God Grace Tv

God Grace Tv Our aim on this media is transfering Gospel Massage program announcement and wonderfu lworks of God through the power of Holy spirit to only his grace.

26/04/2020
24/04/2020

ማንነው አንበሳ እና ጀግና ለክርስቶስ ኖሮ ማለፍ የውስነ?

:- ከግዜው ግርግርና ወከባ ውጥቶ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሽልማት እና ብድራት ወዳለው እውነት መለስ የሚል ማነው?


:- ሰል ክርስቶስ ኢየሱስ እንዴት መመስከር እንችላለን?

:- መንፈስ ቅዱስ በዚህ የመጨርሻው ዘመን የሚፈልገው ጨርቄን ማቄን ሳይል ከተርት ተርት ውጥቶ ያለምንም ፍራሐት እና መሸማቀቅ በሐይል እና በስልጣን ሰለ ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ የሚያስተምረ የሚሰብክ እና የሚመስክር ስው ይፈልጋል:: ማን ነው ለመላክ የተዘጋጀ?

:- እንግዲህ እግዚአብሔርእንዲህ ይላል...

ትንቢተ ኢሳይያስ 6
8፤ የጌታንም ድምፅ፡— ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል? ሲል ሰማሁ። እኔም፡— እነሆኝ፥ እኔን ላከኝ፡ አልሁ።
:- እነዚህን የእግዚአብሔር ቃሎች በማስተዋል እና በጥንቃቄ በጾምና በፀሎት ሆናችሁ አንብቡቧቸው አስላስሏቸው ከዚህይም በኃላ በእምነት እና በተሰበር ልብና መንፈስ ሆናችሁ መንፈስ ቅዱስ ሆይ እኔን ላከኝ እኔ እሄዳለው በሉት ከዚያም በኃላ መንፈስ ቅዱስ የወደደውን ያደርጋል::

1ኛ ጴጥሮስ 2
9፤ እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤
10፤ እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።

የሐዋርያት ሥራ 4
33፤ ሐዋርያትም የጌታን የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ በታላቅ ኃይል ይመሰክሩ ነበር፤ በሁሉም ላይ ታላቅ ጸጋ ነበረባቸው።

የማርቆስ ወንጌል 1
17፤ ኢየሱስም፡— በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ፡ አላቸው።


የሐዋርያት ሥራ 1
8፤ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ፡ አለ።

የሉቃስ ወንጌል 8
39፤ ነገር ግን፡— ወደ ቤትህ ተመለስ፥ እግዚአብሔር እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረግልህ ንገር፡ ብሎ አሰናበተው። ኢየሱስም እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረገለት በከተማው ሁሉ እየሰበከ ሄደ።

የማቴዎስ ወንጌል 10
32፤ ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤

የማርቆስ ወንጌል 16
15፤ እንዲህም አላቸው፡— ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፡ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።
16፤ ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።
17፤ ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤ እባቦችን ይይዛሉ፥
18፤ የሚገድልም ነገር ቢጠጡ አይጎዳቸውም፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ።
19፤ ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ።
20፤ እነርሱም ወጥተው በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፥ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፥ በሚከተሉትም ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር።

መዝሙረ ዳዊት 119
46፤ በነገሥታት ፊት ምስክርህን እናገራለሁ፥ አላፍርምም፤

ትንቢተ ኢሳይያስ 52
7፤ የምስራች የሚናገር፥ ሰላምንም የሚያወራ፥ የመልካምንም ወሬ የምስራች የሚናገር፥ መድኃኒትንም የሚያወራ፥ ጽዮንንም፡— አምላክሽ ነግሦአል፡ የሚል ሰው እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው።

ትንቢተ ዳንኤል 12
3፤ ጥበበኞቹም እንደ ሰማይ ፀዳል፥ ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ።

ትንቢተ ሚልክያስ 3
17፤ እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የእኔ ገንዘብ ይሆናሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ሰውም የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚምር፥ እንዲሁ እምራቸዋለሁ።

ትንቢተ ኢሳይያስ 6
8፤ የጌታንም ድምፅ፡— ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል? ሲል ሰማሁ። እኔም፡— እነሆኝ፥ እኔን ላከኝ፡ አልሁ።

የሐዋርያት ሥራ 18
9-10፤ ጌታም ሌሊት በራእይ ጳውሎስን፡— እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ ማንም ክፉ ሊያደርግብህ የሚነሣብህ የለምና አትፍራ፥ ነገር ግን ተናገር ዝምም አትበል፤ በዚህ ከተማ ብዙ ሕዝብ አሉኝና፡ አለው።

የሐዋርያት ሥራ 5
19፤ የጌታ መልአክ ግን በሌሊት የወኅኒውን ደጅ ከፍቶ አወጣቸውና፡—
20፤ ሂዱና ቆማችሁ የዚህን ሕይወት ቃል ሁሉ ለሕዝብ በመቅደስ ንገሩ፡ አላቸው።

የማርቆስ ወንጌል 16
20፤ እነርሱም ወጥተው በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፥ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፥ በሚከተሉትም ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር።

ከሐዋሪያ ይዲድያ ጳውሎስ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና!!!

24/04/2020

አገልጋይ ሰለ መከራና ሰለ ስደት ሊኖርው የሚገባው አመለካከትና መርዳት ምንድነው?

