የጤና መረጃ

የጤና መረጃ This page is Created to provide BEST Medical information ወዳጅ ዘመድዎ እንዲደርሰው ሼር በማድረግ ያሳውቁ
FACEBOOK
www.facebook.com/ethiomedhealth
ፔጃችንን Like በማድረግ ይከታተሉን
(1)

10/05/2026

!!!
ልጆች ስሜታቸውን እንዲቆጣጠሩ ማስቻል
==========================
ልጆች ሲያድጉ ደስተኛ እና ስኬታማ እንዲሆኑ ከሚያስችሉ ነገሮች ዋነኛው ስሜትን መቆጣጠርና ጊዜያዊ ፍላጎትን ለዘላቂ ደስታ ሲሉ ማሳለፍ መቻል ነው። ይህንን ለማድረግ የሚያግዙ 4 ነጥቦች።

1) የመጀመሪያው አመት ወሳኝ ነው፦
በዚህ እድሜ ህፃናቱ ንግግር ስለማይችሉ ፍላጎታቸውን በለቅሶ ነው የሚገልፁት። የመጀመሪያ አመት ላይ በቂ ትኩረት ካገኙ ወደፊት በራስ የመተማመናቸው ከፍ ያለ ይሆናል። "ማቅበጥ እንዳይሆን" ብላችሁ ለምትሰጉ ወላጆች የመጀመሪያ አመት ላይ በጭራሽ ልታቀብጡ አትችሉም። እንደውም የመጀመሪያ አመት ላይ በደንብ እንክብካቤ መስጠት በኋላ ስራ ይቀንስላችኋል።

2) በልጆችዎ እይታ ውስጥ ኖት፦
አንዳንድ ዘመናዊ ህንፃዎች ውስጥ "በካሜራ እይታ ውስጥ ኖት።" የሚል ፅሁፍ አለ። በቅርቡ ደግሞ "በኮሮና እይታ ውስጥ ኖት" በሚል ተቀይሯል።😁 ወላጆች ደግሞ በልጆቻችሁ እይታ ውስጥ ናችሁ። ልጆች በመመልከትና አርአያነትን በመከተል (Observational learning and modeling) ብዙ ነገር ይማራሉ።

3) ስሜቶች በራሳቸው ችግር እንደሌላቸው ማስተማር፦
ሁሉም ስሜቶች ጠቃሚ ናቸው። ነገር ግን የምንገልፅበት መንገድ ችግር ሊፈጥር ይችላል። ለምሳሌ አንድ ልጅ ተናዶ ታናሽ ወንድሙን ቢመታ "እንደተናደድክ ተረድቻለሁ። ነገር ግን እኛ ቤት ውስጥ አንዱ ሌላውን መምታት አይቻልም።" ስንለው መናደድ ችግር እንደሌለው ነገር ግን ንዴቱን የሚገልፅበትን መንገድ መምረጥ እንዳለበት ጠቆምነው ማለት ነው።

4) ስሜትን መቆጣጠር ወጥ በሆነ መልኩ ማስተማር። ለምሳሌ፦ እናትም አባትም በአንድ አቋም
"ፊልም የምታየው የቤት ስራህን ከጨረስክ በኋላ ነው።"
"ኬክ የምትበላው እራትህን ከበላህ በኋላ ነው።"
"ብስክሌት እንደፈለግህ ተረድቻለሁ። ነገር ግን አሁን በቂ ብር ስለሌለኝ በየወሩ አጠራቅሜ ሰኔ ላይ እገዛልሀለሁ።"....

