Ethio Health

Ethio Health Here we are for better Health care

05/07/2026
25/06/2026
11/06/2026

Vacancy Announcement : Tazma Medical & Surgical Specialized Center

Location: Ethiopia, Addis Ababa, Gotera Condominium Compound
Positions

1. Position: Matron
Education: BSc in Nursing with relevant skills and experience (3 years of experience and above)
Required Number: 1

2. Position: Clinical Coordinator
Education: BSc in Nursing or Public Health with relevant skills and experience (1 year of experience and above)
Required Number: 2

3. Position: Clinical Nurse
Education: BSc in Nursing, 0 years of experience and above
Required Number: 5

4. Position: General Practitioner
Education: Degree in Medicine (MD), 0 years of experience and above
Required Number: 2

5. Position: Laboratory Technologist
Education: BSc in Medical Laboratory Technology, 0 years of experience and above
Required Number: 2

Application Deadline: June 18, 2026

N.B.: All applicants must possess a valid professional license. Please indicate the position you are applying for in the subject line of your email.

E-mail Address: [email protected]

In-Person Application: Tazma Medical & Surgical Specialized Center, Gotera Condominium Compound, Addis Ababa, Ethiopia

Gmail is email that’s intuitive, efficient, and useful. 15 GB of storage, less spam, and mobile access.

11/06/2026

ጉዳዩ፦ የአምስት ወር የትርፍ ሰዓት (Overtime) ክፍያ ጥያቄን እና የስራ ማቆም ማስጠንቀቂያን ይመለከታል
በመጀመሪያ እኛ በሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል የምንገኝ የጤና ባለሙያዎች፣ ማህበረሰባችን ጥራት ያለውና ቀልጣፋ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ ሌሊት ከቀን በቅንነት እና በቁርጠኝነት እያገለገልን እንገኛለን። የጤናው ዘርፍ የሚጠይቀውን ከፍተኛ መስዋዕትነት በመረዳት፣ ከተለመደው የስራ ሰዓት ውጭ እጅግ አድካሚ በሆነ ሁኔታ የትርፍ ሰዓት ስራዎችን ስንሸፍን ቆይተናል።
ነገር ግን ላለፉት አምስት (5) ወራት የሰራንበት የትርፍ ሰዓት ክፍያ እስካሁን ሊከፈለን አልቻለም። ይህ መዘግየት በባለሙያው ላይ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ፣ ስነ-ልቦናዊ እና ማህበራዊ ቀውስ እያስከተለ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት የጤና ባለሙያው ያለበትን ችግርና እንግልት በሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ማብራራት እንወዳለን፦
ከፍተኛ የኑሮ ውድነት እና እንግልት፦ ላለፉት አምስት ወራት ተገቢው ክፍያ ባለመፈጸሙ ምክንያት፣ ባለሙያዎች መሰረታዊ የኑሮ ፍላጎቶቻቸውን (የቤት ኪራይ፣ የምግብ እና የትራንስፖርት ወጪዎችን) መሸፈን አቅቶን ለከፍተኛ እንግልትና ለብድር ተጋልጠናል።
እኛ የጤና ባለሙያዎች በስራው ባህሪ ምክንያት በየቀኑ ለተለያዩ አደገኛና ተላላፊ በሽታዎች (እንደ ቲቢ፣ ሄፓታይተስ፣ ኤች.አይ.ቪ እና ሌሎች ወረርሽኞች) በከፍተኛ ሁኔታ የተጋለጥን እንገኛለን። ይህንን ህይወትን ለአደጋ የሚያጋልጥ ስራ እየሰራን፣ መሰረታዊ መብታችን የሆነው ክፍያ አለመከፈሉ ሞራላችንን በእጅጉ ነክቶታል።ያለ ምንም ተጨማሪ ክፍያ ለረጅም ሰዓታት መስራት በባለሙያው ላይ ከፍተኛ የአካልና የአእምሮ ድካም (Burnout) እየፈጠረ ይገኛል። ይህም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በህክምና አገልግሎት አሰጣጡ ላይ የራሱን አሉታዊ ጥላ ማሳረፉ የማይቀር ነው።
እስካሁን ድረስ ጉዳዩን በውይይት ለመፍታት እና የታካሚዎቻችን እንክብካቤ እንዳይጓደል በማሰብ በትዕግስት ስራችንን ስናከናውን ቆይተናል። ሆኖም ግን የችግሩ አሳሳቢነት ትኩረት ያጣ በመሆኑ እና የባለሙያው የመሸከም አቅም ማለቁን ለመግለጽ እንወዳለን።
ስለሆነም፣ ይህ ደብዳቤ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት ውስጥ ላለፉት አምስት ወራት ያልተከፈለን የትርፍ ሰዓት ክፍያ ሙሉ በሙሉ ተፈጽሞ እንዲጠናቀቅ እንጠይቃለን።
ይህ የማይሆን ከሆነ ግን፣ ከአቅም በላይ በሆነ የኢኮኖሚ እና የድካም ችግር ምክንያት ከ 8] ጀምሮ የትርፍ ሰዓት (Overtime) ስራዎችን ሙሉ በሙሉ የምናቆም መሆኑን በታላቅ አክብሮት እናሳውቃለን። በዚህም ምክንያት በሆስፒታሉ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ለሚፈጠረው ለማንኛውም ክፍተትና መስተጓጎል ኃላፊነቱን የሚወስደው ጥያቄያችንን በወቅቱ ያልመለሰው የሚመለከተው አካል መሆኑን እንገልጻለን።
የተፈጠረው ችግር ታይቶ በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጠው እንጠይቃለን።
ከአክብሮት ሰላምታ ጋር!
የሸጋው ሞጣ ጠ/ሆስፒታል ባለሙያዎች በሙሉ
ግልባጭ፦
ለሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክቶሬት
ለምስ/ጎጃም ጤና ፅ/ ቤት
ለጤና ባለሙያዎች ተወካዮች ኮሚቴ
ለአብክመ ጤና ቢሮ
ለሆስፒታል ቦርድ ሰብሳቢ
ለሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ
ለሞጣ ከተማ ከንቲባ ፅ/ቤት
ለሞጣ ከተማ ብልፅግና ፅ/ቤት
ለሁት እጁ ብልፅና ፅ/ቤት
ለሁለት እጁ ፍትህ ፅ/ቤት
ለሞጣና አካባቢው ኮማንድ ፖስት ሀላፊ

2025 updates
10/02/2026

2025 updates

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Health posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share