Dr Birlew Teshome

Dr Birlew Teshome Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dr Birlew Teshome, Medical and health, Addis Ababa.

Trauma & Adult Reconstruction
Sport Medicine and Bone Health
የአጥንትና መገጣጠሚያ፣ የጂማትና ጡንቻን ጤና በተመለከተ ማብራሪያ ይሰጣል። ጥያቄዎችን ተቀብሎ መልስ ይሰጣል። የጤና እውቀቶችን ለማህበረሰቡ በማጋራት ጤናማና አምራች ማህበረሰብ ለመፍጠር የድርሻውን ይወጣል።
ጥያቄዎትን በአክብሮት እንቀበላለን። ገፃችን Follow ያድርጉ።YouTube.com/

ለሪህ (Gout) ተስማሚ የሆኑ ምግቦች             ~~~ሪህ በደም ውስጥ ያለው የዩሪክ አሲድ (Uric Acid) መጠን ሲጨምር የሚከሰት በሽታ ነው። ትክክለኛ የአመጋገብ ልምድ የሪህ ...
22/07/2026

ለሪህ (Gout) ተስማሚ የሆኑ ምግቦች
~~~
ሪህ በደም ውስጥ ያለው የዩሪክ አሲድ (Uric Acid) መጠን ሲጨምር የሚከሰት በሽታ ነው። ትክክለኛ የአመጋገብ ልምድ የሪህ ጥቃትን ለመቀነስ ትልቅ ሚና ይጫወታል።

👌 በብዛት የሚመከሩ ምግቦች፦
~~
🥬 አረንጓዴ አትክልቶች – ጎመን፣ ሰላጣ፣ ካሮት፣ ዱባ
🍎 ፍራፍሬዎች – ፖም፣ ብርቱካን፣ ሙዝ
🥛 ዝቅተኛ ቅባት ያለው ወተትና እርጎ
🌾 ሙሉ እህሎች – ገብስ፣ አጃ፣ ቡናማ ሩዝ
💧 በቂ ውሃ – በቀን 2 ሊትር (የልብ ወይም የኩላሊት ችግር ከሌለብዎ)

👌 ይቀንሱ ወይም ያስወግዱ፦
~~
🍖 ቀይ ሥጋ – በግ፣ በሬ፣ ፍየል (ይቀንሱ)
🫀 የውስጥ አካል ሥጋዎች – ጉበት፣ ኩላሊት፣ ልብ (ያስወግዱ)
🥤 ስኳር የበዛባቸው መጠጦች
🍺 አልኮል – በተለይም ቢራ (ያስወግዱ)
~~~
ምክር፦ የአመጋገብ ዘዴዎን ማስተካከል ጥሩ መፍትሔ ነው። በዚህ ተዘናግተው ግን ባለሙያ ከማማከር ሊቆጠቡ አይገባም።

ጠቃሚ ሆኖ ካገኙት #ያጋሩት

የጉልበት ህመም ምን ያስከትላል?                       ~~~የጉልበት ህመም በማንኛውም ዕድሜ ሊከሰት ይችላል። ህመሙን ችላ ማለት ችግሩን ሊያባብሰው እና መራመድ ሊከለክል ስለሚች...
22/07/2026