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

10/05/2026

📌"ልጄን ብርድ መታት" .... ብርድ የሚባል በሽታ አለ ወይስ የለም?
ብዙውን ጊዜ በስራ ገበታ ጨቅላ ሕፃናት ለህክምና ሲመጡ ተሸፋፍነው ሲሆን ለምርመራም እናት ልብስን ገልጣ ማሳየት ይከብዳታል ምክንያት ብርድ እንዳይመታት ወይም እንዳይመታው ይባላል።
ልጆችም ከረጅም የቤት ውስጥ ቆይታ ወደ ትምሀርት ገበታቸው እየተመለሱ እንደመሆኑ ብዙ የሚያስሉ ሕፃናት መመልከት የተለመደ እንደመሆኑ ይህን እንደ መነሻ አሳብ ለዚህ ፅሁፍ በመውሰድ እስኪ ስለ ልጆች የሳምባ ምች (ኒሞኒያ) ትንሽ ጀባ ልበላችሁ
- እናቶች ልጄን ብርድ መታው የሚሉት ነገር እሳ?
ሳምባ ምች (ኒሞኒያ) ማለት የሳንምባችን የታችኛው እና የመጨረሻው ክፍል በኢንፌክሽን ወይም በኬሚካል ሲጠቃ ሳንባችን ሲቆጣ እና ሲታመም የሚከሰት በሽታ ነው።
ሳምባችን ለሰውነታችን ኦክስጅን የሚባለውን ጠቃሚ አየር የምናስገባበት እና ካርቦንዳይ ኦክሳይድ የሚባለውን የተቃጠለ አየር የሚናስወግድበት አካላችን እንደመሆኑ ይህ የሰውነታችን አካል በተለያዩ ነገሮች የመጎዳት እድል ሲገጥመው ይህ ተግባር ይስተጓጉላል። ከነዚ ውስጥ ዋነኛው ደሞ ኒሞኒያ የሚባለው በሽታ ነው።
ይህ የማይታይ ጀርም ወደ ሳምባችን በሚገቡ ጊዜ ሳንባችን ዉስጥ ያሉ ህዋሳት በከፍተኛ መጠን ስለሚቆጡ አየር የሚቀያየርበት የሳምባ ቅንጣት አካላት (Alveolus) በፈሳሽ ነገር ይሞላሉ በዚህም ምክንያት ጠቃሚውን ኦክስጅን የማስገባት እና ጠቃሚ ያልሆነውን ካርበን ኦክሳይድ የማስወጣት ኢደትን ስለሚገታ ሰውነታችን በቂ የሆነ ኦክስጅን እንዳያገኝ ያደርገዋል። ይህም የኦክስጅን እጥረት በወቅቱ ካልታከመ እስከ ህይወት ህልፈት ሊያስከትል ይችላሉ ።
እንደ ዓለም የጤና ድርጅት (WHO) መረጃ መሰረት በ2017 ብቻ በዓለም ላይ 808,694 እድሜያቸው ከ 5 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት በሳምባ ምች ምክንያት ህይወታቸውን አተዋል:: ይህም ከአጠቃላይ የልጆች ሞት 15% ይይዛል:: እንዲሁም በአገራችን እድሜያቸው ከ 5 ዓመት በታች ካሉ ህፃናት ገዳይ በሽታዎች የሳምባ ምች ዋነኛው ገዳይ በሽታ እንደሆነ ያውቃሉን 😱👌።
- የሳምባ ምች መንስኤው ምንድነው?
ይህ በሽታ ብዙ ጊዜ በአይን በማይታዩ የበሽታ አምጭ ጀርሞች ማለትም በቫይረስ ፣ በባክቴርያ ፣ በፕሮቶዝዋ አልፎ አልፎም በፓራሳይት አማካኝነት ሊመጣ ይቻላል:: ከነዝህም ዉስጥ በአብዛኞቹ ጀርሞች በሳል ወይም በንጥሻ ወቅት በትንፋሽ የሚተላለፉ ናቸው :: ከነዚህ በሽታ አምጭ ጀርሞች በተጨማሪም ኒሞኒያ በተለያዩ ኬሚካሎችም ሊመጣ ይቻላል:: ለምሳሌ የጨጓራ አሲድ በድንገት ወደ ሳምባ ሲገባ ልጆች በድንገት ኬሚካሊ ሲጠጡ ለምሳሌ ኬሮሲን ወዘተ ሳንባ ውስጥ የመግባት እድል ሲያገኙ ኒሞኒያ ሊያስከትሉ ይችላል:: ከ5 ዓመት በታች ያሉ ልጆች ላይ የሳምባ ምች ብዙ ጊዜ መንስኤው ቫይረሶች ሲሆኑ የሚጀምረውም በጉንፋን መሰል ምልክቶች ነው።
