31/05/2026
▶️ሄፓታይተስ 'ሲ' የጉበት ቫይረስ ኢንፌክሽን በጊዜ ከታወቀ እንደሚታከም ያውቃሉ?
📌ሄፓታይተስ ሲ ኢንፌክሽን በቫይረስ ሳቢያ የሚመጣ የጉበት በሽታ ነው።
🔷ይህ በቫይረሱ ምክንያት የሚመጣው የጉበት ጉዳት ቋሚ ወይም ጊዜያዊ ሊሆን ይችላል።
📌ሄፓታይተስ ሲ ቫይረስ የሚተላፈው:- በደም ንኪኪ ነው ፤ ይህም ስለት ያላቸውን መሳሪያዎች እና ሲሪንጅ ጥንቃቄ በሞላበት መንገድ ባለመጠቀም ሊከሰት ይችላል።
📌የ Acute Hepatitis C ምልክቶች ፦
1-ትኩሳት
2-ድካም
3-አይን እና ቆዳ ቢጫ መሆን እና የጡንቻ ህመም ሲሆን፤ ነገር ግን ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆይ(Chronic) የሄፓታይተስ ሲ ኢንፌክሽን ምልክት ሚታየው ቫይረሱ ጉበትን በከፍተኛ ሁኔታ ከጎዳ በኋላ ነው፤ ከታች የተዘረዘሩት ዋና ዋናዎቹ ናቸው👇
1-በቀላሉ መድማት
2-ድካም
3-አይን እና ቆዳ ቢጫ መሆን
4-የሽንት መጥቆር
5-የቆዳ ማሳከክ
6-የሆድ እና እግር ማበጥ
7-ክብደት መቀነስ
8-የምግብ ፍላጎት ማጣት ናቸው።
#