አሌፍ ክሊኒክ። ። Aleff Clinic MOTTA

አሌፍ ክሊኒክ። ። Aleff Clinic        MOTTA ''Realy we care!!''

Abortion
30/09/2022

Abortion

በኢትዮጵያ ውርጃ የሚፈቀድባቸው 5 ምክንያቶች

🖲 የጤና ባለሞያዎች ለሁለቱም ፃታዎች የእርግዝና መከላከያ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የሚመክሩት ያለምክኒያት አይደለም

🖲ጥንቃቄ በጎደለው ግንኙነት ምክኒያት ያልታቀደ እርግዝና ሲያጋጥም የአብዛኞች ውሳኔ እንደምታቁት ህገወጥ ወርጃ ነው።

🖲በሀገራችን ውስጥ ውርጃ የሚፈቀድባቸው 5 መንገዶች ብቻ ናቸው።

👉1. በመደፈር እና በዘመድ መካከል ግንኙነት የተፈጠረ አርግዝና ከሆነ

👉2. የእርግዝናው መቀጠል የእናትየዋን ህይወት የሚያጨናግፍ ከሆነ

👉3. ፅንሱ ሊድን የማይችል የአካል ጉድለት ካለው

👉4. እናትየዋ ለአቅመ ሄዋን ያልደረሰች ወይም የአእምሮ በሽታ እና የአካል ጉድለት ተጠቂ ከሆነች እንዲሁም

👉5. ግዜ በማይሰጥ ድንገተኛ አደጋ እና በበሽታ ምክኒያት አፋጣኝ ህክምና የሚደረግ ከሆነ። ውርጃ በህግ ይፈቀዳል

🖲 ከዚህ ውጪ የሚደረጉ ውርጃዎች ፣በፍርድ ቤት ውሳኔ ፣በባለሞያው እና ፈቅዳ ውርጃን የምታከናውነው እርጉዝ ሴት ላይ በወንጀል ህግ ያስቀጣል

🖲አሳሳቢው ሁኔታ በህግ ተጠያቂ መሆን ብቻ ሳይሆን ፡ አንዳንዴ ከውርጃ በኋላ የሚያጋጥም የጤና ችግር፣ ከግዜ በኋላ የሚፀፅት የእድሜ ልክ ጠባሳንም ትቶ ሊያልፍ ይችላል።

ለተጨማሪ ጤና መረጃ የቴሌግራም ቻላናች ይቀላቀሉ
https://t.me/+UbojqWNhpSZ01_-m

Wrong medical certificate
30/09/2022

Wrong medical certificate

28/09/2022

የሕክምና ስህተት ምን ማለት ነው ❓

የሕክምና ስህተት ሕግ ዶክተሮች ወይም ሌላ የሕክምና አገልግሎት ሰጪ አካላት የሕክምና አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት በታማሚው ላይ በችልተኝነት ለሚያደርሱት ጉዳት ያለባቸውን ተጠያቂነት የሚገዛ ሕግ ነው፡፡ ይህ የሕግ ዘርፍ ከሀገር ሀገር የተለያየ ይዘት ቢኖረውም በአብዛኛው ሀገር ግን በሕክምና ስህተት ግለሰቦች ለሚደርስባቸው ጉዳት ጉዳቱን ያደረሰው አካል ተጠያቂ የሚሆንበት የአሠራር ሥነ ሥርዓት አላቸው፡፡ አንድ የሕክምና ባለሙያየሕክምና አገልግሎት ሲሰጥ በተመሳሳይ ጉዳይ ሌሎች የሕክማና ባለሙያዎች ሊያከብራቸውወይም ሊፈጽሟቸው የሚገባውን መደበኛ ጥንቃቄ (“standard of care”) ሊያከናውን ወይም ሊከተል ባለመቻሉ ምክንያት በታማሚው ላይ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ የሕክምና ባለሙያው ለጥፋቱ ተጠያቂ የሚሆንበት አሠራር የሕክምና ስህተት ሕግ ይባላል፡፡