የጉልበት ህመም ምን ያስከትላል?
~~~
የጉልበት ህመም በማንኛውም ዕድሜ ሊከሰት ይችላል። ህመሙን ችላ ማለት ችግሩን ሊያባብሰው እና መራመድ ሊከለክል ስለሚችል መዘግየት አስፈላጊ አይደለም።

ዋና ምክንያቶች

✔️ የመገጣጠሚያ ብግነት (Osteoarthritis)
✔️ የጅማት ወይም የሜኒስከስ ጉዳት
✔️ የሩማቶይድ አርትራይተስ
✔️ ኢንፌክሽን ወይም ስብራት

መፍትሔዎች
✅ ትክክለኛ ምርመራ ያድርጉ።
✅ ከባድ እንቅስቃሴን ለጊዜው ይቀንሱ።
✅ የጡንቻ ማጠናከሪያ እንቅስቃሴዎችን በባለሙያ ምክር ያድርጉ።
✅ ክብደትዎን ይቆጣጠሩ/ይቀንሱ።
✅ መድሃኒት በራስዎ አይውሰዱ በሐኪም ትዕዛዝ ብቻ ይውሰዱ

የሚከተሉት ምልክቶች ካሉ በአፋጣኝ ሐኪም ያማክሩ፦
1. ከባድ ወይም የሚጨምር ህመም
2. ከፍተኛ እብጠት ወይም መቅላት
3. መራመድ አለመቻል
4. ትኩሳት ከጉልበት ህመም ጋር
5. ከአደጋ በኋላ የተጀመረ ህመም
~~
📞ምክር ፦ የጉልበት ህመም የእርጅና ምልክት አይደለም። ቀደም ብሎ ምርመራና ህክምና በማድረግ የቋሚ ጉዳትን መከላከል ይችላል።

የሽያቲካ መፍትሔዎች / Remedies for sciatica 1. 👉በሐኪም ወይም በፋርማሲ ባለሙያ ትዕዛዝ የህመም ማስታገሻዎችን ይውሰዱ2. 👉አካላዊ እንቅስቃሴ ከማድረግ አይቆጠቡ። ህመሙ እስኪ...
16/07/2026

የሽያቲካ መፍትሔዎች / Remedies for sciatica

1. 👉በሐኪም ወይም በፋርማሲ ባለሙያ ትዕዛዝ የህመም ማስታገሻዎችን ይውሰዱ
2. 👉አካላዊ እንቅስቃሴ ከማድረግ አይቆጠቡ። ህመሙ እስኪሻል ብሎ መተኛት በፍፁም አይመከርም
3. 👉በሐኪም ወይም የፊዚዮቴራፒ ባለሙያ ምክር መሰረት ነፊዚዮቴራፒ ህክምና ያድርጉ። ( የተሻለ ውጤት የሚያመጡ የፊዚዮቴራፒ አይነቶች ብዙ ሲሆኑ የተመረጡት ከታች ተያይዘዋል።)
4. 👉አቀማመጥዎን፤ አቋምወን ማስተካከል ላይ በርትተው ይስሩ።
5. 👉 ክብደት ሲያነሱ ትክክለኛውን የክብደት አነሳስ ዘዴ ይጠቀሙ።
6. 👉ከሐኪም ጋር በመመካከር የቀዶ ህክምና ማድረግ። አብዛኛው የሽያቲካ ህመም በፊዚዮቴራፒና በማስታገሻ የሚጠፋ ቢሆንም በተወሰኑ ሰዎች ላይ ግን ቀዶ ህክምና ግዴታ የሚሆንበት አጋጣሚ አለ።

ማሳሰቢያ: ሽያቲካ (Sciatica) በራሱ በሽታ ሳይሆን ምልክት ነው። ስለሆነም መንስኤው ምን እንደሆነ በሐኪም መታየት መልካም ነው። ከሚከተሉት አንዱ ካለዎ ደሞ በአስቸኳይ ሐኪም ማማከር አስፈላጊ ነው።
#የእግር መስነፍ ካለዎት
#ሽንትና ሰገራ ለመሽናት መቸገር ወይም ለመቆጣጠር አለመቻል ካለ
#ሽያቲካ በሁለቱም በኩል ካለዎ
#የመደንዘዝ ስሜት በብልትዎ ዙሪያ ካለ (Numbness around your genitalias & a**s)

የሪህ በሽታ ምንድነው? What is Gouty Arthritis?~~~ሪህ በደም ውስጥ የዩሪክ አሲድ (Uric Acid) መጠን ሲጨምር በመገጣጠሚያዎች ውስጥ ትንንሽ ክሪስታሎች በመከማቸታቸው የሚ...
13/07/2026

የሪህ በሽታ ምንድነው? What is Gouty Arthritis?
~~~
ሪህ በደም ውስጥ የዩሪክ አሲድ (Uric Acid) መጠን ሲጨምር በመገጣጠሚያዎች ውስጥ ትንንሽ ክሪስታሎች በመከማቸታቸው የሚከሰት የመገጣጠሚያ በሽታ ነው።

