ZEMEN Pharmarcy

ZEMEN Pharmarcy ZEMEN Pharmacy 🚀
Smart healthcare for a smarter Ethiopia. Pharmacy • Health Tech • Digital Services • AI-Powered Care, Bringing modern pharmacy to Ethiopia 🇪🇹

18/02/2026

የረመዳን ፆምን የማያበላሹ የህክምና ተግባራት

1, የአይን ጠብታና የጆሮ ጠብታ መድሀኒቶች ፆምን አያበላሹም።

2, የአስም በሽተኞች የሚነፋ መድሃኒታቸውን (Salbutamol puff) እየፆሙ ቢወስዱ ችግር የለውም።

3, ጥርስን ማስነቀል ወይም ጥርስን ማስሞላት ፆምን አያጠፋም።

4, በምላስ ስር የሚደረጉ ኪኒኖች: የልብ በሽታን (MI) ለማከም ... ለሌሎችም በሽታዎች የሚረዱ መድሀኒቶች እስካልተዋጡ ድረስ ፆምን አያበላሹም።

5, ፆመኛ ሰው የደም ምርመራ ለማስደረግ ብሎ ደሙን ቢሰጥ ፆሙ አይፈርስም።

6, በደምስር (IV) ወይም IM የሚሰጡ ምግብን የማይተኩ መድሀኒቶች (ማስታገሻዎች ፣ ክትባቶች ፣ Antibiotics) እንዲሁም ሲቲስካን (CT Scan) ወይም MRI ለመነሳት በደምስር የሚሰጡ መድሀኒቶች (Intravenous contrast) ፆምን አያበላሹም።

7, በበሽታ ወይም በማንኛውም ምክንያት ሳያውቁ ማስታወክ ፆምን አያጠፋም።

8, ሂጃማ (ዋግምት) ፆምን ያበላሻል ወይስ አያበላሽም በሚሉት ሀሳቦች በዑለማዎች (በዲን አዋቂዎች) መካከል ብዙ ሀሳቦች የተሰጠበት ሲሆን ለመጠንቀቅ ያክል በፆም ሰዓታት ዋግምት ከመደረግ ብንቆጠብ የተሻለ ነው። የሂጃማ (የዋግምት) ድንጋጌ በዘመናዊ የህክምና መንገድ ለምንጠቀመው Phelbotomy ይውላል።

9, ነስር ያለበት ሰው በብዛት እንኳን ደም ቢፈሰው ፆሙ አይበላሽም። እየፆመ ያለ ሰው በአደጋ ወይም በሌላ ምክንያት በብዛት ደም ቢፈሰው ፆሙ ላይ ችግር አይኖረውም። ነገር ግን በዚህ ምክንያት ከታመመና ከደከመ ፆሙን አጥፍቶ መመገብ ይችላል።

10, በጤናዋ ላይ ችግር የማያስከትልባት ከሆነ አንዲት ሴት የወር አበባ የሚያስቆም መድሀኒት ተጠቅማ ረመዳንን ብትፆም ችግር የለውም። አንዲት ሴት የረመዳን ቀናት ፆሞችን ፣ ለይለቱል ቀድር ፣ በሀጅና ዑምራ ላይ ያሉ አንዳንድ ተግባራት የመሳሰሉትን ዒባዳዎች እንዳያመልጧት የወር አበባን የሚያስቆም መድሀኒት መጠቀምዋ ጤናዋ ላይ ችግር የማይስከትል ከሆነ ችግር አይኖረውም። ነገር ግን መድሀኒቶቹ የጎኒዮሽ ጉዳት ስላላቸውና ሴቷ ራሷን ተከሉፍ (ራሷን ማስገደድ) ውስጥ ባታስገባ የተሻለ ይሆናል። ኪኒን ተጠቅማ ግን ብትፆምና ዒባዳዎችን ብትተገብር ተቀባይነት አለው።

11, በሴት ማህፀን ወይም ብልት ውስጥ የሚከተቱ የህክምና መሳሪያዎች ፣ ምርመራዎች ፣ መድሀኒቶችና የእርግዝና መከላከያዎች ፆምን አያበላሹም።

[ እነዚህ የረመዳን ፆምን የሚመለከቱ የህክምና ብያኔዎች ቁርዓንና ሀዲስን ብሎም የአራቱ አዒማዎች መዝሀቦችን ተመርኩዘው በዘመናችን ዑለማዎች (የዲን ዓዋቂዎች) የተሰጡና የተጠናቀሩ ናቸው።]

🟢የሳምንቱ ፋርማ-ነክ መረጃዎች💊🌍(📅ዘመን ፋርማሲ- ቅዳሜ የካቲት 8/2018) 1️⃣ ኢትዮጵያ በመንግስት ሆስፒታሎች የዲጂታል ጤና ስርዓትን እያሰፋች ነው።የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስቴር በመንግስ...
16/02/2026

🟢የሳምንቱ ፋርማ-ነክ መረጃዎች💊🌍
(📅ዘመን ፋርማሲ- ቅዳሜ የካቲት 8/2018)