:- የዚህ ትምህርት መታሰብያነቱ በዓለም ሁሉ ዙሪያ ሰለ ውንጌል እና ሰለ ክርስቶስ ኢየሱስ በልዩ ልዩ ጉዳይ በመከራ እና በሰደት ውስጥ ለሚያልፉ እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልጋይ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ይሁንልኝ ከውንድማችሁ ይዲድያ ጳውሎስ::

:- አንድ እውነት በሰማይ እና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር ፊት ሆኜ ልንገራችሁና ወደ ትምህርቱ ልውሰዳችሁ የእግዚአብሔር ምህርት እና ፍቅሩ በዝቶልኝ ገና የ10 ዓመት ልጅ ሆኜ ነው ጌትዬን እና አዳኜን ኢየሱስ ክርስቶስን አግኝቶኝ እኔም እኔም ያኔ ነው ያገኝውት:: ነገር ግን እሰከ አስር አመቴ ድርሰ አንድም ቀን ክርስቲያን ( ጴንጤ ) ወይም አገልጋይ እሆናለው ብዬ አስቤም አላውቅም ፈጽሞ ለክርስትና እና ለአገልጋይነት ጥላቻ ሰለነበርኝ ምክኒያቱም በሀይማኖተኛ ቤተሰብ ውስጥ በመውለዴ ምክኒያት አንዴ በአበሾች አንዴ በፈርንጆች አንተ የኔ ነህ ታገለግለኛለ እያለ ሲነግርኝ እኔ ግን ባለማውቅ እቀልድ እና አሾፍባቸው ነበር:: ነገር ግን በዘላለማዊ ፍቅር የተሞላ አምላክ የማልፈልገውን እና የጠላውትን እውነት ግን ወደ እኔ ወደታናሹ ስው በፍቅር ይዞ መጣ እኔም ሳላውቀው በልጅነቴ የገፋውትን ክርስትና እና የአገልግሎት ጥሪ በተሰበር ልብና መንፈስ ሆኜ ተቀበልኩት በሕይውት ዘመኔ ሁሉ ለተቀበልኩት ክርስትና እና አገልግሎት የሚያስከፍለኝን ዋጋ ሁሉ ለመክፈል ቃል ገባውለት:: አገልጋይም ከሆንኩ በኃላ ከ ከሰላሳ ስምንት ( 38 ) ግዜ በላይ በወንጌል ምክኒያት ታስሬያለው በጣም ብዙ ግዜ በርካታ አገር ተደብድቤለው ከአስራ አንድ (11 ) ግዜ በላይ ተፈንክቻለው እጅግ ብዙ ዋጋ በእግዚአብሔር ፀጋ ከፍያለው ለዚህ ክብር በመመርጤ ደግሞ በጣም እድለኛ ነኝ:: አስታውሳለው ለአመታት በከባድ የጭንቅላት ወባ ሕመም እሰቃይ ነበር በስተመጨረሻም ከዶክተሮች አቅም በላይ ሆነና ወደ ቤት ውሰዱት ተስፋ የለውም ተባልኩ ቤተሰቤም ወድቤት ይዘውኝ መጡ ብዙም ሳልቆይ ነብሴ ከስጋዬ ተለየች ስዎች ሀብታሙ ሞተ ብለው ሲያለቅሱ ያኔ ነበር የምውደውን እና የማፈቅርውን ጌታዬን እና አዳኜን ኢየሱስ ክርስቶስን ፊት ለፊት ያየውት እርሱም እንዲህ አለኝ ፍቅር በተሞላበት ድምጽ ከዛሬ ጀምሮ ቃሌን በሐይል እና በስልጣ እንድታስተምር እና እንድትሰብክ መርጫካለው በቃሌና በመንፈሴ የታጠቀ ትውልድ ታስነሳለህ ብዙዎችንም ከጨለማ እስራት ነፃ ታውጣለክ በድንቅና በተአምራት ቃሌን በአንተ አፀናለው ሰለ ስሜም ብዙ መከራ ትቀበላለክ እኔ አንተን ለሐዋሪያዊ አገልግሎት መርጫካለው ብሎ ኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ለፊት ተናገርኝ እኔም እንዲህ አልኩት እንደኔ አይነቱ ተራና ምስኪኑን ስው ከመርጥክ እኔም በሕይውት ዘመኔ ሁሉ በታማኝነት አገለግልካለው ብዬ ቃል ገባውለት:: እሰከ ዛሬ ድርሰ ያኔ በልጅኔቴ ጌታ ፊት ለፊት ያለኝ ነገር በሙሉ እንደ ቲቪ እስካሁን ድርሰ ይታየኛል:: እሰከ እለተ ሞቴ ድርስ በልጅነቴ የመረጠኝን የልጅነቴ አምላክ ከቀድሞ በተሻለ በብዙ ትጋት በጽድቅ በቅድስና በትህትና በፍቅር እርሱን በመፍራት በታማኝነት አገለግለዋለው ደግሞም ለአገለግለው ቃል ገብቼለታለው:: እኔ ሳልሆን የመርጥኩት እሱ ነው የመርጠኝ ምክኒያቱም እሱን ለማገልገል እኔ በቁ አልነበርኩም እሱ ነው ብቁ ያደርገኝ:: የነገርኩአችሁን እውነት ለማውቅ ከፈለጋችሁ አስር ደቂቃ ብቻ በርከክ ብላችሁ እግዚአብሔርን በትጠይቁት በቅንነት ወድያው የእኔ አባት መልሱን ይሰጣችሁኃለ::