🔍 ምልክቶቹ
µ. በድንገት የሚጀምር ከባድ የመገጣጠሚያ ህመም
µ. እብጠት፣ መቅላት እና ሙቀት
µ. መገጣጠሚያውን ለመንካት እንኳን የሚያስቸግር ህመም
µ. ብዙ ጊዜ የእግር ትልቁን ጣት ይጀምራል፣ ነገር ግን ጉልበት፣ ቁርጭምጭሚት፣ እጅ ወይም ክርን ላይም ሊከሰት ይችላል።
~~
ተጋላጭ የሚያደርጉ ምክንያቶች
• ቀይ ሥጋና አንዳንድ የባህር ምግቦችን በብዛት መመገብ
• አልኮል አዘውትሮ መጠጣት
• ውፍረት
• የኩላሊት ችግር
• የቤተሰብ የሪህ ታሪክ

መከላከል ይቻላል?
💧 በቂ ውሃ ይጠጡ።
© ጤናማና ሚዛናዊ አመጋገብን ይከተሉ።
© መደበኛ የአካል እንቅስቃሴ ያድርጉ።
©ጤናማ ክብደትን ይጠብቁ።
©ተደጋጋሚ የመገጣጠሚያ ህመም ካለዎት የዩሪክ አሲድ ምርመራ በማድረግ ሐኪም ያማክሩ።

®®® ሪህ በትክክል ካልታከመ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን፣ የመገጣጠሚያ ጉዳትን እና የኩላሊት ችግርን ሊያስከትል ይችላል። በጊዜው ህክምና መጀመር አስፈላጊ ነው።

የሪህ በሽታ ምንድነው? What is Gouty Arthritis?~~~ሪህ በደም ውስጥ የዩሪክ አሲድ (Uric Acid) መጠን ሲጨምር በመገጣጠሚያዎች ውስጥ ትንንሽ ክሪስታሎች በመከማቸታቸው የሚ...
13/07/2026

የሪህ በሽታ ምንድነው? What is Gouty Arthritis?
~~~
ሪህ በደም ውስጥ የዩሪክ አሲድ (Uric Acid) መጠን ሲጨምር በመገጣጠሚያዎች ውስጥ ትንንሽ ክሪስታሎች በመከማቸታቸው የሚከሰት የመገጣጠሚያ በሽታ ነው።

🔍 ምልክቶቹ
µ. በድንገት የሚጀምር ከባድ የመገጣጠሚያ ህመም
µ. እብጠት፣ መቅላት እና ሙቀት
µ. መገጣጠሚያውን ለመንካት እንኳን የሚያስቸግር ህመም
µ. ብዙ ጊዜ የእግር ትልቁን ጣት ይጀምራል፣ ነገር ግን ጉልበት፣ ቁርጭምጭሚት፣ እጅ ወይም ክርን ላይም ሊከሰት ይችላል።
~~
ተጋላጭ የሚያደርጉ ምክንያቶች
• ቀይ ሥጋና አንዳንድ የባህር ምግቦችን በብዛት መመገብ
• አልኮል አዘውትሮ መጠጣት
• ውፍረት
• የኩላሊት ችግር
• የቤተሰብ የሪህ ታሪክ

መከላከል ይቻላል?
💧 በቂ ውሃ ይጠጡ።
© ጤናማና ሚዛናዊ አመጋገብን ይከተሉ።
© መደበኛ የአካል እንቅስቃሴ ያድርጉ።
©ጤናማ ክብደትን ይጠብቁ።
©ተደጋጋሚ የመገጣጠሚያ ህመም ካለዎት የዩሪክ አሲድ ምርመራ በማድረግ ሐኪም ያማክሩ።

®®® ሪህ በትክክል ካልታከመ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን፣ የመገጣጠሚያ ጉዳትን እና የኩላሊት ችግርን ሊያስከትል ይችላል። በጊዜው ህክምና መጀመር አስፈላጊ ነው።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ጤንነትዎን ይጠብቁ። Remain active and keep your musculoskeletal health.         Following  fans GreatestH...
11/07/2026

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ጤንነትዎን ይጠብቁ። Remain active and keep your musculoskeletal health.

Following fans GreatestHighlights

Keep your Musculoskeletal health, remain active.
11/07/2026

Keep your Musculoskeletal health, remain active.

ሽያቲካ ምንድነው?~~~ሽያቲካ (Sciatica) የሚባለው በጀርባ ታችኛው ክፍል ያለው የነርቭ ጫና ሲፈጠር ወደ እግር የሚወርድ የህመም አይነት ነው። ይህ ህመም በSciatic nerve ላይ ጫ...
04/07/2026

ሽያቲካ ምንድነው?
~~~
ሽያቲካ (Sciatica) የሚባለው በጀርባ ታችኛው ክፍል ያለው የነርቭ ጫና ሲፈጠር ወደ እግር የሚወርድ የህመም አይነት ነው። ይህ ህመም በSciatic nerve ላይ ጫና ሲኖር ይመጣል።
፩. ዋና ዋና ምልክቶች
0.ከጀርባ ወደ እግር የሚወርድ ህመም
0.እግር ውስጥ ማቃጠል
0. እግር ድካም፣ መዛልና ድንዛዜ
0. ቁርጭምጭሚት ህመም

