Aroressa Woreda Hare chafa Health center

Directions

Aroressa Woreda Hare chafa Health center Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Aroressa Woreda Hare chafa Health center, Medical and health, Addis Ababa.

26/06/2026

This version of Facebook uses less data and works in all network conditions.

የሁለተኛ ዘመን የጤና ዘርፍ መካከለኛ ዘመን ልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድ (HSDIP-II) እና የጤና ሴክተር ሪፎርም ላይ ሀገር አቀፍ የውይይት መድረክ ተጀመረ።  የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ሰኔ...
26/06/2026

የሁለተኛ ዘመን የጤና ዘርፍ መካከለኛ ዘመን ልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድ (HSDIP-II) እና የጤና ሴክተር ሪፎርም ላይ ሀገር አቀፍ የውይይት መድረክ ተጀመረ።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ሰኔ 18/2018 ዓ.ም

በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት የኢትዮጵያን የጤና ዘርፍ የሚመራውን ሁለተኛውን የጤና ዘርፍ መካከለኛ ዘመን ልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድ (HSDIP-II) እና የጤና ሴክተር ሪፎርምን የሚመለከት ሀገር አቀፍ የውይይት መድረክ በይፋ ተጀምሯል።

እንደ ሀገር ከ10 ሺህ በላይ የጤና ባለሙያዎች ተሳትፎ የሚያደርጉ ሲሆን፣ በሲዳማ ክልል ደግሞ 592 የጤና ባለሙያዎች ከጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች እስከ ሲኒየር ሐኪሞች ድረስ በንቃት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ኢትዮጵያ ከመከላከል ባሻገር አክሞ በማዳን የጤና ፖሊሲን በመተግበር በጤናው ዘርፍ አበረታች ውጤቶችን ማስመዝገብ መቻሏን ገልጸዋል። በተለይም በእናቶችና በሕፃናት ጤና ዘርፍ የተገኙ ለውጦች፣ የጨቅላ ሕፃናት ሞትን በመቀነስና የጤና አገልግሎት ውጤታማነትን በማሳደግ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን አስታውቀዋል።

ሚኒስትሯ አክለውም፣ ሀገሪቱ በወረርሽኞች፣ በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ አደጋዎች ውስጥ ተግዳሮቶችን በመቋቋም በጤናው ዘርፍ ተጨባጭ ውጤቶችን ማስመዝገብ መቻሏን ገልጸዋል።

እንደተገለጸው፣ HSDIP-II ከዝግጅት ምዕራፍ ወደ ትግበራ የሚሸጋገርበት ወሳኝ ደረጃ ላይ ደርሷል። በቀጣይ ጊዜ የዲጂታል ጤና ሥርዓትን ማጠናከር፣ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ አሰጣጥን ማሳደግ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤን ማጠናከር እና ዘላቂ የጤና ፋይናንስ ሥርዓት መገንባት ቁልፍ ትኩረቶች እንደሚሆኑ ተጠቁሟል።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይነህ በቀለ በበኩላቸው፣ HSDIP-II የክልሉን የጤና ሴክተር ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ከሀገራዊ ሪፎርም አቅጣጫዎች ጋር በማጣጣም ዕቅድን ከሀብትና ከበጀት ጋር በተግባር ለማስተሳሰር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል።

በዕቅዱ ውስጥ “አንድ ዕቅድ፣ አንድ በጀት፣ አንድ ሪፖርት” የሚለው መርህ ተግባራዊ እንደሚሆን የተገለጸ ሲሆን፣ ቀደም ሲል 14 የነበሩ ስትራቴጂያዊ ግቦች ወደ 7 በመቀነሳቸው የተበታተኑ ተግባራትን በአንድ ማዕቀፍ ውስጥ በማስተባበር ውጤታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

የጤና ሚኒስቴር የሚኒስትሯ ከፍተኛ አማካሪ ዶ/ር አበራ በቀለ ባቀረቡት ሰነድ መሠረት፣ HSDIP-II በእናቶችና ሕፃናት ጤና፣ በበሽታ መከላከል፣ በጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት፣ በዲጂታል ጤና፣ በመድኃኒት አቅርቦት እና በጤና ፋይናንስ ማጠናከር ላይ በዋናነት ያተኮረ መሆኑን አስረድተዋል።

በመድረኩ ላይ የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻን ጨምሮ ከፌዴራል፣ ከክልልና ከከተማ አስተዳደሮች፣ ከተጠሪ ተቋማት፣ ከጤና ተቋማት የተውጣጡ አመራሮች፣ ባለሙያዎች፣ አስተባባሪዎች እና የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች ተሳታፊ መሆናቸው ታውቋል ።

HSDIP-II የጤና ሴክተሩን ለቀጣዮቹ ዓመታት የሚመራ ቁልፍ ስትራቴጂካዊ ሰነድ በመሆኑ፣ በጤና አገልግሎት ጥራት፣ ተደራሽነት እና ውጤታማነት ላይ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል ::

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
ሰኔ 18/2018 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000

👇Sidama National Regional State Health BureaudNisha Nagarkatti-Gudecom/1000

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Aroressa Woreda Hare chafa Health center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share