Dobi Medium Clinic

Dobi Medium Clinic Am Health profesion man

Emmregency care with causes
07/04/2025

Emmregency care with causes

29/04/2024

ቀን 21/08/16ዓ.ም
ለስራ ፈላጊዎች
ክፍት አስቸኳይ የስራ ማስታወቂያ
የስራ መጠሪያ:- ሬዳት ነርስ (Assistant Nurse)
ተፈላጊ ችሎታ :-በደረጃ 4 ክሊኒካል ነርስንግ የተመረቀ/ች ስኦስ ያላት/ለው የስራ ልምድ ያለው ብሆን ይመረጣል
የስራ ቦታ :-ቡለን ወረዳ ዶቢ ቀበሌ
የድርጅቱ ስም :-ዶቢ መካ/ክሊኒክ
የስራው ሁኔታ:- በኮንትራት
ደመወዝ :-በስምምነት
ለበለጠ መረጃ ስልክ:-+251917622228 ይደውሉ።
follow fb

ኒሞንያ ወይም የሳንባ ምች(pneumonea) በሳንባ ውስጥ የአየር ከረጢቶች አሉ። እነዚህ ከረጢቶች በተዋህስያን ሲጠቁ ኒሞንያ ይባላል። መገለጫውም የአየር ከረጢቶቹ በፈሳሽ ወይም በመግል መሳ...
26/04/2024

ኒሞንያ ወይም የሳንባ ምች(pneumonea)

በሳንባ ውስጥ የአየር ከረጢቶች አሉ። እነዚህ ከረጢቶች በተዋህስያን ሲጠቁ ኒሞንያ ይባላል። መገለጫውም የአየር ከረጢቶቹ በፈሳሽ ወይም በመግል መሳይ ፈሳሽ ስለሚሞሉ የሚከተሉትን ምልክቶች ያንፀባርቃሉ።

1. ሲስሉ ወይም ሲተነፍሱ የደረት ህመም
2. ሳል3. ድካም
4. ትኩሳት፡ ላብ፡ ብርድ ብርድ ማለት
5. የትንፋሽ ማጠር
6. ማቅለሽለሽ፡ ማስታወክና ሸርተቴ
7. የምግብ ፍላጎት መቀነስ

ምክንያቶቹ
• ባክቴሪያ ወይም ቫይረስ ወይም ፈንገስ ወደ ሳንባ ሲገባ
• በሽታ የመከላከል አቅም ሲቀንስ• በእድሜ መጨመር
• ህፃናት መሆን
• ሆስፒታል ብዙ ለብዙ ቀናት መተኛት
• ማጤስ
ማሳሰቢያ፡ ኒሞንያ ከቅዝቃዜ ጋር ይያያዛል ወይ ብላችሁ ለምትጠይቁ መልሱ አዎ ነው። በተለይ ለህፃናትና አዛውንቶች በብርድና ቅዝቃዜ ወቅት የመተንፈሻ ቱቦ እንቅስቃሴ ስለሚገደብ ቱቦውና የአየር ከረጢቶቹ በዝልግልግ ፈሳሽ ይሞላል። ይህ ደግሞ ለተዋህስያን መራቢያ በጣም አመች ይሆናል።
እንድህ አይነት የጤና ምክሮች እንዲደርሳችሁ የfb ገፃችንን Dobi Medium Clinic አድርጉት

አልማዝ ባለጭራ(Herpes zoster)ጉድፍ የሚባል በብዛት ልጆችን የሚያጠቃ ቯሪሴላ ዞስተር በተባለ ቯይረስ የሚከሰት ህመም ሲድን ነርቭ ውስጥ ተደብቆ ይቆይና ሰውነታችን በሚጎዳበት ጊዜ ቫይ...
26/04/2024

