Dr Temesgen

Dr Temesgen የተለያዩ ለጤና ጠቃሚ መረጃዎችን በተመለከተ ለማስተላለፍ የተከፈተ ገፅ ነው።

09/04/2026

የአንጎል የሀይዳቲድ በሽታ (Cerebral Hydatid Disease) እጅግ በጣም አልፎ አልፎ የሚከሰት ሲሆን፥ በጥናት ውጤቶች መሰረት በጥቅላላው በሽታው ከያዛቸው ሰዎች መካከል ከ1% እስከ 3% የሚሆኑት ላይ ብቻ ነው በአንጎል ውስጥ የሚታየው።

[ ] የመከላከያ መንገዶች
• ውሾችን በየጊዜው በሀኪም ማስመርመር፦ ውሾች በየጊዜው በእንስሳት ሀኪም የትል ማጥፊያ መድኃኒት እንዲወስዱ ማድረግ።

• ከታመሙ እንስሳት ጋር ንክኪ አለማድረግ፦ በበሽታው ከተያዙ ወይም ሊያዙ ይችላሉ ተብለው ከሚጠረጠሩ እንስሳት ጋር ያለውን ግንኙነት ማስወገድ።

• ጥሬ ስራ መመገብንና ለውሾችም መስጠትን ማሶገድ።

• ውሾችን ያለ ክትትል ወደ ውጭ አለመልቀቅ፦ ውሾች የሜዳ ላይ ቆሻሻ ወይም ጥሬ ስጋ እንዳይበሉ ክትትል ማድረግ።

• የምግብ አያያዝ መመሪያዎችን መከተል፦ ምግብ በሚዘጋጅበት ጊዜ ንጽህናን መጠበቅ።

• እጅን በሳሙና መታጠብ፦ ምግብ ከማዘጋጀትዎ በፊት ወይም ውሾችን ከነኩ በኋላ እጅዎን በሳሙናና በውኃ በደንብ መታጠብ።

ቪድዮ
ሚያዝያ 1/2018
ዘዉድቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የሰራንው ቀዶ ህክምና

18/10/2025

Brain Aneurysm Management

🇪🇹የፊት ህመም Trigeminal Neuralgia🇪🇹[  ] በአንደኛው የፊት ክፍል ላይ እንደ የኤሌክትሪክ ንዝረት ጋር የሚመሳሰል ከባድ ህመም ነው።[  ] ፊትን በመንካት፣ በማኘክ፣ በመናገር...
18/10/2025

🇪🇹የፊት ህመም Trigeminal Neuralgia🇪🇹

[ ] በአንደኛው የፊት ክፍል ላይ እንደ የኤሌክትሪክ ንዝረት ጋር የሚመሳሰል ከባድ ህመም ነው።

[ ] ፊትን በመንካት፣ በማኘክ፣ በመናገር፣ ጥርስዎን መቦረሽ ወይም ሜካፕ ማድረግ የመሳሰሉ ቀላል ንክኪ እንኳን ህመምን ሊቀሰቅሱ ይችላል።

[ ] በመጀመሪያ አጭር፣ መለስተኛ የሕመም ስሜቶች የሚኖሩ ሲሆን እየቆየ ሲመጣ ቶሎ ቶሎ መነሳት ጠንካራ ህመም መሰማት ህመሙ እረዘም ላለ ጊዜ መቆየት ይስተዋላል።

🇪🇹ምርመራው🇪🇹
[ ] የህመም ምልክቱንና እሚያስነሳውን ነገር ማስተዋል።
[ ] ኤም አር አይ ምርመራ።

🇪🇹ህክምናው🇪🇹

[ ] 1.የመድሀኒት ህክምና (ወደ አንጎል እሚሄደውን የህመም ስሜት እሚቀንስ ወይም እሚያቋርጥ).
[ ] 2. የቀዶ ህክምና ህመም አስተላላፊው ነርቭ ላይ ጫና ያሳደረ ነገር ካለ እሱን ከነርቩ ላይ መለየት(ማሶገድ)።

[ ] 3. ህመም አስተላላፊውን ነርቭ የተለያዩ መድሀኒት በመውጋት ወይም ጨረር በመጠቀም ህመም እንዳያስተላልፍ ጉዳት ማድረስ።

12/10/2025

Brain Aneurysm Prevention

04/10/2025

ከቀዶ ጥገና በኋላ መደረግ ያለበት ጥንቃቄ

ትራንስ ስፌኖይድ ቀዶ ህክምና ከፒቱታሪ እጢ ላይ እንድሁም ከራስ ቅል ግርጌ ላይ የሚከሰቱ እጢችን ለማስወገድ የሚጠቅም የቀዶ ህክምና ነው።

ፒቱታሪ ግላንድ ከአፍንጫ ጀርባ ባለው የራስ ቅል ውስጥ ያለ ትንሽ የአተር መጠን ያለው እጢ ሲሆን በሰውነት ውስጥ የሚኖርን የሆርሞን መጠን ይቆጣጠራል።

