26/04/2026
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የህክምና ኦክስጅን ማምረት መጀመሩ ተገለጸ
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በሰዓት 600 ሊትር የማምረት አቅም ያለው እንደሆነ የተገለጸው የህክምና ኦክስጅን ማምረቻ ማሽን ተከላ ሥራ ተጠናቆ ምርት መጀመሩን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
በኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ባለቤትነት ከአለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፕሮጀክት አገልግሎት /UNOPS/ በ300 ሚሊዮን ብር የተገነባ መሆኑ ተገልጿል።
መረጃውን ያገኘነው ከዩኒቨርሲቲው ኮሙኒኬሽንና ሕዝብ ግንኙነት ነው።