- የትኞቹ ልጆች ናቸው በዋነኛነት ለሳንባ ምች የሚጠቁት?
1. የላይኛው የትንፋሽ አካላት ኢንፌክሽን ለምሳሌ ጉፋን፤ የቶንሲል ኢንፌክሽን እና የመሳሰሉት ሲይዛቸው
2. ቤት ዉስጥ የሚጨሱ ማንኛዉም የጭስ አይነቶች ለምሳሌ የሲጋራ እጣን ሺሻ የከሰል እና የእንጨት ጭሶች ዋነኛዎቹ ናቸው። በሀገራችን በከፍተኛ መጠን ብዙ ህፃናትን ለሳምባ ምች እያጋለጣቸው ይገኛል::
3. ዝቅተኛ የበሽታ መከላከል አቅም ያላቸው (በምግብ እጥረት ወይም በተለያዩ በሽታዎች ምክንያት ለምሳሌ HIV, Cancer etc)
4. በጣም ተጠጋግቶ መኖር እና በቂ የሆነ የአየር ዝውውር በሌለበት ቤት እና አካባቢ መኖር
5. የሳምባ የተፈጥሮ ችግሮች
6. የቫይታሚን ዲ እጥረት (ሪኬትስ)፦ በተለይ ፀሐይ በደምብ ያልሞቁ ህፃናት ለሳምባ ምች ተጋላጭ ናቸው::
- በሳንባ ምች የተጠቃ ልጅ ምን አይነት ምልክቶቹች ያሳያል?
★ ቶሎ ቶሎ መተንፈስ
★ ትንፋሽ ማጠር እና ለመተፈስ መቸገረ
★ ትኩሳት
★ ማቃሰት
★ ትውከት
★ ማስመለስ
★ የምግብ ፍላጎት መቀነስ
★ የደረት ውጋት ወይም ህመም
★ ሲተነፍሱ የታችኛው ደረት ክፍል ወደ ዉስጥ ግብት ግብት ማለት ዋና ዋናዎቹ ናቸው::
ልብ ይበሉ ልጆት ላይ እነዚህ የተጠቀሱት ምልክቶችን ከተመለከቱ ባፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም በመውሰድ ማሳከም ይኖርቦታል ::
- የሳምባ ምች መከላከያ መንገዶች ምንድናቸው?
★ ክትባት በወቅቱ ማስከተብ
★ ቤት ዉስጥ ማንኛዉም ጭስ አለማጨስ
★ ቤት ዉስጥ በቂ የአየር ዝውውር እንዲሮር ያድርጉ
★ ልጅዎን የተመጣጠነ ምግብ ይመግቡ
★ እስከ 6 ወር የእናት ጡት ወተት ብቻ መስጠት
★ ልጆች የፀሀይ ብርሃን በበቂ ሁኔታ እንዲያገኙ ያድርጉ
★ ልጆችን ጉንፋን ከያዛቸዉ ሰዎች ወይም ልጆች በተቻለ መጠን ያርቁ
በመጨረሻም ብርድ የሚባል በሽታ አለ ወይስ የለም? ለሚለው ጥያቄ በአጭሩ በዘመናዊ ሕክምና ዉስጥ ብርድ የሚባል ነገር በልምድ ይህንኑ ነው ! አንዳንድ ሰዎች ብርድ የሚለውን ቃል ከሳምባ ምች (ኒሞኒያ) ጋር ሲያምታቱ ይታያል ይሄ ትክክል አይደለም ቀዝቃዛ አየር የሳምባ ምች አያመጣም ! በርግጥ ቀዝቃዛ አየር ሊያነሳሳቸው የሚችሉ በሽታዎች ይኖራሉ ለምሳሌ የአፍንጫ ወይም የሳይነስ አለርጂ አስም ወዘተ የመሳሰሉት :: ለማንኛዉም ማህበረሰቡ ብርድ የሚለውን ቃል ምን ለማለት ፈልጎ እንደሆነ ማወቁ አይከፋም።