ሁሉም ስህተቶች የሕክምና ስህተት አይባሉም፡፡ አንድ ታካሚ የሚጠብቀውን የሕክምና ውጤት አላገኘሁም በማለት የሕክምና ባለሙያን ለመክሰስ አይችልም፡፡ በአጭሩ የሙያ ስህተት የሚባለው በአንድ የሙያ ዘርፍ የተሠማራ ባለሙያ ሥራውን በሚያከናውንበት ጊዜ ሊከተላቸው ወይም ሊመራባቸው የሚገባውን የሙያ ደንቦችና መመሪያዎች አውቆ ወይም በቸልተኝነት ሳያከብር መቅረት ወይም የሙያ ደንቦችን ባለማክበሩ በሌላ ሰው ላይ ጉዳት ማድረስ እንደሆነ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2031 እና 2035 ይደነግጋል፡፡

በመሆኑም አንድ የሕክምና ባለሙያ የሕክምና ስህተት ፈጽሟል ለማለት የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች በሙሉ መሟላታቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

1. #የአካሚና ታካሚ ሕጋዊ ግንኙት መኖሩን ማረጋገጥ ❗️

የሕክምና ስህተት አለ ብሎ ክስ ለመመሥረት የአካሚና ታካሚ ሕጋዊ ግንኙነት መኖሩን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ በሕክምና ባለሙያ እናበታካሚ መካከል ለሚኖረው ግንኙነት መሠረቱ የሕክምና አገልግሎት ውል ነው፡፡ ታካሚው ከሕክምና ባለሙያው ወይም ከሕክምና ተቋሙጋር የሚኖረው የሕክምና ግንኙነትየሚመሠረተው በውል እንደሚሆን የፍትሐብሔር ሕግ ከቁጥር 2639-2652 ያስረዳል፡፡ በአንድ የመዝናኛ ሥፍራ አንድ ዶክተር በሰጠዎት መድኃኒት ምክንያት ጉዳት ደርሶብኛል ለማለት አይቻልም፡፡ በሕክምና ተቋሙ ካርድ አውጥተው የሕክማ ባለሙያውን አግኝተውት እንደሆነ ግን የአካሚ ታካሚ ሕጋዊ ግንኙነት እንዳለ ማስረጃ ይሆናል፡፡

2. #የሕክምና ባለሙያው ቸልተኛ መሆኑን ማረጋገጥ ❗️

የሕክምና ጥፋቱን ፈጽሟል የተባለው የህክምና ባለሙያ ጥፋቱን የፈጸመው ቸልተኛ ሆኖ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ቸልተኛ የሚለው ቃል ብዙ ጊዜ በሕግ የራሱ የሆነ የአተረጓጎም ስልት ያለው ሲሆን አንድ የሕክምና ባለሙያ ቸልተኛ ነው የሚባለው የፈጸመው ድርጊት አንድ የሕክምና ባለሙያ አንድን የተወሰነየሕክምና አገልግሎት ሲሰጥ ሊያከብራቸውወይም ሊፈፅማቸው ይገባል ተብለው የተቀመጡን ዝቅተኛ የሕክምና አገልግሎት ደረጃን (minimum standard of care) ሊጥስ እንደሚችል ማወቅ እያለበት ወይም እየቻለ፣ ባለመገመት ወይም ባለማሰብ ድርጊቱን የፈጸመ እና ጉዳቱን ያደረሰ እንደሆነ ነው፡፡ በተለይም በሕክምናው ዓለም ሲመዘን በጉዳዩ ዙሪያ ሊደረጉ ይገባል ተብሎ በአግባቡ የሚጠበቁትን ጥንታቄዎች ያላደረገ እንደሆነ ድርጊቱ በቸልተኝነት ተፈጽሟል ያስብላል፡፡ይህንንም ለማስረዳት በሙያው የተሠማሩ ሌሎች የሕክምና ባለሙያዎች እንደ አዋቂ ምስክርነት (expert witness) መጠቀም ይግድ ይላል፤ ምክንያቱም የሕክምና ስህተት ተፈጽሟል ለማለት ድርጊቱን ፈጸመ በተባለው ባለሙያ ልክ የትምህርት ደረጃው፣ የአካባቢ ሁኔታው፣ ልምድ ከግምት በማስገባት የሕክምና ሙያ ስህተት ተፈፅሟል ወይስ አልተፈፀመም የሚለውን ለማስረዳት መጠቀም ይቻላል፡፡