:- እንደ እግዚአብሔር አገልጋይ በዚህ ምድር ስትመላለስ በብዙ መከራና ስደት ስታልፍ ራስህን እና ሌሎችን ለማዳን ጤናማ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል በሙላት በሕይውትህ ሊኖረህ ይገባል::

2ኛ ቆሮ 1:3-11 ሮሜ 12:1- ፊል 2:1- ቆላ 3:12 ዕብ 10:28 ዩሐ 14:15-18 ዩሐ 3:16 ሮሜ 5:8- ኤፌ 2:4-7 መዝ 103:17- ሰቆቃው ኤር 3:22- መዝ 108:4-

:- በመከራ እና ሰደት መንገድ በምታልፍበት ጊዜ እግዚአብሔር የሚያጽናናህ ለሌሎች በመከራ እና በስደት ለሚያልፉት ቅዱሳን ሁሉ እነርሱን በማፅናናት መልካም ምስክር እና ምሳሌ እንድትሆን ነው:: ምክኒያቱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተውለደበት ጀምሮ ወደ እግዚአብሔር አብ እስኪመለስ ድርስ በብዙ መከራ እና ስደት እንዳለፈ እና ይህንን በፅናት በማለፍ ዛሬ ለእኛ ትልቅ ምሳሌና ትምህርት ሆኖናል:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእንደዚህ ዓይነት መከራና ሰደት ካለፈ እንግዲህ የእርሱ ባሪያዎች ( አገልጋዬች ) በእርግጠኝነት ለማፅናናት እንደሚችል የእግዚአብሔር ቃል በግልጽ ይናገራል::

:- ሌሎችን እንድታጽናና እግዚአብሔር ያናናሃል

:- >> እንድታበርታታ እግዚአብሔር ያበርታታሃል

:- >> እንድትርዳ እግዚአብሔር ይርዳሃል

:- ሰለ ሌሎች እንድታስብ እግዚአብሔር ሰለ አንተ ያስባል

ኢሳ 40:1-2 1ተስ 5:14- 2ቆሮ 1:5-

:- ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰለ ብዙዎች እጅግ በጣም የከፋ መከራ እና ሰደት እንዲሁም ያልተቀበለው ስቃይና ወርደት የለም:: ገና ከውልደቱ ጀምሮ እሰከ ሞቱ ድርሰ እንዴት እንዳለፈ የእግዚአብሔር ቃል በግልጽ ይነግርናል::

ማቴ 1:18-19 ሉቃ 2:7 ሉቃ 2:22-24 ማቴ 2:13-16 ሉቃ 2:39- ማቴ 13:53-58 ማቴ 8:20- ሉቃ 9:58- ማር 14:1-2 ማር 3:21-22 ማር 3:31-32 ሉቃ 4:28-29 ማር 14:50- ዩሐ 18:33- ዩሐ 19:16-

:- ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጨረሻ ውርደት ቢደርስበትም እሱ ግን በደርሰበት መከራ እና ሰደት ፈተና ሁሉ ግን አንዳች ሐጢያት ሳይሰራ ፍጽም ሆኖ አገልግሎቱን በድል ጨርስ::

ዕብ 4:15-16

:- እንደ እግዚአብሔር አገልጋይ በተለያየ መከራና ሰደት በምታልፉበት ጊዜ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ያጽናናችኃል:: ሰለዚህ እንደ እጋ አገልጋይ በቀረልን ዘመን ውስጥ በእግዚአብሔር ፊት በምነት እንመላለስ:: እግዚአብሔር እንደ ቃሉ ፈጽሞ አይተውህም አይጥልህም::

ሉቃ 7:13- ዩሐ 14:18- ዩሐ 16:33- ማቴ 24:13- ሮሜ 8:17-

:- እግዚአብሔር አንዳንድ ግዜ መከራ እና ሰደትን ለክብሩ እንደ መሳሪያ አድርጎ ይጠቀምበታል:: ምክኒያቱም በእግዚአብሔር ይህን የሚያደርገው አገልጋዮች እርስ በእርሳችን እንድንጽናና ሰለ እግዚአብሔር ማፅናናት ሰለ ተስፋው ቃል በትጋት እንድንመሰክር ሰለሚፈልግ ነው::

ፊል 2:1-2 2ቆሮ 4:17-18

:- መከራ እና ሰደትን እግዚአብሔር ይጠቀምበታል:: ምክኒያቱም እግዚአብሔር እንደ አባት የበለጠ በእርሱ እንድንታመን ይፈልጋል::

2ቆሮ 1:8-11 የሐዋ 19:23-41

:- እግዚአብሔር እምላክ ታማኝ አገልጋዮችን በመከራ እና በስደት የሚያሳልፋቸው ለምንድነው? እግዚአብሔር ይህን የሚያደርገው አገልጋዮቹ በመከራና በስደት ሁሉ ውስጥ እርሱን እንዲታመኑትና ማዳን እንደሚቻለው ሊያስተምራቸው እና እምነት እንዲኖራቸው ሰለሚፈልግ ብቻ ነው:: ሐዋርያው ጳውሎስ እግዚአብሔር በመከራውና በስደት ሁሉ ሲያድነውና ሲታደገው ከተመለከተ በኃላ በድካሙ እግዚአብሔር እንደሚከብር ተረድቶ ነበር::