09/05/2026


04/05/2026

✅ በወር አበባ ጊዜ ያለ
ህመም(Dysmenorrhea)
=======[[=============i
➤ ከወር አበባዎ በፊት ወይም በወር አበባ ወቅት ህመም መሰማት በጣም የተለመደ ነው፡፡ በወር አበባቸው ወቅት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሴቶች እና ልጃገረዶች በወር ከ 1 እስከ 2 ቀናት ውስጥ ህመም ይኖራቸዋል

➤ በወር አበባ ጊዜ ከሚከሰት ህመም ጋር የተያያዙ ምልክቶች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ

በታችኛው ሆድ ወይም ጀርባ ላይ የህመም ስሜት

ማቅለሽለሽ

ማስታወክ

ተቅማጥ

ራስ ምታት

በወር አበባዎ ወቅት ህመሙ ከባድ ከሆነ የእንቅልፍ ችግር ሊያጋጥምዎም ይችላል፡፡
✅ የወር አበባ ህመም መንስኤው ምንድን ነው?

በወር አበባ ወቅት ማህፀን ይኮማተራል፡፡

በተጨማሪ ማህፀን ፕሮስታግላንዲን(prostaglandins) የተባሉ የተፈጥሮ ኬሚካሎችን ይለቃል።

እነዚህ ኬሚካሎች ቁርጠት ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ ይህ ዋና ምክያት ሲሆን በተጨማሪም በሌሎች ከማህጽን ችግር ጋር ተያይዞ ሊከሰት ይችላል፡፡ ከነዚህ መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል

📌ኢንዶሜትሪዮሲስ(Endometriosis)

📌በኦቭየርስ ውስጥ ያለ ሲስት(Cysts in the ovaries)

📌አዴኖማዮሲስ(Adenomyosis)

📌ፋይብሮይድስ(Fibroids/Myoma)

✅ በወር አበባ ጊዜ ህመምን በተመለከተ ወደ ህክምና መሄድ ያለብኝ መቼ ነው?

ከትምህርት ቤት ወይም ከስራ ካስተጓጎለ ወይም የእለት ተእለት እንቅስቃሴዎን ሊያስተጓጉልዎት ይችላል፡፡ በተለይም ህመምዎ ከባድ ከሆነ፣ ከወትሮው የከፋ ከሆነ ወይም በየወሩ ህይወትዎን ከባድ የሚያደርግ ከሆነ ወደ ህክምና መሄድ እና እርዳታ ማግኘት በጣም አስፈላጊ ነው።

✅ የወር አበባ ህመም እንዴት ይታከማል?

እንደ ibuprofen ያሉ የህመም ማስታገሻዎች ቁርጠትን ሊያቀልሉ ይችላሉ። የወር አበባዎ ከመድረሱ ከ 1 እስከ 2 ቀናት በፊት የህመም ማስታገሻ መውሰድ ከጀመሩ እና በመጀመሪያዎቹ 2 እና 3 ቀናት ደም መፍሰስ ከቀጠሉ በተሻለ ሁኔታ ሊሰራ ይችላል።

እንደ የወሊድ መከላከያ ክኒኖች ወይም ሆርሞናዊ ውስጠ-ማህፀን መሳሪያ የወሊድ መከላከያ (IUD) ያሉ የሆርሞን ህክምና የወር አበባ ህመምን ሊቀንስ ይችላል።

መድሀኒት ህመሙን ካልቀነሰው ወይም ካላስወገደው ምክንያቱን ለማወቅ ምርመራዎችን ማድረግ ያስፈልጋል። እንደ ኢንዶሜሪዮሲስ( Endometriosis) ወይም ፋይብሮይድስ(Fibroids/myoma) ያሉ የጤና እክል ካለብዎ የተለየ ህክምና ሊያስፈልግ ይችላል።

