Haje nuru adem tradtional medical service

Haje nuru adem tradtional medical service Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Haje nuru adem tradtional medical service, Medical and health, Shegole, Addis Ababa.

25/02/2020

ጤናአዳም ያድናልም፣ ይገድላልም!! (ሼር ሳታደርጉ እንዳታልፉ)

✔ ጤናአዳም ብዙ የጤና በረከቶች እንዳሉት ሁሉ መጠኑ ሲበዛ ፅንስ እስከማስወረድ የሚደርስ አደገኛነት እንዳለው ያውቃሉ? ለወዳጆችዎ ማጋራት አይዘንጉ!

በኢትዮጵያ የባሕል ሕክምና ጤናአዳም ለሆድ ሕመም፣ ለተቅማጥ፣ ለጆሮ፣ ለልብ ሕመም፣ ለኪንታሮት፣ ለኢንፍልዌንዛና ከአንጀት መታወክ ጋር ለተያያዙ አገልግሎት ላይ ይውላል፤ የደረቀው ፍሬ ከተፈጨ በኋላ ተፈልቶ በመጠጣት ለተቅማጥ ሕክምና ሲውል፣ ቅጠሉ ከተከተከተ በኋላ በውኃ ተደርጎ ለሕፃናት ሆድ ሕመም ይሰጣል፤ ተክሉ ተድጦ ሲልም ደግሞ ለኪንታሮት በሽታ ይወሰዳል፡፡

በሰሜን አፍሪካ በሚገኙ አገሮች ደግሞ ከተክሉ ተዘፍዝፎ የሚገኘው ፈሳሽ ለጉንፋን፣ ለጆሮ ሕመምና ለአንጀት መታወክ ይወሰዳል፡፡ የጤናዳም ሽታ በጣም ጠንካራ በመሆኑ ሰዎች ጊንጦችን ከአካባቢያቸው ለማራቅ ይጠቀሙታል፡፡ በአልጀሪያ ሰዎች ተክሉ ከተዘፈዘፈ በኋላ የሚገኘውን ፈሳሽ በጠብታ መልክ በአፍንጫ ይወስዳሉ፤ በተለይ ለሕፃናት ይህ ሕክምና የሚሰጠው ለሚያስመልስና ትኩሳት ላለበት ነው፡፡ በመሆኑም ጤናአዳም እንደ ቀንድአውጣና ሦሥት አፅቄ ያሉ ነፍሳትን የማራቅ አቅም ስላለው በጓራችን ቢኖር ተመራጭ ነው፤ እንዲሁም ለቁንጫ መድኃኒት ነው፡፡

✔ የጤናአዳም የተለያዩ የጤና ጥቅሞች

ጤናአዳም በጡንቻ ላይ የሚያጋጥም ሕመምን፣ ውጥረትንና በወር አበባ ወቅት የሚያጋጥም ሕመምን የማርገብ ሁኔታ ያለው ሲሆን መጠቀም ያለብን ግን የእፅዋት ባለሙያን በማማከር መሆን አለበት፡፡ በሻይ መልክ መጠቀም ለሽንት ቧንቧ፣ ለአንጀትና በአጠቃላይ ለደንደኔ ኢንፌክሽን መድኃኒት መሆን ይችላል፤ ጤናአዳም ለምግብ መመረዝ በተለይ ደግሞ ሳልሞኔላ የተባለውን ባክቴሪያና ሌሎች አደገኛ ተህዋስያን ሊከላከለን ይችላል፤ ከዚህ በተጨማሪ ጤናአዳም የፀረ ባክቴሪያ ባሕሪ ስላለው ልንጠቀመው እንችላለን፡፡ ይህ እጽ ነርቮችን የማረጋጋት ኃይል ማለትም የአራጌነት( sedative) ባሕሪ እንዳለው ጥናቶች የሳያሉ፤ በመሆኑም የእንቅልፍ ማጣት ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን ብንጠቀመው ሊያረጋጋን ይችላል፡፡

ጤናዳም በአንዳንድ መርዛማ እንስሳት(ለምሳሌ በእባብ) ከተነደፍን ማርከሻ የሚሆንበት ሁኔታ ያለ ሲሆን ይኸውም የተነደፍነው የነርቭ ስርዓት ላይ እክል በሚፈጥሩ የመርዝ ዓይነቶች ከሆነ ነው፡፡ ጤናዳም በአንጓ ላይ የሚያጋጥም ብግነትን ሰከን የማድረግ ኃይል ስላለው ችግሩ ያለበት ሰው አንድ ወይም ሁለት ብርጭቆ በሻይ መልክ ቢጠጣ እፎይታን ሊያገኝ ይችላል፡፡