አልማዝ ባለጭራ(Herpes zoster)
ጉድፍ የሚባል በብዛት ልጆችን የሚያጠቃ ቯሪሴላ ዞስተር በተባለ ቯይረስ የሚከሰት ህመም ሲድን ነርቭ ውስጥ ተደብቆ ይቆይና ሰውነታችን በሚጎዳበት ጊዜ ቫይረሱ በድጋሚ ተመልሶ ተባዝቶ ሲወጣ አልማዝ ባለጭራ ያመጣል::
አጋላጭ ነገሮች
- በኤች አይ ቪ ወይም በሌሎች ምክንያቶች የበሽታ መከላከል ዐቅም መቀነስ
- የዕድሜ መግፋት በተለይ ከ60 ዐመት ብሀላ
- ሴት ፆታ
- ጭንቀት ወይም stress
- አልኮል መጠቀም ማብዛት
- የወጣበት ቦታ ላይ ቀደም ብሎ ኦፕራሲዮን ተደርጎ ወይም አካላዊ ጉዳት ደርሶ ከሆነ
- 20 % የሚሆነው ያለምንም አጋላጭ ነገር ሊከሰት ይችላል
ምልክቶች
- በብዛት ውሀ የቋጠሩ አንዳንዴም ያልቋጠሩ አንድ ቦታ ላይ ሰብሰብ ያሉ ትንንሽ ሽፍታወች
- ሽፍታወቹ የሚወጡት ከሰውነታችን መሀል አካፋይ በግራ ወይም በቀኝ በኩል ሆኖ የሰውነታችንን መሀል አያቓርጡም
- ውጋት ወይም ማቃጠል ያለው ከባድ ህመም በተለይ ዕድሜያቸው የገፋ ሰወች ላይ ይብሳል
ህክምና
- በልምድ ወይም በባህል ዘመናዊ ህክምና በሽታውን ይደብቀዋል የሚባለው የተሳሳተ አመለካከት ነው
- ሽፍታው በሂደት በራሱ ቢጠፋም አሳይክሎቪር የሚባል ፀረ- ቫይረስ መድሀኒት መውሰድ ቶሎ እንዲጠፋ ያደርገዋል
- በዋናነት ትኩረት ተሰጥቶ መታከም ያለበት በሽታው የሚያመጣው የውጋት ህመም ነው
- የተለያዩ የነርቭ ህመምን የሚያስታግሱ በተለምዶ ከምንጠቀምባቸው የህመም ማስታገሻወች ለየት ያሉ መድሀኒቶች ከ1 ወር - 3 ወር መወሰድ አለባቸው

, like, share and comment DobiMediumClinic

የ ሰንፈተ ወሲብ መንስኤዎች ..ለሰንፈተ ወሲብ ሊያጋልጡ ይችላሉ  ተብለው በጥናት የተረጋገጡ መንሰኤዎችን የተወሰኑትን እንጠቁማችሁ ። ሰንፈተ ወሲብ ሲባል ..ቶሎ መርጨት..ፍላጎት ለማጣት ....
25/04/2024

የ ሰንፈተ ወሲብ መንስኤዎች ..
ለሰንፈተ ወሲብ ሊያጋልጡ ይችላሉ ተብለው በጥናት የተረጋገጡ መንሰኤዎችን የተወሰኑትን እንጠቁማችሁ ።
ሰንፈተ ወሲብ ሲባል ..ቶሎ መርጨት..ፍላጎት ለማጣት ..ና የብልት አለመጠንከር ከምክኒያቶች ውሰጥ በዋናነት ይጠቃሳሉ ።
ለነዚህ ችግሮች እንደ መንሰኤ የሚጠቀሱት ..
1,,ራስን በራስ ማርካት /ሴጋ /
2..ጭንቀት / በሕይወት የሚያጋጥሙን ማኀበራዊ ና ኢኮኖሚ ቀውስ /
3..እንቅልፍ በበቂ ሁኔታ አለመተኛት
4..ጫት መቃም
5..የአልኮል መጠጥ ማብዛት
6..የክብደት መጨመር
7..ሴክስ ፊልም ለረዥም ግዜማየት ..
8.ፍርሃት /ከአስተዳደግ ጋር የሚያያዝ /
9 ሜዲካል ችግሮች ..የሰኳር ሕመም ..የልብ ሕመም ..የወገብ ሕመምና የደም ብዛት ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው ።
10 ማጪስ /ሲጋራና ና አሸሽ /
በሰንፈተ ወሲብ የተጠቃ አንድ ግለሰብ የችግሩን መንሻ ካወቀና ችግሩን ለመቅርፍ ተነሳሽነትና ትዕግስት ካለው ችግሩን በመድኃኒትና በሚደረግለት የሳይኮ ትራፒ አማካኝነት ችግሩ ሙሉ ለሙሉ መቅረፍ ይቻላል ።
ከዕድሜ ና ከሜዳካል ችግር የተያያዙ ከሆነ የሜዳካል ሕክምናን ከሰነ ልቦና ምክር በማግኘት ማሰተካከል ይቻላል
👉 DobiMediumClinic.com /page

15/04/2024

የኩላሊት ጠጠር (Nephrolithiasis) ምንድን ነው?