ስነተዋልዶ ጤና ዙሪያ ጠቃሚ ጽሁፎች ለማንበብ ገፃችን ይቀላቀላሉ

የጤና መረጃ

04/05/2026

#ጤና #መረጃ
በእርግዝና ወቅት አነዚህ ምግቦች አትመገቡ
🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫
1.ጥሬ ስጋ/የትኛውም አይነት ያልበሰለ ስጋ
⭐️በተለይም ደግሞ ለፅንስ እጅግ አደገኛ ቶክሶፕላዝማ የተባለ ህዋስ እንቁላል ወይም ሲስት በጥሬ ስጋ ውስጥ ሊኖር ስለሚችል በፅንስ ላይ ውርጃን፣የፅንስ ኪሎ መቀነስ፣መቀንጨር፣ የጭንቅላት መስፍትና መተለቅ እንዲሁም የእድገት መዘግየት ሊያስከትል ይችላል።ከዚህ በተጨማሪ ሊስቴሪያ፣ሳልሞኔላ እንዲሁም ኢኮላይ የተባሉ የባክቴሪያ አይነቶች በጥሬ ስጋ ውስጥ ሊገኙ ስለሚችሉ ፅንስን ሊጎዱ ይችላሉ።
🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫
2.ያልበሰለ ጥሬ አሳ ስጋ
⭐️ ያልበሰለ ጥሬ አሳ ከላይ የተጠቀሱትን የባክቴሪያና የፓራሳይት አይነቶች የተበከለ ሊሆን ስለሚችል ባይበላ የተሻለ ነው። ከዚህ በተጨማሪም
አንዳንድ የአሳ አይነቶች ከፍተኛ የሜርኩሪ መጠን ያላቸው ሲሆን ይህም በፅንስ አእምሮ በመከማቸት የአእምሮ እድገት ዝግመት እንዲሁም የዕድገት መዘግየት ሊያስከትል ይችላል።
🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫
3.ያልተፈላ ወተት
⭐️ በአግባቡ ያልተፈላ ወተት በውስጡ የተለያዩ ፅንሱን ሊጎዱ የሚችሉ ባክቴሪያዎች ሊይዝ ይችላል።ሳልሞኔላ፣ሊስቴሪያ ሞኖሳይቶጂን እንዲሁም ብሩሴላ የተባሉ ባክቴሪያዎች ፅንስን በከፍተኛ ሁኔታ ሊጎዱ የሚችሉ ሲሆን አንዳንዶቹ ፅንስን የሚያጨናግፉ ውርጃ የሚያስከትሉ እንዲሁም ምጥ ካለጊዜው እንዲመጣ የሚያደርጉ ናቸው።
ሁልጊዜ ወተት ስትጠጡ የተፈላና ፓስቸራይዝድ የሆነ መሆኑን አረጋግጡ
🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫

4.በአግባቡ ያልታጠበ ሰላጣና አትክልት
⭐️ ያልታጠበ ሰላጣና የተለያዩ አግባቡ ያልታጠቡ የአትክልት ውጤቶች በባክቴሪያና በተለያዩ ጎጂ የአንጀት ትላትል እንቁላሎች የተበከሉ ሊሆኑ ይችላሉ።ይህም እንደ አሜባ፣ጃርዲያ፣ብሩሴላ፣ሊስቴሪያ ያሉ ጎጂ ተህዋሲያን የተበከሉ ሊሆኑ ይችላሉ።
🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫

5.ካፌይን የበዛባቸው መጠጦች
⭐️ እንደ ቡና እና ሻይ ያሉ ካፌይን የበዛባቸው መጠጦች ማብዛት ፅንስ ላይ የኪሎ መቀነስ ካለጊዜው መወለድ እንዲሁም መቀንጨርን ሊያስከትሉ ይችላሉ።የአለም የጤና ድርጅት እንደሚያዘው አንዲት ነፍሰጡር ሴት በቀን ከ2ስኒ ቡና በላይ መጠጣት የለባትም።
🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫🚫
6.አልኮሆል
⭐️ የትኛውም መጠን ያለው አልኮል በእርግዝና ጊዜ መወሰድ የለበትም።
በእርግዝና ጊዜ የሚወሰድ የትኛውም መጠን ያለው አልኮል በፅንስ ላይ ጉዳት
ያስከትላል። በተለይም ደግሞ በእርግዝና የመጀመሪያ ክፍል ወይም የመጀመሪያ 3 ወር (First Trimester) የሚወሰዱ ከሆነ በፅንስ ላይ የሚያስከትለው ጉዳት የከፍ ነው።
በአልኮሆል መጠጦች ውስጥ የሚገኘው ኢታኖል(Ethanol) የተባለው ኬሚካል የፅንስ አፈጣጠር ችግር(Malformation) እንዲከሰት በማድረግ መከላከል ከምንችላቸው ምክንያቶች ቀዳሚውን ደረጃ ይይዛል።

