23/05/2026
!
ስንፈተ ወሲብ (Erectile Dysfunction) በወንዶች ላይ በብዛት የሚከሰት ነገር ግን በግልፅ ለመነጋገር የሚፈራ የጤና ችግር ነው። ችግሩ ወሲባዊ ግንኙነት ለመፈጸም የሚያስችል የብልት መነሳት ማጣት ወይም የቆመውን ብልት እስከ ግንኙነቱ ፍጻሜ ድረስ ማቆየት አለመቻል ነው።
ይህ ችግር ሙሉ በሙሉ ሊታከም የሚችል ሲሆን፣ መንስኤዎቹን እና መከላከያ መንገዶቹን ማወቅ መፍትሄውን ያቀልላል።
1. አካላዊ ችግሮች፦ የስኳር በሽታ፣ ከፍተኛ የደም ግፊት፣ የልብ ህመም እና የሆርሞን መዛባት።
2. የአኗኗር ዘይቤ፦ ሲጋራ ማጨስ፣ ከመጠን በላይ አልኮል መጠጣት፣ ጫት መቃም እና ስፖርት አለመስራት።
3. ሥነ-ልቦናዊ ምክንያቶች፦ ከመጠን ያለፈ የኑሮ ውጥረት (Stress)፣ ጭንቀት እና ድብርት።
1. ጤናማ አመጋገብ፦ የቅባት ምግቦችን በመቀነስ ፍራፍሬ፣ አትክልትና አሳ መመገብ።
2. አካል ብቃት እንቅስቃሴ፦ የደም ዝውውርን ለማሻሻል ዘወትር ስፖርት መስራት።
3. ሱሶችን ማስወገድ፦ ሲጋራ፣ አልኮል እና ጫት መጠቀምን ማቆም ወይም መቀነስ።
4. የጤና ክትትል፦ የደም ግፊት እና ስኳርን በየጊዜው መለካት።
#የህክምና አማራጮችበሀኪም የሚታዘዙ የአፍ ውስጥ መድሃኒቶችበብልት አካባቢ የደም ዝውውርን የሚያሻሽል የሾክዌቭ ህክምና (Shockwave Therapy)የሆርሞን ማነስ ላለባቸው የሚሰጥ የሆርሞን መተኪያ ህክምናከጭንቀት ጋር የተያያዘ ከሆነ የስነ-ልቦና ምክር አገልግሎት (Counseling)👉 መልዕክታችን፦ ስንፈተ ወሲብ የጤና ችግር እንጂ የውርደት ምንጭ አይደለም! ችግሩ ካጋጠመዎት በራስ የመተማመን ስሜትዎን ሳይነካ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ የህክምና ባለሙያ ያማክሩ።
#የወንዶችጤና #ስንፈተወሲብ #ጤናማህይወት
0921785903
0932338485