15/05/2026
የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ የwk19/2026 PHEOC መገምገሙን እና የወባ ወረርሽኝን ለመግታት ድጋፍና ክትትል ቡድን ማሰማራቱን አስታወቀ፣
ጂንካ_ግንቦት 7/2018 ዓ/ም (ኣዞጤመ)
በ19ኛ ሳምንት PHEOC በተገመገመበት ወቅት የወባ በሽታ 2429 ሰው በበሽታው ተይዘው የሕክምና አግልግሎት ማግኘታቸው ተገምግሟል።
ከፍተኛ የወባ ጫና ያለባቸው መዋቅሮችን በመለየት ልዩ ድጋፍና ክትትል ቡድን በማዋቀር ወደስራ የተገባ ሲሆን በጂንካ ከተማ ፣ በደቡብ ኣሪ ፣ በባካ ዳውላ እና በጋዜር ከተማ ጫናው ከፍ ማለቱን በማንሳት በእነዝሁም ወረዳዎች የተመደቡ የድጋፍ ቡድኖች ከዛሬ ጀምሮ ትግበራ መጀመራቸውን አመላክተዋል ። በቀሪ መዋቅሮችም የመከላከያ መንገዶች እንድተገበሩ እና የታመሙት የፈወቀስ ሕክምና እንድያገኙ በሁሉም መዋቅር በትኩረት እንድሰራ ያሳሰቡት የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ በድሉ ባጊማስ ነቸው።
በተጨማሪም የባካዳውላ ወረዳ የዞኑ ደጋፊዎች ወደ ወረዳው እየተንቀሳቀሱ ሲሆን በዛሬው ውሎ በጤና ጽ/ቤት ማኔጅመንት ጋር በመወያየት በወባማ ቀበሌዎች የጽ/ቤት ደጋፊዎች በመመደብ እና ከጤና ጣቢያው ባለሙያዎች ጋር በመተባበር በቀጣይ 1 ሳምንት በዘመቻ መልኩ የወባ መከላከል ንቅናቄ እንድሰራ በመግባባት ተጠናቋል ።
በመጨረሻም በወረዳው አስተዳደር በመገኘት ከባካ ዳውላ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሠረት ቦጋለ ጋር የዞኑ ደጋፊዎች የመከሩ ሲሆን በመጨረሻም በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ተደርሷል ።
1, በወረዳው ባሉ ወባማ ቀበሌዎች ከሚገኙ የቀበሌ አስተዳዳሪዎች እና የወረዳ ደጋፊዎች ጋር በመሆን የንቅናቄ መድረክ ግንቦት 10/2018 እንደሚደረግ
2, ዘመቻው በወረዳ ኮማንድ ፖስት በየቀኑ እንድገመገም
3 በቀበሌ ደረጃ የንቅናቄ ሥራዎች በልዩ ዲስፒሊን እንድመራ እና
4, ለሕሙማን የፈውስ ሕክምና ለመስጠት አስፈላጊ ግብዓቶች እንድሟሉ በአስተዳደር ደረጃ በተቻለው መጠን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ገልጸዋል ።
በመጨረሻም ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል የወባ በሽታ ወረርሽኝን ለመከላከል በትኩረት የራሱንና አካባቢውን ጽድት በመጠበቅ ለወባ ትንኝ መራቢያ ምቹ ቦታዎችን እንድያስወግዱ አቶ መሠረት ቦጋሌ የባካ ዳውላ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ጥሪ በማስተላለፍ ውይይቱን አጠቃለዋል ።
በሽታው በወረዳው ስር ከምገኙ ከ12ቱ ቀበለያት በግስቴ፣ ካይሣ፣ ባያሞር፣ አርክሻ ፣ አሊ እና ጌዛ ቀበሌዎች ላይ በወረርሽኝ መልክ መከሰቱን የጠቆሙት የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ኃላፊው አቶ አባቴ ባማይ ናቸው።
// የዜጎች ጤና ለሀገር ብልጽግና//
የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ ሚከተሉትን ገጾች Follow በማድረግ እንድከታተሉን እንጋብዛለን ።
ተለግራም https://t.me/AariZoneHealthDepartment
tiktok.com/
https://www.facebook.com/profile.php?id=61565064929502