1️⃣ ኢትዮጵያ በመንግስት ሆስፒታሎች የዲጂታል ጤና ስርዓትን እያሰፋች ነው።
የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስቴር በመንግስት ሆስፒታሎች ውስጥ የዲጂታል የታካሚዎች መዝገብ ስርዓቶችን ማስፋፋት ቀጥሏል። ይህ የወረቀት ስህተቶችን ለመቀነስ እና የመድኃኒት ክትትል እና የመድኃኒት ማዘዣ ትክክለኛነትን ለማሻሻል እንደሚረዳ ታምኗል።

2️⃣ የሀገር ውስጥ የመድኃኒት ማምረቻ ላይ ትኩረት ጨምሯል
ኢትዮጵያ ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ጥገኝነትን ለመቀነስ የሀግር ውስጥ የመድኃኒት ምርት ለማሳደግ ጥረቶችን እያጠናከረች ነው። ይህ በመጪዎቹ ዓመታት የመድኃኒት አቅርቦትን ሊያሻሽል እና የመድኃኒት ዋጋን ሊያረጋጋ ይችላል።

3️⃣ የዓለም ጤና ድርጅት በአፍሪካ ውስጥ ስለሚጨምር የአንቲባዮቲክ አላግባብ መጠቀም አስጠንቅቋል
የዓለም ጤና ድርጅት በአፍሪካ አገሮች ውስጥ ስለ አንቲባዮቲክ ከመጠን በላይ መጠቀም ስጋት አንስቷል። ፋርማሲዎች የመቋቋም አቅምን ለመከላከል ኃላፊነት የሚሰማቸውን የአንቲባዮቲክ ስርጭት እንዲያስተዋውቁ ይበረታታሉ።

4️⃣ በአፍሪካ የበሽታ ምርመራን የሚደግፉ አዳዲስ የAI መሳሪያዎች ተግባራዊ እየተደረጉ ነው።
በርካታ የአፍሪካ የጤና ተቋማት በሽታዎችን ቀደም ብለው ለመለየት በAI ላይ የተመሰረቱ የምርመራ መሳሪያዎችን እየተጠቀሙ ነው። ይህ ቴክኖሎጂ ቀደም ብሎ ሕክምናን ሊያሻሽል እና የሆስፒታል ሸክምን ሊቀንስ ይችላል።

5️⃣ ጥቆማ፡ ወቅታዊ የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽኖች እየጨመሩ መጥተዋል
የጤና ባለሙያዎች በዚህ ወቅት የሳል፣ የኢንፍሉዌንዛ እና የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽኖች መበራከታቸውን ሪፖርት እያደረጉ ነው። ታካሚዎች ቀደም ብለው ህክምና እንዲፈልጉ እና ራስን ከማከም እንዲቆጠቡ ይመከራሉ።
---------------------------------------
👉ለተመሳሳይ መረጃዎች ገፃችንን ይከታተሉ!

ዘመኖ በጤና ይባረክ!
ዘመን ፋርማሲ

ZEMEN Pharmarcy

🟢የሳምንቱ ፋርማ-ነክ መረጃዎች💊🌍(ዘመን ፋርማሲ- የካቲት 1/2018)1️⃣ ኢትዮጵያ የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝ ማብቃቱን አውጃለች🇪🇹 ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝ ከ...
08/02/2026

🟢የሳምንቱ ፋርማ-ነክ መረጃዎች💊🌍
(ዘመን ፋርማሲ- የካቲት 1/2018)

1️⃣ ኢትዮጵያ የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝ ማብቃቱን አውጃለች
🇪🇹 ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝ ከ42 ቀናት በኋላ ያለምንም አዲስ ኬዝ ማብቃቷን በይፋ አስታውቃለች። ይህም የበሽታ ክትትል እና የአደጋ ጊዜ ምላሽ አቅምን የበለጠ ያጠናክራል።

2️⃣ አዲስ አበባ የአፍሪካ የጤና ኮንፈረንስ አስተናግዳለች
🌍 ኢትዮጵያ በጾታዊ እና በመራቢያ ጤና ላይ አህጉራዊ ኮንፈረንስ አስተናግዳለች፣ የጤና አጠባበቅ ጥራትን እና ተደራሽነትን ለማሻሻል ከ20 በላይ የአፍሪካ አገሮች ባለሙያዎችን አስተናግዳለች።

3️⃣ የአካባቢ መድኃኒት ምርት በቂሊንጦ ፋርማ ፓርክ ተስፋፍቷል
💊 ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ከውጭ የሚገቡ መድኃኒቶችን ማምረቷን አስፋፍታ ቀጥላለች፣ ይህም የመድኃኒት እጥረትን እና በውጭ አቅርቦት ላይ ያለውን ጥገኝነትን ለመቀነስ ይረዳል።

4️⃣ የኤአይ ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ የቲቢ ምርመራን እንደሚያሻሽል ተስፋ ተትሎበታል።
🤖 በኤአይ የሚንቀሳቀሱ ዲጂታል ኤክስሬይ ስርዓቶች አሁን የሳንባ ነቀርሳን በፍጥነት እና በትክክል ለመለየት ጥቅም ላይ ይውላሉ፣ የመጀመሪያ ህክምናን ያሻሽላሉ እና ህይወትን ያድናሉ።

5️⃣ አዲስ አስፈላጊ መድሃኒቶች ዝርዝር ወጥቷል
📋 የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና የኢትዮጽያ ምግና መድጋኒት ባለስልጣን (EFDA) የተሻሻለውን አስፈላጊ መድሃኒቶች ዝርዝር አስጀምረዋል፣ ይህም የሆስፒታሎችን እና የፋርማሲዎችን ደህንነቱ የተጠበቀ እና የበለጠ ውጤታማ የመድኃኒት አጠቃቀምን መምራት ያስችላል ተብሏል።
---------------------------------------
👉ለተመሳሳይ መረጃዎች ገፃችንን ይከታተሉ!