3. #የሕክምና ባለሙያው ቸልተኝነት #በታካሚው ላይ ጉዳት መድረሱን ማረጋገጥ ❗️

አብዛኛውን ጊዜ ወደ ሕክምና ቦታ የሚመጡ ታማሚዎች ጉዳት የደረሰባቸው በሕመሙ ምክንያት ነው ወይስ የሕክምና ባሙያው በሠራው ስህተት የሚለውን ነጥብ ማስረዳት አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ በመሆኑም የሕክምና ባለሙያው ቸልተኝነት ጉዳቱን ያደረሰው መሆኑን በግልጽ ማመለካት አለበት፡፡ ለምሳሌ በካንሰር የተያዘ አንድ ታካሚ ሕክምና ሲያገኝ ቆይቶ ከዚህ ዓለም በሞት ቢለይና ሰውዬው የሞተው የሕክምና ባለሙያው በፈጸመው ስህተት ነው ቢባል ሰውየው የሞተው በካንሰሩ ምክንያት ነው ወይስ የሕክምና ባለሙያው በፈጸመው ስህተት ነው የሚለው በግልጽ መለየትና መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡

(ምንም እንኳን የሕክምና ባለሙያው የሕክምና ስህተት ቢፈጽምም ወይም የፈጸመው ድርጊት በተመሳሳይ የሕክምና ባለሙያ መስፈርት ከደረጃ በታች ቢሆንም ስህተት የተፈጸመበት ታማሚ ጉዳት እንደደረሰበት እስካላረጋገጠ ድረስ ጉዳዩን ወደፍርድ ቤት ይዞ ለመሔድ አይችልም) 🤔 🇪🇹



ስህተቶች የሕክምና ስህተት የሚባሉት በተለያዩ ዘርፍ ውስጥ ሊወድቁ ይችላሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል፡-

· የታማሚውን ሁኔታ አለመመርመር ወይም የታማሚውን ሁኔታ ለመመርመር መዘግየት፣
· የኤክስ ሬይ ወጤቶችን አሳስቶ ማንበብ ወይም መረዳት፣
· ትክክል ያልሆነ ወይም የተሳሳተ የመድኃኒት ትዕዛዝ መስጠት፣
· አንድ የሕክምና ሥነ ሥርዓት ያለውን ጉዳት ወይም ሥጋት ለታማሚው አለመንገር፣ አለማስረዳት ወይም አለማስጠንቀቅ፣
· ታማሚው በግልጽ ፈቃዱን ሳይሰጥ በታማሚው ላይ ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን መፈጸም፣ በቀዶ ጥገና ወቀት ወይም ልጅ በማስወለድ ጊዜ ስህተት መፈጸም ይገኙበታል፡፡

on Telegram 👇👇

t.me/joinchat/AAAAAExPP_EV3XyLKhhCpw
t.me/joinchat/AAAAAExPP_EV3XyLKhhCpw
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 💥💥💥

ከማህፅን ውጭ እርግዝና (ECTOPIC PREGNANCY) ከማህፅን ውጭ እርግዝና የሚከሰተው የዳበረው እንቁላል ከዋናው የማህፀን ክፍል ውጭ ሲያድግ ነው። ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው በማህፀን ቱቦ ...
19/08/2022

ከማህፅን ውጭ እርግዝና (ECTOPIC PREGNANCY)

ከማህፅን ውጭ እርግዝና የሚከሰተው የዳበረው እንቁላል ከዋናው የማህፀን ክፍል ውጭ ሲያድግ ነው። ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው በማህፀን ቱቦ ውስጥ ነው። አንዳንድ ጊዜ በሌሎች የሰውነት ክፍሎች ማለትም ኦቫሪ (ovary)፣ የሆድ ዐቃ (abdominal cavity) ወይም የማህፀን ጫፍ (cervix) ላይ ይከሰታል።

