Healthy Children ጤናማ ልጆች

Healthy Children ጤናማ ልጆች ጤናማ ልጆች ስለ በህፃናት አመጋገብ ፣ አስተዳደግና ጤንነት ዙርያ ለማህበረሰቡ በቂ ግንዛቤና አገልግሎት ለመስጠት ያለመ ገፅ ነው።

የጡት አጠባብ ዘዴዎች ፣ ትክክለኛ አስተቃቀፍ እና የጡት ትክክለኛ አጎራስ! ከወደዱት ሼር ያድርጉት! 😍
30/08/2026

የጡት አጠባብ ዘዴዎች ፣ ትክክለኛ አስተቃቀፍ እና የጡት ትክክለኛ አጎራስ!

ከወደዱት ሼር ያድርጉት! 😍

11/08/2026

የእናት ጡት ማጥባት መቼ መጀመር አለበት? 👶🤱

​እናት ጡት ማጥባት ሕፃኑ ከተወለደ በትክክለኛው የመጀመሪያው 1 ሰዓት ውስጥ መጀመር አለበት!

​ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሕፃኑ ከተወለደ ወዲያውኑ ጡት ማጥባት መጀመሩ ለእናቱም ሆነ ለልጁ እጅግ ብዙ የጤና ጥቅሞች አሉት፡-
​☑️ ኮሎስትረም (የመጀመሪያው ወተት)፦ ከተወለደ ወዲያው የሚመነጨው ቢጫ ወተት ለሕፃኑ የመጀመሪያው "የተፈጥሮ ክትባት" ሆኖ ያገለግላል፤ ለበሽታ የመከላከል አቅሙም እጅግ ወሳኝ ነው።
☑️ የወተት መጠንን ማሳደግ፦ ሕፃኑ ወዲያውኑ መጥባት መጀመሩ በእናት አካል ውስጥ ወተት በበቂ ሁኔታ እንዲመነጭ ያነቃቃል።
☑️ የእናትና ልጅ ትስስር፦ በሁለቱ መካከል ጠንካራ ስሜታዊ ትስስር እንዲፈጠር ይረዳል።

ማሳሰቢያ፦ ሕፃኑ ከተወለደበት ጊዜ አንስቶ እስከ 6 ወር ድረስ ከእናት ጡት ወተት ውጪ ማንኛውም ዓይነት ውሃ፣ ምግብ ወይም ሌላ መጠጥ በፍጹም መሠጠት የለበትም።

​መልዕክቱን ለሌሎች ሼር በማድረግ ያካፍሉ።

09/08/2026

የእናት ጡት ወተት መተኪያ የለውም!

የእናት ጡት ወተት ለተስተካከለ ጤናማ እድገት !

የመጀመሪያዎቹ 1,000 ቀናት፡ የትውልድ ዕጣ ፈንታ የሚወሰንበት ወርቃማ ወቅትየአንድ ሰው የህይወት ዘመን ጤና፣ ብልህነት እና ስኬት የሚወሰነው በዩኒቨርስቲ ቆይታው ሳይሆን ገና በጨቅላነቱ በ...
25/02/2026

የመጀመሪያዎቹ 1,000 ቀናት፡ የትውልድ ዕጣ ፈንታ የሚወሰንበት ወርቃማ ወቅት

የአንድ ሰው የህይወት ዘመን ጤና፣ ብልህነት እና ስኬት የሚወሰነው በዩኒቨርስቲ ቆይታው ሳይሆን ገና በጨቅላነቱ በሚያገኘው እንክብካቤ እንደሆነ ያውቃሉ? ከፅንሰት እስከ ሁለት ዓመት ያሉት 1,000 ቀናት የአንድን ሰው የነገ ማንነት የሚወስኑ "የወርቃማ ዕድል ቀናት" ናቸው። እነዚህ ቀናት በሦስት ዋና ዋና ምዕራፎች ይከፈላሉ፡- የእርግዝና ወቅት (270 ቀናት)፣ ከመወለድ እስከ ስድስት ወር (180 ቀናት) እና ከስድስት ወር እስከ ሁለት ዓመት (550 ቀናት)። በእነዚህ ቀናት ውስጥ የሚሰጥ ጥንቃቄ ለህፃኑ ብቻ ሳይሆን ለሀገርም የሚተርፍ ትልቅ መዋዕለ ንዋይ ነው።