የጤናዳም ዘይት በዘመናዊው ዓለም ለሳሙናዎችና ለኮስሞቲክስ ምርቶች ጥሩ መዓዛ ጥቅም ላይ ይውላል፤ ይህ ዘይት መጠኑ ሲበዛ የመርዛማነት ባሕሪ ስላለው በቀጥታ በቆዳ ላይ በጥቅም ላይ አይውልም፤ ነገር ግን ተመጥኖ ለቆዳ የተለያዩ ጥቅሞች እንዳስገኘ ትናቶች ያሳያሉ፤ ይኸውም የፀረ-ፈንገሽ ባህሪ ስላለውና ቆዳን የማጥራት አቅም ስላለው ነው፡፡

✔ የጤናዳም የጎንዮሽ ጉዳት

ከጤናዳም የሚወጣው ዘይት በሰውነት ላይ በቀጥታ ከተጠቀምን ሰውነት ውኃ ሊቋጥር እንዲሁም ሊቀላ ይችላል፤ በከፍተኛ መጠን ከተጠቀምነው ደግሞ የሰውነት መመረዝ ሊያከትል ይችላል፤ በተለይ ደግሞ ፅንስ ያላቸው እናቶች በከፍተኛ መጠን ከተጠቀሙት ፅንሳቸውን ሊያስወርድ ይችላል፤ እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የጨጓራ ሕመም ሊያስከትል ይችላል፡፡ ይህም በመሆኑ በዘመናዊው ዓለም የጤናአዳም የሕክምና አገልግሎቱ የተገደበ እየሆነ መጥቷል፡፡

ከጤናዳም የሚገኘው ዘይት በብዛት ከተወሰደ ውርጃ ሊያስከትል ይችላል፤ በፈረንሳይ ተክሉ ሳያገቡ ያረገዙ እንስቶች ይጠቀሙት ስለነበር (herbe à la belle fille) በእንግሊዝኛ (Herb of fair maidens) በመባል ይጠራ ነበር፡፡

04/02/2020

እንዳሁላ ውሀማ የተባሉ ተክሎች ናቸው የተለያዩ ዝርያወች መልኮች አሏቸው። በዋናነት ለቤት ማገጫ ይታደጋል።

በኢትዮጵያ ባህላዊ መድሃኒት፣ የእንዳሁላ ቅጠሎች ለቁስል፣ ለብጉንጅ፣ ለእባጭ፣ ለቆዳ ችግሮች ለማከም ተጠቅመዋል። እንዲሁም የበሬ ቀንበር ቁስል ለማከም ተጠቅመዋል።

ትኩስ ሥሮቹ ለጨብጡ፣ ለሆድ ትል ሕክምና ተጠቅመዋል። ይህ ሥር እንደ ሻይ ይጠመቃል፣ በጣም ሃይለኛ ሲሆን ጉዳት እንዳያደርግ በአነስተኛ መጠን ብቻ ይጠጣል።[1]

በሌላ ጥናቶች ዘንድ፣ የK. petitiana (የአንጩራ) አገዳ መረቅ ለኪንታሮት፣ የቅጠሉም ጭማቂ በቅቤ ለጥፍ ለተሰበረ አጥንት ያክማል።[2] ወይም ለማበጥ፣ ሥሩ በቀጥታ ማስገባት ይደረጋል።[3]

ብዙ ዝርያዎች፣ በተለይ ለከብት፣ ለልብ መርዛም ናቸው።[4][5]

በሌሎች አገራት በህላዊ ሕክምናዎች፣ ለቁርጥማት፣ ለማበጥ፣ ለልክፈቶች ተጠቅመዋል። በትሪኒዳድ ባህላዊ ሕክምና፣ K. pinnata ለደም ግፊት እንዲሰጥ ይዘገባል።[6]
Image may contain: plant, flower and nature
22

Ali Yimam
Like
Comment
Share
Comments
Ali Yimam
Write a comment...
Press Enter to post.

Write a post...

Photo/Video
Tag friends
Check in

ባህላዊ ህክምና
5 December 2019 ·
አብሺ ኢትዮጲያ ውሥጥ የሚገኚ ተክል ነው ቅጠሎቹ እና ዘሮቹ በብዙ አበሳሰሎች ውስጥ ቅመሞች ናቸው። ዘሮች ወይንም ዱቄቱ በአገር ቤት ገበያ ይታያል።

ዱቄቱ ወደ ማር ሲጨመር ለጥሩ መጠት ያደርጋል። መጠቱ ሞርሟሪ ሲሆን ክብደት ለመጨመር እንዲረዳ ተብሏል። እንዲሁም እንደ ቡና ሊፈላ ይችላል።

አብሽ ከባቄላ ተቀላቅሎ ለብጉንጅ ያከማል። ለጥፉ በእብጠቱ ላይ ይለጠፋል።...
See more
Image may contain: plant, flower, outdoor and nature

24/01/2020

ፎረፎርን ለማጥፋት የሚረዱ መፍትሄዎች

ውድ የሀጂ ኑሩ አደም የባህል ህከምና እንዴት ዋላችሁ ለፎረፎር ማስታገሻ የሚረዱ ተግባራት እና ውህዶች እነሆ!!!

