22/09/2022
በእርግዝና ወቅት የተመጣጠነ ምግብ መመገብ አስፈላጊ ነው።
♦️የወተት ተዋጽኦዎች
በእርግዝና ወቅት, የፅንሱን ፍላጎቶች ለማሟላት ተጨማሪ ፕሮቲን እና ካልሲየም ማግኘት ያስፈልጋችኋል። እንደ ወተት ፣ አይብ እና እርጎ ያሉ የወተት ተዋጽኦዎች ለዚህ ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳሉ።
የወተት ተዋጽኦዎች ከፍተኛ የፕሮቲን እንዲሁም የካልሲየም ምንጭ ናቸው።
እርጎ፣ ከሌሎች የወተት ተዋጽኦዎች በበለጠ ካልሲየምን ይይዛል። ከዚህም ሌላ የወተት ተዋፅዖዎች የምግብ መፈጨትን ጤንነት የሚደግፉ ፕሮባዮቲኮችን ይይዛሉ።
♦️ስኳር ድንች
ስኳር ድንች ጣፋጭ ብቻ ሳይሆን በቤታ ካሮቲን የበለፀገ ነው ። ይህም ውህድ በሰውነታችሁ ውስጥ ወደ ቫይታሚን ኤ የሚቀየር ውህድ ነው።
ቫይታሚን ኤ ለህፃኑ እድገት አስፈላጊ ነው።
ስኳር ድንች በቂ የእጽዋት-ተኮር የቤታ ካሮቲን እና የፋይበር ምንጭ ነው። ፋይበር የደም ስኳር መጠንን ይቀንሳል እና የምግብ መፈጨትን ጤና ያሻሽላል (ይህ በእርግዝና ጊዜ የሚከሰተውን የሆድ ድርቀት ለመከላከል ይረዳል ።
♦️እንቁላል
እንቁላል ሁሉንም ከምግብ የሚገኙትን ንጥረ ነገሮች ከሞላ ጎደል በጥቂቱ ስለሚይዝ ዋናው የምግብ አይነት ነው። አንድ እንቁላል ወደ 80 ካሎሪ, ከፍተኛ ጥራት ያለው ፕሮቲን, ስብ እና ብዙ ቪታሚኖች እና ማዕድናት ይይዛል።
ከዚህም ሌላ እንቁላል በእርግዝና ወቅት ጠቃሚ የሆነ የ choline ምንጭ ነው። ይህም ለፅንሱ ወይም ለህፃኑ አእምሮ እድገት ጠቃሚ ነው እና የአዕምሮ እና የአከርካሪ እድገቶች መዛባትን ለመከላከል ይረዳል።
አንድ እንቁላል በግምት 147 ሚሊግራም (ሚሊግራም) choline ይይዛል፣ ይህም በእርግዝና ወቅት በቀን ከሚያስፈልጋችሁን 450 ሚ.ግ የcholine መጠን ጋር ተቀራራቢ ያደርገዋል።
♦️ብሮኮሊ
ብሮኮሊ እና አረንጓዴ አትክልቶች፣ ለምሳሌ ስፒናች፣ በእርግዝና ወቅት የሚያስፈልጋችሁን ብዙ ንጥረ ነገሮች የያዙ ናቸው።
እነዚህም ፋይበር፣ ቫይታሚን ሲ፣ ቫይታሚን ኬ፣ ቫይታሚን ኤ፣ ካልሲየም፣ ብረት፣ ፎሌት እና ፖታሲየምን ያካትታሉ።
ከዚህም በተጨማሪ አትክልቶች በዝቅተኛ ክብደት የመውለድ እድላችሁን ይቀንሳሉ።
♦️አቮካዶ
አቮካዶ ብዙ monounsaturated ፋቲ አሲድ የያዘ ነው። ይህም ማለት ከፍተኛ የእፅዋት ስብ ማለት ነው።
በተጨማሪም አቮካዶ በፋይበር፣ በቫይታሚን ቢ (በተለይ ፎሌት)፣ ቫይታሚን ኬ፣ ፖታሲየም፣ አይረን፣ ቫይታሚን ኢ እና ቫይታሚን ሲ የበለፀገ ነው።
ከፍተኛ መጠን ያለው ጤናማ ስብ፣ ፎሌት እና ፖታሲየም ይዘት ስላለው አቮካዶ በእርግዝና ወቅት (እና ሁልጊዜም) በአመጋገብ ውስጥ ተመራጭ ምግብ ነው።
በአቮካዶ ውስጥ ያሉት ቅባቶች የፅንሱን ቆዳ፣ አእምሮ እና ቲሹዎች እንዲገነቡ ያግዛሉ፣ እና ፎሌት የነርቭ ቱቦ ጉድለቶችን፣ የአንጎል እና የአከርካሪ እክሎችን እንደ ስፒና ቢፊዳ ያሉ እድገቶችን ለመከላከል ይረዳሉ።
ፖታስየም የእግር ቁርጠትን ለማስታገስ ሊረዳ ይችላል። ይህም በአንዳንድ ሴቶች ላይ በ እርግዝና ጊዜ የሚኖር የጎንዮሽ ጉዳት ነው።
♦️ውሃ
በእርግዝና ወቅት, የደም መጠን በ 45 በመቶ ገደማ ይጨምራል።
ሰውነትታችሁ እርጥበትን ወደ ፅንሱ ያሰራጫል,። ይህም የሚወሰነው የውሃ አወሳሰዳችሁ ላይ ይወሰናል።
የውሃ አወሳሰድን መጨመር የሆድ ድርቀትን ለማስታገስ እና በእርግዝና ወቅት የተለመዱትን የሽንት ቱቦዎችን ኢንፌክሽኖችን የመያዝ እድልን ይቀንሳል።
ቀላል የሰውነት ድርቀት ምልክቶች ራስ ምታት፣ ጭንቀት፣ ድካም፣ መጥፎ ስሜት እና የማስታወስ ችሎታ መቀነስ ናቸው።
እርጉዝ ሴቶች በየቀኑ (2.3 ሊትር) ውሃ እንዲጠጡ ይመከራል። ነገር ግን ይህ እንደ ፍላጎታችሁ መጠን ይለያያል።
ከሌሎች ምግቦች እና መጠጦች ለምሳሌ ከፍራፍሬ እና አትክልት ውሃን ማግኘት ትችላላችሁ።