ዘመኖ በጤና ይባረክ!
ዘመን ፋርማሲ

በአፍሪካ ውስጥ ሄፓታይተስ ቢ  ዝምተኛው ገዳይ በሽታ ነው።በሚሊዮን የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ሄፓታይተስ ቢን ሳያውቁት ይኖራሉ። ይህም የሚከተሉትን ሊያስከትል ይችላል፡👉የጉበት ችግር👉የጉበት ካን...
19/01/2026

በአፍሪካ ውስጥ ሄፓታይተስ ቢ ዝምተኛው ገዳይ በሽታ ነው።

በሚሊዮን የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ሄፓታይተስ ቢን ሳያውቁት ይኖራሉ። ይህም የሚከተሉትን ሊያስከትል ይችላል፡
👉የጉበት ችግር
👉የጉበት ካንሰር
👉ያለ እድሜ መሞት

መልካም ዜና 🌍
በመጨረሻ ደረጃ ላይ በተደረጉ ሙከራዎች አዳዲስ መድኃኒቶች ይህንን በሽታ በቅርቡ ሊቆጣጠሩት ወይም ሊፈውሱ ይችላሉ።

ይህ ማለት ለኢትዮጵያ ፡
💉 የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ይቀንሳል
🏥 የሆስፒታል ሸክም ይቀንሳል
💊 የተሻለ የረጅም ጊዜ ሕክምና

ከሁሉም ግን: ቀድሞ መመርመር ሕይወትን ያድናል።
--------------------
👉ለተመሳሳይ መረጃዎች ገፃችንን ይከታተሉ!

ዘመኖ በጤና ይባረክ!
ዘመን ፋርማሲ
------------

🟢የሳምንቱ ፋርማ-ነክ መረጃዎች💊🌍(ዘመን ፋርማሲ- ጥር 10/2018)---------------------------- 🔹 የክኒን መድኃኒቶች መርፌዎችን እየተኩ ነው። ትላልቅ የመድኃኒት ኩባንያዎች...
18/01/2026

🟢የሳምንቱ ፋርማ-ነክ መረጃዎች💊🌍
(ዘመን ፋርማሲ- ጥር 10/2018)
----------------------------
🔹 የክኒን መድኃኒቶች መርፌዎችን እየተኩ ነው።

ትላልቅ የመድኃኒት ኩባንያዎች የስኳር በሽታ እና የውፍረት መድኃኒቶችን የኪኒን (ታብሌት) ስሪቶችን እያዘጋጁ ነው። ይህም መድሃኒቶቹ;
✔ ርካሽ
✔ ለማጓጓዝ ቀላል
✔ የቀዝቃዛ ማጓጓዣ ሰንሰለት አያስፈልግም

👉 ይህ ለኢትዮጵያ እና ለሌሎች የአፍሪካ አገሮች ጥሩ ዜና ነው።

🔹 ለሄፓታይተስ ቢ ታካሚዎች ተስፋ

በመጨረሻ ደረጃ ሙከራዎች ላይ ያሉ አዳዲስ መድኃኒቶች በአፍሪካ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚጎዳውን ዝምተኛው ገዳይ በሽታ የሆነውን ሄፓታይተስ ቢን በቅርቡ ሊቆጣጠሩ ወይም ሊፈውሱ ይችላሉ።

🔹 ፋርማሲ ወደ ዲጂታል እየተቀየረ ነው

AI፣ ስማርት የአቅርቦት ሰንሰለቶች እና ዲጂታል ፋርማሲዎች እየተበራከቱ ነው። ይህም

❌ የመድኃኒት እጥረት
❌ የውሸት መድኃኒቶች
❌ ከፍተኛ ወጪዎች ለመቀነስና ለመቆጣጠር እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ትልምኖበታል

የኢትዮጵያ የጤና አጠባበቅ የወደፊት ዕጣ ተመጣጣኝ፣ ዲጂታል እና በታካሚ ላይ ያተኮረ ይሆናል።

---------------------------------------
👉ለተመሳሳይ ታማኝ የጤና እና የመድኃኒት መረጃዎች የዘመን ፋርማሲ ማህበራዊ ሚዲያ ገፃችን ይከታተሉ!

ዘመኖ በጤና ይባረክ!
ዘመን ፋርማሲ
------------

ይህን ያውቁ ኖሯል?በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ መድሃኒቶች የሚበላሹት የውሸት በመሆናቸው ሳይሆን በተሳሳተ መንገድ ስለተቀመጡ ነው።🚫 ሙቀት🚫 የፀሐይ ብርሃን🚫 እርጥበትመድሃኒት ሊያበላሹ ይችላሉ፦👉አ...
11/01/2026

ይህን ያውቁ ኖሯል?

በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ መድሃኒቶች የሚበላሹት የውሸት በመሆናቸው ሳይሆን በተሳሳተ መንገድ ስለተቀመጡ ነው።
🚫 ሙቀት
🚫 የፀሐይ ብርሃን
🚫 እርጥበት
መድሃኒት ሊያበላሹ ይችላሉ፦
👉አንቲባዮቲክስ/ፀረ ባክቴሪያ መድሃኒቶች
👉ኢንሱሊን (የስኳር መድሃኒት)
👉የደም ግፊት መድሃኒቶችን ሁልጊዜ፦

✔ መድሃኒቶችን ቀዝቃዛና ደረቅ ቦታ ያስቀምጡ
✔ ምድጃዎች ወይም መስኮቶች አጠገብ አያስቀምጡ
✔ የሚያበቁበትን ቀን ያረጋግጡ
✔በተጨማሪም ስለመድሃኒቶች አግባቢ አቀማመጥ ፋርማሲስት ያማክሩ!

ጥሩ ማስቀመጫ = ጥሩ ህክምና።
--------------------
👉ለተመሳሳይ መረጃዎች ገፃችንን ይከታተሉ!

ዘመኖ በጤና ይባረክ!
ዘመን ፋርማሲ
------------

የሳምንቱ ፋርማ-ነክ ዜናዎች (ዘመን ፋርማሲ)----------------------------1) ርካሽ የክብደት መቀነሻ መድሃኒቶች እየመጡ ነው።ትላልቅ የመድኃኒት ኩባንያዎች በመርፌ ምትክ የታወ...
08/01/2026

የሳምንቱ ፋርማ-ነክ ዜናዎች
(ዘመን ፋርማሲ)
----------------------------

1) ርካሽ የክብደት መቀነሻ መድሃኒቶች እየመጡ ነው።

ትላልቅ የመድኃኒት ኩባንያዎች በመርፌ ምትክ የታወቁ የውፍረት መድኃኒቶችን ታብሌት (ክኒን) ስሪቶችን ማስተዋወቅ ጀምረዋል። ​​ይህ ዋጋዎችን ሊቀንስ፣ የማከማቻ ሂደታቸውን ቀላል ሊያደርግ እና እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ቀዝቃዛማ ሀገራት የሎጂስቲክስ ሰንሰለት ውስን በሆኑ አገሮች ውስጥ ተደራሽነትን ሊያሻሽል ይችላል።

2) የሄፐታይተስ ቢ ግኝት

በመጨረሻ ደረጃ ሙከራዎች ውስጥ ያለው አዲስ መድሃኒት ሄፐታይተስ ቢን ለማከም ወይም በጠንካራ ሁኔታ ለመግታት እውነተኛ አቅም እያሳየ ነው። ይህ ለአፍሪካ ትልቅ ዜና ነው፣ ሄፐታይተስ ቢ እንደኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት የተለመደ እና የጉበት ካንሰርን እንዲሁም ብሎ ሞትን ያስከትላል።

3) የመድኃኒት ዋጋ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየጨመረ ነው።

ብዙ የምርት ስም ያላቸው (Branded Medicines) መድኃኒቶች ውድ እየሆኑ መጥተዋል፣ ይህም አገሮች በጄኔሪክ እና በአካባቢው ማምረቻ ላይ የበለጠ እንዲተማመኑ ይገፋፋቸዋል - ይህ ለኢትዮጵያ የመድኃኒት አስመጪዎች እና የወደፊት አምራቾች ትልቅ እድል ነው።

4) የፋርማ ኢንደስትሪው በAI እና በመረጃ ላይ ከፍተኛ ኢንቨስት እያደረገ ነው።

ዓለም አቀፍ የመድኃኒት ኩባንያዎች የመድኃኒት ግኝትን እና የአቅርቦት ሰንሰለቶችን ለማፋጠን AI እየተጠቀሙ ነው። ይህ ዲጂታል ፋርማሲዎች፣ የኢ-መድሃኒት ማዘዣዎች (E-Periscriptions) እና የAI መሳሪያዎች የወደፊቱ የፋርማና ህክምናው ዘርፍ ክስተቶች መሆናቸውን ያሳያል።
---------------------------------------
👉ለተመሳሳይ መረጃዎች ገፃችንን ይከታተሉ!

ዘመኖ በጤና ይባረክ!
ዘመን ፋርማሲ
------------

"ምች" - Oral Herps /Cold Soresበብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከንፈራችን ላይ፣ አፋችን አካቢቢ እና ውስጥ በድንገት የህመም ስሜት ያላቸው ትንንሽ ውሃ የቋጠሩ ሚመስሉ አይነት እብጠ...
07/01/2026

"ምች" - Oral Herps /Cold Sores

በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከንፈራችን ላይ፣ አፋችን አካቢቢ እና ውስጥ በድንገት የህመም ስሜት ያላቸው ትንንሽ ውሃ የቋጠሩ ሚመስሉ አይነት እብጠቶች ወይም ቁስለት ሲያጋጥመን 'ምች መቶኝ ነው' የሚል የተለመደ የህመም አገላለፅ አለን።

በተለይ' የተወሰኑ ምግቦችን ከተጠቀምኩ ቡሀላ አፌን በደንብ ሳልታጠብ ወደ ፀሀይ ስወጣ... ነው ምች ያገኘኝ' እንላለን።

'ፀሀይ ላይ ምግብ አትብላ ምች ይመታሀልም' ስንባል ያደግንም ብዙዎች ነን።

'ምች ይደጋገምብኛል : ይፀናብኛል: ያስቸግረኛል... እያሉ 'የሚናገሩም ብዙ ሰዎች አሉ።

'ምች ይምታህ' .. የሚለው ቃል ደግሞ የልጅነት የእርግማን ወይም ስድብ ትዝታችን ነው

ምች ምንድነው?