🏩🏨ምልክቶች

መጀመሪያ ላይ ምንም ምልክቶች ላይታዩ ይችላሉ። ይሁን እንጂ አንዳንድ ከማህፀን ውጭ እርግዝና ያለባቸው ሴቶች የተለመዱ የእርግዝና ምልክቶች አሏቸው - የወር አበባ መቋረጥ, የጡት ህመም እና ማቅለሽለሽ።

ሶስት ክላሲክ ምልክቶች የምንላቸው - የሆድ ህመም፣ ደም መፍሰስ (vaginal bleeding) እና የወር አበባ መቆረጥን (amenorrhea) ያጠቃልላል።

🌡🧪🩸ስለ ከማህፀን ውጭ እርግዝና ቅድመ ማስጠንቀቂያ

ብዙውን ጊዜ ቀለል ያለ ደም መፍሰስ (light vaginal bleeding) አና ማህፀነ አካባቢ ህመም (pelvic pain) ናቸው።

🩺🩹🖍 አደገኛ ምልክቶች

በሆድ ውስጥ ከባድ የደም መፍሰስ።
ራስን መስት, የደም ግፊት መውረድ እና የልብ ምት መጨመር።

🖋🦠🏨ከማህፀን ውጭ እርግዝና እንዲከሰት የሚያደርጉ ምክንያቶች

-ከዚ ቀደም ከማህፀን ውጭ እርግዝና ተከስቶ
ከነበረ
-ኢንፌክሽን (በግንኙነት የሚተላለፉ)
-የማህፀን ቱቦ ቀዶ ጥገና
_ሲጋራ ማጨስ

👨‍⚕🩸💉 ምርመራ
- የእርግዝና ምርመራ
- አልትራሳውንድ እና
- ሌሎች የደም ምርመራዎች።

🧬🔬የማህፀን ውጭ እርግዝና ሕክምና

ከማህፀን ውጭ እርግዝናው ከባድ ደም መፍሰስ ካስከተለ, ድንገተኛ ቀዶ ጥገና ያስፈልጎታል።

🧬💊🩺 እንዴት መከላከል ይቻላል?

- በግብረ ሦጋ ግንኙነት የሚተላለፉ ኢንፌክችኖችን
መከላከል (የጾታ አጋሮችን ቁጥር በመገደብ አና
ኮንደም በመጠቀም)
- አለማጨስ

 #ልጅዎ በቂ ወተት እያገኘ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች1.ልጅዎ መመገብ የሚጀምረው በጥቂት ፈጣን ጡት መጥባት፣ ከዚያም በረጅም  ይጠባል እና አልፎ አልፎ በቆመበት ይውጣል።2.ልጅዎን ሲውጥ መ...
15/08/2022

#ልጅዎ በቂ ወተት እያገኘ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች

1.ልጅዎ መመገብ የሚጀምረው በጥቂት ፈጣን ጡት መጥባት፣ ከዚያም በረጅም ይጠባል እና አልፎ አልፎ በቆመበት ይውጣል።

2.ልጅዎን ሲውጥ መስማት እና ማየት ይችላሉ.

3.በሚጠቡበት ጊዜ የልጅዎ ጉንጮዎች ክብ እንጂ ባዶ አይደሉም።

4.በምግብ ወቅት የተረጋጉ እና ዘና ያለ ይመስላሉ.

5.ልጅዎ በምግቡ መጨረሻ ላይ በራሱ ከጡት ላይ ይወጣል.

6.ከተመገቡ በኋላ አፋቸው እርጥብ ይመስላል.

7.ልጅዎ ከአብዛኛዎቹ ምግቦች በኋላ እርካታ እና እርካታ ይታያል.

8.ከተመገቡ በኋላ ጡቶችዎ ለስላሳ ይሆናሉ።

9.ከተመገባችሁ በኋላ የጡት ጫፍዎ ያነሰ ይመስላል

10.ከተመገቡ በኋላ እንቅልፍ እና መዝናናት ይሰማዎል

11.ልጅዎ ከመጀመሪያዎቹ 2 ሳምንታት በኋላ ክብደቱ እየጨመረ ይሄዳል - በመጀመሪያዎቹ 2 ሳምንታት ውስጥ ህጻናት የተወሰነ የውልደት ክብደታቸውን መቀነስ የተለመደ ነው.