ብዙዎቻችን ውሀን የመጠጣት ባህላችን በጣም ዝቅ ያለ ነው። ይህ ልምድ ደሞ ብዙ መዘዝን ይዞብን ምጣቱ አይቀሬ ነው።

አንድ ወንድማችን "ኩላሊቴ በጠጠር ምክንያት ፈሳሽን ሙሉ ለሙሉ ማስወገድ አልቻለም እና ሀኪሞቹ አሁን መውጣት አይችልም ፣ ገና ነው የሚል መልስ ነው የሰጡኝ ፣ እና ለምንድን ነው" የሚል ጥያቄ አንስቶልኝ ነበር።

የኩላሊት ጠጠር በአብዛኛው ጊዜ 80% በውስጡ ካልሺየም ኦግዛሌት (calcium oxalete) የተቀሩት ደግሞ ከካልሺየም ፍስፌት (calcium phosphate) ፣ ዩሪክ አሲድ (uric acid) ፣ ሲስቲን (cystine) ሊሰሩ ይችላሉ።

የኩላሊት ጠጠር በአብዛኛው በአንድ ኩላሊት በኩል ይታያል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በሁለቱም ኩላሊት ሊኖር ይችላል።

ለኩላሊት ጠጠር የሚያጋልጡን ነገሮችስ?

ለኩላሊት ጠጠር የመጋለጥ እድላችን የሚወሰነው ሽንት በተሰራበት (composition) ለምሳሌ በካልሼየም ኦግዛሌት የተሰራ ጠጠር ከሆነ በሽንት ወስጥ የሚገኝ ከፍተኛ መጠን ካልሺየም እና ኦግዛሌት ሲኖር እንዲሁም ዝቅተኛ ካልሽየም እና ፖታሺየም መውሰድ እና ፈሳሽ ነገር ያላቸው ምግቦች አለማዘውተር እንዲሁም ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከስኳር የተሰሩ ጣፋጭ መጠጦች ተጋላጭነተን ይጨምረዋል ተብሎ ይታሰባል።

ሌሎች አጋላጭ ምክንያቶች ለምሳሌ አንድ ሰው ከዚህ በፊት የኩላሊት ጠጠር ከነበረበት ድጋሚ የመመለስ እድል ሊኖረው ይችላል። ከዚህ በተጨማሪ በዘር (በቤተሰብ) ወስጥ ጠጠር ያለበት ካለ ፣ በተደጋጋሚ የላይኛው የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ተጠቂ መሆን ፣ መድሀኒቶች ለምሳሌ Idinavir, Acyclovir, Sulfadiazine፣ መድሀኒቶችን ከሚገባው መጠን በላይ መውሰድ፣ ከመጠን በላይ ውፍረት፣ ከመጠን በላይ በፕሮቲን እና Vitamin C የበለፀጉ ምግቦች መመገብ ፣ ከከመጠን በላይ የሰውነት እንቅስቃሴ ለምሳሌ የማራቶን ሯጮች ፣ ደም ግፊት ፣ ስኳር ፣ ሪህ ችግር ያለባቸው ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ።

ምልክቶቹስ?
- በአብዛኛው ከ20-60 ደቂቃ ሄድ መጣ የሚል ህመም በጎናችን አካባቢ ሊሰማን ይችላል። ህመሙ በጣም ሀይለኛ ውጋት ፣ ቁርጠት ስለሆነ ህመምተኛው የመንቆራጠጥ ነገር ሊያሳይ ይችላል።

አንዳንዴም ህመሙ እስከ ሽንት ፌኛ አካባቢ ሊደርስ ይችላል። ይህም አንደ ጠጠሩ ያለበት ቦታ ይወሰናል። ከዚህ በተጨማሪ የሽንት ቀለም ወደቀይነት (ደም) መቀላቀል ፣ ማቅለሽለሽ ፣ ማስመለስ ፣ ሽንት ማጥ ፣ ሽንት ማጣደፍ ሊኖር ይችላል።