በአብዛኛው ማህበረሰባችን ዘንድ' ምች ተብሎ' ተብሎ የሚታወቀው ፦በአፍ ውስጥ ከንፈር እና አካባቢው የሚከሰት እና በትንንሽ ህመም ያላቸው ውሃ የቋጠሩ ሚመስሉ እብጠቶች ወይም ቁስለት ምልክቶቹ በዋናነት የሚገለፀው ሲሆን ፥በሳይንሳዊ መጠሪያው 'Oral Herps/Cold sores' ወይም አንዳንዴ ከንፈረ ላይ ብቻ ሲወሰን 'Herps labialis' ተብሎ ከሚጠራው የቫይረስ ኢንፌክሽን ጋር የሚስተካከል ህመም ነው።

ሆኖም ግን ሌሎች ከ Herps ቫይረስ ውጪ ባሉ ምክንያቶች የሚከሰቱ የአፍ ውስጥ እና አካባቢው ቁስለቶችም አንዳዴ በምልክት መመሳሰል የተነሳ በሰዎች ዘንድ ምች ተብለው ሊገለፁ እንደሚችሉም ማስተዋል ያስፈልጋል።

እናም በዚህ ፅሁፍ ላይ' ምች' ስል ለመገልፅ እየሞከርኩ ያለሁት በ herps ቫይረስ ሚከሰተውን እና ከአብዛኛው ማህበረሰባችን የምች ምልክቶች አገላለፅ ጋር የሚጣጣመውን 'Oral Herps' መሆኑን ቀድሜ ላስገነዝብ እፈልጋለሁ።

ምች/Oral Herps

ይህ 'Herps simplex virus 1 (HSV-1) ተብሎ በሚታወቅ የቫይረስ አይነት የሚመጣ በአፍ ውስጥ ስጋዎች (ምላስ : ድድ...): ከንፈር እና አካባቢው ባለው ቆዳ ላይ የሚከሰት ኢንፌክሽን ነው።

ሁለት አይነት የ HSV አይነቶች ሲኖሩ HSV-1 አፋ እና አካባቢውን ሲያጠቃ HSV-2 ተመሳሳይ ኢንፌክሽን በመራቢያ አካላት ላይ ያስከትላል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ 3.8 ቢሊየን (64%) እድሜያቸው ከ50 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎች የOral Herps (ምች) የሚያመጣው ቫይረስ ተጠቂዎች ናቸው።

ቫይረሱ እንዴት ነው የሚሰራው?

ምች (Oral herps) በከፍተኛ ሁኔታ ተላላፊ ኢንፌክሽን ሲሆን በዋነኝነትም በቀጥታ የበሽታው ምልክት (ቁስለት : እብጠት : ምራቅ..) ጋር በሚደረግ ቀጥተኛ ንክኪ ይተላለፋል።

አንዳንድ ጊዜ ምንም ምልክቱ ከማይታይባቸው (ከሌለባቸው) የቫይረሱ ተሸካሚ ሰዎችም ጋር በሚደረጉ የጠበቁ ንክኪዎች (በመሳሳም : በምራቅ...) ሊተላለፍ ይችላል።

አንድ ሰው አንዴ በዚህ ቫይሰረስ (HSV-1) ከተጠቃ (ቫይረሱ ወደ ሰውነቱ ከገባ) ቡሀላ; ቫይረሱ እድሜ ልኩን አብሮት የሚኖሮ ሲሆን ፤ አብዛኛውን ወቅት ላይ ግን ምንም አይነት ምልክቶችን (ህመሞችን) አያሳይም።

ቫይረሱ አንዴ ወደሰውነታችን ከገባ ቡሀላ አብዛኛው ጊዜውን ፊታችን አካባቢ በሚገኝ ነርቭ ህዋስ (Trigeminal ganglion) ውስጥ ተደብብቆ(ፀጥ ብሎ/አድፍጦ/Dormant/inactive) የሚቀመጥ ሲሆን ፤ ምቹ አጋጣሚዎችን ሲያገኝ ግን ከመጠን በላይ በመራባት እና በመሰራጨት ጥቃት መፈፀሙን ጀምሮ ጉዳቶቹን/ምልክቶችን በአፍ ውስጥ ከንፈር እና አካባቢው ላይ ያሳያል። የዚያኔ 'ምች መታኝ' ወይም Oral Herps ተከሰተ እንላለን።