12.ሲነቁ ጤናማ እና ንቁ ሆነው ይታያሉ።

13.ከ 5 ኛው ቀን ጀምሮ, እርጥብ ዳይፐሮች በብዛት መከሰት መጀመር አለባቸው, ቢያንስ 6 ጊዜ በየ 24 ሰዓቱ. በመጀመሪያዎቹ 48 ሰዓታት ውስጥ፣ ልጅዎ 2 ወይም 3 እርጥብ ዳይፐር ብቻ ሊኖረው ይችላል።

10/08/2022

የጡት ማጥባት 12 ጥቅሞች
በዶ/ር ቤቴል ደረጀ

የጡት ወተት ለህፃናት ከምግብነት ባለፈ የሚሰጠው ጥቅምና አንዲት እናት በማጥባቷ ብቻ የምታገኛቸውን ጥቅሞች እናያለን።

ጡት ማጥባት ለልጅሽ

1. ከብዙ ኢንፌክሽኖች ይከላከላል። ለምሳሌ; የሳንባና የጆሮ ኢንፌክሽን፣ የማጅራት ገትር፣ የሆድ ቫይረስ
2. ከአለረጂክ ይከላከላል።
3. ብሩህ አዕምሮ እዲኖራቸው ያደርጋል
4. ከመጠን በላይ ውፍረትን በመከላከል አስተማማኝ እድገት እንዲኖራቸው ያደርጋል
5. በህፃናት ላይ የሚከሰትን ካንሰር መጠንን ይቀንሳል
6. ድንገተኛ የሆነ የጨቅላ ህፃናትን ሞት ይቀንሳል

ጡት ማጥባት ላንቺ

7. በእርግዝና ወቅት ያደገው ማህጸን ቶሎ ወደቦታው ስለሚመለስ የሚፈሰው የደም መጠን ይቀንሳል
8. ከልጅሽ ጋር የሚኖረው ፍቅር ይጨምራል
9. ከወሊድ በኃላ ቶሎ ክብደት ለመቀነስ ይረዳል
10. እድሜ ሲገፋ የሚፈጠረውን የስኳር በሽታ ይቀንሳል
11. ከጡት እና ከእንቁላል ማምረቻ ካንሰር ይከላከላል
12. ወጪ ቆጣቢ ነው።

ቸር እንሰንብት

Tonsilites
28/07/2022

Tonsilites

28/07/2022

"ስለ ቶንሲል የምናውቀው አና የምንሳሳተው ምንድን ነው?" - ዶ/ር ንጉሴ ጫኔ ፤ የህጻናት ስፔሻሊስት ሀኪም

- ቶንሲል ምንድን ነው?

ቶንሲል ለብዙዎቻችን እንደሚመስለን በሽታ አይደለም።
ቶንሲል ማለት ትንንሽ አበጥ ያሉ የተፈጥሮ የበሽታ መከላከያ አካላት ስብስብ ነው። ይህም በክብ ቀለበት ከምላስ ጀርባ የላንቃን የጎን ግድግዳ እና የላንቃን ክዳንና የአፍንጫን የውስጠኛ ክፍሎች ያስተሳስራል።

- ቶንሲል ጥቅሙ ምንድን ነው?
በአፍም በአፍንጫም የሚገቡ ተዋህስያንን መዋጋት ነው። የሰውነትን በር ከጠላት መከላከያ ነው።

- ቶንሲል እና እንጥል አንድ ናቸው?
ሁለቱም በላንቃ አካባቢ ይገኛሉ። ግንኙነታቸው ግን ጉርብትና እንጅ በአገልግሎት አይገናኙም።

- Uvula/እንጥል
እንጥል ማለት ከላንቃ ላይ የተንጠለጠለ ማለት ነው። ከቶንሲል ጋር ምንም ግንኙነት የለውም።

- የቶንሲል ህመም/tonsialiophayngitis?
ይህ የቶንሲል እና የላንቃ አካባቢ በተዋህስያን መወረር ነው።

- የህመም ምልክቶች
ትኩሳት ፣ ለመዋጥ መቸገር ፡ ራስ ምታት ፣ የአፍ መሽተት ፣ የአንገት ንፍፊት እብጠት ፣ ማንኮራፋት ፣ ሳል

የቶንሲል ህመም መተላለፊያ መንገዶች
1. በትንፋሽ ጠብታ
2. በንክኪ

- የባክቴሪያ ቶንሲል በብዛት የሚያጠቃው ማንን ነው?