1ቆሮ 10:13- 2ቆሮ 1:10-11 2ጢሞ 4:18- ዕብ 2:14-15 2ጴጥ 2:9-10 ኤር 1:8-

:- የሐዋርያው ጳውሎስን መከራ እና ሰደት የሚቀጥሉትን የእግዚአብሔር ቃሎች በመመልከት ከመከራውና ከስደቱ መንፈስ ቅዱስ እንዲያስተምርን እንጠይቀው

2ቆር 1:8-10 የሐዋ 20:18-27 ሮሜ 16:3-7 1ቆሮ 4:9-13 1ቆሮ 15:32 2ቆሮ 6:4-11 2ቆሮ 11:23-27 ፊል 2:27-

:- እግዚአብሔር አንዳንድ ግዜ መከራ እና ሰደትን የሚጠቀመው ለምድነው? አገልጋዮቹን ፀሎት እና ምስጋናን ሊያስተምራቸው ሰለሚፈልግ ነው::

2ቆሮ 1:10-11 ሮሜ 15:30-32 ኤፌ 6:18- ፊል 1:19- ያቆ 5:16-

:- የእግዚአብሔር አገልጋይ ሆይ በሕይውትህ የምትጋፈጠው መከራ እና ሰደት ሁሉ ለክርስቶስ ኢየሱስ ስትል ማሽነፍ እና መቻል እለብህ::

2ቆሮ 12:7-10 ገላ 4:13-15 ማቴ 26:36-46

:- ከክርስቶስ ውጭ በራስህ ድካማ እንደሆንክ እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋይ በማመን በጌታህ ፊት መቅርብ ልማድህ ይሁን:: ጌትም በድካምህ ሐይሉን እና መንፈሱን በልብህ ላይ ያፈሳል::

ማቴ 19:26- ሉቃ 1:37 ኤፌ 3:16-17 ኢሳ 40:31- ኢሳ 41:10- ኢሳ 43:1-2

:- በአንተ ላይ በሚመጣብህ መከራ እና ስደት ሁሉ ላይ ድንልን እያውጅክ በአምላክ በእግዚአብሔር ፀጋ በአሽናፊነት መንፈስ መቀጠል እና መወጣት አለብህ ወደ ፊት እና ወደ ላይ ብቻ::

ከሐዋሪያ ይዲድያ ጳውሎስ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና!!!

23/04/2020

በመንፈስ ቅዱስ ''መሞላት''

:- በሰው ሐይል እና ብርታት የእግዚአብሔርን ሥራ ፈጽሞ መሥራት ሰለማይቻል እና በእርሱም ዘንድ ያለ መንፈስ ቅዱስ የሆነ አገልግሎት ተቀባይነት ሰለማይገኝ አማኝ ሁል ጊዜ በመንፈሰ ቅዱስ መሞላት ይኖርበታል:: ዘካ 4:6

:- በመንፈስ ቅዱስ መሞላትን አንድ ግዜ ብቻ አማኝ ሊለማመደው የሚገባው ልምምድ ሳይሆን አማኝ በሕይውት ዘመኑ ሁሉ ሊለማመደው የተገባ ልምምድ ነው::

:- የመንፈስ ቅዱስ ሙላት በተደጋጋሚ እና በቀጣይ በአማኙ የሕይውት ዘመን ሁሉ የሚፈጸም ነው::

- ሐዋሪያት መንፈስ ቅዱስ ሞልቶባቸዋል የሐዋ 2:4

በሐዋ ሥራ 2:1- ላይ ካለው የአገልግሎት ሸክም እና ስፋት የበለጠ ሥራና ፈተና ሰለተጋረጠባቸው የበለጠ ልምምድ ያስፈልጋቸው ነበር::

- ሐዋሪያት በድጋሚ በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ የሐዋ 4:31

- እስጢፋኖስ በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ሰው ነበር የሐዋ 6:5

የመጣበትን የሞት አደጋ በምስጋና ለመቀበል እና ጠላቶቹን ለመባርክ እንዲችል ተጨማሪ ሙላት እና ሐይል ያስፈልገው ነበር:: የሐዋ 7:55

:- አንድን የእግዚአብሔር ሥራ ለመስራት የግድ አማኝ በመንፈስ ቅዱስ መሞላት ይኖርበታል:: በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስዎች በመንፈስ ቅዱስ ከተሞሉ በኃላ የሚፈጽሙት አንድ ተልኮ ይኖራቸው ነበር::

ለምሳሌ ያክል:- አንዳንድ የእግዚአብሔር ስዎችን ከእግዚአብሔር ቃል ውስጥ እንመልከታቸው

- ባስልኤል + መንፈስ ሞላበት = የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስ ሥራ ሰራ ዘፀ 31:1-6

- ኢያሱ + መንፈስ ሞላበት = የእግዚአብሔርን ሕዝብ መራ ዘዳ 34:9

- አጥማቂው ዩሐንስ + መንፈስ ሞላበት = ሕዝብን ወደ አምላካቸው እግዚአብሔር መለሳቸው ሉቃ 1:15

- ኤልሳቤጥ + መንፈስ ሞላባት = ሰለ ማሪያም እና ሰለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ትንቢት ተናገርች ሉቃ 1:41