ምልክቶቹ

1. የህመም ስሜት ያለቸው ውሀ የቋጠሩ ሚመስሉ ትንንሽዬ እብጠቶች

2. የተላጠ ቁስለት (እብጠቶቹ ፈንድተው ሊፈጠር ሚቾል ቁስለት አይነት)

3. በተጨማሪም ማቃጠል: ማሳከክ: መውጋት: የመቅላት... አይነት ስሜቶች ሊኖሩ ይችላሉ

እንዲሁም ኢንፌክሽኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ የተከሰተው ከቁስለቶቹ እና እብጠቶች በተጨማሪ የሰውነት ህመም : ትኩሳት :ራስ ምታት :የጉሮሮ ህመም እና አንገት አካባቢ ያሉ ንፍፊቶች (cervical lymphnodes) እብጠት ሊኖር ይችላል።

ምች አንድ ሰው ላይ ለምን በየጊዜው ይመላለስ? (Recurrent Oral herps)

ምች ድንገት ወይም ደግሞ በተለያዩ አጋላጭ ነገሮች ምክንያት ሊነሳ ይችላል

ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው አንዴ ሰውነታችን ከገባ ቡሀላ የማይወጣ እና አፍ አካባቢ በሚገኝ ነርቭ ህዋሳችን ውስጥ በትንሽ መጠን ራሱን ደብቆ በአብዛኛው ምንም ምልክት ሳያሳይ (ጉዳት ሳያደርስ) አጋጣሚዎችን እየጠበቀ የሚኖር ሲሆን ፤ ራሱን ለማውጣት አቅም በሚያገኝበት እና ይበልጥ መራባት የሚችልበት እድል ሲያገኝ የተለመደው የአፍ እና አካቢው ቁስለቶች እብጠቶች እና ህመሙን ያስከትላል።

ለቫይረሱ አቅም ማግኘት እና ድጋሚ ህመም የመፍጠር ብቃትን የሚሰጡት ነገሮች ምንድናቸው?

1. አጠቃላይ የሰውነታችን የበሽታ መከላከል አቅም መዳከም ሲኖር

2. የተለያዩ የሰውነት ህመሞች ወይም ትኩሳት ሲኖር

3. ቀጥታ ፊታችንን ለፀሀይ ጨረር በምንጋለጥበት ወቅት

4. ከፋተኛ ጭንቀት: ድባቴ:.. በሚኖርበት ወቅት

5. የወር አበባ እና የሆርሞን መቀያየር ሲኖር

6. አፍ አካባቢ አደጋ ወይም ቀዶ ህክምናዎች

እነዚህ ከላይ የተገለፁ አጋላጭ ምክንያቶች በሚኖሩበት ወቅት በዋነኝነት የሰውነታችን አጠቃላይ በሽታን የመከላከለ አቅም ስለሚዳከም አካባቢያዊ ምክንያቶችም ተዳብለው ቫይረሱ በቀላሉ ከተደበቀበት ወጥቶ በመራባት እና በመሰራጨት አፋችን እና አካባቢው ላይ ጉዳቶቹን (ህመመሞቹን) ያስከትላል።

እውን እንዳንድ ምግቦች ምችን ያስከትላሉ?

እስካሁን ባለው ተጨባጭ የትኛውም አይነት ምግብ በቀጥታ ምች (Oral herps) ያመጣል ተብሎ አይታሰብም።

ሆኖም ግን አንዴ ቫይረሱ ወደ ሰውነታችን ገብቶ ከተደበቀ ቡሀላ አንዳንድ የምግብ አይነቶች ውስጥ የሚገኙ ኬሚካሎች ቫይረሱ እንዲነቃቃ እንዲራበ እና ህመም እንዲፈጥር ሊያደርጉት ይችላሉ።

አመጋገባችን ታድያ በሁለት አይነት መንገድ ቫይረሱን ጉልበት እንዲያገኝ (እንዲነቃቃ) ሊያደርገው ይችላል

1. አመጋገባችን በቂ እና ተመጣጣኝ ሳይሆን ሲቀር እና የሰውነት የመከላከል አቅማችንን መደገፍ ሲሳነው

2. አንዳንድ የምግብ አይነቶች በውስጣቸው የያዙት ኬሚካል (አርጂኒን የተባለ ፕሮቲን) የቫይረሱን የመራባት እና የመስራት አቅም ስለሚጨምር

ጥናቶች እንደሚያሳዩት 'አርጂኒን 'የተባለው በተለያዩ የምንመገባቸው መአዶች ውስጥ የሚገኝ ፕሮቲን(አሚኖ አሲድ) የተወሰኑ ቫይረስ አይነቶች እድገትን በሰውነታችን ውስጥ የሚያነቃቃ እና የሚደግፍ ሲሆን ከእነሱም አንዱ ደግሞ ምች የሚስከትለው ቫይረስ HSV1 ነው።

ሰለሆነም አንዳንድ ሰዎች የተመረጡ ምግቦችን በልተው ለፀሀይ ሲጋለጡ በተደጋጋሚ ወዲያው ምች ይመታናል የሚሉት አንዱም ምክንያት ;ምን አልባትም ምግባቸው ከፍተኛ አርጂኒን ይዘት ያለው ሆኖ :፤ ቫይረሱ ፀሀይ እና አርጂኒኑ አንድ ላይ ድንገት ተገጣጥመውለት በአንዴ ከፍተኛ ጉልበት አግኝቶ ተጠቅሞበት ሊሆን ይችላል።
ምች ይታከማልን?