የቀዶ ጥገና ሐኪሙ ወደ ፒቱታሪ ዕጢ ለመድረስ የራስ ቅልዎን መክፈት ስለማያስፈልገው እጢዎችን ለመድረስ በጣም ትናንሽ መሳሪያዎችን በመጠቀም, በአፍንጫው ውስጥ አልፎ ከአንጎል በታች በመድረስ ቀዶ ጥገና ይከናወናል።

በመሆኑም የጭንቅላት አጥንትን ከፍቶ ከመስራት ይልቅ በአጠቃላይ ያነሱ የጎንዮሽ ጉዳቶች እና አጭር የሆስፒታል ቆይታ ይኖርዎታል ።

ትራንስ ስፌኖይድ ቀዶ ጥገና በኋላ መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች

ከቀዶ ጥገናው በኋላ ባሉት 6 ሳምንታት እነዚህን ልዩ ጥንቃቄዎች ማድረግ አለብዎት
[ ] ከ4.5 ኪሎግራም በላይ የሚመዝን ነገር አያንሱ።
[ ] እንደ ከባድ ክብደት ማንሳት ወይም መሮጥ ያሉ ጠንካራ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን አያድርጉ።
[ ] አፍንጫዎን በኃይል አይናፈጡ።
[ ] አፍንጫዎትን በጣትዎ መነካካትና ወስጥ ላይ የደረቁ ቆሻሻ የመሰሉ ነገሮችን ለማፅዳት መሞከር አያስፈልግም።
[ ] በቀን የሚጠጡትን የውሃ መጠን (1.5 ሊትር) በታች ቢሆን ይመረጣል።
[ ] በማንኛውም ጊዜ የሰውነት ውጥረትን ላለማድረግ ይሞክሩ በተለይ ሽንት ቤት ሲጠቀሙ ማማጥን ያሶግዱ።
[ ] በተደጋጋሚ ጎንበስ ቀና ማለት ይቀንሱ።

Standard drink ሴቶች 1 ወንዶች ደሞ 2 መጠጥ ይፈቀዳል።አንድ ስታንዳርድ መጠጥ መጠኑ በየመጠጦቹ የአልኮል ይዞታ ይወሰናል።የአልኮል ይዞታቸውቢራ 4.5_5.5%ጠላ 4%ጠጅ 10%አረቄ ...
12/04/2025

Standard drink
ሴቶች 1 ወንዶች ደሞ 2 መጠጥ ይፈቀዳል።

አንድ ስታንዳርድ መጠጥ መጠኑ በየመጠጦቹ የአልኮል ይዞታ ይወሰናል።
የአልኮል ይዞታቸው
ቢራ 4.5_5.5%
ጠላ 4%
ጠጅ 10%
አረቄ 40-70% ሲሆን በዚህም መሰረት ስናሰላው

በቀን ለሴቶች
ቢራ 225 ሚሊ ሊትር
ጠላ 250 ሚሊ ሊትር
ጠጅ 100 ሚሊ ሊትር
አረቄ 25 ሚሊ ሊትር

ለወንዶች ደሞ
ቢራ 450 ሚሊ ሊትር
ጠላ 500 ሚሊ ሊትር
ጠጅ 200 ሚሊ ሊትር
አረቄ 50 ሚሊ ሊትር

በቀን ከዚህ መጠን የበለጠ መጠጥ ብዙ የጤና ጉዳቶች አሉት።

አልኮሆል ከመጠን በላይ ለረጅም ጊዚያት መጠጣት የአንጎል መጎዳትና መጠኑ መቀነስ ያስከትላል። ይህም የማስታወስ አቅም መቀነስ, የፀባይ ለውጥ, የባላንስ አለመጠበቅ እና ተያያዢ ችግሮችን ያስከ...
07/04/2025

አልኮሆል ከመጠን በላይ ለረጅም ጊዚያት መጠጣት የአንጎል መጎዳትና መጠኑ መቀነስ ያስከትላል።

ይህም የማስታወስ አቅም መቀነስ, የፀባይ ለውጥ, የባላንስ አለመጠበቅ እና ተያያዢ ችግሮችን ያስከስታል።

If its needed, please use only standard drink.
Thank you!

