05/11/2021
#የሳምባ ምች እና #ብርድ
የሰሞኑ ቅዝቃዜ ከባድ ነው ልጄንም ብርድ መታው መሰለኝ በጣም ያስላል ምን ላድርግለት❓️" 🫁
🤔 ግን ብርድ የሚባል በሽታ አለ ወይስ የለም❓️
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
✔️ ይሄንን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት እስኪ ስለ ሳምባ ምች(ኒሞንያ) አጠር መረጃ ልስጣችሁ ::
🌍 በአለም ላይ አንደኛ የህፃናት ገዳይ በሽታ የሳምባ ምች(ኒሞንያ) እንደሆነ ያውቃሉ⁉️
🌍 እንደ ዓለም የጤና ድርጅት (WHO) መረጃ መሰረት በ2017 ብቻ በዓለም ላይ 808,694 እድሜያቸው ከ 5 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት በሳምባ ምች ምክንያት ህይወታቸውን አተዋል‼️ ይህም ከአጠቃላይ የልጆች ሞት 15% ይይዛል::
✔️ ሳምባ ምች (ኒሞኒያ) ማለት የሳምባችን የታችኛው እና የመጨረሻው ክፍል መቆጣት እና መታመም ነው::
🫁 ሳምባችን ለሰውነታችን ኦክስጅን የሚባለውን ጠቃሚ አየር የምናስገባበት እና ካርቦንዳይ ኦክሳይድ የሚባለውን የተቃጠለ አየር የሚናስወግድበት አካላችን ነው።
🫁 ይህ አካል በዝህ በሽታ ሲጠቃ ሰውነታችን በቂ የሆነ ኦክስጅን አያገኝም ይሄም ትንፋሽ ማጠር እና ማቃሰትን ያመጣል።
👦 የልጆች ሳምባ ደሞ በደምብ ያልዳበረ እና ጠባብ ስለሆነ በወቅቱ ካልታከመ እስከ ሞት ሊያደርስ ይችላል::
🔹 ሳምባ ምች (ኒሞኒያ) መንስኤው ምንድነው?
👉 በዋናነት በቫይረስ እና በባክቴርያ ይመጣል ከነዝህም ዉስጥ በአብዛኞቹ ጀርሞች በሳል ወይም በንጥሻ ወቅት በትንፋሽ የሚተላለፉ ናቸው::
👉 ከነዚህ በሽታ አምጭ ጀርሞች በተጨማሪም ኒሞኒያ በተለያዩ ኬሚካሎችም ሊመጣ ይቻላል::
ለምሳሌ የጨጓራ አሲድ በድንገት ወደ ሳምባ ከገባ ኒሞኒያ ሊያስከትል ይችላል::
🔺 ልጆችን ለሳምባጨምች(ኒሞኒያ) የሚያጋልጡ ነገሮች ምንድናቸው ❓️
🔹 የላይኛው የትንፋሽ አካላት ኢንፌክሽን ለምሳሌ ጉንፋን
🔹 ቤት ዉስጥ የሚጨሱ ማንኛዉም የጭስ አይነቶች
🔹 የከሰል እና የእንጨት ጭስ
🔹 ዝቅተኛ የበሽታ መከላከል አቅም
🔹 የምግብ እጥረት
🔹 በጣም ተጠጋግቶ መኖር እና በቂ የሆነ የአየር ዝውውር በሌለበት ቤት እና አካባቢ መኖር
🔹 የሳምባ በተፈጥሮ የሚመጡ ችግሮች
🔹 የቫይታሚን ዲ እጥረት(ሪኬትስ)፦ በተለይ ፀሐይ በደምብ ያልሞቁ ህፃናት ለሳምባ ምች ተጋላጭ ናቸው::
#ምልክቶቹ ምንድናቸው?
🔺 ቶሎ ቶሎ መተንፈስ
🔺 ትንፋሽ ማጠር እና ለመተፈስ መቸገረ
🔺 ትኩሳት
🔺 ማቃሰት
🔺 ትውከት
🔺 የደረት ውጋት ወይም ህመም
🔺ህፃናት ሲተነፍሱ የታችኛው ደረት ክፍል ወደ ዉስጥ ግብት ግብት ማለት ናቸው::
🛑 ልጆች ሳምባምች(ኒሞኒያ) እንዳይዛቸው ምን እናድርግ መከላከያ መንገዶችስ ምንድናቸው?
📌ክትባት
📌ቤት ዉስጥ ማንኛዉም ጭስ አለማጨስ
📌 ቤት ዉስጥ በቂ የ አየር ዝውውር እንዲኖር ማድረግ
📌የተመ ጣ ጠ ነ ምግብ መመገብ
📌 እስከ 6 ወር ያሉ ህፃናት የእናት ጡት ወተት ብቻ እንዲወስዱ ማድረግ
📌ልጆች የፀሀይ ብርሃን በበቂ ሁኔታ እንዲያገኙ ማድረግ
📌ልጆችን ጉንፋን ከያዛቸዉ ሰዎች በተቻለ መጠን ማራቅ
🛑 በመጨረሻም ብርድ የሚባል በሽታ አለ ወይስ የለም?🤔 ወደሚለው ጥያቄ ስንመጣ፦
✔️ በአጭሩ በዘመናዊ ሕክምና ዉስጥ ብርድ የሚባል ነገር የለም‼️
✔️ አንዳንድ ሰዎች ብርድ የሚለው ቃል ከሳምባ ምች (ኒሞኒያ) ጋር ሲያምታቱ ይታያል ይሄ ትክክል አይደለም ቀዝቃዛ አየር የሳምባ ምች አያመጣም❗️
🇪🇹 እኛ የሚንኖረው ሀገር ስትኖር ነውና ሀገራችንን ሰላም ያርግልን❗️❗️
#ውድነህ ሕዝቅኤል ኡርጌሣ/ጤና መኮንን/
❤️ መረጃውን ከወደዱት ያድርጉት❗️