘር ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚውንኬሽን

Address

Jinka Gazer
Jinka

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gazer Primary Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share