በPET SCAN በድብርት ጊዜ (የመጀመሪያው ) የአንጎል እንቅስቃሴን ከመደበኛ የአንጎል እንቅስቃሴ (ሁለተኛው) ጋር ሲወዳደር የሰማያዊ እና አረንጓዴ ቀለሞች መጨመር, ነጭ እና ቢጫ ቦታዎች ...
07/04/2025

በPET SCAN በድብርት ጊዜ (የመጀመሪያው ) የአንጎል እንቅስቃሴን ከመደበኛ የአንጎል እንቅስቃሴ (ሁለተኛው) ጋር ሲወዳደር የሰማያዊ እና አረንጓዴ ቀለሞች መጨመር, ነጭ እና ቢጫ ቦታዎች መቀነሱ, በመንፈስ ድብርት የተነሳ የአንጎል እንቅስቃሴ ምን ያክል እንደሚቀንስ የመጀመሪያው ምስል ያሳያል።

ድብርት ያለባቸው ሰዎች ነገሮችን ለማስታወስ እና ለመፈፀም መቸገር ይስተዋልባቸዋል።

06/04/2025

You only have one 🧠 - take good care of it! There is a lot you can do for a healthy brain:

🏃‍♂️ Keep physically active
🍌 Eat a healthy diet
😴 Get enough sleep
🧩 Stimulate your mind
💟 Look after your heart
⛑️ Wear a helmet

የአንገት ላይ የድስክ መንሸራተት (የሰርቫይካል ስፖንዲሎቲክ ማዮሎፓቲ)[  ] የአንገት ላይ ድስካ, የአከርካሬ አጥንት, እጢ ወይም በጉዳት ምክንያት ከአንጎል ወደታች የሚወርደው መስመር ላይ ...
14/03/2025

የአንገት ላይ የድስክ መንሸራተት (የሰርቫይካል ስፖንዲሎቲክ ማዮሎፓቲ)

[ ] የአንገት ላይ ድስካ, የአከርካሬ አጥንት, እጢ ወይም በጉዳት ምክንያት ከአንጎል ወደታች የሚወርደው መስመር ላይ በመንሸራተት ጫና ሲያሳድር ይከሰታል።
[ ] እድሚያቸው በገፋ ሰዎች ላይ በብዛት ይስተዋላል።

🇪🇹የምልክቶች ምንድ ናቸው?🇪🇹
[ ] አንገት ላይ ህመም መሰማት ወይም ድርቅ ማለት(አንገትን ለማንቀሳቀስ መቸገር)።
[ ] በእጆችዎ ላይ የመደንዘዝ ወይም የመጠዝጠዝ ስሜት።
[ ] የእጆችዎ እና ክርንዎ ጡንቻ መድክም እና መዛል።
[ ] ሚዛን ማጣት እና የመራመድ ችግር/ደረጃዎችን መውጣት መቸገር/።
[ ] ቀልጣፋነት መቀነስ (እንደ ሸሚዝ መቆለፍ መቸገር፤ ትንንሽ እቃዎችን ከጅ ላይ ማምለጥ)።
[ ] ሽንት የመቆጣጠር ችግር።

🇪🇹ህክምናው 🇪🇹
[ ] ፊዚዎቴራፒ መስራት
[ ] መድሀኒት መውሰድ
[ ] የቀዶ ጥገና ማድረግና ነረቩን የተጫነውን ነገር ማስተካከል

🇪🇹የቀዶ ህክምና አማራጮች 🇪🇹
[ ] 1. የተንሸራተተውን ድስካ በማውጣት የድስክ ቦታ ላይ ከዳሌ አጥንት ትንሽ ወስዶ ማስቀመጥ
[ ] 2.የተንሸራተተውን ድስካ በማውጣት የድስክ ቦታ ላይ ከዳሌ አጥንት ትንሽ ወስዶ ማስቀመጥ ከዛም ከታችና ከላይ ካለው የአከረከሬ አጥንት ጋር በፕሌት ማሰር
[ ] 3.የተንሸራተተውን ድስካ በማውጣት የድስክ ቦታ ላይ ኬጅ(ብረት) ማስገባትና ከከታችና ከላይ ካለው የአከረከሬ አጥንት ጋር በቡለን ማሰር።
[ ] 4.ከኋላ በኩል ያለውን የአከረከሬ አጥንት ክፍል(ላሜላ) ማንሳትና ህብረ ሰረሰር እሚያልፍበት ቦታ ሰፋ እንድል ማድረግ።

🇪🇹በፍፁም ማረግ የለለብዎት ነገር 🇪🇹
[ ] አንገቴን ህመም ተሰማኝ ብለው መታሸት(ያንገት ማሳጅ), በአከረከሬ አጥንት ውስጥ አልፈው ወደ አንጎል የሚሄዱትን የደም ስር በመጎዳት እስከ ሞት አልያም መሉ ሰውነት የመዛል ችግር የማጋለጥ አደጋ አለው።

ምስሎች ለታካሚዎቻችን ከሰራናቸው ቀዶ ህክምናዎች ላይ የተወሰደ

ዶ/ር ተመስገን ሹሜ የአንጎልና ህብረ-ሰረሰር ቀዶ ህክምና ሬዚዴንት, አድስ አበባ ዩኒቨርሲቲ.

መጋቢት 5/2017 ዓ.ም

Address

Addis Ababa

Telephone

+251902766558

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr Temesgen posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Dr Temesgen:

Share