ለምን 1,000 ቀናት ልዩ ትኩረት ተሰጣቸው?
ምክንያቱ ግልጽ ነው፤ የሰው ልጅ አእምሮ 80 በመቶ የሚሆነውን እድገቱን የሚጨርሰው በእነዚህ ቀናት ውስጥ ነው። በዚህ ወቅት የሚከሰት የምግብ እጥረት ወይም የእንክብካቤ መጓደል "መቀንጨርን" (Stunting) ያስከትላል። መቀንጨር ማለት ህፃኑ እንደ እድሜው አለማደግ ብቻ ሳይሆን፣ የአእምሮው ሴሎች በሚገባ አለመቀጣጠል ማለት ነው። ትልቁ አሳዛኝ እውነታ ደግሞ፣ አንዴ በእነዚህ ቀናት ውስጥ መቀንጨር ከተከሰተ በኋላ ላይ በምንም አይነት ጥረት ሊቀለበስ የማይችል (Irreversible) መሆኑ ነው። በመሆኑም፣ እነዚህ ቀናት አንዴ ካመለጡን አንመለሳቸውም፤ ካልተጠቀምንባቸው ግን የትውልድን እጣ ፈንታ እናበላሻለን።

የእርግዝና ወቅት፡ ህይወት በማህፀን ሲጀምር
የመጀመሪያዎቹ 270 ቀናት በእናትየው ማህፀን ውስጥ የሚቆዩበት ጊዜ ነው። ፅንሱ የሚያስፈልገውን ንጥረ ነገር ሁሉ የሚያገኘው ከእናቱ ደም በመሆኑ፣ የእናትየው አመጋገብ ወሳኝ ነው። ነብሰጡር እናቶች በቀን ቢያንስ አራት ጊዜ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ፣ የብረት ማዕድን እና ፎሊክ አሲድ (Iron-Folate) እንክብሎችን መውሰድ እንዲሁም ቢያንስ አራት ጊዜ የቅድመ ወሊድ የጤና ክትትል ማድረግ አለባቸው። እናት ደስተኛና ከጭንቀት ነፃ ስትሆን፣ ፅንሱም በጤናማ ሁኔታ ያድጋል። በዚህ ወቅት የሚደረግ ጥንቃቄ ህፃኑ ዝቅተኛ የውልደት ክብደት (Low Birth Weight) እንዳይኖረው ይከላከላል።

ከመወለድ እስከ 6 ወር፡ ተፈጥሯዊው ጋሻ
ህፃኑ እንደተወለደ በመጀመሪያው አንድ ሰዓት ውስጥ የእናት ጡት ወተት መጀመር አለበት። በተለይም "እንገር" (Colostrum) ተብሎ የሚጠራው ወፍራም ቢጫ ወተት ለህፃኑ የመጀመሪያውና ተፈጥሯዊው "ክትባት" ነው። እስከ ስድስት ወር ድረስ ህፃኑ ከጡት ወተት ውጭ ውሃ እንኳን ሳይቀላቀል መመገብ አለበት። የእናት ጡት ወተት 88 በመቶው ውሃ በመሆኑ ህፃኑን ከጥማትም ከረሃብም ይከላከላል። ይህ ወቅት የህፃኑ በሽታ የመከላከል አቅም የሚገነባበት እና ከእናቱ ጋር ጥልቅ የሆነ ስሜታዊ ትስስር የሚፈጥርበት ጊዜ ነው።

ከ6 ወር እስከ 2 ዓመት፡ የተመጣጠነ ምግብ እና ማነቃቃት
ከስድስት ወር በኋላ የልጅዎ የምግብ ፍላጎት እና የአካል እድገት በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል። በዚህ ጊዜ ጡት ማጥባቱን እየቀጠሉ፣ በየቀኑ ቢያንስ ከአራት የምግብ ምድቦች (ጥራጥሬ፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ የእንስሳት ተዋፅኦ እና ቅባት) የተውጣጡ ተጨማሪ ምግቦችን መስጠት ያስፈልጋል። ከምግብ በተጨማሪም ህፃኑን ማጫወት፣ ማውራት እና አዳዲስ ነገሮችን እንዲረዳ ማነቃቃት ለአእምሮው ግንኙነት (Synapse formation) እጅግ አስፈላጊ ነው። ንፅህናን መጠበቅ ደግሞ ህፃኑ በተቅማጥ በሽታ ተይዞ ያገኘውን ንጥረ ነገር እንዳያጣ ይረዳዋል።