ምርምራዎቹስ?
- ከላይ የጠቀስኳቸውን ምልክቶች በምናይበት ግዜ ቶሎ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ተገቢውን ምርመራ ማድረግ ይጠበቅብናል። የጤና ባለሙያውም እንደ አስፈላጊነቱ የተለያዩ ምርመራዎችን ለምሳሌ የሽንት ምርመራ ፣ የሆድ አልትራሳውንድ ፣ የሆድ x ray ፣ የሆድ ሲቲ ስካን ፣ ሊያዝልን ይችላል

ነፍሰ ጡር እናት ላይ ምርመራዎችን ስናዝ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅብናል። ምክንያቱም ከx-ray ፣ እና ሲቲ ስካን የሚወጣው ጨረር በተለይ ፅንሱን ሊጎዳው ስለሚችል ነው። ስለዚህ በዚህ ጊዜ አልትራሳውንድ ተመራጭ ይሆናል።

የሚያመጣውስ ችግር?
-የኩላሊት ጠጠር ካልታከመ ለኢንፌክሽን ፣ ደጋሚ ተመልሶ የመምጣት ችግር (recurrence) ፣ የሽንት ቱቦ መዘጋት ፣ ኩላሊትን ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ እስከማድረስ ሊደርስ ይችላል።

ህክምናውስ?
- አመጋገባችንን ማስተካከል
- ጠጠሩን ያመጣብን ችግር ከታወቀ ማከም
- የህመም ስሜት ላላቸው ታካሚዎች እንደ አስፈላጊነቱ የህመም ማስታገሻ ሊሰጥ ይችላል።

- ማንኛውም የኩላሊት ጠጠር በቀዶ

ዛሬ ደግም ስለ (Rabies) የብድ ውሻ በሽታ ምንነት እንነግራቹለን ?የእብድ ውሻ በሽታ'ምንድን ነው?💡ሬቢስ በተባለ ቫይረስ በተያዘ እንስሳ አማካኝነት ወደ ሰው በንክሻ ወይም በመ'ቧጨር የ...
12/04/2024

ዛሬ ደግም ስለ (Rabies) የብድ ውሻ በሽታ ምንነት እንነግራቹለን ?

የእብድ ውሻ በሽታ'ምንድን ነው?

💡ሬቢስ በተባለ ቫይረስ በተያዘ እንስሳ አማካኝነት ወደ ሰው በንክሻ ወይም በመ'ቧጨር የሚተላለፍ ሲሆን; ይህም የተጎጂውን ዋነኛ ነርቮች በማጥቃት ለህልፈት የሚዳርግ በሽታ ነው።

💡በተለምዶ የእብድ ውሻ በሽታ ይሰኛል; ይህም ዘጠና በመቶ በላይ በሽታው የሚከሰተው ቫይረሱን በተሸከሙ ውሾች አማካኝነት በመሆኑ ነው።

አንድ ሰው በውሻ ከተነከሰ ምን ያድርግ?

💡 በመጀመሪያ ተጠቂው ወደ ጤና ተቋም ማቅናት ይኖርበታል።
ይህን ማድረግ ያልቻለ ሰው ግን:-

1. ቁስሉን በውሃና በሳሙና ማጠብ; ለ15ደቂቃ ቁስሉ ላይ ውሃ ማፍሰስ

2. በመቀጠል በፖቪዶን አዮዲን ማፅዳት(ቫይረሱን የመግደል ባሕሪ አለው)

{ቁስሉን በዚህ መልኩ በማፅዳት በቫይረሱ የመያዝ እድልን 90% በላይ መቀነስ ይቻላል}

3. ውሻውን በማሰር ቢያንስ ለ10 ቀን ያክል መከታተል።
(ክትባት የወሰደ ከሆነ; ያንን ማረጋገጥ ያስፈልጋል)

4. ጤና ተቋም በመቅረብ የክትባት አማራጮችን መማከር; የቴታነስ መድሃኒት መውሰድና የቁስሉን ሁኔታ መከታተል ያስፈልጋል።
ድረገፆችን በፌስቡክ:- Medium Clinic(Follow , Share, Like and Comment) ያድርጉት

Address

Bulen Woreda, Dobi Kb
Metekel

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dobi Medium Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share