Warka Medical and Business SC - ዋርካ ሜዲካል እና ቢዝነስ አ/ማ

  • Home
  • Ethiopia
  • Motta
  • Warka Medical and Business SC - ዋርካ ሜዲካል እና ቢዝነስ አ/ማ

Warka Medical and Business SC - ዋርካ ሜዲካል እና ቢዝነስ አ/ማ ዋርካ ሜዲካልና ቢዝነስ አ/ማ በሞጣ ልጆች የተመሠረተ አጠቃላ?

28/12/2021

It is on moving to wards the goal.

የሞጣ ከተማ ት/ፅ/ቤት ምስጋና ይገባዋል፡፡ ይህ ቅንነት ለሌሎችም አርአያ ነዉ፡፡
16/09/2021

የሞጣ ከተማ ት/ፅ/ቤት ምስጋና ይገባዋል፡፡ ይህ ቅንነት ለሌሎችም አርአያ ነዉ፡፡

04/03/2021

የሙያ ፈቃድ ክራይን ይመለከታል:-
በሞጣ ከተማ አስተዳደር በቅርብ የተከፈተዉ ዋርካ የመጀመርያ ደረጃ ሆስፒታል በህክምና ሳይንስ እና በፋርማሲ የሙያ ፈቃድ (ላይሰንስ) ያላቸዉን ብቁና ተወዳዳሪ ባለሙያዎች ከታች በተዘረዘረዉ መስፈርት መሠረት አወዳድሮ የሙያ ፈቃድ መከራየት ይፈልጋል። በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ የጤና ባለሙያዎች አስፈላጊዉን መረጃ በማቅረብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
1. አስፈላጊ መረጃዎች (ዶክመንቶች)
1.1 በሙያዉ በመንግስት ስራ ላይ አለመሆኑን የሚገልፅ መልቀቂያ ማቅረብ የሚችል/ምትችል
1.2 የሙያ ፈቃድ (ላይሰንስ) ማቅረብ የሚችል/ምትችል
1.3 የትም/ት መረጃዎች የ8ኛ:የ10ኛ :12ኛ: የዲግሪ ሰርተፊኬት እና ስቱደንት ኮፒ ማቅረብ የሚችል/ምትችል
1.4 ከታወቀ ተቋም በፋርማሲ ድግሪ ወይም በህክምና ዶክትሬት የተመረቀ/ች
1.5 የዋርካ ሜዲካልና ቢዝነስ አ/ማ አባል ከሆኑ የሚበረታታ ይሆናል።
1.6 በሞጣ ከተማ ወይም በቅርብ ርቀት በግል ተቋም በስራ ላይ ያሉ ወይም በዋርካ የመጀመርያ ደረጃ ሆስፒታል ተቀጥረዉ ለመስራት ፈቃደኛ የሆኑ።
1.7 የሙያ ፈቃዱን ቢያንስ ለ6 ወር ክራይ ዉል የሚወስድ /የምትወስድና ዉሉን ማቋረጥ ሲፈልግ 6 ወር የማፈላለጊያ ጊዜ የሚሰጥ/ምትሰጥ
2. ብዛት-በህክምና ሳይንስ 1(አንድ) እና በፋርማሲ 1(አንድ)
3. ክፍያ------ተመጣጣኝ ክፍያ የሚጠይቅ ቅድሚያ ይሰጠዋል።
4. የስራ ቦታ: ዋርካ የመጀመርያ ደረጃ ሆስፒታል (ታደሰ ጉራቻ ህንፃ) ሲሆን ከአደባባይ ወደ ግብርና በሚወስደዉ ዋና መንገድ 100 ሜትር ላይ: ሞጣ ከተማ አስተዳደር።
5.የምዝገባ ጊዜ: ከየካቲት 26 ቀን እስከ መጋቢት 10 ቀን 2013ዓ.ም ድረስ ይሆናል።
6. የምዝገባ ቦታ: አበቡ መድኃኒት መደብር (ታደሰ ጉራቻ ህንፃ)።
7.ማመልከቻ: የሙያ ፈቃድ አከራዮች የሙያ ፈቃድ ወርሀዊ ክፍያን: የሚሰራበትን ተቋም ወይም በዋርካ ሆስፒታል መቀጠር እንደሚፈልግና ተቋሙና አጋር አካላት በሚፈልጉት ጊዜ ሁሉ በወቅቱ አስፈላጊዉን መረጃ እንደሚሰጥ የሚገልፅ ማመልከቻ እና ከላይ በተ.ቁ 1 (አንድ) ስር የተጠቀሱትን መረጃዎች በፖስታ በማሸግ መመዝገብ ይኖርበታል። በተጨማሪም ከፖስታዉ ደርባ ላይ የዶክመንት ዝርዝር መግለፅ አለበት።
8. ለበለጠ መረጃ +251913934164/+251921668159 በመደወል መረዳት ይቻላል።