የትውልድ መዛባትን የመስበር ሚስጥር
ሌላው ትኩረት የሚሻው ነጥብ፣ የሥርዓተ-ምግብ መዛባት ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገር መሆኑ ነው። አንዲት እናት በአፍላ ወጣትነቷ (Adolescent) የተመጣጠነ ምግብ ካላገኘች እና ካንቀነጨረች፣ የምትወልደውም ህፃን የመቀንጨር እድሉ ከፍተኛ ነው። ስለዚህ ይህንን ዑደት ለመስበር የአፍላ ወጣት ሴቶችን (ከ10-19 ዓመት) ጤና እና አመጋገብ ማሻሻል ግድ ይላል። ጤናማ አፍላ ወጣት ማለት ጤናማ እናት፣ ጤናማ እናት ማለት ደግሞ ጤናማ ትውልድ ማለት ነው።

ማጠቃለያ
በአገራችን ኢትዮጵያ "የአርባ ቀን እድል" የሚባለው ባህላዊ አመለካከት አለ። ይህንን አመለካከት ወደ ሳይንሳዊው "የ1,000 ቀናት ዕድል" በመቀየር ለልጆቻችን ብሩህ የወደፊት ጊዜን መፍጠር እንችላለን። ዛሬ በእነዚህ ቀናት ላይ የምናደርገው ጥንቃቄ፣ ነገ አገር የሚረከብ ብልህ፣ ጤናማ እና ምርታማ ዜጋ እንዲኖር ያደርጋል። ልጆቻችንን በመልካም አመጋገብ፣ በፍቅር እና በእንክብካቤ እናሳድግ!
ሀሳብ አስተያየት ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን? 👇
#ልጆች #ጤና #አመጋገብ #1000ቀናት

22/02/2026

ወርቃማ 1ሺህ ቀናት ምን ማለት እናቶች? አባቶች?

13/12/2025

ልጆቻችሁን ስታዩ የምታገኙት ደስታ 😀
እንዴት ትገልፁታላችሁ?

በ   በወገኖቻችን ላይ የደረሰው የተፈጥሮ አደጋ እጅግ አሳዝኖናል😭። ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን። ለተጎጂ ወገኖች ድጋፍ እንድናደርግ ጥሪ ተላልፏል።  #ጤናማልጆች World Visio...
24/07/2024

በ በወገኖቻችን ላይ የደረሰው የተፈጥሮ አደጋ እጅግ አሳዝኖናል😭። ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን። ለተጎጂ ወገኖች ድጋፍ እንድናደርግ ጥሪ ተላልፏል። #ጤናማልጆች World Vision Ethiopia Ministry of Health,Ethiopia Tedros Adhanom Ghebreyesus

🔺  #በብረት የበለፀጉ ምግቦች ጠቀሜታ ለህፃናት ፤ ይህ መረጃ ከጠቀመ ለሌሎች  #ሼር ያድርጉ።  #ጤናማልጆች
17/01/2024

🔺 #በብረት የበለፀጉ ምግቦች ጠቀሜታ ለህፃናት ፤ ይህ መረጃ ከጠቀመ ለሌሎች #ሼር ያድርጉ። #ጤናማልጆች

በ  #ቫይታሚን ኤ የበለፀጉ ምግቦች ጥቅም  #ለህፃናት ፤ በቫይታሚን የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ አይርሱ! ⤵️ለሌሎች ሼር ያድርጉ!    #ጤናማልጆች
16/01/2024

በ #ቫይታሚን ኤ የበለፀጉ ምግቦች ጥቅም #ለህፃናት ፤ በቫይታሚን የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ አይርሱ!
⤵️
ለሌሎች ሼር ያድርጉ! #ጤናማልጆች

Address

Garment
Addis Ababa
105

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Telephone

+251930821111

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Healthy Children ጤናማ ልጆች posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Healthy Children ጤናማ ልጆች:

Shortcuts

Share