ፎረፎር ወይንም ሴቦሪክ ደርማቲቲስ ተብሎ የሚታወቀው ብዙ ሰው ላይ የሚታይ የጭንቅላት ቆዳ በሽታ ነው። በደረቅ ወይም በተቆጣ ቅባታማ ቆዳ ምክንያት ሊከሰት ይችላል። ጭንቅላት ላይ የሚያድጉ ባክቴርያ እና ፈንገሶችም የበሽታው መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ። በሽታው የጭንቅላታችን ቆዳ እንዲደርቅ እና እንዲያሳክከን ያደርጋል።

የጸጉርን ጤና በመጠበቅ የበሽታውን ስሜቶች መቆጣጠር ይቻላል። ወይም እንዳማራጭ ቤት ውስጥ በምናዘጋጃቸው መፍትሄዎች በሽታውን መቆጣጠር እንችላለን። ፎረፎርን ለማከም ቤት ውስጥ የምናዘጋጃቸው መፍትሄዎች በሽታውን ለማከም ግዜ የሚፈጁ ቢሆኑም ለበሽታው መፍትሄ የሚሰጡ ናቸው።

1) የኮኮናት ዘይት

የኮኮናት ዘይት ውስጡ ባለው የጸረ ፈንግስ ንጥረ ነገር ፎረፎርን ለማከም ጥሩ መፍትሄ ነው። የጭንቅላታችንንም ቆዳ ልስላሴ በመስጠት የሚያሳክከንን ስሜት ለማጥፋት ይረዳናል።

መጀመርያ የኮኮናት ዘይቱን ከሱ በመጠን ግማሽ ከሚያንስ የሎሚ ጭማቂ ጋር ማቀላቀል። ከዛ ጭንቅላታችን ላይ ለተወሰን ደቂቃ ማሸት። ከ20 ደቂቃ በኋላ ጸጉራችንን መታጠብ። ይህንን መፍትሄ በሳምንት ሁለት ወይም ሶስት ግዜ መደጋገም ያስፈልጋል።

2) አፕል ሲደር አችቶ

የራስ ቅላችንን በአፕል ሲደር አችቶ ማከም ለፎረፎር ፍቱን መፍትሄ ይሆናል። ራስ ቅላችን ላይ ያለውን የፒኤች መጠን ወደ ተፈጥሮአዊ መጠኑ በመመለስ ጸጉራችን ላይ የፈነገስ እድገትን ይገታል።
ሁለት የሻይ ማንኪያ አችቶ ከሁለት ሻይ ማንኪያ ውሃ ጋር በማቀላቀል ጸጉራችንን ማሸት ይኖርብናል። ለተወሰነ ደቂቃ አቆይተነው ጸጉራችንን መታጠብ እንችላለን። መፍትሄውን በሳምንት ሁለት ወይም ሶስት ግዜ መደጋገም ይኖርብናል።

3) የመጋገርያ እርሾ

እርሾ በጭንቅላታችን ላይ የሞቱ ሴሎችን ለማስወገድ ይረዳል። ጭንቅላታችን ላይ ያለውን ትርፍ ዘይት ይመጣል። የቅላችንን ፒኤች መጠን በማመጣጠን የጸጉር ፈንገስ ይቀንሳል።

መጀመርያ ጸጉራችንን አርጥበን የአንድ መዳፍ መጠን የሆነ እርሾ ጸጉር ላይ አድርጎ ማሸት። ከተወሰነ ደቂቃ በኋላ ጸጉራችንን በሙቅ ውሃ መታጠብ። ለተወሰኑ ሳምንታት በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ግዜ ማድረግ በቂ ነው።

4) የወይራ ዘይት

የራስ ቅል መድረቅን ልስላሴ ይዘት ባለው በወይራ ዘይት መታከም ይቻላል።

የወይራ ዘይቱ ትንሽ ሞቅ እስኪል እሳት ላይ መጣድ
ጭንቅላታችን ላይ ካሹ በኋላ ጸጉራችንን በፎጣ መጠቅለል
ለ45 ደቂቃ እንደተጠቀለለ መተው። ከዛ ጸጉራችንን በደንብ መታጠብ
መፍትሄውን በሳምንት ለተወሰኑ ግዚያቶች መደጋገም አስፈላጊ ነው።
5) የሎሚ ጭማቂ