09/02/2021

ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ዋርካ የመጀመርያ ደረጃ ሆስፒታል በጥንታዊቷ ሞጣ ከተማ በቅርብ ቀን ስራ ይጀምራል። ሆስፒታሉ በምስ/ጎጃም የመጀመርያዉ የግል ሆስፒታል ሲሆን ለሞጣ ከተማ አስተዳደር ብሎም ለዞኑ ህዝቦች የጤና ችግሮችን በከፍተኛ ደረጃ ከመቅረፉ በተጨማሪ ትልቅ ኢኮኖሚያዊና በማህበራዊ ጥቅም እንደሚኖረዉ ይታመናል።
ሆስፒታሉ በቅርብ ስራ ለመጀመር አስፈላጊዉን ሁሉ እያደረገ ሲሆን በሚከተሉት የስራ ክፍሎች ባለሙያዎችን ለማሟላት እየሰራ ይገኛል።
የሆስፒታሉ ዋና ዋና አገልግሎቶች:-
1. የዉስጥ ደዌ ምርመራና ህክምና (የልብ: የኩላሊት: የጉበት: የጨጓራ: የሳንባ:የስኳር በሽታ:የደም ግፊት:የነርቭ ህክምናና ሌሎችም)
2.የቀዶ ጥገና ህክምና ( መለስተኛና ከፍተኛ ቀዶ ጥገና:የአጥንት ህክምና)
3.የቆዳና አባላዘር በሽታዎች ህክምና
4.የፅንስ ክትትልና የማህፀን ህክምና
5.የቅድመ ወሊድና የድህረ ወሊድ ክትትልና የማዋለድ አገልግሎት
6. ከአንገት በላይ ምርመራና ህክምና
7. የተሟላ የናሙና ጥናት(ላቦራቶሪ) አገልግሎት
8. የራጅ (ኤክስ ሬይ:አልትራሳዉንድና ሌሎች) አገልግሎት
9. የተሟላ የመድኃኒት አቅርቦትና የምክር አገልግሎት
10. አጠቃላይ ምርመራ (ሜዲካል ቸክ አፕ) በዋናነት የሚሰጡ ይሆናል።
👉ተኝተዉ ለሚታከሙ ህሙማን በተሟላ የምኝታ ክፍል አገልግሎቱ ይሰጣል።
"ጥረታችን ጤናማ ህዝብ መፍጠር ነዉ!"

02/02/2021

types of share company

27/01/2021

ዋርካ ሜዲካልና ቢዝነስ አ/ማ በሞጣና አካባቢው ተወላጆች ህብረት የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን በቅርብ ቀን በጤናው ዘርፍ በምስ/ጎጃም የመጀመርያ የሆነዉን የግል ሆስፒታል በጥንታዊቷ ሞጣ ከተማ ለመክፈት ቅድመ ዝግጁቱን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል። ሆስፒታሉ ዋርካ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሲሆን የተሟላ የህክምና አገልግሎትና የማህበረሰብ አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል። ስለሆነም ድጋፍዎ እንዳይለየን በማለት እንጠይቅዎታለን!!! ሌሎች የስራ መስኮችም ወደፊት ይቀጥላሉ....
"ጥረታችን ጤናማ ማህበረሰብ መፍጠር ነዉ"።

Address

Motta City, Amhara
Motta

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Warka Medical and Business SC - ዋርካ ሜዲካል እና ቢዝነስ አ/ማ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Warka Medical and Business SC - ዋርካ ሜዲካል እና ቢዝነስ አ/ማ:

Share