- ዘካሪያስ + መንፈስ ሞላበት = እርሱም ትንቢት ተናገር ሉቃ 1:67

በነገራችን ላይ አንድ እውነት ልናስታውል ይገባል እርሱም ሰለ ትንቢት ነው:: እርሱም አንድ ስው ትንቢት መናገር የሚችለው በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ስር ሲሆን ነው ብቻ ነው:: ሰለዚህ አንድ ስው ትንቢት ተናገር ስንል በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥ ስር ሆና የእግዚአብሔር ሀሳብ አስተላለፈ ማለት ነው::

- ሐዋሪያት + መንፈስ ሞላባቸው = በልሳኖች ተናገሩ የሐዋ 2:4

- ሐዋሪያት + መንፈስ ሞላባቸው = ቃሉን በግልጥ ተናገሩ የሐዋ 4:31

- እስጢፋኖስ + መንፈስ ሞላበት = ኢየሱስን በሰማይ ቆሞ አየ የሐዋ 7:55

- አማኞች + መንፈስ ይሙላባችሁ = ለጌት ዘምሩ ኤፌ 5:18

:- እለት እለት በመንፈስ ቅዱስ ለመሞላት እና በእርሱ ቁጥጥር ስር ለመሆን እራሳችንን ለመንፈስ ቅዱስ አሳልፈን እንስጥ ምክኒያቱም ያለ እርሱ ምንም ማድርግ አንችልምና ሁላችንንም መንፈስ ቅዱስ ይርዳን በኢየሱስ ከርስቶስ ስም አሜን ጨርስኩ::

ከሐዋሪያ ይዲድያ ጳውሎስ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና!!!

22/04/2020

#መጽሐፍ ቅዱሳዊ #ፀሎት #እንዴት #ነው #መፀለይ #የምችለው?

የማቴዎስ ወንጌል 7
7፤ ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። 8፤ የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል።

ሀ) እውነተኛ ጸሎት በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ብቻ የሚቀርብ ነው። ዕብ 10:19-22 ዩሐ 14:6 1ዩሐ 5:14 ፀሎት በክርስቶስ በኩል ብቻ ነው ወደ እግዚአብሔር መቅረብ የሚችለው። ሰለዚህ ክርስቶስን የማያምኑ ( የማይቀበሉ ) ሰዎች ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ሳይደርስ በመንገድ የሚቀር ነው። መዝ 66:18 ኢሳ 59:1-2 ዩሐ 1:9

ለ) ፀሎት በአምልኮ ሆነን ከእግዚአብሔር ጋር የመንነጋገርው ንግግር ነው። ጌታ እራሱ ከአባቱ ጋር ያልተቋርጠ የፀሎት ግኑኘነት ነበርው።
1) በሉቃስ 3:21 መሠረት ኢየሱስ አገልግሎቱን በፀሎት ጀመረ።

2) ማቴ 26:36-44 በማር 1:35 ሉቃ 5:16 ሉቃ 9:18-22 ሉቃ 6:12-13 ከተለያዩ አገልግሎቶች በፊት ይጸልይ ነበር። መለኮትነት ላለው ኢየሱስ ፀሎት አሰፈላጊ ከሆነ ይልቁንስ ለእኛ ለሰብአዊው ሰው ምን ያህል ጸሎት ያሰፈልገናል።

ሐ) ፀሎት የቤተክርስቲያን እስትንፋስ ነው። 1ተሰ 5:17 ፀሎት የሰይጣን ፈተና መቋቋምያ ነው። ማቴ 26:41 ኤፌ 6:10-12 ፀሎት የመንፈሳዊ ስጦታዎች መፈለግያ (መቀበያ) ነው። የሐዋ 4:31 1:14 2:4 ጸሎት ከችግር የምንወጣበት መንገድ ነው። ኤፌ 6:18 ያቆ 5:15 1ዩሐ 5:16 ፀሎት የወንጌል መደገፊያ ነው። ቆላ 4:2-4 ጸሎት የጌታ ዳግም ምጻአት መፈለግያ ነው (መጠበቅያ) ነው። እራዕ 22:20

መ) የፀሎት ዓይነት በእንግሊዘኛ ። ( ACTS )

A-Adoration ( የውዳሴ ጸሎት ) እራዕ 5:13 17:12

C-Confession ( የኑዛዜ ጸሎት ) 1ዩሐ 1:8- 9 ምሳ 28:13

T-thanks God ( የምስጋና ጸሎት ) መዝ 50:23 103:1-4

S-Supplication ( የልመናና የምልጃ ጸሎት ) 1ጢሞ 2:1-2 ፊል 4:6

ረ) ፀሎት ለሁሉም ቅዱሳን ትዕዛዝ ነው። 1ተሰ 5:16 ማር 14:37-40 ሉቃ 18:1-14 ዩሐ 17:1- ቅዱሳን ባለመጸለይ ሀጢያት ስለሚሆንባቸው እንጂ ከጌታ ለምኖ ማግኘት በሚል ሀሳብ ብቻ መጸለይ የለባቸውም። ለምሳሌ ፦ ዳንኤል በቀን ለ3 ግዜ መጸለይ ልማዱ ነበር ዳን 6:10 የንጉስን አዋጅ አልፈራም የንጉስንም እልም የፈታው በፀሎት ብርታት ነው። ዳን 2:14-20