የሎሚ ጭማቂ ጸረ ፈንገስ የሆነ አሲዳማዊ ይዘት አለው። የማሳከክ ስሜት ለማጥፋትም ይረዳናል።

ግማሽ ሎሚ ከሩብ ስኒ እርሾ ጋር ቀላቅለን ማቀላቀል።
ውህዱን ጸጉር እና ራስ ቅላችን ላይ ማሸት።
ለ20 ደቂቃ ጭንቅላታችን ላይ ከተውነው በኋላ ማጠብ
በሳምንት ለተወስነ ግዜ ማድረግ ያስፈልጋል።

6) አስፕሪን

አስፕሪን በውስጡ ሳሊሳይክሊክ አሲድ የሚባል ፎረፎርን መቆጣጠር የሚችል ንጥረ ነገር ይዟል።

ሁለት የአስፕሪን ክኒኖችን ማድቀቅ
ከትንሽ ሻምፑ ቅባት ጋር ማቀላቀል።
ጸጉራችንን በውህዱ ካሸን ብኋላ ለተወሰኑ ደቂቃዎች መተው።

7) እሬት (ኦሊ ቬራ)

በፎረፎር የተገጎዳ ቆዳን እሬት መቀባት የሞቱ ህዋሳቶችን ከማስወገዱም ባሻገር ለፀጉር እድገት አይነተኛ ሚና እንዳለውም ይታመናል።

መልካም የጤንነት ጊዜ ተመኘን !

23/01/2020

ከምንሰጣቸው ህክምናወች ለዉሰጥና ለውጭ ክታሮት,ለነቀርሳ,ለአሰም,ለተለያዬ ኢፌክሺን,ለጨጎራ,ለጉበት.ለኩላሊት ,ለቃቁቻ,ችፌ,ፎረፎር,.ለወሲብ ዲክመት,ለደም ግፈት ,ለሱካር,ለብርርዲ በሺታ,ለአልማዝ ባለጭራ,ለአይነጥላ,ለእጀ ሰብ,ለእቅርት,ለአባለዘር በሺታ,ለምች,ለማዲያት,ለሚጥል በሺታ ,ለአእምሮ በሺታ,ለወፋ,እንዲሁም ለተለያዬ በሺታወችና ጠንቆች እኝዘንዲ መዲሀኒትይገኝለታል።በተጨማሪም ንፁህና ምንም ነገር ያልተጨመረበት የጥቁር አዝሙድ ዘይት በባህል ህክምናችን የተመረተ በጂምላና በችርቻቻሮ እናከፍፊላለን። ለበለጠመረጃ አዲሰ አበባ ሸጎሌ ሜዳ አንበሳ ጋራጂ ፈትለፈት እንገኛለን።ሰልክቁጥር 0911205957 በዚህ ደውለው ማማከር ይችላሉ

18/01/2020

----- ............
ይህ ዕፅ በሀገራችን #ለመድሀኒትነት ከሚዉሉት አንዱ ሲሆን ከ65 በላይ ለሆኑ በሽታዎችና ችግሮች
ይዉላል፡፡
ከነዚህ ዉስጥም ለአብነት ያህል እንጠቅሳለን
-እግሩ ላበጠ ሰዉ
-በምጥ ለታመመች ሴት
-ጉሮሮዉ ላበጠ
-ስንፈተ ወሲብ ላለበት
-ለችፌ
-ለተስቦ
-ብልቱ ለደከመ
-ትከሻዉ ላበጠ
-ለሥራይ(መድሀኒት ለበላ)
-ቅንቅን በጆሮዉ ለገባበት
-ለነሥር
-ለሳል
-ለራስ ነቀርሳ
-ሆዱ ለሚጮህና ለሚያቃጥለዉ
-ሲበላ ወደ ላይ ለሚለዉ
-ለአስም
-ለጉርምጥ
-ለጥላ ወጊ
-እንስሳትን አዉሬ እንዳይበላቸዉ
-በመብልና በመጠጥ ለተደረገ መድሀኒት
-መስተፋቅር ለተደረገበት ሰዉ
-ቁስሉ አልድን ላለ
-ከብትና በግ ፍየል እንዳይከሱ
-ሀገሩን ለቆ እንዲሄድ ለተደረገበት
-ልቡን ለሚያመዉ
-ለሌባ
-ለታመመ በመንፈሰ ርኩስ
-ለወገብና ለጀርባ ህመም
-ጆሮዉ ለደነቆረ
-ሰዉነቱ ለሚመነምን
-ቡዳ ለበላዉ
-የዛር ዉላጅ ላስቸገረዉ
-ለደም ብዛት
-ለሾተላይ...........ወዘተ.....ይጠቅማል፡፡

Address

Shegole
Addis Ababa

Telephone

0911205957

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Haje nuru adem tradtional medical service posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share