፪. ዋና ምክንያቶቹ
0. የዲስክ መንሸራተት/ Disc prolapse
0. የአጥንት መሳሳት
0. ረጅም ጊዜ በማይመች ነገር ላይ ተቀምጦ መስራት
0. ክብደት መጨመር
0. የዳሌ ጡንቻዎች ከልክ በላይ መወፈር
~
-->ሽያቲካ በብዙ ሰዎች የሚታይ ችግር ሲሆን ብዙ ጊዜ ያለ ኦፕሬሽን መዳን ይችላል።
(መፍትሔዎቹን በሚቀጥለው ፖስት ያግኛሉ)

ጥያቄዎች በዛ ስላሉ በአንድ ላይ ለመመለስ ነው  ~~~ጥያቄ፦የዳሌ አጥንት ስብራት ይታከማል ወይ?መልስ፦አዎ በደንብ ይታከማል። ህክምናው ሙሉ ዳሌ ቅዬራ ወይንም ግማሽ ዳሌ ቅየራ ሊሆን ይችላል...
04/07/2026

ጥያቄዎች በዛ ስላሉ በአንድ ላይ ለመመለስ ነው
~~~
ጥያቄ፦የዳሌ አጥንት ስብራት ይታከማል ወይ?

መልስ፦አዎ በደንብ ይታከማል። ህክምናው ሙሉ ዳሌ ቅዬራ ወይንም ግማሽ ዳሌ ቅየራ ሊሆን ይችላል። በሚቀጥለው ቀን ጀምረው መንቀሳቀስ ይችላሉ።
ጥያቄ፦ ጎንደር ይሰጣል ወይ?
መልስ፦ አዎ በጎንደር ዩኒቨርሲቲም በግል ተቋማትም ይሰጣል።
Birlew Teshome

ጤና እንዲያድግ የታችኛውን የጤና አመራር ማጎልበት ያስፈልጋል።~~~Department level leadership has its own challenges, particularly unique and ex...
03/07/2026

ጤና እንዲያድግ የታችኛውን የጤና አመራር ማጎልበት ያስፈልጋል።
~~~
Department level leadership has its own challenges, particularly unique and extraordinary challenges for young and new Department leaders.
1. Lack of skills how to influence the higher tier of leaders in Hospitals and Teaching universities.
2. Very limited circle of social influence
3. The higher leadership will know very few problems of the lowest tier in healthcare. It is natural.
4. Leadership has a lot of hardships but no reimbursement for your effort. This in reality will discourage people to waste proportionally adequate time for leadership activities. (አንዳንድ ጊዜ እውነቱን መነጋገር ያስፈልጋል።)
~~~
In the Ethiopian healthcare structure, leadership is often treated as a voluntary or unpaid responsibility. Leads to limited accountability, reduced motivation, and slower implementation of reforms. As a result, the healthcare system struggles to bring palpable healthcare changes which will benefit the interest of the people but repeatedly without real tangible changes

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr Birlew Teshome posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Dr Birlew Teshome:

Shortcuts

Share