30/04/2026

#ጤና
✅✅ በእርግዝና ወቅት ፓፓያ እና አናናስ መብላት ተገቢ ነውን ?

እንደ ሮያል የማህፀንና የጽንስና ሀኪሞች ኮሌጅ (RC0G) እና የአሜሪካ የጽንስና የማህፀን ሐኪሞች ኮሌጅ (ACOG) ካሉ ድርጅቶች የተሰጡ መደበኛ የሕክምና መመሪያዎች እንደዋና የህክምና መመርያ መከተል እና ለሚሰጡ ህክምናዎች ከነዚህ መመርያዎች አለመራቅ በመላው አለም የሚመከር ሲሆን ሁለቱም የህክምና መመርያዎች በእርግዝና ወቅት ፓፓያ አለመብላትን አይመክሩም ።

በተቃራኒው በእነዚህ መመሪያዎች መሰረት በአጠቃላይ በእርግዝና ወቅት ሁለቱንም መመገብ ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን በግልፅ ያሳያሉ።

✅ የበሰለ ፓፓያ ጥቅሞች

በቫይታሚን ኤ፣ ቢ እና ሲ እንዲሁም ቤታ ካሮቲን፣ ቾሊን፣ ፋይበር የበለፀገ ነው። የበሰለ ፓፓያ በእርግዝና ወቅት ብቻ ሳይሆን በተለይም እንደ የሆድ ድርቀት ያሉ የምግብ መፈጨት ችግሮችን ለመፍታት ጠቃሚ መሆኑን የተመሠከረለት ነው።

✅ ያልበሰለ ፓፓያ በእርግዝና መጠቀም የሚያስከትለውን ጉዳት ።

ያልበሰለ ፓፓያ የላቴክስ እና ፔፒን በውስጡ የያዘ ሲሆን ይህም የማኅፀን መኮማተር፣ ደም መፍሰስ እና የፅንስ ከረጢት ከማህፀን እንዲለይ ያደርጋል። የእነዚህ ንጥረ ነገሮች ተጽእኖ ከሰው ወደ ሰው ሊለያይ ይችላል ነገርግን በአጠቃላይ በእርግዝና ወቅት ያልበሰሉ ፓፓያዎችን ከመጠቀም መቆጠብ ሊያስከትሉ የሚችሉ ችግሮችን ለማስወገድ ይመከራል።

✅ አናናስ በእርግዝና ወቅት ጎጂ ነው የሚለውን የተሳሳተ ግንዛቤ ማብራሪያ

ይህም ህመምን፣ ደም መፍሰስን ወይም ያለጊዜ ምጥ ሊፈጥር ይችላል የሚለው የተዛባ ነው። አናናስ የፕሮቲን ትስስርን የሚሰብር ብሮሜሊን የተባለ ኢንዛይም በውስጡ ቢይዝም በቫይታሚን ሲ፣ ፋይበር እና አንቲኦክሲዳንትስ ምክንያት ደህንነቱ የተጠበቀ እና ጠቃሚ ነው። ከመጠን በላይ መመገብ ወደ አሲድነት ወይም ወደ ቃር ሊያመራ ይችላል። አናናስን በአመጋገብ ውስጥ ማካተት እና በእርግዝና ወቅት ለተመጣጣኝ አመጋገብ አስተዋፅኦ ያደርጋል ፣ ይመከራል።