የባክቴሪያ ቶንሲል ከሁለት አመት በላይ የሆኑ ህጻናትን የሚያጠቃ ሲሆን አብዛኛዎቹ ከ5-15 እድሜ ያሉት ይጠቃሉ። የቫይረስ ሲሆን ለጋ ህጻናትም ይጠቃሉ።

የቶንሲል ህመም ተያያዥ ችግሮች
1 ፡ መግል መቋጠር tonsiar, peritosilar or retropharyngeal abscess
2. የሳንባ ምች / የማጅራት ገትር
3. የልብ ህመም rheumatic heart disease ይህን ለመከላከል ቶንሲል እንዳመመን ወደ ጤና ተቋም መሄድ።
4. የኩላሊት ህመም PS glomerulonephritis
5. የቶንሲል መፋፋት adenotonsilar hyperthrophy

- የቶንሲል ህመም ህክምና
መጀመሪያ የባክቴሪያ ወይስ የቫይረስ ነው የሚለውን መለየት ያስፈልጋል።

መለያ መንገዶች
1. የቫይረስ ከሆነ የጉንፋን ምልክት አብሮ ይኖራል ግን አንዳንድ ጊዜ እንደ ቫይረስ ጀምሮ ወደ ባክቴሪያ ሊቀየር ስለሚችል ጥንቃቄ ይፈልጋል።
2. መግል የያዘ ከሆነ የባክቴሪያ ምልክት ነው ግን ይህን በደንብ እርግጠኛ መሆን ይፈልጋል።
3. ድድ፣ ከንፈር ወይም ምላስ የቆሰሉ ከሆነ የቫይረስ ምልክት ነው።
4. የነጭ የደም ሴል እና ተያያዥ ምርመራ

መድሃኒት
1. የህመም ማስታገሻ
2. እንደ ቶንሲሉ ህመም መነሻ የተለያዩ ጸረ ባክቴሪያ አለበለዚያም ፀረ ቫይረስ መድሃኒት
3. በቂ ፈሳሽ መውሰድ ረፍት ማድረግ።
4. ማር እና የውሃ ኢንፋሎት መታጠን
5. የብርቱካን ወይም ሎሚ ጭማቂ።

Melkam beal
18/10/2021

Melkam beal

***የጨጓራ ህመም፣ቁስለት ና አሲድ መብዛት***       *              (dyspepsia, PUD)❤መግቢያ**የጨጓራ የመያዝ አቅም (30 ሚ ሊ(ጨቅላ ህጻናት) እስከ 2 ሊትር ድረስ...
12/06/2021

***የጨጓራ ህመም፣ቁስለት ና አሲድ መብዛት*** * (dyspepsia, PUD)

❤መግቢያ

**የጨጓራ የመያዝ አቅም (30 ሚ ሊ(ጨቅላ ህጻናት) እስከ 2 ሊትር ድረስ ነው)
**የበላነውን ና የጠጣነውን ነገር ይቀበላል፤የምግብ ስርአተ ፍጭት ያካናዉናል
**ከዚያም ወደ አንጀት ለቀሪ ስርአተ ፍጭት ይልካል
ምግብ ከበላን 4-5 ሰአታት በኋላ ምግቡ ከጨጓራ ያልቃል

