28/05/2026
፡ የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ፦
ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የብቃት ምዘና ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ ወይም በድጋሚ ለመውሰድ ስማችሁን ከፋይዳ ቁጥራችሁ ጋር አስተሳሰራችሁ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ የጤና ሙያ ተመራቂዎች በሙሉ፤ ጤና ሚኒስቴር በሰኔ ወር 2018 ዓ.ም ፈተናውን ለመስጠት እየተዘጋጀ በመሆኑ ሁላችሁም ተመዛኞች ከግንቦት 20 – 26/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ https://hple.moh.gov.et/ ማስፈንጠሪያ /Link/ በመጫን FAYDA and Password በማስገባት የፈተና ጣቢያ እንድትመርጡ ጤና ሚኒስቴር ያሳስባል።
🎯ማሳሰቢያ፦
▪ እያንዳንዱ የፈተና ጣቢያ በየሙያ መስኩ ማስተናገድ በሚችለው ከፍተኛ የተመዛኝ ቁጥር ልክ ገደብ ስለተቀመጠለት የፈተና ጣቢያ ምርጫ ቀድማችሁ በማጠናቀቅ ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ከፍተኛው የተመዛኝ ቁጥር በደረሰበት የፈተና ጣቢያ ላይ ተጨማሪ ምዝገባ ማከናወን የማይቻል መሆኑን እናሳስባለን።
▪ ለብቃት ምዘና ፈተና የመፈተኛ ጣቢያ መምረጥ የምትችሉት ስማችሁን ከፋይዳ ቁጥር ጋር ያያያዛችሁ ተመዛኞች ብቻ ይሆናል፡፡
▪ በምዝገባ ወቅት ለሚገጥማችሁ ማንኛውም ችግር በነጻ የስልክ መስመር 952 በመደወል ከዚያም 3 ቁጥርን በመጫን በቀጥታ እገዛ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳስባለን፡፡