Yirgalem Primary Health Care Unit

Yirgalem Primary Health Care Unit Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Yirgalem Primary Health Care Unit, Medical and health, Sidama Yirgalem, Yirgalem.

06/06/2026
የክረምቱን መግባት ተከትሎ ከሚከሰት የወባ በሽታ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል። ባሕር ዳር: ግንቦት 27/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ወቅቱን መገንዘብ እና ተገቢውን ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እጅግ መሠረታ...
06/06/2026

የክረምቱን መግባት ተከትሎ ከሚከሰት የወባ በሽታ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።

ባሕር ዳር: ግንቦት 27/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ወቅቱን መገንዘብ እና ተገቢውን ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እጅግ መሠረታዊ ነገር ነው። ሞቃታማው ወራት አልፎ ቅዝቃዜ ከሚተካበት ወራት ልንደርስ ጫፍ ላይ እንገኛለን። ይህ ወቅት ታዲያ ጥንቃቄ የሚፈልግ ጊዜ ነው።

በተለይም ለሰው ልጅ የጤና ጠንቅ የኾነችው ወባ አምራቹን በስፋት ልታጠቃ የምትችልበት ምቹ አጋጣሚ የሚፈጠርበትም ጊዜ ነው። በባሕር ዳር ከተማ አንዳንድ አካባቢዎች ዜጎች በወባ ተጠቅተው በጤና ጣቢያዎች መገኘት ጀምረዋል።

በባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ጤና መምሪያ የኅብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከያ እና መቆጣጠሪያ አሥተባባሪ ይዘንጋው መኮንን በክረምት መግቢያ እና መውጫ ላይ ያሉ ጊዜያቶችን ሰዎች ጥንቃቄ ማድረግ ካልቻሉ በወባ መጠቃታቸው አይቀሬ ይኾናል ይላሉ።

አሁን ላይ በከተማው በወባ የመጠቃት ሁኔታ በየሳምነቱ እየጨመረ መሄዱን ከጤና ጣቢያዎች የሚደርሰው መረጃ እየጠቆመ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

ከተማ አሥተዳደሩ ቀድሞ ወባን ለመከላከል ቅድሚያ ተጠቂ ናቸው ላላቸው እና አቅማቸው አነስተኛ ለኾኑ 26 ሺህ ዜጎች አጎበር ማሰራጨቱን ጠቁመው ሰዎች በተገቢ መንገድ እንዲጠቀሙበትም አስገንዝበዋል።

አጎበር ያላገኙ የከተማዋ ነዋሪዎችም ለበሽታው ትኩረት በመስጠት ከዚህ በፊት የተሠራጨውን በሚገባ ጥቅም ላይ የማዋል እና መግዛት የሚችሉ ደግሞ ገዝተው በመጠቀም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ነው አስተባባሪው የመከሩት።

ከተማ አሥተዳደሩ የዜጎችን ጤና መጠበቅ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው የሚሉት አሥተባባሪው የአርብ ጠንካራ እጆች በሚል የጽዳት ዘመቻ ሲያካሂድ መቆየቱን ገልጸዋል። ኅብረተሰቡ ከጥቅሙ አንጻር ተረድቶ በሚገባው ልክ እየተረባረበ ባለመኾኑ እንዲሳተፍ ነው ያስገነዘቡት።

ወባን ለመከላከል ዋነኛው ሥራ የአካባቢ ጽዳት እንደኾነ ጠቁመው ለሥራው ትኩረት እንዲሰጥም ነው ያስረዱት።

በባሕር ዳር ከተማ አሁን ላይ በወባ የመጠቃት አዝማሚያ እያሳዩ ያሉት ቀበሌ 11 (ዓባይ ማዶ)፣ መሸንቲ እና በላይ ዘለቀ ክፍለ ከተማ መኾናቸውን ለአብነት አንስተዋል። ለጊዜው እነዚህ አካባቢዎች ይበልጥ ትኩረት እንደሚሹ ነው ያብራሩት።

ሌሎች አካባቢዎችም ወቅቱ ለወባ ምቹ የኾነ ጊዜ መኾኑን በመረዳት ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል ነው ያሉት።

በከተማዋ 10 ጤና ጣቢያዎች፣ 11 ጤና ኬላዎች፣ እና 3 ሆስፒታሎች ኅብረተሰቡን እያገለገሉ ስለመኾኑ የጠቆሙት አስተባባሪው ተቋሞቹ ለወባ ለካርድ ክፍያ ካልኾነ በስተቀር መድኃኒት በነጻ በመኾኑ ትኩሳት ሲኖር በፍጥነት ወደ ሕክምና መሄድ ይገባል ነው ያሉት። በጤና ተቋሞቹም በቂ የኾነ መድኃኒት ስለመኖሩም ነው ያስረዱት።

አምራች እና ለሀገር ወሳኝ የኾነው ኃይል በወባ እንዳይጎዳ ግን ጥንቃቄ ማድረግ እና ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባም ነው የጠቆሙት።



በምሥጋናው ብርሃኔ

የጨረታ ማስታወቂያ የይ/ዓለም ከተማ ጤና ጣቢያ የተለያየ የአሮጌ/ ያገለገሉ ንብረት ለመሸጥ ያወጡት ማስታወቂያ ይህ ይመስላል።ዝርዝሩን በማስታወቂያ ያገኙ!!
21/01/2026

የጨረታ ማስታወቂያ

የይ/ዓለም ከተማ ጤና ጣቢያ የተለያየ የአሮጌ/ ያገለገሉ ንብረት ለመሸጥ ያወጡት ማስታወቂያ ይህ ይመስላል።

ዝርዝሩን በማስታወቂያ ያገኙ!!

Address

Sidama Yirgalem
Yirgalem

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yirgalem Primary Health Care Unit posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share