27/11/2025

═════════════════
ልጆች መቼ ነው አልጋ ላይ መሽናት የሚያቆሙት?
═════════════════
አብዛኞቹ ህፃናት 5 ዓመት ሲሆናቸው ሌሊት ላይ ሽንታቸውን መቆጣጠር ይችላሉ:: ሆኖም 10-15% የሚሆኑ ህፃናት እስከ 7 አመታቸው ድረስ ይቸገራሉ፡፡ ሽንት ለሊት ሊያመልጣቸው ይችላል፡፡ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ይህ ችግር ያለባቸው ህፃናት እድሜያቸው በ 1 ዓመት በጨመረ ቁጥር ቺግሩ በ15% እየቀነሰ ይሄድና እድሜያቸው 15 ዓመት ሲሞላ 99 በመቶ ህፃናት ከዚህ አይነቱ ችግር ሙሉ ለሙሉ ነፃ ይሆናሉ፡፡
::
ሆኖም አንድ ሕጻን 6 አመት እና ከዛ በላይ ሆኖ ሽንትን ለመቆጣጠር ካልቻለ ወላጆች ሐኪም መማከር አለባቸው፡፡ ሽንትን መቆጠጠር ያለመቻል ችግር በወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ላይ ከሚፈጥረው ስነ-ልቦናዊና ማሕበራዊ ተፅዕኖ ይልቅ በልጆች ላይ የሚፈጥረዉ ስነ ልቦናዊ ተፅዕኖ እጅግ የበረታ ነው፡፡
ወላጆች ሊያወቁት የሚገባ ጉዳይ ቢኖር ልጆች ሆነ ብለው አሰበውና አቅደው ወይም በእነርሱ ግድ የለሽነትና ሥንፍና የሚመጣ ችግር እንዳልሆነ ልረዱ ይገባል፡፡ ስለዚህ እንዲህ አይነት ቺግር ያለባቸውን ህፃናት ማሸማቀቅ ማናደድ እንዲሁም በሰዉ ፊት ʺለሊት አልጋ ላይ ሸንቷል!ʺ ብሎ ማሳፈር በፍፁም ተገቢ አይደለም፡፡

ሽንትን ሌሊት ያለመቆጣጠር ችግር መንስኤው ምንድነው? ምክንያቱ ብዙ ቢሆንም ዋና ዋናዎቹ የምከተሉት ናቸው
═════════════════
1. ትልቅ የሆነ እንቅልፍ እና የሽንት ፊኛ ከመጠን በላይ ሲወጠር መንቃት አለመቻል
2. የጉሮሮ መጥበብ እና ትንፋሽ መቆራረጥ እና ማንኮራፋት (obstructive sleep apnea)
3. በቤተሰብ ተመሳሳይ ችግር ካለ(በተለይ እናት እና አባት ላይ በ ልጅነታ ቸው አጋጥሞቸው ከሆነ)
4. የሆርሞን መዛባት በተለይ የቫሶፕሬሲን (ADH) የሚባለው ሆርምን ማታ ላይ በአግባቡ የማይመረት ከሆነ
5. የሽንት ፊኛ ተገቢውን የሽንት መጠን መያዝ ወይም መሸከም አለመቻል(በነርቭ ቺግር ወይም የአፈጣጠር ችግር ምክንያት)
6. የአይምሮ ጭንቀት
7. አስቸጋሪና አሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ ማለፍ እና ያን ተከትሎ ከፍተኛ ድንጋጤ እና ፍርሃት
8. አሰቃቂ አካላዊ ድብደባና ቅጣት
ወሲባዊ ጥቃት/የአስገድዶ መደፈር በተለይ ሴት ታዳጊዎች ላይ
10. የነርቭ ዘንግ(spinal cord) ችግሮች(spina bifida)
11. ከፍተኛ የሺንት መጠን ማምረት - polyuria (በስኳር ፣ በኩላሊት ችግሮች ወይም በሌሎች ምክንያቶች)
12. ረጅም ጊዜ የቆየ ሆድ ድርቀት
13. የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

═════════════════
ዶ/ር ፋሲል መንበረ (በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የሕፃናት ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር)
═════════════════
Via:- SPMMC.
═════════════════

27/02/2025

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የጤና መረጃ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share