አብዛኛውን ጊዜ የሰውነት በሽታ መከላከል አቅማቸው ደህና የሆኑ እና ብዙም 'ያልተጎዱ' ሰዎች ከሽታው በራሳቸው ከአንድ እስከ ሁለት ሳምንት ባለው ጊዜ ውስጥ ያገግማሉ

በተጨማሪም የተለያዩ መድሀኒቶች ምችን ለማከም ሊታዘዙ የሚችሉ ሲሆን ፤ህክምናውም በዋነኝነት በተቻለ አቅም በፍጥነት የህመሙን ስሜቶች ቁስለቶችን እና ደረጃ መቀነስ እና ማጥፋት ነው

እንዲሁም አንዳንዴ ምች በጣም በተደጋጋሚ የሚያስቸግራቸው ሰዎች ከቅድመ ጥንቃቄዎች በተጨማሪ አነስተኛ መጠን ያለው ፀረ ቫይረስ መድሃኒት በየቀኑ አንዴ መውሰዱ (Suppressed therapy ) ድግግሞሹን ለመቀነስ ሊረዳቸው ይችላል።

እንዴት መከላከል ይቻላል?

1. የምች ምልክት ከሚያሳዩ ግለሰቦች ጋር ቀጥታ የአፍ ንክኪን መቀነስ (መሳሳም: የገራ መጠጫዎች...

2. የተመጣጠነ ምግብ መመገብ እና የሰውነት ጤናን መጠበቅ

3. በቂ ፈሳሽ መውሰድ

4. በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ

5. ጭንቀት:ድባቴ... መቀነስ

6. በ'አርጅኒን' ይዘት ባላቸው ምግቦች ምክንያት የሚመጣን የቫይረስ መነቃቃት ለመቀልበስ 'ላይዚን' በተባለው ፕሮቲን የበለፀጉ ምግቦችን (እርጎ :አይብ: አፕል: አሳ...) ማዘውተር ወይም የላይዚን ሰፕልመንት ፒልሶችን መጠቀም።

7. እለንዲሁም ለፀሀይ ጨረር በመጋለጥ ምክንያት ምች በተደጋጋሚ ለሚያጠቃቸው በተቻለ መጠን ራስን ከቀጥታ የፀሀይ ጨረር ተጋላጭነት ማራቅ እና የፀሀይ መከላከያዎችን (Sunscreens) መጠቀም ይመከራል።

በመጨረሻም ፥ 'ምች አይምታቹ'

ŠHakim

ብዙ ሰዎች ሀኪም ቤት ለመሄድ ለምን ያመነታሉ?👇👇👇👇ብዙ ሰዎች ህመም ሲሰማቸውም እንኳ ዶክተር ጋር ለመቅረብ የሚያመነቱባቸው በርካታ የተለመዱ ምክንያቶች አሉ። ይህ የስነልቦና፣ የፋይናንስ፣ ...
07/12/2025

ብዙ ሰዎች ሀኪም ቤት ለመሄድ ለምን ያመነታሉ?
👇👇👇👇

ብዙ ሰዎች ህመም ሲሰማቸውም እንኳ ዶክተር ጋር ለመቅረብ የሚያመነቱባቸው በርካታ የተለመዱ ምክንያቶች አሉ። ይህ የስነልቦና፣ የፋይናንስ፣ የባህል እና የተግባር ምክንያቶች ድብልቅ ነው። ዋናዎቹ እነሆ፡-

1. የመጥፎ ዜና ፍርሃት

ብዙ ሰዎች ዶክተሩ ከባድ ነገር እንደሚነግራቸው ይፈራሉ።
ሊሆን የሚችል ምርመራ ከማድረግ ይልቅ "አላወቁም" የሚለውን ይመርጣሉ።

2. የህክምና ወጪ

በብዙ አገሮች - በተለይም የጤና ኢንሹራንስ ውስን በሆነባቸው - ሀኪም ቤት መሄድ ውድ ሊሆን ይችላል። በዚህም ወጪውን ፍራቻ ሰዎች ህመማቸው እስኪባባስ ወይስ አስገዳጅ ደረጃ ላይ እስከሚደርሱ ድረስ ይጠብቃሉ።

3. ምልክቶችን አቅልሎ መመልከት

ሰዎች ብዙውን ጊዜ በህመም ወቅት እንዲህ ያስባሉ፡-

👉"ጉንፋን ብቻ ነው"

👉"ይተወኛል።"

👉"አንድ ተጨማሪ ቀን ልየው ።"

ይህ መዘግየት ሁኔታውን ሊያባብሰው ይችላል።

4. የባህል እምነቶች እና መገለል

አንዳንድ ባህሎች "ጠንካራ" ወይም "የማያቋርጥ ታጋሽ" መሆንን ያበረታታሉ።
ሌሎች ወደ ሐኪም መሄድን እንደ ድክመት ምልክት አድርገው ይመለከቱታል።