❤የጨጓራ አሲድ
**ሃይድሮክሎሪክ (HCl) የተባለው አሲድ በጨጓራ ይመረታል
ይህ አሲድ በርካታ ጥቅሞች አሉት ፤ ዋናዋናዎቹም ፦
**የፕሮቲናማ ምግቦች ፍጭትን ያሳልጣል
**የተለያዩ ጠቃሚ ማእድናትን ወደ ሰዉነት እንዲወሃዱ ይረዳል (የብረት፣ ካልሺየም፣ ቪታሚን ቢ 12)
**የባክቴሪያ በሽታዎችን ይከላከላል
**ጨጉራ ከአሲድ ዉጪ ሊፔዝ ፣ ኢንትሪንሲክ ፋክቶር ና ሌሎች ንጥረ ነገሮችንም (HCO3−, K+, and Cl−) ና ሚውሲን የተባለ ዘለግላጋ ፈሳሽ ያመነጫል
**የምግብ መፈጨት ሂደትን የምግቡ አይነት ይወስነዋል (ለምሳሌ ሳንድዊች እስከ 4 ሰአት ጨጓራ ዉስጥ ሊቆይ ይችላል፤ በአንጻሩ 500 ሚሊ ሾርባ ከ 30 እስከ 60 ደቂቃዎች ዉስጥ ከጨጓራ ይወገዳል)

❤የጨጓራ ህመም ምክንያቶች፦
**የጨጓራ ባክቴሪያ (helicobacter pylori)
**መድሃኒቶች (ዳይክሎፌናክ፣ ኢንዶሜታሲን፣ አስፒሪን.....)
**የምግብ አለመስማማት
**ፋንክሽናል (አይዲዮፓቲክ) ምክንያቱ የማይታወቅ

❤የቤት ዉስጥ የጨጓራ ህመም ህክምና
ቀለል ያለ የጨጓራ ህመም ያለባቸው የሚከተሉትን ማድረግ ብቻ ሊበቃቸው ይችላል፦
**ለጨጓራ የሚከብዱ ምግቦችን ማስወገድ (ቅባት የበዛበት)
**ሶዳ ካላቸው መጠጦች (ሚሪንዳ፣ ኮካ ኮላ፣ ፔፕሲ) ይልቅ ዉሃ መጠጣት
**ቡናና አልኮል መተው ወይም መቀነስ
**ትንሽ ትንሽ ምግብ ቶሎ ቶሎ መብላት (3 በዛ ያለ ከመብላት 5 ትንንሽ ምግቦችን መመገብ)
**ቀስ እያሉ መመገብ
**የሚያጣብቁ ልብሶችን አለመልበስ
**ራት በግዜ መመገብ
**ትራስ መጠቀም
**ሲጋራ ማቆም (የሚያጨሱ ከሆነ)

❤ማቅለሽለሽ ና ማስታወክ ላስቸገራቸው ሰዎች የሚመከር አመጋገብ፦
1.ኮምጠጥ ያለ ፈሳሽ በትንሽ በትንሹ መጠጣት (በሰአት 120 ሚሊ)
2.ተራ ቁጥር 1 ላይ ያለዉን ከተስማማ፤ ሾርባ፣ ወተት መውሰድ
4.ዝንጅብል ማቅለሽለሽ ና ትዉከት ላላቸው ሰዎች ጥሩ ነው

❤የጨጓራ ህመም መድሃኒቶች
**የጸረ አሲድ መድሃኒቶች (አልሙኒየም፣ ማልኦክስ)
**ኤች ቱ ብሎከርስ (ሲሜቲዲን፣ ራኒቲዲን)
**ፕሮቶን ፓምፕ ኢንሂቢቶርስ (ኦሜፕራዞል፣ ፓንቶፕራዞል)
**የጸረ ትዉከት መድሃኒት (ፕላዚል)_ትዉከት ላለባቸው)
**የባክቴሪያ መድሃኒቶች (የጨጓራ ባክቴሪያ ላለባቸው)

❤የጨጓራ ህመም መዘዞች (ኮምፕሊኬሽንስ)
**የጨጓራ መድማት (ደም ማስታወክ፣ በሰገራ ደም መውጣት)
**የጨጉራ መሸንቆር (PUD)
**የጨጓራ መውረጃ መጥበብ (GOO)
**የጨጓራ ካንሰር

Vacancy  # 2
10/06/2021

Vacancy # 2

Vacancy  #1 Drugist
10/06/2021

Vacancy #1 Drugist

Address

Kebelle 03, Around Motta Hospital
Motta
4545

Telephone

+251928382548

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አሌፍ ክሊኒክ። ። Aleff Clinic MOTTA posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to አሌፍ ክሊኒክ። ። Aleff Clinic MOTTA:

Share