30/03/2026
መልካም የዶክተሮች ቀን !
HAPPY DOCTORS DAY !
የተከበሩና ክብር የሚገባቸው የዶክተሮች ቀን፤ ከፈጣሪ በታች የሰው ልጅ ተስፋዎች!
መጋቢት 21፣ 2018 ዓ.ም (March 30, 2026 )
ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሐኪሞች ቀን (Doctors' Day) እየተከበረ ይገኛል።
ይህ ቀን ስለ ራሳቸው ምቾት ሳይሆን ስለ ሌላው ህመም፣ ስለ ራሳቸው እረፍት ሳይሆን ስለ ሰው ልጅ ህይወት ቀንም ሌሊት ለሚተጉት የህክምና ባለሙያዎች የምስጋና ቀን ነው።
በሀገራችን ኢትዮጵያ የሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች የሚከፍሉት መስዋዕትነት ከምንም በላይ የሚከበር ነው።
ምንም እንኳን የሚያገኙት ወርሃዊ ክፍያ ከደከሙበት የትምህርት ጥልቀትና ካለባቸው የሥራ ጫና ጋር የሚመጣጠን ባይሆንም፤ በቁሳቁስ እጥረትና በከባድ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነው ለወገናቸው የሚያሳዩት ርህራሄና ቁርጠኝነት የክፍለ ዘመናችን እውነተኛ "እንቁዎች" ያደርጋቸዋል።
ያስተማራቸውን ህዝብ በቅንነት እያገለገሉ፣ በገንዘብ የማይተመን የህይወት ዋጋ እየከፈሉ ያሉት ሐኪሞቻችን የህብረተሰባችን የቁም መከታዎች ናቸው።
ዛሬ የደከሙላችሁን፣ በፈገግታቸው ተስፋ የሆኗችሁን፣ በዕውቀታቸው ከህመም የታደጓችሁን ሐኪሞች ስም የምንጠራበት ቀን ነው።
1. የምትወዱትንና የምታከብሩትን ሐኪም በኮሜንት (Mention) በማድረግ የዛሬውን ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያድርሱላቸው!
2. ስለ አደረጉላችሁ መልካም ነገር በስም እየጠቀሳችሁ አመስግኗቸው!
እንኳን ለዓለም አቀፍ የሐኪሞች ቀን በሰላም አደረሳችሁ!