5. ያለፉ መጥፎ ልምዶች

አንድ ሰው ከሐኪም ጋር አሉታዊ ተሞክሮ ካጋጠመው (ለምሳሌ፣ እንደተፈረደበት፣ እንክብካቤ እንደተነፈገው ወይም እንደተበደለ ከተሰማው) እንደገና ከመሄድ ሊቆጠቡ ይችላል።

6. የሕክምና ሂደቶች ፍርሃት

የህክምና ምርመራዎች ፍራቻ ሌላው በጣም የተለመድ ምክንያት ነው። ከነዚህም፡

👉መርፌዎች

👉የደም ናሙናዎች ቅጂ

👉ቀዶ ጥገና

👉ሆስፒታሎች ራሳቸው

ይህ አንድ ሰው እርዳታ ከመፈለግ ሊያግደው ይችላል።

7. በጤና ባለሙያዎች ላይ እምነት ማጣት

አንዳንድ ሰዎች ዶክተሮች ከመጠን በላይ መድሃኒቶችን እንደሚያዙ ወይም እነሱን እንደማይሰሟቸው ያምናሉ።
ሌሎች ደግሞ ባህላዊ ፈዋሾችን የበለጠ ያምናሉ።

8. ጊዜ እና ምቾት

የተጨናነቀ የጊዜ ሰሌዳ፣ ረጅም የጥበቃ ጊዜ እና የትራንስፖርት ተግዳሮቶች ሰዎች የዶክተር ጉብኝቶችን እንዲያዘገዩ ያደርጉታል።

9. የራስ መድሃኒት ልማድ

በተለይ ፋርማሲዎች ያለ ማዘዣ ብዙ መድሃኒቶችን በሚሸጡባቸው ቦታዎች ሰዎች በመጀመሪያ እራሳቸውን በመድሃኒት ለማከም ይሞክራሉ።

10. የአእምሮ ጤና እንቅፋቶች

ጭንቀት፣ ድብርት ወይም ጭንቀት ጤናን ለመፈለግ ጉልበት እና ተነሳሽነት ሊያሟጥጥ ይችላል።
--------------------
እነዚህ በጥናት የተረጋገጡ ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸው። የእርሶ ምክንያት ከእነዚህ የተለየ ነበር? ኮሜንት ላይ ይፃፉልን!!

-----------------------------
ዘመኖ በጤና ይባረክ!
ዘመን ፋርማሲ
------------

05/12/2025

ለማርበርግ ቫይረስ የሙከራ ክትባት ሊሰጥ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

ዓርብ፣ ሕዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም ( )

የማርበርግ ቫይረስ ምላሽን ለማሳደግ የሚረዳ የሙከራ ክትባት ለተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎች ሊሰጥ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ክትባቱ ከሕዳር 29 ቀን ጀምሮ መስጠት የሚጀመር ሲሆን የጤና ባለሙያዎችን እና ከፍተኛ ተጋላጭ ለሆኑ ቡድኖች ቅድሚያ የሚሰጥ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ተናግረዋል።

ለዚህም የማርበርግ ቫይረስ ምላሽ ለመስጠት የሚደረገውን ጥረት የሚደግፍ 2 ሺ 500 የማርበርግ ቫይረስ የሙከራ ክትባት ከአሜሪካ መንግስት በድጋፍ የተገኘ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ክትባቱ በአርማወር ሃንሰን የምርምር ተቋም በሚመራ ፈጣን የደረጃ 2 ክሊኒካዊ ሙከራ ተደርጎለት ጥቅም ላይ እንደሚውልም ነው የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ የገለጹት።

ጤና ሚኒስቴር ወርሽኙን ለመግታት ከሚመለከታችዉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የምላሽ አሰጣጡን አጠናክሮ የቀጠሉ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር መቅደስ፤ ለዚህም የቅኝትና ቁጥጥር ስራዉን ማጠናከር፣ የጤና ባለሙያዉንና ጤና ሰራተኞች ጨምሮ ተጋላጭ የሆኑትን በመጠበቅ ላይ ትኩረት በማድረግ የመከላከል ስራው አጠናክሮ መቀጠል አስፈላጊ መሆኑን አመልከተዋል።

ክትባቶቹን ለጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ያስረከቡት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በበኩላቸው አሜሪካ ክትባቶቹን በባርዳ እና ሳቢን የክትባት ተቋም በኩል ለኢትዮጵያ ድጋፍ ማድረጓን ተናግረዋል።

አሜሪካ የማርበርግ ቫይረስን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለውን ጥረት የበለጠ ሊያግዝ የሚያስችል የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጓን አዲስ ማለዳ ትናንትና መዘገቧ የሚታወስ ሲሆን ከድጋፎቹ መካከል አንደኛው ክትባት መሆኑን ዛሬ የቴና ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ይህም ኢትዮጵያ የማርበርግ ቫይረስን ለመቆጣጠር እያደረገችው ያለውን ጥረት የበለጠ ሊያግዝና ወደፊት ሊያራምድ የሚያስችል መሆኑን አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት መግለጻቸው ይታወሳል።
------
ŠAddis Maleda

23/11/2025
23/11/2025

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ መከላከያ መንገዶች



Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ZEMEN Pharmarcy posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ZEMEN Pharmarcy:

Share