ሰ) ፀሎት በጾምም ያለጾምም ይቻላል። ባለመጾም ማንም አይኮነንም ነገር ግን ፆም ከጸሎት ጋር ሲሆን ትልቅ ሐይል እንዳለው ጌታ ኢየሱስ ተናግሯል። ማቴ 17:18-21

# በህመም በተለያየ ምክኒያቶች ግን መጾም መጸለይም ይቻላል። በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕዝብ በተለያየ ምክኒያቶች ጾመዋል። 1ሳሙ 31:13 2ሳሙ 1:12 12:15-22 ኢዩ 2:12 2ዜና 20:14 መዝ 35:13 ዳን 9:1-3 ነህ 1:1-

1) ኢየሱስ አገልግሎት ከመጀመሩ በፊት ጾሟል። ማቴ 4:1-2 ሉቃ 4:1-2

2) ኢየሱስ ሰለ ጾም ፀሎት አስፈላጊነት አስተምሯል። ማር 2:18-21 ሉቃ 4:33-35 ማቴ 17:16-21 ማቴ 6:16-18 ጾም ፀሎት መልካም ጽድቅ ስራ ከመስራትና ከተሰበር ልብ ያልሆነ በመድከም ስጋቸውንም በመጎሰም ሀይልን በመቀበል ሊያገለግሉ ይገባል።

ሸ) በእምነት መጸለይ። ዕብ 4:16 ያቆ 1:5

ቀ) ሳንታክት ዘወትር መጸለይ። ሉቃ 18:1- ፊል 4:6

በ) እንደ እግዚአብሔር ቃል መጸለይ። ዩሐ 15:7

# እንዳንጸልይ እንቅፋት የሚሆኑ ነገሮች።

A) ጸሎትን በትርፍ ጌዜ እንደምናደርገው ተግባር
መቁጠር
😎 በጸሎት የምናገኘውን ድልና በረከት ያለመለማመድ

C) መጽሐፍ ቅዱስ ሰለ ጸሎት የሚያስተምርውን ያለመርዳት

D) በራሳችን የመደገፍና የመተማመን ሁኔታ

E) ለእግዚአብሔር ፍቃድ ሳይሆን ለግል ጉዳያችን ቅድሚያ መስጠት

F) ጸሎት እግዚአብሔርን የምናመልክበትና የምናከብርበት መንገድ መሆኑን መዘንጋት

G) ጸሎት የድልና የበረከት ምንጭ መሆኑን አለመረዳት

H) እግዚአብሔርን አለመፍራትና ትዕዛዙን አለማክበር ወዘተ...

ከሐዋርያ ይዲድያ ጳውሎስ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና!!!

21/04/2020

# መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም የእግዚአብሔር ቃል ነው!!!

መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን የሚደግፉ ሁለት ዓይነት ማርጋገጫዎች አሉ::

1). ውስጣዊ ማረጋገጫ እና
2). ውጫዊ ማረጋገጫ ናቸው::

1). ውስጣዊ ማረጋገጫ :- የምንለው በመጸሐፍ ቅዱስ በራሱ ውስጥ የተመለከቱት እወነታዎች እና መጽሐፋ በራሱ የሚሰጣቸው ምስክርነቶች ናቸው::

:- መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን በብዙ መቶ በሚቆጠሩ የንባብ ክፍሎቹ ያርጋግጣል:: ለምሳሌ ያህል :- ዘፍ 1:1- እና 2 :1- እግዚአብሔርም ...አለ
ዘዳ 6:6-9 እኔ ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል
ኢያ 1:8 የዚህ ሕግ መጽሐፍ ... ብዬ አላዘዝሁምን?

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔርም አለ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል የሚሉ ቃላት እጅግ በጣም በመደጋገም ተጽፈዋል:: ይህም የተናጋሪው ቃል ከራሱ አፍ በቀጥታ መውጣቱን ያሳያል:: ሌሎችም ጥቅሶች የመጽሐፍ ቅዱስን የእግዚአብሔር ቃልነት ያርጋግጣሉ::

2ሳሙ 22:31 መዝ 1:2 12:6 ምሳ 30:5-6 ኢሳ 55:10 ኤር 15:16 ዳን 10:21 ዘው 22:38 ዘዳ 18:18-20 ኤር 1:9 23:16-22 ሕዝ 2:7

:- ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከብሉይ ኪዳን መጽሐፍት በመጥቀስ የእግዚአብሔር ቃልነቱን አረጋግጧል::

በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተፃፋትን ታሪኮች ተአምራቶች በመጥቀስ እውነተኛነታቸውን አረጋግጧል::

ለምሳሌ:-

- የፍጥረት ታሪክ በዘፍጥረት እንደተፃፈው መሆኑን ማቴ 19:4
- የአዳም እና የሔዋን ታሪክ እውነተኛነቱን ማቴ 19:4-6
- ሰለ አቤል ማቴ 23:35
- ሰለ ሰይጣን ሉቃ 11:18 ሕዝ 28:11-19
- ሰለ ኖህ ማቴ 24:37-38
- ሰለ ዮናስ ማቴ 12:39
- ሰለ ሎጥ ሚስት ሉቃ 17:32 ብዙ ማለት ይቻላል.......
ኢየሱስ ክርስቶስ የብሉ ኪዳን መጽሐፍትን በመጥቀሱ እና በርሱም ላይ የሚፈጸሙ ትንቢታዊ ቃሎችን ጠቅሶ እውነተኛነቱን በማረጋገጡ የመጽሐፍቱን የእግዚአብሔር ቃልነት ይበልጥ አሳይቷል::

