15/09/2021
የዓለም የህሙማን ደህንነት ቀን መስከረም 7፣2014 የጤና ሚ/ር ሀላፊዎች፣ ሰራተኞች እና በጤናው ዘርፍ ያለዉን ጤና አገልግሎት ጥራት እና ደህንነት ተደራሽነት ለማሳደግ የምትጉ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት “ደህንነቱ የተጠበቀ የእናቶች እና የጨቅላ ሕፃናት ክብካቤ’’ በሚል መሪ ቃል እና ‘’ደህንነቱ ለተጠበቀ እና አክብሮት ላለው የማዋለድ አገልግሎት በጋራ እንረባረብ’’ በሚል መፈክር የማህበረሰቡን እና ባለድርሻ አካላትን ግንዛቤ እና ትኩረት ለማሳደግ ይክበራል። የ2014 የዓለም የህሙማን ደህንነት ቀን ዓላማዎች:
1. በእናቶች እና ጨቅላ ሕፃናት የጤና አገልግሎት ደህንነት ላይ በተለይም በወሊድ ጊዜ ግንዛቤ ማሳደግ
2. ባለድርሻ አካላትን በማሳትፉ የእናቶችን እና ጨቅላ ሕፃናት ደህንነት ለማሻሻል የሚረዱ ውጤታማ ዘዴዎችን መለየት
3. ደህንነቱ የተጠበቀ እና አክብሮት ያለዉ የማዋለድ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ
4. የጤና ተቋማት ውጤታማ ዘዴዎችን በማላመድ እንዲተገበሩ ጥሪ ማድረግ ናቸዉ
ዝግጅቱን በZoom ሊንክ
https://ubc.zoom.us/j/68286823898?pwd=dE5wRHQ2dS9ZSiswRkVIeitlbitZUT09
እንድትከታተሉ አስተያየት እንድሰጡ እንጋብዛልን
Zoom is the leader in modern enterprise video communications, with an easy, reliable cloud platform for video and audio conferencing, chat, and webinars across mobile, desktop, and room systems. Zoom Rooms is the original software-based conference room solution used around the world in board, confer...