10/04/2022
በወቅቶች መቀያየር ምክንያት የሚፈጠር አለርጂ
በወቅቶች መቀያየር ምክንያት የሚፈጠር አለርጂ ወይም Seasonal allergy እየተባለ የሚጠራው የህመም አይነት ጉንፋን መሰል ምልክቶች ያሉት ወቅቶች ሲፈራረቁ ወይም በዓመት አንዴ የሚከሰት የአለርጅ አይነት ነው፡፡
ምልክቶች
📌 የጆሮ ህመም፣ራስ ምታት፣የጉሮሮ መከርከር
📌 የአፍንጫ መደፈን፣ያለማሽተት እንዲሁም ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ መብዛት
📌 ማስነጠስ፣የአክታ ስሜት መሰማት፣ማሳል
📌 የአይን ማሳከክ፣መቅላት፣ ማስለቀስ እና ማበጥ
📌 ድብርት
📌 የድካም /አቅም ማጣት/ ስሜት
📌 የምግብ ፍላጎት መቀነስ የመሳሰሉት ናቸው፡፡
ወቅታዊ የአፍንጫ አለርጂን የሚቀሰቅሱ ነገሮች
📌 እርጥበት እና ቅዝቃዜ
📌 ጭስ
📌 የዛፍ ፣የአበባ/አረምና የሳር ሽታዎች
📌 በሞቃታማ ወቅት የአፍንጫ አለርጂን የሚያባብሱ
መፍትሄው
📌 የሚያስነሳብንን ነገሮች በመለየት እሱን ለመከላከል መሞከር
📌 ቫይታሚን ሲ አዘውትሮ መውሰድ
📌 በተቻለን መጠን የአየር ሁኔታው የማይስማማን ከሆነ ቦታ ለመቀየር መሞከር
📌 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
📌 በቅዝቃዜ እና በብናኝ ለሚፈጠር አለርጂ አልፎ አልፎ እንፋሎት መታጠን
በዶ/ር አለ