:- ቀጥተኛ የሆነ የእግዚአብሔር ቃል በፀሐፊዎቹ ነብያት በኩል ተላልፏል::

እግዚአብሔር በተደጋጋሚ በነብያት አፍ ውስጥ በማለፍ ተናግሯል:: እንዲሁም ራሱ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት እየነዳቸው ቃሉን ሳይጨምሩ ሳይቀንሱ ጽፈዋል::

ለምሳሌ:- 1ነገ 14:18 16:12(34) 2ነገ 9:36 14:25 ዘካ7:7(12) ኤር 37:2 በዚህም ምክኒያት የነብያቱን ቃል የማያከብር የእርሱን ቃል እንዳላከበር ተጽፏል::

1ሳሙ 10:8 13:13-14 15:3 (19,23) ዘዳ 18:19 1ነገ 20:35-36 ብዙ ማለት ይቻላል.......

1ቆሮ 11:23 14:37 7:12 ( ሐዋሪያው ጳውሎስ የራሱን ቃል ከጌታ ቃል ለይቶ አስቀምጧል)

ከዚህ በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስ ስዎች በራሳቸው ለስዎች የፃፉት ሳይሆን በእግዚአብሔር መንፈስ በመነዳት ቅዱሳን ስዎች የፃፋት እንደሆነ ይናገራል:: 2ጴጥ 1:20-21

2). ውጫዊ ማርጋገጫዎች :- መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን በራሱ ብቻ የሚያስረግጥ ሳይሆን ተጠራጣሪዎችን እንኳን ለማሳመን በሚችሉ ብዙ መረጃዎች የተሞላ ነው::

:- የመጽሐፍ ቅዱስ ተከታታይ እና ወጥነቱ

- መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ ለማለቅ የፈጀው ግዜ ወደ 1600 ዓመታት ያህል ነው:: እንግዲህ በዘፍጥረት ፀሐፊ እና በራዕይ መጽሐፍ ፀሐፊ መካከል ያለው ትልቅ የዘመን እርቀት አለ:: እንዲሁም አምላክ ቃሉን ለማፃፍ የተጠቀመባቸው ሰዎች የተለያየ የእውቅት የአኗኗር የስፍራ ልዩነት ያላቸው ሲሆኑ ታድያ በተለያያየ ዘመናት ላይ የነበሩ የማይተዋውቁ ሰዎች እንዴት ተከታታይነት ያለውን ውጥነት ያለው መጽሐፍት ሊፅፉ ቻሉ? ይህ ማንም ሊከራከርው ያልቻለውእና የተፃፈው በአንድ መንፈስ መሪነት ብቻ መሆኑን ያረጋገጠ እውነት ነው::

:- የመጽሐፍ ቅዱሳዊ መገለጥ ጥልቀት

- መጽሐፍ ቅዱስ እውነትን በሙላት እና በረቂቅነት የሚያሳየንን ያህል የሚያሳይ ሌላ መጽሐፍ በዓለም ላይ የለም:: ፀሐፊዎቹ ሰለዘመናዊ ግኝቶች ምንም እውቀት ሳይኖራቸው የፃፏቸው ነገሮች ዛሬ በሳይነሳዊ ምርምሮች በከርስ ምድር ቁፋሮዎች የበለጠ ሊረጋገጡ ችለዋል:: የእግዚአብሔርን ቃል ረቂቅ ስራዎች እቅድ እና ዓላማን በመግለጥ እንዲሁም ትንቢታዊ ቃቹ ሲፈፀሙ በማየት የእግዚአብሔር ቃልነቱን በቀላሉ ማረጋገጥ ይቻላል:: የምድርንም ክብነት የዝናብን ዑደት የምድርን በሕዋ ላይ መንሳፈፍ የድብ ኮከብ የተፈጥሮን ቅደመ ተከተል ምድር ቅርጸ አልባ እንደነበርች በውኃ የተሸፈነች እንደነበር ተክሎች የሕይውት ጅማሬ መሆናቸውን ሌሎች የተፈጥሮ ጥበቦች ብዙ ማለት ይቻላል....... ገና ከጅማሬው በጥንቱ ዘመን የተፃፈ ሲሆን ዛሬ እንደብርቅ ግኝት በሳይንሱ አለም ተረጋግጠዋል ይህ ድንቅ ነው::

:- በሰነ ፅሁፍ ይዘቱ

-በዚህ ርገድ ሲታይ በእርግጥ በስዎች በራሳቸው ችሎታ አለመፃፋን በፍጥነት ማወቅ ይቻላል:: በውስጡ የሚገኘው ይዘት ሁሉንም የሰነ ፅሁፍ ዘርፎች ያካተተ ነው:: የታሪክ ዘገባዎች ትንቢቶች ቅኔዎች ተውኔቶች የጦርነት የፍቅር ታሪኮች የያዘ ነው:: ይህም በየትኛውም የእውቅት ደርጃ ላይ ያሉ ሰዎችን የመማረክ ኃይል እንዲኖርው አድርጎታል::

:- የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ታላቅነት

መጽሐፍ ቅዱስ ከሰው እውቀት በላይና ውጪ የሆኑትን ሚስጥር ይገልጣል:: በማንኛውም ጉዳይ ላይ የሚሰጠው ትምህርታዊ ገላለጣ እጅግ በጣም ፍፁም እና ትክክል ሲሆን ጊዜ የማይለውጠው ቴክኖሎጂ የማይሽረውን እውቀት ይገልጣል:: ከዚህም የተነሳ ጥንታዊ መጽሐፍ ውይም ዘመናዊ መጽሐፍ ነው ለማለት ሰለሚይስቸግር ዘላለማዊ ቃል ሊባል ችሏል::

:- የመጽሐፍ ቅዱሱ የማያዳላው ሥልጣን

መጽሐፍ ቅዱስ በማንኛውም የሰው ልጅ ላይ በስልጣን ይናገራል:: የሰውን ሁሉ ሐጢያተኝነት ደካማነት በግልጽ አጋልጧል:: በስዎች ብዕር ቢፃፍም ከስዎች ወደ ስዎች ሳይሆን ከእግዚአብሔር ወደ ሰው የሆነ የስልጣን ቃል ያስተላልፋል:: በነገስታት ላይ በድሆች ላይ በባለጠጎች በመላዕክት ላይ በልዩ ፍጥረት ላይ የፍርድን ቃል የማሳለፍ ስልጣን አለው::

:- የመጽሐፍ ቅዱስ ሉአላዊ ባህሪያት

- የተፃፈ ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ እና ሕያው ስጋ የሆነው ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ በተመሳሳይ መልኩ ስልጣናቸው ተግልጧል:: ይህም ማለት ስጋ የሆነው ቃል በጹሑፍ የሰፈርውን ቃል መለኮታዊ ቃል እንደሆነና በመንፈሳዊ ነገሮች ሁሉ ላይ የመበየን ስልጣን እንዲሁም ማንም ሊቃወመው የማይችለው ሉዓላዊነት እንዳለው አመልክቷል::

:- የመጽሐፍ ቅዱስ የመለውጥ ሐይል እና የሕትመት ብዛቱ

- በእለማችን የመጽሐፍ ቅዱስን ይህል ለተለያየ ሕዝቦች እና ቋንቋዎች የተተርጎመ መጽሐፍ የለም:: በሕትመትም ብዛት አንፃር ፈጽሞ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚወዳደር አይገኝም :: ከዚህም በተጨማሪ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባለው መልዕክት እና ትምህርት ስዎች ስር ነቀል የሆነ የሕይወት እና የዓላማ ለውጥ ማምጣታቸው መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር መለኮታዊ ቃል ለመሆኑ ማስርጃ ነው:: ከቃሉም የተነሳ የብዙ እልፍ ግለሰቦች እንዲሁም ሀገራት ታሪክ ተለውጧል:: ሰውን የማንፃት የመቀደስ የማጽደቅ እግዚአብሔር ወደ መምሰል የመለውጥ ችሎታው ያለ ጥርጥር የእግዚአብሔር ቃል ለመሆኑ ማስረጃ ነው::

ከሐዋሪያ ይዲድያ ጳውሎስ:- ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና!!!

21/04/2020

የማቴዎስ ወንጌል 24
42፤ ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ። 43፤ ያን ግን እወቁ፤ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ ቤቱም ሊቈፈር ባልተወም ነበር። 44፤ ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና። 45፤ እንኪያስ ምግባቸውን በጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተ ሰዎች ላይ የሾመው ታማኝና ልባም ባሪያ ማን ነው? 46፤ ጌታው መጥቶ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ያ ባሪያ ብፁዕ ነው፤ 47፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ባለው ሁሉ ላይ ይሾመዋል። የማቴዎስ ወንጌል 24
48፤ ያ ክፉ ባሪያ ግን፡— ጌታዬ እስኪመጣ ይዘገያል፡ ብሎ በልቡ ቢያስብ፥ 49፤ ባልንጀሮቹን ባሮች ሊመታ ቢጀምር ከሰካሮችም ጋር ቢበላና ቢጠጣ፥ 50፤ የዚያ ባሪያ ጌታ ባልጠበቃት ቀን ባላወቃትም ሰዓት ይመጣል፥ 51፤ ከሁለትም ይሰነጥቀዋል፥ እድሉንም ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉእንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በሰላም አደረሳችሁ!!! እርሱ እንደተናገርው ከሞት ተነስቷል መቃብሩ እሰከ ዛሬ ድርስ ባዶ...
19/04/2020

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በሰላም አደረሳችሁ!!! እርሱ እንደተናገርው ከሞት ተነስቷል መቃብሩ እሰከ ዛሬ ድርስ ባዶ ነው!!!

የትንሳኤ ዋናው እና ትልቅ ቁም ነገሩ በስው እና በእግዚአብሔር መካከል የነበርው የጥል ግድጊዳ ፈርሶ የሰው ልጅ በክርስቶስ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር ታርቆ ከዘላለም ሞት ወደ ዘላለም ሕይወት የተሸጋገርበት ትልቅ ድልድይ ነው ዋናው ቁም ነገሩ ይህ ነው ሌሎች በሙሉ ተከታዬች ናቸው ከሁሉ የሚበልጠው የዘላለም ሕይወት ጉዳይ ነውና!!!

Address

Adama
801

Telephone

+251911588378

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when God Grace Tv posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to God Grace Tv:

Share